በደ/ኦሞ: በሀ/ስብከቱ እና በማኅበረ ቅዱሳን መተባበር ከ16 ሺሕ በላይ ምእመናን ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ተጨመሩ፤ ‹‹ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ ደስታ ነው›› /ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ/

baptism and church inaguration Jinka 2007the newly consecrated Jinka Dabre Keraniyo Medhanielm church

  • ከ1300 በላይ አዲስ አማንያን በቅዱስ ፓትርያርኩ እና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተጠመቁ
  • በዓመቱ 17‚000 አዲስ አማኞችን ለማፍራት በመርሐ ግብር የተያዘው ዕቅድ አካል ነው
  • ከተጠማቂዎቹ፣ ከባዕድ አምልኮ የተመለሱ አርብቶ አደሮች እንደሚገኙበት ተመልክቷል

*              *              *

ተጠማቂዎች ከየስብከት ኬላዎች ወደ ጂንካ ለጥምቀተ ክርስትና ሲገጓዙ

ተጠማቂዎች በታላቅ መንፈስ ከየስብከት ኬላዎች ወደ ጂንካ ለጥምቀተ ክርስትና ሲያመሩ

ተጠማቂዎች ወደ ጥምቀተ ክርስትና በጉዞ ላይበዲዛይን ሥራው የማኅበረ ቅዱሳን ሞያዊ አስተዋፅኦ ከተገለጸበት አዲሱ የጂንካ ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት (ምረቃ) ጋራ ጥምቀተ ክርስትና የተፈጸመላቸውና ከሰባት የስብከት ኬላዎች የተውጣጡት 1350 ምእመናን ጂንካ የደረሱት ከየስብከት ኬላዎቻቸው (ሼፒ ጋኢላ፣ አልጋ ኪለት፣ ዛቢ፣ ጉርጨት፣ ሰንሰለት፣ አይዳ እና ጋራ) ለሰዓታት በእግራቸው ተጉዘው ነው፡፡

የሀገረ ስብከቱን ነባር አብያተ ክርስቲያን በመደገፍና አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በማነፅ ላይ አተኩሮ የሚንቀሳቀሰው የደቡብ ኦሞ የስብከተ ወንጌል፣ የልማት እና ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ ለጥምቀተ ክርስትናው መከናወን የገንዘብና ከፍተኛ የቁሳቁስ እገዛ አድርጓል፡፡

ኮሚቴው በጂንካ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም በ45 ሚልዮን ብር ወጪ ለሚያሠራው የአብነት ት/ቤት ግንባታ እና ለሚያከናውናቸው የልማት ተግባራት ፓትርያርኩ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠዋል፡፡

*                *               *

the newly convert cathecumen being baptized

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በጥምቀተ ክርስትና

ጠረፋማ የአገራችን አካባቢዎች አተኩሮ በሚካሔደውና ከ፳፻፫ – ፳፻፲፩ ዓ.ም. የተዘረጋው የማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራም ከተጀመረ ወዲህ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተጨመሩት አዲስ አማኞች ጠቅላላ ቁጥር ከ26 ሺሕ በላይ መድረሱ ተገልጧል፡፡

በ፳፻፭ ዓ.ም. የአገልግሎት ዓመት መርሐ ግብሩ በሸፈናቸው የጉምዝ፣ ካፋ(ጫራ) እና ደቡብ ኦሞ አካባቢዎች በተከናውነው ጥምቀት ክርስትና 8,744 አዲስ አማኞች የቅድስት ሥላሴ ልጅነት እንዲያገኙ የተደረገ ሲኾን በተያዘው የ፳፻፯ ዓ.ም. የአገልግሎት ዓመት በአምስት ቦታዎች 17‚000 አዲስ አማንያንን ለማፍራትና የተጨመሩትን ምእመናን ለማጽናት ከብር አምስት ሚልዮን በላይ በጀት በመርሐ ግብሩ ተይዟል፡

being baptized

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በጥምቀተ ክርስትና

ሀብተ ውልድና ጥምቀተ ክርስትና አግኝተው ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን የተመለሱትን ምእመናን የሚያጸኑ የትግበራ ዕቅዶች ከአህጉረ ስብከት፣ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያንና ከሰንበት ት/ቤቶች ጋራ በመቀናጀት ይፈጸማሉ፡፡

