ዋ/ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ: ፓትርያርኩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከቅ/ሲኖዶሱ ያጡትን ይኹንታ በአቋራጭ ለማግኘት ‘በመልካም አስተዳደር’ ስም የጠሩትን ስብሰባ ተቃወሙ!

  • ስብሰባው ፓትርያርኩ ‹‹አጥፍቸው እጠፋለኹ›› ባሉት ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ቅስቀሳ በማካሔድ በቅዱስ ሲኖዶሱ ላይ ጫና ለማሳደርና ለኃይል ርምጃ ምቹ ኹኔታ ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡

*         *        *

  • ‹‹ባላወጣነውና ባላጸደቅነው ሕግ ማኅበራትን መፈረጅና ሕገ ወጥ ማለት አንችልም፡፡››
  • ‹‹አቡነ ጳውሎስ በአማካሪዎች ክፋት ዕድሜያቸውን አሳጥረዋል፤ ቅዱስነትዎም ያስቡበት፡፡››
  • ‹‹ከአለቆችና ጸሐፊዎች ጋራ የተደረገው ውይይት አባቶች የተዘለፉበትና ያዘኑበት ነው፡፡››
  • ‹‹ለእገሌ ሚኒስትር እናገራለኹ፤ ለእገሌ ደኅንነት እደውላለኹ እያሉ አያስፈራሩን!!››

                                                                                /ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ/

*          *          *

(ምንጭ፡- አዲስ አድማስ፤ ቅፅ ፲፫ ቁጥር ፯፻፷፱፤ ጥቅምት ፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.)

His grace Abune Mathewos gen sec of the patriarchate

የመ/ፓ/ጠቅ/ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ተጠርቶ መስከረም ፳፯ እና ፳፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የተካሔደው ስብሰባ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ወቅታዊ ኹኔታ የማይገልጽ፣ መዋቅሩን ያልጠበቀ እና ጽ/ቤታቸው የማያውቀው መኾኑን በመግለጽ ተቃወሙ፡፡

‹‹የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልጸግ›› በሚል ርእስ ከትላንት በስቲያ በመንበረ ፓትርያርኩ አዳራሽ የግማሽ ቀን ስብሰባ በተደረገበት ወቅት፣ የፓትርያርክ አቡነ ማትያስን የመግቢያ ንግግር ተከትለው ቅድሚያውን በመውሰድ የተናገሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ÷ ‹‹አኹን ወደ ስብሰባው ስገባ ነው መልእክቱን የሰማኹት፤ አጀንዳውም ከመቅረቡ በፊት ከቋሚ ሲኖዶሱ ወይም ከእኔ ጋራ ምክክር አልተደረገበትም፤›› በማለት ስብሰባው መዋቅሩን ሳይጠብቅና ከዕውቅናቸው ውጭ የተጠራ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡

የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት አስተላልፎታል በተባለው የቃል ትእዛዝ መጠራቱ በተገለጸው በዚኹ ስብሰባ÷ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመምሪያዎች ዋናና ምክትል ሓላፊዎች፣ የየመምሪያው ዋና ክፍሎች ሓላፊዎች፣ የድርጅቶች ዋናና ምክትል ሥራ አስኪያጆች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአስተዳደር ሓላፊዎች፣ የዋና ክፍሎችና የክፍሎች ሓላፊዎች፣ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች ዋናና ምክትል ሥራ አስኪያጆች መሳተፋቸው ተገልጧል፡፡

በ፳፻፩ ዓ.ም. በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴ መቀጣጠሉን ተከትሎ የቀድሞው ፓትርያርክ መዋቅሩን ሳይከተሉና ከቅ/ሲኖዶሱ ጋራ ሳይመክሩ ወስደዋቸው ነበር ያሏቸውን ርምጃዎች በመቃወም በወቅቱ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ የነበሩት የአኹኑ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የሰጡት ቃለ ምልልስ በማስረጃነት ተይዞ እንደሚገኝ ያስታወሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ‹‹ቅዱስነትዎ በምትካቸው ሲቀመጡ መዋቅሩን ሊጠብቁ ይገባል፤ መዋቅሩን ሳይከተሉና ከሚመለከተው አካል ጋራ ሳይመክሩ የሚሠሩት ሥራ ቤተ ክርስቲያኒቱን አደጋ ላይ የሚጥል ነው፤›› እንዳሏቸው ተመልክቷል፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ ‹‹ውድቀት እንዳይደረስብዎ አማካሪዎችዎ ሊያዝንልዎ ይገባል፤›› ማለታቸውን የገለጹት የስብሰባው ተሳታፊዎች አያይዘውም ‹‹ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በአማካሪዎቻቸው ክፋት ከዕድሜያቸው ዐሥር ዓመት አሳጥረዋል፤ እርስዎም በአማካሪዎችዎ የተነሣ ዕድሜዎ እንዳያጥር ያስቡበት፤›› ሲሉ መምከራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ውይይቱን በሰብሳቢነት የመሩት ፓትርያርኩ፤ ‹‹በሥራ ባለመታገዛቸውና ብቻቸውን በመኾናቸው›› ስብሰባውን ወደ ታች ወርደው ለመጥራት እንደተገደዱ አስረድተዋል፡፡ ፓትርያርኩ ባቀረቡት በጽሑፍ የተደገፈ ገለጻ÷ በቤተ ክህነቱ የመልካም አስተዳደር ዕጦቶች እንዳሉ፣ በሙሰኝነት፣ በዘረኝነትና በአድሏዊነት የሚገለጹ የብልሹ አሠራር ሒደቶች እንደሚታዩ ዘርዝረዋል፡፡

