ሚኒስትር ሺፈራው: በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የክርስቲያንነት መታወቂያችንን ማዕተብ ከማሰር እንደምንከለከል አስታወቁ፤ ማዕተባችንን እናጥብቅ!

  • ከሥልጠናው ተሳታፊዎች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሟቸዋል፤ ከሥራ ባልደረቦቻቸውም ጠንካራ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል፡፡
  • ‹‹በሴኩላሪዝም ሰበብ ማዕተብኽን በጥስ ማለት ሃይማኖትን ከማስካድና እንደ ሰቃልያነ አምላክ አይሁድ መስቀሉን ለመቅበር ከመሞከር ተለይቶ አይታይም፡፡ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እና ታሪካዊ ትውፊት እንዳይፋለስ የመጠበቅና የማስጠበቅ ሓላፊነት ያለበት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥንቃቄ ሊከታተለው ይገባል፡፡›› /የሥልጠናው ተሳታፊዎች/
  • ‹‹ፈትል አንድነት እየሸረቡ ለክርስትና ሕይወት መግለጫ በክርስትና ጥምቀት ጊዜ አንገት ላይ ማሰር በቤተ ክርስቲያናችን የጸና ኾኖ ሲሠራበት ይኖራል፡፡›› /የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ/

*              *             *

  • ‹‹ሚኒስትሩ የመንግሥትን ሴኩላርነት ለማረጋገጥ በሚል የሰጧቸው አስረጅዎች የግልጽነትም የአግባብነትም ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ የሚበዛው ኢትዮጵያዊ አማኝ ከመኾኑ አንፃር ትርጉም እንዳለውና በሕገ መንግሥቱ እምነት ነክ ድንጋጌዎች እንደተንጸባረቀ ከሚታመነው የሴኩላሪዝም ፈርጅ (positive secularism) ይልቅ በርእዮትና አሠራር የተደገፈ ሃይማኖትንና ሃይማኖተኝነትን የማዳከም (negative secularism) አዝማሚያዎች ያይልባቸዋል፡፡ ከእምነት ተቋማት ጀርባ የግንባሩን አባላት ጨምሮ ሰፊው አማኝ ሕዝብ መኖሩን ታሳቢ ያደረገ ‘በነፃነት ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ መስተጋብር’ እንደሚኖር በመንግሥት የኢንዶክትሪኔሽን ጽሑፎች ከተቀመጡት አቅጣጫዎች ጋራም የሚጣጣሙ አይደሉም፡፡ በተለይ ከቤተ ክርስቲያናችን አንፃር ለተነሡ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ፣ በፓወር ፖይንት ካቀረቡት ዶኩመንት ያለፈና ‘more of personal’ የሚመስል ‘issue’ ያላቸው ነው የሚመስለው፡፡ በዚኽ አኳኋን እንዴት ነው ዜጎች ‘ሚዛናዊ አስተሳሰብ’ እንዲያዳብሩ የሚጠበቀው? ከመንግሥት ጋራ አብሮ መሥራትስ እንዴት ይቻላል?››
  • ‹‹ክርስትናችን ‘የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጥ’ የሚል ሴኩላሪዝምን በአዎንታዊነትና በቀላሉ የሚገልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ያለው ነው፡፡ በሚኒስትሩ የተብራራው የሴኩላሪዝም መርሖ ግን ምእመኑን ለእምነቱ ለዘብተኛ በማድረግ በሒደት ወደ ሃይማኖት አልባነት የመምራት ተንኰል የተሸሸገበት ያስመስላል፡፡››
  • ‹‹ክርስቲያንነታችንን በየራሳችን የምንመሰክርበት መለዮአችን ማዕተብ ለመንግሥት ሴኩላርነት ተፃራሪ እንደኾነና ሊከለከል እንደሚችል መናገር ስለ መንግሥት የሴኩላሪዝም መርሖ የተሳሳተ መልእክት በማስተላለፍ ሰፊውን አማኝ ፀረ – ሴኩላር የሚያደርግ፣ ሕዝቡንና መንግሥትንም ፊት ለፊት የሚያፋጥጥ እንዳይኾን ያሰጋል፡፡››

