ሰበር ዜና – ቅዱስ ሲኖዶስ ድንገተኛ ልዩ ስብሰባ ተቀመጠ፤ ማዕከላዊነትን ስላልጠበቁ አሠራሮችና ወቅታዊ ጉዳዮች ይወያያል

  • ድንገተኛ ልዩ ስብሰባው የተጠራው በቋሚ ሲኖዶሱ ነው
  • በፓትርያርኩና በማኅበረ ቅዱሳን ውዝግብ ላይ ይወያያል
  • በዐቢይ ጾም የጸሎተ ምሕላ ጉዳይም ውሳኔ ያሳልፋል

Holy Synod Tik2008

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ዛሬ የካቲት ፳፭ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ጀምሮ ድንገተኛ ልዩ ስብሰባ መቀመጡ ተገለጸ፡፡

ድንገተኛ ልዩ ስብሰባውን የሚያካሒዱት፣ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሞተ ዕረፍትና ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በዓለ ሢመት በመዲናይቱ አዲስ አበባ የተሰበሰቡ ከ25 ያላነሱ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ናቸው፡፡

ስብሰባው እንደሚካሔድ የታወቀው፣ ፓትርያርኩ በመጪው ሰኞ የሚጀመረውን ዐቢይ ጾም በማስመልከት ዛሬ ረፋድ ላይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ በተገኙበት በቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው እንዳበቁ ሲኾን አስቀድሞ መረጃው እንዳልነበራቸው ተገልጧል፡፡

ፓትርያርኩ መግለጫውን በንባብ ካሰሙ በኋላ ከአዳራሹ ለመውጣት ተነሥተው እንደቆሙ፤ በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጥያቄ ተመልሰው እንዲመቀጡ መደረጉን የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ፓትርያርኩ ተመልሰው እንደተቀመጡ፣ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቡነ ማቴዎስ፣ ማእከላዊ አሠራርን ባለመጠበቅ እየተከሠቱ ስለሚገኙና እልባት ለመስጠት ስላዳገቱ ችግሮች በስፋት አስረድተዋል፡፡ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በበላይነት የሚመራው ጠቅላይ ጽ/ቤታቸው ሳያውቀው ከቅዱስነታቸው ልዩ ጽ/ቤት ለአስፈጻሚ አካላትና ተቋማት የሚወጡ ደብዳቤዎችን ብፁዕነታቸው በማሳያነት አቅርበዋል፡፡ ይህም በሥራ ግንኙነቶች ላይ ቀውስ እንደፈጠረና አለመግባባቱ በውጭ አካላት ዘንድ ሳይቀር ትዝብት ላይ እየጣለን በመኾኑ ቅዱስ ሲኖዶሱ አንድ መፍትሔ እንዲሰጠው ብፁዕነታቸው ጠይቀዋል፡፡

ማዕከላዊነቱን ስላልጠበቀ የአሠራር ችግር በማብራራት ተጨማሪ አጽንዖት የሰጡት የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ በኦሮሚያ ክልልና በአንዳንድ የአገራችን ክፍሎች ስላጋጠመው የሰላም ቀውስና ስለ ተቃጠሉት አብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ሲጠይቁ መቆየታቸውን ጠቅሰው፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ በዚኹ መልካም አጋጣሚ በእነዚኽና ሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች  ተወያይቶ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ጠይቀዋል፡፡

የብፁዕ ዋና ጸሐፊውንና የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁን መግለጫ ያዳመጠው ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ ጉዳዩ በአጀንዳ ተቀርጾ እንዲቀርብለት፤ ከኹለቱ ብፁዓን አባቶች ጋር ብፁዕ አቡነ ሕዝኤልን፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስንና ብፁዕ አቡነ ያሬድን በመጨመር በአርቃቂነት ከሠየመ በኋላ ተዘጋጅቶ በቀረበለት መሠረት ከቀትር በኋላ ስብሰባውን መጀመሩ ታውቋል፡፡

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ድንገተኛ ልዩ ስብሰባው እንደቀጠለ ሲኾን በአርእስተ ጉዳይ ደረጃም፡-

  • ስለ ሰላም እና ስለ ተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናት፤
  • በድርቁ ምክንያት ለተጎዱት ወገኖች እየተደረገ ስላለው ርዳታና ጸሎተ ምሕላ፤
  • ማዕከላዊነትን ስላልጠበቁ አሠራሮችና ስላስከተሏቸው ችግሮች፤
  • ከልዩ ጽ/ቤት ስለሚወጡ ደብዳቤዎችና መጻጻፎች በተመለከተ፤
  • ሐዋርያዊ ጉዞን(የፓትርያርኩን የውጭ ጉዞዎች) በተመለከተ፤