በቤተ ክርስቲያን ስም የሚደራጁ ማኅበራትና ግለሰቦች ሕግና ደንብ እየጣሱ መዋቅሯን እየተፈታተኗት እንዳለና ከመዋቅራዊ ቁጥጥር ውጭ የሚንቀሳቀስ ሀብትና ንብረት እያካበቱ በመኾኑ አካሔዳቸው ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ጥንካሬና ህልውና ፍጹም አደጋ እንደኾነ አብራርተዋል፡፡ መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አንጻር ኹሉም የሥራ ሓላፊዎች ራሳቸውን በመፈተሽና በማጽዳት ችግሩን በዘላቂነት ለማስወገድ በሚደረግ ጥረት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፤ ያልተገባ ነው ያሉትን የማኅበራት አካሔድም ኹሉም ሊቃወመው ይገባል ብለዋል፡፡

ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ይወቁባቸው ስላሉት የአማካሪዎቻቸው ጉዳይም ‹‹አማካሪዎቼ ዓላማዬን የሚጋሩና የሚያስፈጽሙልኝ ሰዎች ናቸው፤›› ያሉት አቡነ ማትያስ ‹‹አኹንም የምቀጥልበት መኾኑን አሳውቃለኹ፤›› ብለዋል፡፡

[በስብሰባው የተሳተፉት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአስተዳደር ዋና ክፍል ሓላፊ፣ ‹‹አንድ ጣታችንን ወደሌላው ስንጠቁም ሦስቱ ወደ እኛ እንደሚያመለክት አንዘንጋ፤›› በማለት ፓትርያርኩ ስለ ሙስናና ብልሹ አሠራር፣ ስለ ጎጠኝነትና ብኩንነት፣ ፍትሕን ስለማጉደልና ንጹሑን ሰው ስለመበደል፣ ስለ ትጋት ማነስና አባቶችን ስለ መከፋፈል፣ ለምእመናን መልካም አርኣያ ስላለመኾንና ለሀገር አለመቆርቆር ሌሎችን ሲገሥጹና ሲኰንኑ ስለራሳቸውና ስለከበቧቸው አማካሪዎቻቸውም እንዲያስቡበት አስታውሰዋቸዋል፡፡]

‹‹ብቻዬን ነኝ፤ በሥራም አልታገዝኹም›› ለሚለው የፓትርያርኩ ወቀሳ ‹‹ቅዱስነትዎ አዝዘው ምን ያልተፈጸመ ነገር አለ?›› በሚል ምላሽ የሰጡት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ‹‹ያልተፈጸመ ነገር ካለ ለጉባኤው በይፋ ይገለጽ›› ሲሉ ጠይቀዋቸዋል፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግርና የችግሩ መገለጫዎች በርግጥም እንዳሉ ያልሸሸጉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ መምሪያዎችና ድርጅቶች የበጀት ዓመቱን ዕቅድ በማውጣት፣ የክንውን ሪፖርት በአስተዳደር ጉባኤ በየወቅቱ እንዲያቀርቡ፣ ድክመቶች እንዲስተካከሉና ጠንካራ ጎኖች ታቅበው እንዲቀጥሉ መደረጉን በመግለጽ በፓትርያርኩ ጽሑፍ የቀረቡትን መረጃዎች ወቅታዊነት ሞግተዋል፡፡

በልማት ተግባራትና በሠራተኞች አያያዝ ባለፈው በጀት ዓመት የተፈጸሙ ተግባራትን የዘረዘሩት የጽ/ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አባ ኃይለ ማርያም መለሰ በበኩላቸው፤ በጥናት በተደገፉና ቀጣይነት ባላቸው የመልካም አስተዳደር ማሻሻያዎች የሚቀርቡ ቅሬታዎችና የተጉላሉ ባለጉዳዮች አለመኖራቸውን ገልጸዋል፡፡ ምክትል ሥራ አስኪያጁ አክለውም፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን የፋይናንስ ፖሊሲና የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት ዘመናዊ ለማድረግ ዝግጅቱ መጠናቀቁን ጠቁመው ፓትርያርኩ በገለጻቸው የተጠቀሙባቸውን የችግር መግለጫዎችን አግባብነት እንደጠየቁ ታውቋል፡፡

mahibere kidusan

መንግሥት የሲቪል ማኅበራትን የሚከታተለው ሕግ አውጥቶና ተቋም መሥርቶ መኾኑን፣ በሕጉ እገዛለኹ ያለ አብሮ እንደሚጓዝ፣ በሕጉ አልተዳደርም ያለ እንደሚወጣ የተናገሩት ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ቤተ ክርስቲያን ግን መንፈሳውያን ማኅበራት የሚቋቋሙበት ሕግ እንዳላወጣችና የምታቅፍበት መዋቅር እንዳልዘረጋች ገልጸዋል፡፡ በአገልግሎት ላይ ያሉትን መንፈሳውያን ማኅበራት በሕገ ወጥነትና በመዋቅር ባለመታዘዝ ለመጠየቅና ለመፈረጅ ሕጉን አውጥቶ በሥራ ላይ ማዋሉ መቅድም እንዳለበት በማስገንዘብ የፓትርያርኩን ግምገማና አፈራረጅ እንደተገዳደሩት ተጠቅሷል፡፡

nebureed-elias-abreha[በተያያዘም የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ሓላፊና ከቀንደኛ አማሳኞች ኃይሌ ኣብርሃና ዘካርያስ ሐዲስ ጋራ በመኾን ስብሰባዎቹን ያስተባበረው የመዝባሪዎች አለቃ ኤልያስ ኣብርሃ፣ ‹‹ማኅበሩ ለሕግ የማይገዛና የማይታዘዝ ነው፤›› እያለ ስሙን ለይቶ ሳይጠራ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሰነዘረው ውንጀላ የብዙኃኑን የስብሰባውን ተሳታፊዎች ተቀባይነት እንዳላገኘ ተመልክቷል፡፡