ተጠማቅያኑ የሚገለገሉበት ቤተ ክርስቲያን መትከል፣ በቋንቋቸው የሚያስተምሯቸውን ሰባክያንና ካህናት ማሠልጠን፣ በቋንቋቸው የሚማሩባቸውን ጉባኤያት እና ሐዋርያዊ ጉዞዎች ማካሔድ፣ የተለያዩ የኅትመት ውጤቶችን (የትምህርት መጻሕፍትንና በራሪ ጽሑፎችን፣ የስብከት እና የመዝሙር ካሴቶችንና ሲዲዎችን) ማዘጋጀትና ማሰራጨት ተጠቃሽ የመተግበርያ ስልቶች ናቸው፡፡

one of sibket kelas(Merafe Sibket)

ቤተ ክርስቲያን ባልተተከለባቸው የገጠር ቀበሌዎች የሚቋቋሙት የስብከት ኬላዎች÷ በቅድመ ጥምቀት የተጠማቂ ምእመናን ቅስቀሳና ሥልጠና፤ በጊዜ ጥምቀት የተጠማቂ ምእመናን ዝግጅት እና በድኅረ ጥምቀት ተጠማቂ ምእመናንን በተከታታይ ትምህርትና የአብነት ትምህርት የማጽናት አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡ የስብከት ኬላዎች/ምዕራፈ ስብከት/ የተሟላ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የሚያስፈልጓቸው የትግበራ ቁሳቁሶች በማስፋፊያ መርሐ ግብሩ ወጪ የሚሸፈን ሲኾን አዲስ ምእመናን እንዲጨመሩና የተጨመሩትም እንዲጸኑ በየቋንቋው የሚያስተምሩ ሰባክያነ ወንጌልም የገንዘብ ድጎማ ይደረግላቸዋል፡፡


አዲስ አማኞችን በማጥመቅ፣ ያሉትን በማጽናትና የካዱትን በመመለስ ላይ ባተኮረው የማስፋፊያ መርሐ ግብሩ÷ የምእመናንን ቁጥር ጨምሯል፤ በቋንቋ የሚያገለግሉና ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑ ካህናትን ለማፍራትና የሰባክያንን ቁጥር ለማሳደግ ተችሏል፤ የሰንበት ት/ቤቶች አገልግሎት ተጠናክሯል፡፡ በቋንቋ የሚያስተምሩ ደቀ መዛሙርት እጥረት፣ የገንዘብ አቅም ማነስና በቂ መጓጓዣ አለመኖር የፕሮግራሙ ዋነኛ ችግሮች ናቸው፡፡

*               *                *

Lique Tiguhan Wondewosen Gabre Sellassieይህ ያለእግዚአብሔር ርዳታ ከፍጻሜ አይደርስም፡፡ በክንዳችን ውስጥ የእግዚአብሔር ክንድ ስላለ በኻያ ዓመት የማያልቀውን ይህን ሕንፃ በአምስት ዓመት ለማጠናቀቅ የረዳን እግዚአብሔር ነው፡፡

ሌላም ብሥራት አለ! የሚገርመው ነገር፣ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ በሚመረቅበት በዚኽ ዕለት 1350 ሕንፃ ሥላሴ በዛሬው ዕለት ተጠምቀው የእናት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ኾነዋል፡፡ ይህ ቀላል አይደለም፡፡ ሕንፃ ሥላሴን ሊባርኩ፣ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑን ሊመርቁ የመጡት ቅዱስ አባታችን ከዚኽ የበለጠ ደስታ የላቸውምና እግዚአብሔር የተመሰገነ ይኹን፡፡