/የመንግሥት መካከለኛ አመራሮች የኾኑ ኦርቶዶክሳውያን የሥልጠናው ተሳታፊዎች/

*              *             *

Dr shiferaw Teklemariam

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም

የክርስቲያንነት መለዮአችን፣ የርትዕት ሃይማኖት ምስክራችን የኾነውን ማዕተብ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና በትምህርት ተቋማት አስሮ ከመታየት ልንከልከል እንደምንችል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ሺፈራው መናገራቸው ተሰማ፡፡

የመንግሥትን የሴኩላሪዝም መርሖና የፀረ አክራሪነት አጀንዳ ተገን በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ርእዮታዊ እና ሃይማኖታዊ ጥላቻቸውን በማስተጋባት የሚታወቁት ሚኒስትር ሺፈራው፣ ይህን መናገራቸው የተጠቆመው፣ ከነሐሴ ፲፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ድረስ በዘለቀውና በኹለት ዙሮች በተካሔደው የመንግሥት መካከለኛ አመራሮች ሥልጠና ላይ ነው፡፡

በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በተካሔደውና 800 ያህል መካከለኛ አመራሮች በተሳተፉበት የፖሊሲና ስትራተጂ ሥልጠና ‹‹የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ግንባታና ፈተናዎቹ›› የሚለውን ሰነድ የሚያብራራና በፓወር ፖይንት የተደገፈ ጽሑፍ ያቀረቡት ሚኒስትሩ የመንግሥትን የሴኩላሪዝም መርሖ መነሻ ያደረገ ነው የተባለ ጥያቄ ከአንዲት ተሳታፊ ቀርቦላቸዋል፡፡

እንደ ስብሰባው ምንጮች፣ የተሳታፊዋ ጥያቄ፣ ‹‹በቢሮ ፊታቸውን ተሸፍነው የሚመጡ ሙስሊሞችን አለባበሳቸው ከቦታው አንፃር ያለውን ተገቢነት በማንሣት እንዲያወልቁ ስንጠይቃቸው ‘እኛ ይኼን የምናወልቅ ከኾነ ኦርቶዶክሱም ክሩን ይበጥስ’ ይሉናል፤ ይኼን እንዴት ነው የምንታገለው?›› የሚል ነበር፡፡

‹‹መንግሥታችን ሴኩላር ነው›› ሲሉ በጠያቂዋ የተጠቀሰውን ዐይነት አለባበስ የተቹት ሚኒስትሩ፣ ‹‹እርሱም [ማተቡም] ቢኾን የጊዜ ጉዳይ ነው፤ እንደ የሃይማኖት መለያ እስካገለገለ ድረስ አደረጃጀታችንን ስንጨርስ ማተብም ቢኾን መውለቁ አይቀርም፤›› የሚል ምላሽ መስጠታቸው ተገልጧል፡፡

የሥልጠናው ተሳታፊዎች ከፍተኛ ማጉረምረም በማሰማት በሚኒስትሩን ምላሽ ላይ ተቃውሟቸውን መግለጣቸው ተጠቅሷል፡፡ ሌላው ተሳታፊም፣ ‹‹በመሠረቱ ፊት መሸፈንን ማዕተብ ከማሰር ጋራ ማመሳሰል ልክ አይመስለኝም፤ ማተብም ቢኾንኮ ከሃይማኖታዊነት አልፎ ማንነትና ባህል ኾኗል፤ ማስቀረቱ አደጋ አለው፤›› ሲሉ ከተሳታፊው ከፍተኛ የጭብጨባ ድጋፍ እንደተቸራቸው ተዘግቧል፡፡