በኹኔታው የተበሳጨው የሚ/ር ሺፈራው ቤተኛ ኤልያስ ኣብርሃ፣ ‹‹እንዴት ሕገ ወጥ አይደለም ትላላችኹ? አክራሪነትና ጽንፈኝነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አለ የሚባለው ከማኅበሩ ጋራ በተያያዘ ነው፤›› የሚል በእብሪትና ተንኰል የተሞላ ክሡ የስብሰባው የጋራ የአቋም መግለጫ ኾኖ እንዲወጣ አካሉ እስኪንዘፈዘፍ እየተወራጨ ያደረገው መፍጨርጨር በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ የሰከነ ምከታና ማኅበሩ እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነቱ በጥናት የታገዘ ምላሽ እንዲሰጠው በሚያሳስቡ የሥራ ባልደረቦቻቸው ጥረት እንዳልተሳካ ታውቋል፡፡

በልዩ ጽ/ቤት ሓላፊነቱ የብፁዕነታቸውን ጽ/ቤት የሥራ ሒደትም ለመቆጣጠር ከጅሎ ከፓትርያርኩ ጋራ አርቅቆ ለአስፈጻሚ አካላት ያሰራጨው ደብዳቤ በቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ ውድቅ የተደረገበት ኤልያስ ኣብርሃ ግን፤ በማኅበሩ ላይ የያዘውን መዋቅሩን የማፍረስ አቋም ለማሳካት የሕይወት መሥዋት እስከ መክፈል ድረስ ቁርጠኝነት እንዳለው በመግለጽ ብዙኃኑ ተሳታፊ ከደረሰበት መግባባት በትይዩ መቆሙን አስታውቋል፡፡]

በሌላ በኩል ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ‹‹ለኢትዮጵያ በረሓ ወርደው፣ ብረት አንሥተው የታገሉትና ዋጋ የከፈሉት ኹሉም ሕዝቦች ናቸው፤›› ብለው እንደተናገሩ የስብሰባው ተሳታፊዎች የጠቀሱ ሲኾን፣ ‹‹ሕገ መንግሥት ለኹሉም እኩል ነው፤ ለእገሌ ሚኒስትር እናገራለኹ፤ ለእገሌ ደኅንነት እደውላለኹ እያሉ አያስፈራሩን፤›› በማለት ፓትርያርኩን እንዳሳሰቧቸውም ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡

meeting on MK

‹‹የመልካም አስተዳደርን አስተሳሰብ ማበልጸግ›› በሚል ርእስ በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ትእዛዝ በአ/አ ሀ/ስብከት የተጠራው ስብሰባ በርግጥም ስለ ርእሱ የተደረገ ሳይኾን በማኅበረ ቅዱሳንና በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ቀንደኛው አማሳኝ ኃይሌ ኣብርሃ ቀድመው የተመረጡ ሰዎች ብቻ እንዲናገሩ በተፈቀደው ‘ውይይት’ ላይ ግልጽ አድርጓል፡፡ የስብሰባው እውነተኛ ዓላማ ደግሞ፣ ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል በይፋ ተነግሯል ከተባለው በተፃራሪ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ቅስቀሳ በማካሔድ ፓትርያርኩ በማኅበሩ ላይ የያዙት ውድቅ የተደረገ አቋም በቅዱስ ሲኖዶሱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ጫና ለመፍጠር አልያም ለኃይል ርምጃ ለማመቻቸት የታቀደበት እንደነበር ‘ንቡረ እድ’ ኤልያስ ኣብርሃ በመንበረ ፓትርያርኩ በተካሔደው ስብሰባ ባራመደው አቋም ግልጽ አድርጓል፡፡ (ፎቶ: አ/አበባ ሀ/ስብከት)

አቡነ ማትያስ በዚኹ ሳምንት ማክሰኞ፣ ከቋሚ ሲኖዶሱ ጋራ ሳይመክሩ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአድባራትና ገዳማት አለቆችና ጸሐፊዎች ጋራ ባደረጉት ስብሰባ፣ ማኅበረ ቅዱሳንን ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጋራ ደርበው በሚወነጅሉ አንዳንድ አማሳኝ አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች ብፁዓን አባቶችን ማዘለፋቸውን የጠቀሱት አቡነ ማቴዎስ፣ በዚኽም ኹሉም አባቶች ቅሬታ እንደተሰማቸውና እንዳዘኑባቸው በግልጽ ነግረዋቸዋል፡፡

ፓትርያርኩ ዓመቱን በሙሉ በየደረጃው እቀጥልበታለኹ ባሉት ስብሰባ÷ አጀንዳዎች መዋቅር ሳይጠብቁ፣ ጥናት ሳይደረግባቸውና ሳይብላሉ ውይይቱ ለሚዲያዎች ዘገባ ክፍት መደረጉ ቤተ ክርስቲያኒቷን ለአላስፈላጊ የውጭ ተጽዕኖና ለአጉል ትችት እንደሚያጋልጣት በተሳታፊዎች አስተያየት ተተችቷል፡፡

44 thoughts on “ዋ/ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ: ፓትርያርኩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከቅ/ሲኖዶሱ ያጡትን ይኹንታ በአቋራጭ ለማግኘት ‘በመልካም አስተዳደር’ ስም የጠሩትን ስብሰባ ተቃወሙ!

  1. TIRSIT WUBIE October 11, 2014 at 1:08 pm Reply

    አባታችን ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እንደ እርስዎ ያሉ አስተዋይ አባቶችን አያሳጣን በእውነት! ኑሩልን!!!አያሳጣን

    • Anonymous October 13, 2014 at 10:23 am Reply

      አባታችን ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እንደ እርስዎ ያሉ አስተዋይ አባቶችን አያሳጣን በእውነት! ኑሩልን!!!አያሳጣን

  2. Anonymous October 11, 2014 at 3:12 pm Reply

    please show video evidence about the meeting

  3. esayas October 11, 2014 at 6:58 pm Reply

    ዉጊያዉ ከእግዚአብሔር ጋር ነዉ!!!…….ከግብፅ ለምን ጳጳስ ይላክ እንደነበር አሁን ገባኝ ……እኛ ብቃት የሌለው አባት በብዛት ስላለን ነው በዚህ ዘመን እንኳን እያየን አይደለ?????

