ስለ እኛ

ሐራ ዘተዋሕዶ – የተዋሕዶ ሠራዊት፣ የተዋሕዶ ወታደር፣ የተዋሕዶ ጭፍራ ማለት ነው፡፡ ሐራ – ሐርነት፣ ነጻነት ያለው ማለት ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ትምህርትና ሥርዐት፣ ትውፊትና ታሪክ ለማጥፋት በውስጥና ከውጭ የሚንበለበሉትን የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ፍላጻ ለመመከት የእምነትን ጋሻ አንሥተን እንጦምራለን፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ብሔራዊ ክብርና ተቋማዊ ነጻነት በማንበር ሐዋርያዊ አገልግሎቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲጠናከርና እንዲስፋፋ የመረጃንና የዕውቀትን ሰይፍ በመያዝ እንጦምራለን፡፡ በአገልጋዮችና ምእመናን አዎንታዊ ተግባቦት ለተጨባጭ ለውጥ የሚያበቃ የመንፈስና የተግባር ተናሥኦት (Uprising) እንዲፋፋም እንጦምራለን፡፡ ስለዚህም ሐራውያን ለተዋሕዶ – የተዋሕዶ ሠራዊት፣ የተዋሕዶ ወታደሮች፣ የተዋሕዶ ጭፍሮች ነን፡፡

119 thoughts on “ስለ እኛ

 1. Anonymous August 31, 2018 at 8:06 pm Reply

  የሰሜን ሸዋ ሀ/ስብከት አስተዳደራዊ ችግሮቹን እየፈታ ነው፤ በሚለው ስር የተፃፈውን ፁሑፍ አነበብኩና እንደ አንድ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ ግዴታ ስላለብኝ፤ ይልቁንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የሁላችን የምእመናን ቤት እንደመሆኑዋ መጠን ሁሉንም የሚደረጉትን እንቅስቃሴ መከታተል ፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሚዛናዊ የሆነ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ ነው፤፤ ስለሆነም እንደተባለው በትንሹ በሚባል መልኩ ለውጦች አሉ፤ግለሰቦች ከሀላፊነታቸው ተነስተዋል ፤ አዳዲስ ምደባዎች ተከናውነዋል፤ ነገር ግን ምደባው ከአድሎ የፀዳ ነው ወይ? በተነሱት ሰዎች ቦታ የተተኩት ሰዎች እውነት ከእንከን የፀዱና በተጨማሪም ምእመኑ የሚያምንባቸው፤ ከዝምድና ፤ከቡድናዊነት የፀዳ ነው ወይ? የመሳሰሉት ነገሮችን በሚገባ መመርመርና በጽሞና መገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነገሮችንም በዝርዝርና በሚዛናዊነት ማዬትን ይጠይቃል፤፤ ከተሰጠው አስተያየት ለመነሳት እያናዳናዱን ሀሳብ ማዬት ጠቃሚ ይሆናል፤፤ ሊቀ አእላፍ ሁሉምይፈር፤በተለያዩ ወረዳዎች በሀላፊነት የሰሩ፤በሙያቸው፤ በስራቸው፤ በግብረገብነታቸው የተመሰገኑና ፤ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤቱ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን በጥብቅ የታገሉ ፤ለባለ ጉዳዮች ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ በጥሩ ስነ-ምግባር ፤በታማኝነት፤ሲሰሩ እንደነበረ መላው በሀገረ ስብከቱ ስር ያሉ ካህናትና ምእመናን ምስክርነታቸውን እየሰጡ ያሉ ለመሆኑ የተለያዩ ምንጮች ያረጋግጣሉ፤፤ይህ ሆኖ ሳለ ግን ከብፁ አቡነ ኤፍሬም ጋር ሲሰሩ የቆዩ ናቸው በሚል ብቻ አለምንም ምክንያት ወደ ሞረትናጅሩ ወረዳ(እነዋሪ)ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እንደተዛወሩ፤ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አሁን ደግሞ አረጋዊውን ሊቀ ጳጳስ በመዘወርና ጫና በመፍጠር ፍላጎታቸውን ሲያስፈጽሙ የኖሩና በአቅም ማነስ(ሞያ-ቢስነት) ተገምግመው ነው ወደ ሞረትናጅሩ ወረዳ(እነዋሪ)ቤተ ክህነት ተመድበው እንዲሰሩ የተደረገው፤ ተብሎ የተሰጠው አስተያየት፤ በፍጹም እሳቸውን የማይገልጽ፤ ከእውነት የራቀ ና ሀላፊነት የጎደለውና ሚዛኑን ያልጠበቀ አስተያየት እንደሆነ አንዳንድ ጹሁፉን (የተጻፈውን) ያነበቡ ምእመናን ገልጸዋል፤፤
  በአጠቃላይ ለወደፊቱም ቢሆን መታረም ያለበት ጉዳይ ፤ የግለሰቦችን የግል ስብእና የማጠልሸት ስራና የራስን ድክመትና የስራ ክፍተት ለመሙላት ተብሎ ለእውነትና ለቤተ-ክርስቲያን የሚተጉ ሰዎችን መጉዳት አስፈላጊ ያለመሆኑንና እንደ ክርስቲያናዊ ተግባር ተገቢ ያለመሆኑን ቢታሰብበት መልካም ነው፤፤

 2. Naly October 28, 2018 at 8:17 pm Reply

  please look into Diet sultan situation

  our fathers are left to wonder where is their support, where is the Eth people? Synod? or Goverment?

  there is a lot to do right now

 3. Rufinos November 1, 2018 at 8:02 am Reply

  በወቅታዊውና ታማኝነት ባለው መረጃችሁ የፔጃችሁ ተከታታይ ነኝ እግዚአብሔር ይርዳችሁ አንድ ጥያቄ አለኝ የአውሮጳ ጳጳሳትን ምደባ አስመልክቶ የየሀገረ ስብከቶቹ የሚመሯቸውን ሀገሮች ዝርዝር መረጃ ብትነግሩን ለምሳሌ በጣሊያን ስር የሚመሩት: በጀርመን የሚመሩት ሀገሮች ወዘተ ዝርዝሩን ግልፅ አድርጉልን አመሰግናለሁ

 4. ሀይለ ማርያም March 22, 2019 at 8:14 am Reply

  በስመአብ: ወወልድ: ወመንፈስ :ቅዱስ :አሐዱ: አምላክ:አሜን!!! የተወደዳችሁ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተሰቦች፣ የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወዳጆች፣ እንደምን አላችሁ፡፡
  https://www.ethiopianorthodox.org/ በሚለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዌብሳይት ላይ ያለኝን ስተያየት ለመግለጽ ያህል ነው
  አዚህ ዌብሳይት ላይ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን በሚነካበት ጊዜ ሊንኩ የሚወስደው https://bible.org/foreign/amharic/
  ወደዚህ አደሬስ ነው ይህ አድሬስ ደግሞ የያዘው 66ቱን ነው፡፡ በቸልታ ተደርጎ ከሆነ ቢስተካከል ምንም የማይጎላት እናታችን ቤተክርስቲያን ለምን በልጆቻ ለዘመናት ታፍራለች ለምንስ መጠቀሚያ ትሆናለች እባካችሁ ይስተካከል ሐራ ዘተዋሕዶች የበኩላችሁን
  ድርሻ ብትወጡ፡፡እግዚአብሔር ልቦና ይስጠን፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: