ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስን አገዱ

pat banned gen mgr0

  • የሠራተኛ ቅጥር እንዳይፈጽሙ እና ከፍተኛ ወጪዎችን እንዳያንቀሳቅሱ አገዱ፤
  • የመሪ ዕቅድ ትግበራ ዐቢይ ኮሚቴ፣ ለጽ/ቤቱ የ5 ከፍተኛ ባለሞያዎችን ቅጥር በውድድር ለመፈጸም እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት የተላለፈ እግድ ነው፤
  • ከፍተኛ ወጪዎቹ፡- በጀታቸው በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀ፣ የ2 ሕንፃዎችንና የጠቅላይ ጽ/ቤቱ አዳራሽ ዲዛይን፣ ግንባታና ቁጥጥር ሥራን እንዲሁም የአህጉረ ስብከት ተሽከርካሪዎች ግዥ አፈጻጸምን ይመለከታሉ፤
  • በነውጠኞች ጥፋት ለተጎዱት የሶማሌ አብያተ ክርስቲያን እድሳት የተሰበሰበው ገንዘብም፣ ወጪ እንዳይኾን ከልክለዋል፤
  • እግዱ፣ “ሀብት ያለ ሥነ ሥርዓት ለከፍተኛ ብክነት እንዳይዳረግ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግን” በመነሻነት ቢጠቅስም፣ ፓትርያርኩ፣ ባልቀረበ የቁጥጥር አገልግሎቱ ሪፖርት፣ ሥልጣንን አላግባብ የተጠቀሙበትና ተቋማዊ ለውጡን ለማደናቀፍ በጽ/ቤታቸው ዙሪያ ሲካሔዱ የከረሙ የጨለማ ምክክሮች ውጤት እንዳይኾን ተጠቁሟል፤
  • የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ የሦስት ዓመት የሥራ ዘመን እየተጠናቀቀ መኾኑን እግዱ ቢጠቅስም፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት፣ ለመረጣቸው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የክንውን ሪፖርት ሲያቀርቡ እንጂ በፓትርያርኩ የሚወሰን አይደለም፤ ለቀጣይ ሦስት ዓመት የሥራ ዘመን የመወዳደር መብትም አላቸውና

***

pat banned gen mgr

  • ሦስት ዓመት የሥራ ዘመን ያላቸው ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ፣ የቤተ ክርስቲያን የሰው ሀብት፣ ገንዘብ እና ንብረት አስተዳደር የበላይ ሓላፊ ናቸው፤
  • ቅዱስ ሲኖዶስ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ በፈቀደው በጀት መሠረት፣ የሒሳቡን አያያዝና የንብረቱን አጠቃቀም ይቆጣጠራሉ፤ ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያን ገንዘብና ንብረት ከቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ጋራ በጣምራ ፊርማ ያንቀሳቅሳሉ
  • ለቅዱስ ፓትርያርኩም ተጠሪ ቢኾኑም፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያንና በቃለ ዐዋዲው መሠረት ዕቅድ እና የአፈጻጸም ሪፖርት የሚያቀርቡት፣ ለአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እና ለቅዱስ ሲኖዶስ አካላት(ለቋሚ ሲኖዶስ እና ለምልዓተ ጉባኤው) ነው፤
  • ፓትርያርኩ፣ ከብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ የአፈጻጸም ሪፖርት የጠየቁባቸውንና አላግባብ እገዳ ያሳለፉበትን ደብዳቤ፣ ቋሚ ሲኖዶስም ኾነ ጽ/ቤቱ አልመከረበትም፤ የአፈጻጸም ሪፖርት መጠየቅ ቢችሉም፣ እግዱ አግባብነት የለውም፤ ሥልጣኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ነው
  • ጠቅላይ ጽ/ቤቱን በዋና ሥራ አስኪያጅነት እንዲመሩ፣ በግንቦት 2008 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተመርጠው በፓትርያርኩ የተመደቡት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ የሥራ ዘመናቸው የሚጠናቀቀው በመጪው ግንቦት የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ ነው፤

***

4 thoughts on “ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስን አገዱ

  1. Anonymous March 21, 2019 at 5:16 am Reply

    esachw limadachwnnw

  2. Anonymous March 21, 2019 at 8:48 am Reply

    ከመጣሽ እመብርሃን ታምጣሽ ስልጣኑ መገደብ ያለበት የማን እንደሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ (እንደ አንድ) ስለሚያውቀው እግዚአብሔር ለፍፃሜ ያብቃቸው። ባይሆን ምርጫው ሲቃረብ ይህን ለምን እንዳደረጉ መገንዘብ ብፁአን አባቶች አይጠፋቸውም። በተረፈ የኃላፊነት ጊዜዎ እየተጠናቀቀ ስለሆነ ብፁዕ አባታችን አቡነ ማቲያስ የንስሃ ጊዜዎን ይጠቀሙባት ወይ መካሪ የለዎት ወይ… ግራ የገባው ነገር ነው።

  3. Anonymous March 21, 2019 at 11:33 am Reply

    እኔ የሚገርመኝ ፓትርያርኩም ሥራ አስኪያጅ ም ለውነት ሁሉም ሌቦች ሁሉም ዘራፊዎች ናቸው ይወገዱ

  4. Anonymous March 22, 2019 at 5:56 pm Reply

    ፓትርያሬኩ አጋሜ ትግሬ።
    ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እራያ ወሎ ናቸው

    ጵጵስና ለመሾም እራያ ትግሬ ተብለው ነው
    ውሥጡ ወይራ ነው ዲዩስቆሮሦ ወሮሞያ አማረኛ ትግሬኛ አቀላጥፎ ይናገራል
    አሁንስ ተግሬ አይደለሁም ወደ ማይ ጨውም አልሄድም በስራ አስካሀ ጂነቴ ቋሚ መሆን አለብኝ ካልሆነ እደራሢ
    ነው እምሆን እያለ ማትያስን እለት እለት ስኳራቸው እዲጨምር አደረገ
    ፓትርያሬኩ ን ለገዳ መጻፍ ያነሣሣቸው ዋነው ይህ ነው

Leave a comment