  4. Anonymous October 12, 2014 at 4:50 am Reply

    መልካም ያልሆነዉን እንዳናደርግ እግአብሄር ይርዳን!

  5. Anonymous October 12, 2014 at 9:56 am Reply

    Yaszinal!!! Ere Abbatochachin Yabertalin Bilachihu Tseliyu Wogen!!!!

  6. lulawit October 12, 2014 at 9:30 pm Reply

    Wugiyaw ke egziabher gar new!

  7. Anonymous October 13, 2014 at 5:35 am Reply

    lebona yesetache berteten entsely

  8. Anonymous October 13, 2014 at 6:38 am Reply

    አባታችን ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እንደ እርስዎ ያሉ አስተዋይ አባቶችን አያሳጣን በእውነት! ኑሩልን!!!አያሳጣን

  9. Anonymous October 13, 2014 at 7:45 am Reply

    Egziabhier Amilak bebytkirstianachinina bemahibrachin laye Yetensubinin asterare bytkirstian yitbikiln.Abatochim bstelotachihu asibun!!!

  10. Anonymous October 13, 2014 at 8:23 am Reply

    bestelot entiga

  11. Samuel October 13, 2014 at 8:30 am Reply

    ለአባታች ጤናውን ያድልልን ረጅም የአገልግሎት ዘመን የስጥልን፡፡ እንደ እርሳቸው ለእውነት ዘብ የሚቆሙ አባቶችን ያብዛልን እኛም ስለእውነት የምንመሰክርበትና ከእውነት ጎን የምንቆምበትን ብርታት ይስጠን፡፡ አሜን!!!ለአባታች ጤናውን ያድልልን ረጅም የአገልግሎት ዘመን የስጥልን፡፡ እንደ እርሳቸው ለእውነት ዘብ የሚቆሙ አባቶችን ያብዛልን እኛም ስለእውነት የምንመሰክርበትና ከእውነት ጎን የምንቆምበትን ብርታት ይስጠን፡፡ አሜን!!!

  12. Anonymous October 13, 2014 at 10:21 am Reply

    tirsit wubie anchi yeddiabilos ehet nesh malet new

  13. Anonymous October 13, 2014 at 11:02 am Reply

    I AM SO SORRY.GOOD AND BAD HISTORIES PASS BUT CHURCH WILL EXIST FOREVER! LET WE PRAY FOR GOD THIS ALL IS DEVILS WORK,TAKE US FROM OUR HOME TO HIS BAD AND EVER WOREST WORK.

    PRY FOR OUR UNITE!
    PRAY FOR CHURCH!
    PRAY FOR OUR FATHERS!
    PRAY FOR OUR COUNTRY!
    PRAY FOR OUR HISTORY!
    PRAY FOR OUR SELVES STRONGLY!

    GOD BLESS AND KEEP CHURCH!

  14. Anonymous October 13, 2014 at 12:53 pm Reply

    ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በስህተት መንገድ ውስጥ ያሉትን ፓትርያርክ መንገዳቸውን እንዲያጤኑት አሰላለፋቸው ከቤተ ክርስቲያን ወገን እንዲሆን የመከሯቸው እና ያደረጉት ጥረት የሚያስመሰግንዎ ሲሆን ሁሉም ብፁዓን አባቶች የእርሰዎን በጎ ተግባር ሕይወታቸውን ለሰጡላት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕልውና ሲሉ ሊደግሙት ይገባል፡፡
    በፓትርያርኩ ሀሳብና ተግባር ብናፍርም በጠ/ሥ/አስኪያጁ ስለኮራን ሌሎች አባቶቻችንም ልጆቻቸውን በመጠበቅ የአባትነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ በማመን ክርስቲያኖች በሙሉ የአባቶቼን ርስት አሳለፌ አልሰጥም ልንልና ልንጸና ይገባል፡፡

  15. Anonymous October 13, 2014 at 1:38 pm Reply

    Yrahylene enba ytemlkt amelake MK yemelketale !!!

  16. Anonymous October 13, 2014 at 4:47 pm Reply

    በእውነት እግዚአብሔር ፍርዱን ይሰጣል፥ በእውነት ስለእውነት ለቆሙት ብፁዓን አባቶች እንደነ ብፁዕ አቡነ ማቲዎስ ያሉትን እግዚአብሔር በጥበብ እና በድፍረት እንዲቀጥሉ እና መልካሙን ገድል እንዲጋደሉ የቅዱሳን አምላክ ከእርሳቸው ጋር እንዲሆን እንለምናለን። ለነዚህ ለቀረቡት ጽሑፎች ተጨባጭ ማስረጃ ብሎ አንድ ሰው ጠይቆ ነበር በሚከተለው ሊንክ ተጠቅመው ሙሉውን መመልከት ይችላሉ
    http://eotcssd.org/the-news/397-eotc-maheberat.html

  17. esaya October 13, 2014 at 9:30 pm Reply

    ልታዩት የሚገባ የስብሰባው አካል ልቦና ይስጠን

  18. esayas October 13, 2014 at 9:41 pm Reply

    abatathen betu abune matiwes erejem yeagelegelute edemai yesetelen be sewe fite yemesekerelejen enaime be abatai fite emesekereletalew yekadejen gen alawekewem awe kale heyewet yawemalen yemenegesetu werashe yekeberuw kedashe yaderegut ketadekane maheber ayeleyut yakuyelen enede eresu yale abate betekereseteyane yemiyasefelegebet weket laye nut enede hawareya eseke metheresh yatenawet bemeder waga likefelu yethelalu besemaye gen hasaiten yaderegalu denegel tela kelela tehunut