የሚሉ መነጋገርያዎች እንደሚገኙበት ተመልክቷል፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት፣ በዓመት ኹለት ጊዜ ከሚደረገው የምልዓተ ጉባኤው መደበኛ ስብሰባዎች በተለየ፣ አስቸኳይና ድንገተኛ ጉዳይ ሲያጋጥም ቋሚ ሲኖዶሱ በብፁዕ ዋና ጸሐፊው አማካይነት ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ከጠቅላላ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከግማሽ በላይ ጉባኤ እንዲደረግ በጠየቁ ጊዜ ጥሪ ሊደረግና ስብሰባው ሊካሔድ ይችላል፡፡

በስብሰባው፣ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ለሚመለከቱ አጀንዳዎች ከአባላት ከሦስቱ እጅ ኹለቱ እጅ ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይኾናል፤ በአስተዳደር ጉዳዮች ውሳኔዎች ሲተላለፉም ከግማሽ በላይ በኾነ ድምፅ የተደገፈው ሐሳብ ያልፋል፡፡

17 thoughts on “ሰበር ዜና – ቅዱስ ሲኖዶስ ድንገተኛ ልዩ ስብሰባ ተቀመጠ፤ ማዕከላዊነትን ስላልጠበቁ አሠራሮችና ወቅታዊ ጉዳዮች ይወያያል

  1. የኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች March 4, 2016 at 4:50 pm Reply

    እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ቸር ወሬ ያሰማን አሜን!!!!

  2. Anonymous March 4, 2016 at 5:36 pm Reply

    turu newe

  3. Anonymous March 4, 2016 at 7:41 pm Reply

    እውነት ሁልጊዜም አሽናፊ ናት፡፡
    ሁልጊዜ የእውነተኞች ባለታሪኮችን ታሪክ፤ የሌሎችን ጀግንነት ወደ ራሳቸው በመገልበጥ፡ ባለታሪካችና ጀግኖች መብሰል የባሕርይ ገንዘባቸው የሆኑት፤ ዘወትር በዘረኝነትና በሥልጣን ጥመኝነት የእየዋተቱ በሚገኙት፤ ጥቂት መሰል ጳጳሳት ማሕበረ ሰይጣን(ማቅ) የሰጣቸውን ግዳጅ ለመፈጸም፣ በሕገ ወጥነት መንገድ የተደረገው ስብሰባ በእውነተኛው አባት ፓትርያርክ ቅዱስ ማትያስና በእውነተኞች አባቶቻችን ሊቃነ ጳጳሳት ከሸፈ፡፡ ቅዱስ ፓትርያሪኩን ለመዝለፍና ብሎም አስቀድሞ ሐራ ተዋህዶ እንደ ዘገበው ለማውረድና ለማሸማቅቅ የተዘጋጀው ስብሰባ በቅዱስ ፓትርያርኩ በድል አድራጊነት ተጠናቋል፡፡
    ስለዚህ በዚህ ስብሰባ የሊቃነ ጳጳሳት አቋምና ማንነት በግልጽ የታየ በመሆኑ ሊቃውንት፤ ካህናት፤ ሰባክያን በአጠቃላይ ሕዝበ ክርስቲያን ለቤተ ክርስቲያናችን ህልውና መጠበቅ ነቅተን ልንነሣ ግድ ይላል፡፡

  4. Anonymous March 4, 2016 at 9:09 pm Reply

    አባ ሉቃስ እንዳሉት ስለሕዝብ ሰላም መወያየት እጅግ አስፈላጊ እንደ ሆነ አምናለሁ፡፡ነገር ግን ሰው ራሱን በቅድሚያ ለሰላም ሳያስገዛ ስለሰላም ማውራት ትክክል አይደለም፡ የአባ ሉቃስ ዓላማ በወልቃይት ጸገዴ ሕዝብ ስም የሚነግዱትን ፖለቲከኞችና እንዲሁም በተመሳሳይ መልኩ ደጉን የኦሮሚያን ሕዝብ እየበደሉ ያሉትን ኦነጋውያን የጫንዋቸውን ጭነት ነው ያራገፉት፡፡ አለማወቃቸው ነው እንጂ የእሳቱ ወላፈን በቅድሚያ የሚልሰው እሳቸውን ነው፡፡ ይህ አስተያየት ስጽፍ ትክክለኛውን መረጃ ይዤ ነው በተጨባጭም አቀርበዋለሁ፡፡ ግን በቅድሚያ ውሴኔውን መጠበቅ ግድ ይላል፡፡

    • ኃይለ ስላሴ March 6, 2016 at 11:49 pm Reply

      ግልፅ አይደለም ትንሽ ይብራራ፣ከቤተክርስትያን እራስ ላይ ወረድ !!!