እንደምታውቁት ስብከተ ወንጌሉን በዞኑ[በሀገረ ስብከቱ] ኹሉ ለማዳረስ ሀገረ ስብከታችን አቅም የለውም፤ ነገር ግን የማኅበረ ቅዱሳን ጂንካ ማእከል ከብፁዕነታቸው[አቡነ ኤልያስ] መመሪያ በመቀበልና ከሀገረ ስብከቱ ጋራ በመተባበር ከ፳፻፬ – ፳፻፯ ዓ.ም. 16‚630 ሰዎች በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ተጠምቀዋል፡፡ ደስ ይበላችኹ! በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ከ፳፻፬ – ፳፻፯ ዓ.ም. የዛሬውን ጨምሮ 16‚630 ሰዎች ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተጨምረዋል፡፡ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይኹን፡፡

/የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ
ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ወንድወሰን ገብረ ሥላሴ/


the convert fathfuls being baptizedበዛሬው ዕለት ሀብተ ውልድና ጥምቀተ ክርስትና የተቀበላችኹ ወገኖች ኹሉ፣ እንኳን ደስ አላችኹ፡፡ ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ ትብብር ስላለ ነው ለዚኽ ውጤት የበቃችኹት፡፡ ዛሬ የቤተ ክርስቲያን ደስታዋ የተፈጸመበት ቀን ነው፡፡ ይኸውም አንደኛ፡- ገንዘባችኹን፣ ዕውቀታችኹን፣ ጊዜአችኹንና ጉልበታችኹን መሥዋዕት አድርጋችኹ ግሩም ድንቅ የኾነ ቤተ ክርስቲያን በመሥራታችኹ ደስ ብሎናል፤ ደስ ሊላችኹ ይገባል፡፡ ከዚኽ በላይ ደግሞ 1350 አዲስ ክርስቲያኖች ተጨምረዋል፡፡ ይህ ለቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ደስታ ነው፡፡ ነገ ከነገ ወዲያ ደግሞ እንዲኹ እያለ ያድጋል ማለት ነው፡፡ በእውነቱ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ እናንተን ይዘው ብዙ ሥራ ሠርተዋል፡፡ ትጉህ አባት፣ ትጉህ ሐዋርያ ናቸው፤ በእናንተ ፊት ላመሰግናቸው እወዳለኹ፡፡

ጂንካ ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን Jinka dabre Keraniyo Medhanialem

ቅዳሴ ቤቱ የተከናወነው የደ/ኦሞ ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን

ምእመናን ከእግዚአብሔር ጋራ የሚገናኙበት ቤተ ክርስቲያን አምሮ ሠምሮ በመሠራቱ አዲስ ምእመናን መጨመራቸው ይቀጥላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ሰባክያን፣ መምህራንና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሕዝቡን ጠንክራችኹ ማስተማርና ወደ ክርስቶስ ጉባኤ እንዲጨመሩ ማድረግ አለባችኹ፡፡ ትልቁ ሥራችኹ ስብከተ ወንጌል ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ተቀዳሚ ሥራዋ ስብከተ ወንጌል ስለኾነ በስብከተ ወንጌል ኹላችን መጠንከር አለብን፡፡ ሕዝብን ኹሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት የመሳብ፣ የእግዚአብሔር የመንግሥቱ ዜጎች እንዲኾኑ የማድረግ ሓላፊነት አለብን፡፡ ሃይማኖታችኹ ጸንቶ ምግባራችኹ ቀንቶ ስናይ ለእኛ ሕይወት መድኃኒት ነው፤ በየጊዜው እንዲጨመሩ ማድረግም ሓላፊነታችን ነው፡፡

የሠራችኹት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለእናንተ ብቻ ሳይኾን ለልጅ ልጆቻችኹ የሚተላለፍ ሥራ ስለኾነ እንኳን ደስ አላችኹ፡፡ ከዚኽ በኋላ ሐሳባችኹ ትምህርት ቤት ወደ መሥራት መኾን አለበት፡፡ ልጆቻችኹ ቋንቋቸውን አጥንተው የጸናችውንና የቀናችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አምልኮቷን፣ ሥርዐቷን፣ ቀኖናዋን፣ ምስጢሯን እንዲጠይቁና እንዲያውቁ ማድረግ ይኖርባችኋል፡፡

/ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፤ ጥቅምት ፴ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከስድስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ተገኝተው የጂንካ ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤትና የ1350 ምእመናን ጥምቀተ ክርስትና በተፈጸመበት ወቅት ከተናገሩት/

26 thoughts on “በደ/ኦሞ: በሀ/ስብከቱ እና በማኅበረ ቅዱሳን መተባበር ከ16 ሺሕ በላይ ምእመናን ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ተጨመሩ፤ ‹‹ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ ደስታ ነው›› /ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ/

  1. serawit Debebe November 15, 2014 at 9:51 am Reply

    አሜን አሜን አሜን እግዚአብሔር ይመሥገን!!!!!!