  19. esayas October 13, 2014 at 10:11 pm Reply

    ✔ፓትርያርኩ ለሾማቸው ኢሓዲግ ማህበረ ቅዱሳንን በማፋረስ ውለታ ሊመልሱ ይሆን…..???
    ★※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※★
    እኔ የማህበረ ቅዱሳን አባል አይለሁም ስለ ማህበሩ ድንቅና መልካም ሥራ ግን ምስክር ነኝ !ስለ ማህበሩ ሕያውና ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች ለመመስከር ደግሞ ኦርቶዶክስ መሆን ብቻ በቂ ነው………..
    ሰሞኑን ቀጠን ባለ የኢሓዲግ ትዕዛዝ ከቅ/ሲኖዶስ እውቅና ውጭ መዋቅሩን ባልጠበቀና ከስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ባፈነገጠ መልኩ ብፁዕ ወቅዱስ አብነ ማቲያስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ጋር ባደረጉ ስብሰባ ባልተለመደ መልኩ ግልፅ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻና አስነዋሪ ከአባቶች የማይጠበቅ በፀያፍ ንግግር የተሞላ አንገታችንን ያስደፋን አሳፋሪ አስተያየቶችን ቁጭ ብለው አንገታቸውን እየነቀነቁ ሲያስተናግዱ አረፈዱ……የሚገርመው ነገር ተናጋሪዎቹ በመንግስት ካድሬ አይዞ የተባሉ በሥነ ምግባር የዘቀጡ በሙስናና በስርቆት የደለቡ በልማት ስም የተሰሩ የአድባራቱን ህንፃዎች ለመናፍቅና እስላም እያከራዩ ኪሳቸውን የሞሉ ባዶ እጃቸውን መጥተው ቤ/ያኒቱን ዘርፈው ቪላ ቤት መኪና ገዝተው ባለ አራትና አምስት ኮከብ ሆቴል ያጣበቡ ውስኪ እየተራጩ የሚዳሩ በእንጦንስና በመቃርስ ቆብ የሚያላግጡ እግዚያብሄርን የማያውቁ የእግዛብሄር ሰዎች የቤ/ያን ዳር ድንበር መስፋት የቀኖናና ዶግማ መፋለስ የተሐድሶ ዘመቻ የመንጋው መበተን የማይደንቃቸው ስለሆዳቸው ብቻ የሚያስቡ ነውረኞች እነዚህ ነው እንግዲ ፓትርያርኩ ሰብስበው ማህበረ ቅዱሣን ለማፍረስ ሲዶልቱ የዋሉት…..እኔ የምለው ለመሆኑ የአሸባሪነት ጉዳይ የመንግስት እንጂ የቤተ ክርስቲያን አጀንዳ ነው እንዴ? እረ ብዙ አንገብጋቢ የቤ/ያቱ አስቸኩዋይ ጉዳዮች እያሉ አክራሪነት፣ አሸባሪነት፣የትራንስፎርሜሽን እቅድ፣ህዳሴ ግድብ ፓትርያርኩን ምን አገባቸው ? ነው ወይስ ወደ ፕትርክና መንበር ያመጣቸውን ኢሓዲግ ታማኝነታቸውንና ታዛዥነታቸውን ለማሳየት ነው? ለነገሩ ከስልጣኑ ጋር የተቀበሉትን ማሕበረ ቅዱሳንን የማፍረስ ተልዕኮአቸውን በይፋ መጀመራቸው ነው፣ ለነገሩ ማህበሩ በመንግስት ይሁንታና በፖትርያርኩ ፈቃድ ሳይሆን በፈቃደ እግዚአብሄር በቅዱሳን ፀሎት በፃድቃን ሰማዕታት ተራዳይነት በድንግል ማርያም ምልጃ ነው የተመሰረተው ነገም በእግዚያብሄር ጥበቃ ወደፊት መጓዙን ይቀጥላል!……..አባታችን ይልቅ ማህበሩን ተጠግተው እርቃናቸውን ቢሸፍኑ መልካም ነበር ሲኖዶሱም እንደራሴ ሾሞላቸው ቅዱስነታቸው ከተጠናወታቸው የአልዛይመር (የመርሳት ችግር)በሽታ በጊዜ ቢያገግሙ መልካም ነው ያለዚያ የዚህን ግራ የገባው መንግስት ምክር እየተቀበሉ ጉድ እንዳያደርጉን……….የተዋህዶ ልጆ ንቁ የማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ነው ያገባናል የመናፍቃንና የአህዛብ ብሎም የተሐድሶች የጎን ውጋት የህገወጥ መነኮሳት ቀበኛ የሆነ ማህበር ለነ ሆዶና ከርሶ አልመች ስላለ ማህበሩን አፍርሰው ቤ/ያኒቱን ወረው ሊቀራመቷት ነውና አንድ ሆነን ለማህበሩ ህልውና እንፀልይ ከውስጥና ከውጭ ጠላት እንከላከለው በቅዱሳን ምልጃና ፀሎት ተዋህዶ እስካለች ማህበሩ ለዘላለም ይኖራል !!!
    ✔በዲ/ን አብርሃም ወርቁ ወ/ሰንበት
    ✔ጥቅምት ፳፻፯
    ✔ፓትርያርኩ ለሾማቸው ኢሓዲግ ማህበረ ቅዱሳንን በማፋረስ ውለታ ሊመልሱ ይሆን…..???
    ★※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※★
    እኔ የማህበረ ቅዱሳን አባል አይለሁም ስለ ማህበሩ ድንቅና መልካም ሥራ ግን ምስክር ነኝ !ስለ ማህበሩ ሕያውና ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች ለመመስከር ደግሞ ኦርቶዶክስ መሆን ብቻ በቂ ነው………..
    ሰሞኑን ቀጠን ባለ የኢሓዲግ ትዕዛዝ ከቅ/ሲኖዶስ እውቅና ውጭ መዋቅሩን ባልጠበቀና ከስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ባፈነገጠ መልኩ ብፁዕ ወቅዱስ አብነ ማቲያስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ጋር ባደረጉ ስብሰባ ባልተለመደ መልኩ ግልፅ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻና አስነዋሪ ከአባቶች የማይጠበቅ በፀያፍ ንግግር የተሞላ አንገታችንን ያስደፋን አሳፋሪ አስተያየቶችን ቁጭ ብለው አንገታቸውን እየነቀነቁ ሲያስተናግዱ አረፈዱ……የሚገርመው ነገር ተናጋሪዎቹ በመንግስት ካድሬ አይዞ የተባሉ በሥነ ምግባር የዘቀጡ በሙስናና በስርቆት የደለቡ በልማት ስም የተሰሩ የአድባራቱን ህንፃዎች ለመናፍቅና እስላም እያከራዩ ኪሳቸውን የሞሉ ባዶ እጃቸውን መጥተው ቤ/ያኒቱን ዘርፈው ቪላ ቤት መኪና ገዝተው ባለ አራትና አምስት ኮከብ ሆቴል ያጣበቡ ውስኪ እየተራጩ የሚዳሩ በእንጦንስና በመቃርስ ቆብ የሚያላግጡ እግዚያብሄርን የማያውቁ የእግዛብሄር ሰዎች የቤ/ያን ዳር ድንበር መስፋት የቀኖናና ዶግማ መፋለስ የተሐድሶ ዘመቻ የመንጋው መበተን የማይደንቃቸው ስለሆዳቸው ብቻ የሚያስቡ ነውረኞች እነዚህ ነው እንግዲ ፓትርያርኩ ሰብስበው ማህበረ ቅዱሣን ለማፍረስ ሲዶልቱ የዋሉት…..እኔ የምለው ለመሆኑ የአሸባሪነት ጉዳይ የመንግስት እንጂ የቤተ ክርስቲያን አጀንዳ ነው እንዴ? እረ ብዙ አንገብጋቢ የቤ/ያቱ አስቸኩዋይ ጉዳዮች እያሉ አክራሪነት፣ አሸባሪነት፣የትራንስፎርሜሽን እቅድ፣ህዳሴ ግድብ ፓትርያርኩን ምን አገባቸው ? ነው ወይስ ወደ ፕትርክና መንበር ያመጣቸውን ኢሓዲግ ታማኝነታቸውንና ታዛዥነታቸውን ለማሳየት ነው? ለነገሩ ከስልጣኑ ጋር የተቀበሉትን ማሕበረ ቅዱሳንን የማፍረስ ተልዕኮአቸውን በይፋ መጀመራቸው ነው፣ ለነገሩ ማህበሩ በመንግስት ይሁንታና በፖትርያርኩ ፈቃድ ሳይሆን በፈቃደ እግዚአብሄር በቅዱሳን ፀሎት በፃድቃን ሰማዕታት ተራዳይነት በድንግል ማርያም ምልጃ ነው የተመሰረተው ነገም በእግዚያብሄር ጥበቃ ወደፊት መጓዙን ይቀጥላል!……..አባታችን ይልቅ ማህበሩን ተጠግተው እርቃናቸውን ቢሸፍኑ መልካም ነበር ሲኖዶሱም እንደራሴ ሾሞላቸው ቅዱስነታቸው ከተጠናወታቸው የአልዛይመር (የመርሳት ችግር)በሽታ በጊዜ ቢያገግሙ መልካም ነው ያለዚያ የዚህን ግራ የገባው መንግስት ምክር እየተቀበሉ ጉድ እንዳያደርጉን……….የተዋህዶ ልጆ ንቁ የማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ነው ያገባናል የመናፍቃንና የአህዛብ ብሎም የተሐድሶች የጎን ውጋት የህገወጥ መነኮሳት ቀበኛ የሆነ ማህበር ለነ ሆዶና ከርሶ አልመች ስላለ ማህበሩን አፍርሰው ቤ/ያኒቱን ወረው ሊቀራመቷት ነውና አንድ ሆነን ለማህበሩ ህልውና እንፀልይ ከውስጥና ከውጭ ጠላት እንከላከለው በቅዱሳን ምልጃና ፀሎት ተዋህዶ እስካለች ማህበሩ ለዘላለም ይኖራል !!!
    ✔በዲ/ን አብርሃም ወርቁ ወ/ሰንበት
    ✔ጥቅምት ፳፻፯
    LikeLike · · Share