  5. Tazabiw March 5, 2016 at 12:14 am Reply

    that is great

  6. Anonymous March 5, 2016 at 12:27 am Reply

    “ማዕከላዊነትን ስላልጠበቁ አሠራሮችና ስላስከተሏቸው ችግሮች፤”…”.ከልዩ ጽ/ቤት ስለሚወጡ ደብዳቤዎችና መጻጻፎች በተመለከተ፤”…The South Africa Diocese is in chaos…

  7. Anonymous March 5, 2016 at 12:54 am Reply

    እግዚአብሔር ከአባቶቻችን ጋር ይሁን፡፡

  8. Selamu March 5, 2016 at 4:19 am Reply

    It’s wonderful that the Holy Synod is meeting at a time when it’s being ignored by the new Patriarch, Abune Mathias. It’s wll known that he had the temerity of taking a trip, recently, to Rome and meet with Pope Francis I without obtaining a prior approval of the Holy Synod, a procedure normally requir4ed from any EOTC Patriarch.

    The fact that the Holy Synod’s authority is completely ignored is attested by the continuing presence of the unauthorized statue erected for the previousl Patriarch, Aune Paulos. It’s recalled that the Holy Synod had decided that the statue be removed but the previous and current Patriarch simply ignored the decision!

    What’s even more important is the lack of attention by EOTC including the Holy Synod to the fact that according to Kidassie’s directive,90% of the church’s Miimenan are currently transgressors of God’s directives because they routinely fail to partake in the holy communion. Unfortunately, the church is preoccupied with a lot of minor issues and is not focussed on this vital issue.

    Another very important issue facing the church is the prevailing extremely high level of corruption.

    Woul the Holy Synod focus, for a change, on the above important issues????????!!!!!!

  9. anonymous March 5, 2016 at 6:23 am Reply

    We need urgent solution. Church leaders should not be dictators! they should not divide the church by ethnicity and heresy! All Orthodox Christians, please please try to pray for our true fathers!

  10. Anonymous March 6, 2016 at 5:18 am Reply

    የቅዱስ ሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ በምን ተደመደመ

  11. Anonymous March 6, 2016 at 6:47 pm Reply

    በዐመጽ የተጀመረው የእነ አባ ማቴዎስና አባ ሉቃስ ስብሰባ በቅዱስ ፓትርያሪኩና በእውነተኞች አባቶች አስተዋይነት የተሞላው መልስ ልኩን አገኘ፡፡ የተስፋ የሰነቀው ፖለቲከኛው ማኅበርም የሐፍረት ካባ ተከናነበ፡፡ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ያለ ቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ፈጽመው ወደውጭ አልየዱም፤ ቢሄዱም ድግሞ የቤተክርስቲያኒቱ ወሰኛና ከማንም በላይ ተጠያቂ ናቸው፡፡ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ከቤተክርስቲያናችን ቀኖናና ዶግማ ከተላለፉ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ከዚህ አልፎ ወደ ውጭ ሄዱ አገር ጎበኙ ወዘተ. የሚለው ሐሳብ ውኃ የማይቋጥር ዋጋ ቢስ ነው፡፡
    አድዮስ የማቅ አቀንቃኞች

    • Anonymous March 7, 2016 at 6:52 pm Reply

      እረባክህ አልቀረብህም ሀሀሀሀሀሀሀ ሀሀሀ!!!!! በሐፍረት እሚከናነበውን አብረን እናየዋለን እድሜ ይስጠን ወንድሜ፡፡

  12. tadi wolde March 7, 2016 at 11:48 am Reply

    እውነቱን አይቶ የሚፈርደው ልዑል እግዚአብሄር እያለ አንተ ከአፉ ስጋ የተነጠቀ ውሻ ይመስል ምን አቅበዘበዘህ!! አንተ ስላልክ አይደለም ምእመኑ እውነቱን ሁሉ ያውቃል። የአባቶቻችንን ሃሳብ እግዚአብሄር አምላክ ያከናውን።

Leave a comment