  2. Anonymous November 15, 2014 at 10:16 am Reply

    1350 ሕንፃ ሥላሴ በዛሬው ዕለት ተጠምቀው የእናት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ኾነዋል፡፡
    EGZIABHER YIMESGEN KEZIH YEMIBELT AGELGILOTIM BEGO SIRAM YELEM!!!

  3. TIRSIT WUBIE November 15, 2014 at 11:54 am Reply

    እግዚአብሔር ይመሥገን

  4. በሀሩ ሸንብር ደጀኔ November 15, 2014 at 12:18 pm Reply

    እንዲህ አይነቱን ዜና ሠንሠማ በጣም ደሥይለናል የተዋህዶ ልጆች ፍላጎታችን አባቶቻችንእናከብራለን ማህበረ ቅዱሠን ደግም ክርሥቶሥ የተናገረውን ቃል በሥራ የገለፁ ናቸው ብርሀናችሁ በሠውፊት ይብራ ያለውን ቃል በተግባር ያሣዩ ናቸው ሥለዚህ ተሥማምተን እጅ ለእጅ ተያይዘን የክርሥቶሥ መንግሥት ለመውረሥ መሥራት ይኖርብናል እያንድ አንዳችን ከእግዝአብሄር የተሠጠን ሀላፊነት መዘንጋት መዘንጋት የለብንም መልካም የሆነውን ሁሉ ለመሥራት እግዝአብሄር ይዳን አሜን

  5. Anonymous November 15, 2014 at 4:35 pm Reply

    Egziabeher yemesgen wanawe fiker newe esu kale abatena lejoche gena bezu yeseralu yehene lasayehen amlake enamesegenehalen.

  6. Dereje Mengesha November 15, 2014 at 5:01 pm Reply

    Egziabher yetemesegene new !

  7. Anonymous November 16, 2014 at 7:44 am Reply

    እግዚአብሔር ይመስገን።

  8. Anonymous November 16, 2014 at 12:30 pm Reply

    Egziabher eske mechereshaw yatsinachehu

  9. Beko November 16, 2014 at 11:52 pm Reply

    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ከጥንት ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሀገሪቱ ላይ ከነበራት ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተጽእኖ አንጻር በአሁን ሰዓት በሀገሪቱ ውስጥ ይህ ሁሉ ኢአማንያንና ምንም እምነት የሌላቸው ማህበረሰብ መኖራቸወን በድፍረት መናገር በእወነት በጣም በጣም ያሳፍራል፡፡ ይህ ሁሉ ቤተክርስቲያኗ በአማርኛና በግእዝ ላይ ሙጭጭ በማለቷ ነው፡፡ አሁንም በጣም ጊዜው የረፈደ ቢሆንም ተቋሙ የቋንቋን ጉዳይ በከፍተኛ ደረጃ ትኩረት ሰጥቶ ካልተንቀሳቀሰ ዛሬ ያጠመቃቸውን ማህበረሰቦች ነገ የማትነጠቅበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ቢያንስ በገጠሪቱ አከባቢ ጥሩ በቋንቋ የሚያስተምር መምህር እስከሚገኝ ድረስ በአስተረጓሚ ቋሚ የትምህት መርሀ ግብር ማዘጋጀት በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ ከአከባቢው ቋንቋ ባለቤት መመህራንና የሀይማኖት መሪዎችን የማብቃት ስራ መስራት፡፡ ቢያንስ መሰረታዊ የሆኑ የሀይማኖት መጽሃፍት ወደ አከባቢው ቋንቋ መተረጎም፡፡ ባጠቃላይ ሀይማቱን የማስረከብ ስራ መስራት፡፡ አዲስ አበባ በየሰፈሩ በቅርብ ርቀት ቤ/ክ ከማቋቋም ወጣ ብሎ ሀዋርያዊ ስራ መስራት፡፡