  20. Anonymous October 14, 2014 at 7:20 am Reply

    patriyarikun litgelut new mesel edmwo endayatr alachihu enante eko ataregutm aybalm balegewoch nachihu

  21. Tiruwork Abera October 14, 2014 at 7:33 am Reply

    በወንጌሉ አንዲትን ሀገር ያለአንድ ቅዱሳን አልተዋትም ያለው አምላክ ለአባታችን እድሜና ጤና ይስጥልን በአቋምዎ ያጽናዎት አሁንም የእርስዎ አይነት አባቶችን ስለእውነት የሚቆረቆሩትን ያብዛልን ለሌሎቹም እግዚአብሔር ልቦናና ማስተዋል ይስጥልን!!!

  22. Anonymous October 14, 2014 at 1:14 pm Reply

    no way, his holiness Abune Matia become Soldier for Dyabilos because of our sins. It is we need to cry at large

    Tesfa ze mercato

  23. tekle giorgis October 14, 2014 at 11:34 pm Reply

    Tewahedo Bete Kristianen yemitebek AMANUEL ayetegnam. Patriarik pop Matias think about it.danger will came soon.

  24. Anonymous October 15, 2014 at 8:09 am Reply

    Ere ebakachuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuu Ere Bemariyam Hulachum besga new yalachut eski be’egziabhier menfes tekagne. Betekhenetem hone MK yalachue sewoche benatachu behodachu atasbu bizu neger enawkalen teqwamatin atasedbu. Bietekrstiyan lememedeb eko 10-500000 birr gubo eyetekebelachu aydel enantem bihon MK dejocheshe ayzegu eyalachu yerasachun bere yemtkeftu tetenkeku. Ybekachewal

    • Anonymous October 15, 2014 at 3:04 pm Reply

      Astewul wondime! wore bicha atsma! yalayehewun neger atawra! zim betel aygodlebehem, yematawkewun betenager gen Egziabheren taskeyimaleh!

  25. Anonymous October 15, 2014 at 3:01 pm Reply

    ኃይል የእግዚአብሔር ነወ! በተንኮል የተነሱ ሁሉ ደግሞ ይጠፋሉ! ይህንንም ዓይተናል፡፡ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን! መልካም እረኛ አያሳጣን፡፡ አጽራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን፡፡ አባቶቻችንን እንደ ንንስጥሮስ ከመሆን ይጠብቅልን!!!

  26. Mihret Mekonnen October 15, 2014 at 3:59 pm Reply

    ዓሀ የነቂያ ጉባዔ ዌሳኔ ኧኔንም ገባኝ፡፡ኧንደነ ዓባ ሽኖዳ ያለ ለሀይማኖቱና ለዕውነት የቆመ ኢትዮጵያዊ ፓትርያረክ ኣንዳንድ ጊዜ ላይኖር ዕንደሚችል ተረድተው ነበር።እግዚአብሄር ይገስጸወት፡ ድንግል ልቦናወት ዕንዲመለስ ትርዳወት።አሜን !

  27. Anonymous October 15, 2014 at 4:08 pm Reply

    የአቡነ ጳውሎስን ዘመነ መንግስት እንበለው በየሚድያው ሲተቹ የነበሩሰው ናቸው ዛሬ ታዲያ ምን ነካቸው ሳይነጹ ወንድምን መተቸት እንዲህ ትዝብት ላይ ይጥላልና ቀጣይ ተሿሚዎች ልብ በሉት እድሜአቸው እንዳያጥር እኛ ልጆቻቸውም እንጸልያለን

  28. Anonymous October 15, 2014 at 4:20 pm Reply

    የአቡነ ጳውሎስን በየሚዲያው ሲተቹ በሌላ እንኳ አይደል በራሳቸው ዘመን የባሱ ሆኑና እርፍአሉት ሳይነጹ ወንድምን መተቸት እንዲህ ያጋልጣል

  29. tadu October 16, 2014 at 2:29 pm Reply

    ዘመኑ የወንጌሉ ቃል የሚፈፀምበት ወቅት በመሆኑ የኣባቶች ስህተት ላይ መውደቅ አይገርምም!! ግን ማ.ቅዱሳን የቆመው በሰው ፍላጎት አይምሰላችሁ በእግዚኣብሄር እንጂ፤
    ይብላኝላቸው እንደ ይሁዳ ለጠፉት እነጂ እግዚኣብሄር የተከለውን ማ.ቅዱሳን ንዋይና ፖለቲካ ባሰከራቸው የዲያብሎስ መልእክተኞች ሊጠፋ አይችልም።

  30. Anonymous October 17, 2014 at 3:30 pm Reply

    oh ! God . do not live us alone ! time is 666 the king is devil .he is coming clothing as bishop holding the cross . this is over may God bless this year.
    Amen!

  31. Anonymous October 17, 2014 at 3:43 pm Reply

    666 is the time ! devil is released in the form of bishop! clothing ,holding cross, may be last time to be opened .

  32. Anonymous October 19, 2014 at 12:21 am Reply

    Bewnate!lene tayelachaw yegabal lala fatana !!! Ferdelen gata!!

  33. ተተ October 20, 2014 at 11:35 am Reply

    ዋ! ምድረ ሆዳም እና የቤተክርስትያን ደም መጣጭ ሁላ ከማ.ቅዱሳን ሳይሆን ከፈጣሪህ እንደተጣላህ የምታስተውልበት አእምሮህን እንዳጣህ እወቅ!!

  34. Anonymous October 20, 2014 at 11:47 am Reply

    የተዋህዶ ልጆች ማ.ቅ አይዞኣችሁ ልጆቼ። እናንተ መንፈስ ቅዱስ ባቀበላችሁ ብዙ ታውቃላችሁ። ይህች ምድር ለኣምላክዋም ፈተና ነበረች እና በእሱ ሃይል ፅኑ! ፍዳው የሚብሰው እያወቁ ላላወቁ ነው። ሁላችንንም ከዚህ አይነቱ ማስተዋል ማጣት ወይም ትንቢት መፈፀሚያ መሆን ያድነን!!