  10. Anonymous November 17, 2014 at 3:11 am Reply

    ገና ምድሪቱን እንሞላለን።

  11. Anonymous November 17, 2014 at 7:48 am Reply

    Yihin Yadrrege Amlakachin EGZIABHER smu Yetemesegene yhun. Besraw mesakat yelefachu hulachu Egziabher Chernetu yabzalachu. Amen!!!

  12. getasetegn November 17, 2014 at 8:32 am Reply

    Egazehaber emasgan.

  13. zerihun Tsegaye November 17, 2014 at 12:16 pm Reply

    አሜን አሜን አሜን እግዚአብሔር ይመሥገን!!!!!!

  14. derie November 18, 2014 at 10:45 am Reply

    THANKS TO GOD!ELELELELELELELELELELEEL

  15. ሙሉጌታ November 18, 2014 at 4:36 pm Reply

    ይህ የሚያስከፋቸው እነ አባ ሰረቀን እና መሰሎቻቸውን ከነአባ ሰላማ ብሎጋቸው ጭምር ነው። ይህ ደስታ በሰማያት ከመላእክቱ ጭምር ነው የኛንማ ደስታ ለመናገር ቃላት ያንሰኛል። እግዚአብሔር በዚህ ማህበር አባላት ላይ አድሮ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን እያደረገልን ነው። ከሳሾቻችሁ ያፈሩበት ዜና ለነገሩ እፍረት ሲኖራቸው አይደል።

    • Anonymous November 19, 2014 at 9:33 am Reply

      Amen !!! Elil elil elil
      tesfalegn ze debre eba

  16. abebech December 2, 2014 at 8:48 am Reply

    እልልልልልልልልልልልልል እግዚአብሔር እንኳን በቸርነቱ ጎበኛችሁ አገልጋይ አባቶቼ እና ወንድሞቼ በአገልግሎታችሁ ያበርታችሁ ዋጋችሁን እግዚአብሔር ይክፈላችሁ

  17. Anonymous December 11, 2014 at 11:47 am Reply

    betam des ylal yebete kiristian mesfat new. Yegeremegn gin MK bemnu new amanian wede bete kiristian yametaw betmhirutu endaybal bebete kirstian timhirt mehaiman nachew. bekihinetachew endybalm kahinat papasat eyesedebu yemiwlu kihinet alba nachew. Weys h/sbketu beseraw sra lemekber new? Min alebet MK besew sra meneged biyakum.

  18. beletuakele December 24, 2014 at 6:03 am Reply

    እውነት መንገዷ ፈተና ይበዛዋል፡፡ እውነት ሁልጊዜ ብዙዎች አይፈልጓትም እውነት የራሷን ማዕድ አዘጋጀች በሩቅ ስብከት እውቀት ያነሳቸውን ትጠራለች ኑ የእኔን ህብስት ብሉ የእኔን ወይንም ጠጡ እያለች እውነት ግን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ በዚህ ዕውነት ላይ አቁሞ ስለሌሎች መዳን ትደርሱ ዘንድ የረዳችሁ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! አሜን ! አሜን !

    • Anonymous April 4, 2015 at 10:46 pm Reply

      Amen

  19. Anonymous October 24, 2015 at 8:24 am Reply

    be ewnet egziabhiar ymesgen endih yalu abatochina sebakian aysatan

  20. fanus October 24, 2015 at 5:34 pm Reply

    ሚስጋና ኒ አግዛቢሄር ኣምላክ ይኩኖ

  21. Anonymous October 24, 2015 at 5:35 pm Reply

    ኣሜን ኣሜን ኣሜን

  22. Anonymous October 29, 2015 at 12:57 am Reply

    THANKS GOD I’M SO HAPPY.

  23. Anonymous October 31, 2015 at 3:02 pm Reply

    kibr lemedhanialem amen

Leave a comment