  35. tadu October 21, 2014 at 2:34 pm Reply

    በህግ አልገዛ ያለው አጠቃላይ የቤተክህነቱ አሳተዳደር እንጂ የማህበረ ቅዱሳን አገልግሎት አይደለም። ማ.ቅ. በቤተክህነቱ የእዝ ሰንሰለት ውስጥ ለመግባት በመጀመሪያ ቤተክህነቱን እንደትኋን ከሚበሏት ካህን ወይም አገልጋይ እና ከማንም በላይ ለቤተክርስትያን ተቆርቋሪ ነን ባዮች ለማፅዳት ቁልፍ የሆነ የአሰራር ስርአት መዘርጋት አለበት፤ የማ.ቅ.አብይ አላማ ይህ ነው። አእምሮ እና ማስተዋል ያለው ሁሉ ይህን ያውቃል። ምእመኑ ሳይተርፈው ቤተክርስቲያኔን ላሳድግ፤ ሃይማኖቴ ትጠንክር ብሎ የሚለግሰውን ከኪሳቸው እንዳይወጣ የበግ ለምድ በመልበስ ቤተክርስትያኒቱ ውስጥ በመሰግሰግ የቤተክርስቲያኗን እድገት ወደታች፤ ምእመኑን ወደ እናት ቤተክርስትያን ከመሰብሰብ ይልቅ በክፉ ምግባራቸው መበተን፤ ወንጌል በመናፍቃን እና በተሃድሶዎች በየቤተክርስቲያኒቱ እንዲሰበክ ማድረግ፤ በየቤተክርስትያኑ ፍቅር እንዲጠፋ ማድረግ፤ የቤተክርስትያን ቅርስ እንዲዘረፍ ማድረግ፤ ምእመኑ የሃይማኖቱን ትሩፋት ጠብቆ እንዳይሄድ የሚያደርጉ እና አትስረቅ እያሉ የሚሰርቁ፤ አታመንዝር እያሉ የሚያመነዝሩ፤ አትሳደብ እያሉ የሚሳደቡ፤ ማ.ቅ.ንን ቢወነጅሉ አይፈረድባቸውም። ምክንያቱም አምላክ የሰጣቸውን ሓዋሪያዊ ተልእኮ ለስጋዊ ጥቅም በመሸጥ ባለፉበት፣ ባልደከሙበት የቤተክርስትያኒቱ ሃብት የቅንጦት ኑሮ ላይ ስላሉ የማ.ቅ.ጉዳይ የእግር እሾህ ቢሆንባቸው አይገርምም ። ይህ ድሮም ይታወቃል እሰከ ዛሬም መቆየታቸው አይዞኣችሁ ግፉበት የሚላቸው ጠፍቶ እንጂ። ታድያ ለፍጥረቱ የሚያስብ እግዚኣብሄር ማረፊያ ቢያጣ ለነዚህ ልጆች ጸጋውን አብዝቶ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ የወጣቱ ተረካቢ ማጣት፤ የምእመኑ ከቤተክርስትያን መራቅ እና ወንጌል መራብ የቤተክርስትያን ቅርስ መጥፋት፤ ቢያሳስባቸው ወደ ኣባቶች ቢጮሁ ሰሚ ማጣታቸው፤ እንቅልፍ ሳያምራቸው ከደምወዛቸው ቆርሰው ፈጣሪ በሰጣቸው እውቀት ካለዋጋ እንዲያገለግሉ አምላክ መረጣቸው። ስለዚህ ከኣባቶች የሚጠበቀው የስራቸውን ፍሬ አይተው ልጆቼ በርቱ እናንተም አግዙን እኛም እንርዳችሁ የኛ ተተኪዎች እናንተ ናችሁ ማለት ነበር እግዜር ልቦና ቢሰጣቸው። አሁንም እዝነ ልቦናቸውን ያብራላቸው! የንስሃ እድሜ ይስጣቸው! ማ.ቅ. ገንዘብ ቢሰበስብ የወደቁትን ኣነሳበት፤ ወንጌል አስተማረበት ፤ ምእመኑን ወደ እናት ቤተክርስትያን መለሰበት፤ ቤተክርስትያን አነፀበት፤ የተበተኑትን ሰበሰበበት፤ ቅርስ አኖረበት እንጂ የውሃ ጠብታ ወደ ጉሮሮው ኣላከበትም!!! ኣላማውም ስላልሆነ።

  36. Anonymous October 22, 2014 at 7:51 am Reply

    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ ሜን ፡፡!!!
    የአባቶቻችነን ጉባኤ ሲባረክ ሲቀድስ የቆየ ልዑለ ባሕሪ ሀያው አምላክ …ዛሬም ያባቶቻችነን ጉባኤ ትባርክልን ዘንድ እንለምንህ አልን… መልካም ልቦና ለተነሳቸዉ ..መለካሙን ልቦና አድልልን …አሜን፡፡!!!
    ዛሬም እንደትናንቱ ለቤተክርስቲያናችን መልካሙን ሁሉ ድርገለነ…!!!

  37. fekadieayalew October 22, 2014 at 7:59 am Reply

    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ ሜን ፡፡!!!
    የአባቶቻችነን ጉባኤ ሲባረክ ሲቀድስ የቆየ ልዑለ ባሕሪ ሀያው አምላክ …ዛሬም ያባቶቻችነን ጉባኤ ትባርክልን ዘንድ እንለምንህ አልን… መልካም ልቦና ለተነሳቸዉ ..መለካሙን ልቦና አድልልን …አሜን፡፡!!!
    ዛሬም እንደትናንቱ ለቤተክርስቲያናችን መልካሙን ሁሉ ድርገለነ…!!!

    • g/silasie w/amanuel October 28, 2014 at 7:20 pm Reply

      በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ ሜን ፡፡!!!
      የአባቶቻችነን ጉባኤ ሲባረክ ሲቀድስ የቆየ ልዑለ ባሕሪ ሀያው አምላክ …ዛሬም ያባቶቻችነን ጉባኤ ትባርክልን ዘንድ እንለምንህ አልን… መልካም ልቦና ለተነሳቸዉ ..መለካሙን ልቦና አድልልን …አሜን፡፡!!!
      ዛሬም እንደትናንቱ ለቤተክርስቲያናችን መልካሙን ሁሉ ድርገለነ…!!!

  38. Anonymous March 22, 2015 at 1:29 am Reply

    Egnih patriarc akahedachew wedet eyamera new? Gena legena besilitan yebalegutin zerochachewun lemedebek silu haimanotachewun eyekadu eko new. Yih eko yafetete ewnet new eskemeche keewnet gar tegaftew yichilutal? Mahiberu endehon yemelaw Ethiopia biheroch enji yand wegen aydele. Yolikunis lemin yemahiberun ewnetegnana zemenawi aserar aykorijum? Ahun yeyazut yegosegninet aserar eko bezih wekit zelakinet yelewum; sewu eko yerasin aemiro yitekemal, ewnetina hasetun leyito yawkal. Ere gize sayalifibewot lezihich betekiristian ewnet meskirew zerochiwo biyatefuwot enkua semaetnet yihoniliwotal!

  39. Anonymous January 29, 2016 at 4:29 am Reply

    እግዚአብሔር አምላክ ለቤተክርስቲያ መሪዎች በሙሉ ልቦና ይስጥልን፡

  40. Anonymous January 30, 2016 at 3:06 pm Reply

    Egziabher Amlak endi be haymanot yekomutin abatoch ayasatan ye bitsuh abatchin Abune mathewosign edme yarzimilign.

  41. berhan haile January 31, 2016 at 4:16 am Reply

    መልካም ያልሆነዉን እንዳናደርግ እግአብሄር ይርዳን

Leave a reply to Anonymous Cancel reply