ሚኒስትሩ ‹‹ይኼ ግን የዚኽ ሥልጠና አካል አይደለም›› በሚል የተሰብሳቢውን ተቃውሞ ለማለሳለስና እንደዋዛ ለማለፍ ቢሞክሩም ጉዳዩ በዕረፍት ሰዓት በከፍተኛ ስሜት ከማወያየት አልፎ የሚኒስትሩን አጠቃላይ አቀራረብና ስውር ፍላጎት የተመለከቱ ቅሬታዎች ሲሰነዘሩም እንደነበር ተሰምቷል፡፡ ‹‹የሰውዬው ዓላማ ኹላችንን ፕሮቴስታንት ማድረግ ነው ወይ?›› ያሉ አንድ ተሳታፊ የሥልጠናውን አስተባባሪዎች ‹‹ለምንድን ነው የማትነግሩት?›› በማለት በቁጣ ጠይቀዋል፡፡

የሚኒስትሩ ምላሽ ጥንቃቄ የጎደለው እንደኾነ የጠቀሱ ሌላ አስተያየት ሰጭ፣ መንግሥታዊ ሥራን ከሃይማኖታዊ ውግንና አድልዎ ተጠብቆ በገለልተኝነት ማካሔድ እንደሚገባ ቢያምኑም ይህ በዋናነት የሚገለጸው በሲቪል ሰርቪሱ ሓላፊዎች አመራርና የውሳኔ አሰጣጥ፣ በሠራተኞች አቀራረብና የሥራቸው አፈጻጸም እንደኾነ አስረድተዋል፡፡ እንደ ጥያቄው አቀራረብና እንደ ሚኒስትሩ ምላሽ፣ ማዕተብ ከአለባበስ ጋራ ተዘምዶ ከተወሰደም የሴኩላር መንግሥትን የገለልተኝነትና የእኩልነት መርሕ የሚጥስበት አልያም የሠራተኛውን ገጽታ በግልጽ ለመለየት የሚያግድበት ከዚኽም ጋራ ተያይዞ የማኅበረሰብ ሰላምና የደኅንነት ጥያቄ የሚያሥነሳበት ኹኔታ በማንም ዘንድ ሊኖር እንደማይችል አብራርተዋል፡፡

MAETEB, Badge of Christianity‹‹ከአለባበስ አኳያ የሴኩላሪዝም መርሖን ለማረጋገጥ ሃይማኖታዊ ግዴታ ያለባቸውንና የሌለባቸውን አለባበሶች ከግምት ያስገባል፤›› ያሉት አስተያየት ሰጭው፣ ማዕተብ *÷ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጥምቀተ ክርስትና አፈጻጸም * * እያንዳንዱ ተጠማቂ የእግዚአብሔር ልጅነትን በጸጋ አግኝቶ የተስፋው ተካፋይ የርስቱ ወራሽ ለመኾን በሰማያዊ ዜግነት የሚታተምበት የሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን አካል የመኾኑን የሃይማኖት መግለጫነት መሠረታዊነት በአጽንዖት አስገንዝበዋል፤ ዕቱባን አንትሙ በቅድስት ጥምቀት እንዲል፡፡

ከዚኽም በተጨማሪ ማዕተብ÷ የሲኦል መሠረት የተናወጠበት፣ ሰውንና እግዚአብሔርን ለዘመናት ለያይቷቸው የነበረው የጠብ ግድግዳ የተናደበት፣ የሞት ኃይሉ ተሽሮ የትንሣኤ መንገድ የተከፈተበት መስቀል ትእምርት በመኾኑ በተሳሳተ የሴኩላሪዝም ግንዛቤ ‹‹ማዕተቡም ሊወልቅ ይችላል›› ማለት፣ ‹‹ሃይማኖትን ከማስካድና እንደ ሰቃልያነ አምላክ አይሁድ መስቀሉን ለመቅበር ከመሞከር ተለይቶ አይታይም፤ ጉዳዩንም ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ታሪካዊ ትውፊት እንዳይፋለስ የመጠበቅና የማስጠበቅ ሓላፊነት ያለበት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥንቃቄ ሊከታተለው ይገባል፡፡›› ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን vs. ቦኮ ሐራም

የሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ምላሽ ጥንቃቄ የጎደለው ነው የሚለውን አስተያየት የሚጋሩት ሌላው ተወያይ የበኩላቸውን ሲያክሉ፣ ‹‹ከዚኽም በላይ ግን በተለይ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ለተነሡ ጥያቄዎች፣ ‘ማኅበራት’ እያሉ በማስረገጥ ምላሽ ሲሰጡ፣ በፓወር ፖይንት ካቀረቡት ዶኩመንት ያለፈና ‘more of personal’ የኾነ ‘issue’ ያላቸው በሚያስመስል ልዩ አጽንዖት ሲናገሩ ነው የሚታዩት፤›› ብለዋል፡፡

‹‹አብረን ተቻችለን በሰላም ኖረናል እየተባለ ስለ አክራሪነት ተጋኖ የሚነሣበት ኹኔታ አለ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለመንግሥት ተጨባጭ ስጋት የኾነ አካል አለ ወይ?›› ተብሎ በጽሑፍ ለቀረበው ጥያቄ ሲመልሱ ትኩረት ያደረጉት÷ ‘በትምክህተኝነት፣ በሥልጣን ጥመኝነት፣ በቀለም ዐብዮት ሰባኪነት’ በከሰሷቸው የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ላይ ነበር፤ ንጽጽራቸውም የፖሊቲካ ፓርቲ ኾኖ መንግሥታዊ ሥልጣን ለመያዝ ከበቃው የግብጹ ሙስሊም ወንድማቾቾች አንሥቶ ከናይጄሪያ መንግሥት ጋራ በትጥቅ የተደገፈ ፍልሚያ ውስጥ እስከገባው የሽብር ቡድን ቦኮ ሐራም ድረስ የጨከነ ነበር፡፡

ውንጀላው ከአነጋገሩ እንደሚታየው በማኅበሩ አባላት ላይ ብቻ ያነጣጠረ እንዳልኾነ የሚያጠይቀው፣ ‹‹የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እዚህ ውስጥ አላችኹ፤ የድርጅትም አባል ናችሁ፤›› ያሉት ሚኒስትሩ፣ ‹‹መታገል ያልቻላችኹት የማኅበሩ አባል ስለኾናችኁ ነው፤ ኹለቱን እያጣቀሳችኹ መሔድ አትችሉም፤›› ለማለት ሲደፍሩ እንደነበር ተወያዩ አስረድተዋል፡፡ ይህም ሚኒስቴሩ በሚያዝያ ወር ፳፻፮ ዓ.ም. ባወጣው ሰነድ፣ ‹‹በማኅበሩ ውስጥ የመሸጉ ግለሰቦችና ቡድኖች መኖራቸውን መጠቆም ማኅበሩን አክራሪ/ጽንፈኛ ብሎ መፈረጅ አይደለም፤ ማኅበረ ቅዱሳንም በዚኽ አልተፈረጀም፤›› በማለት የሰፈረውን ማብራሪያ ተቀባይነት እንደሚያሳጣው ተመልክቷል፡፡

ሚኒስትሩ ከአክራሪነት በአንጻሩ ‹‹አጥባቂነት›› ትክክለኛና ሰብአዊ መብት እንደኾነ ገልጸዋል፡፡ ይኹንና ርቱዕነት፣ ቀናዒነት፣ ጽንዓት፣ ታማኝነት እና ትጉህነት እንጂ ‘አጥባቂ’ የሚባል ሃይማኖታዊ ቅጽል እንደማይስማማቸው፤ ልዝብነት ይኹን አጥባቂነት በቤታቸውም ይኹን በመጽሐፋቸው እንደሌለና እንደማይቀበሉትም ተወያዮቹ በግልጽ ይናገራሉ፡፡ በሚኒስትሩ አነጋገር ከትምክህት ርእዮት ጋራ በመዳበል ይታያሉ ያሏቸው የአክራሪነት አስተሳሰቦችም÷

  • የራስን እምነት በሌላው ላይ መጋት፤
  • የትምህርት ሥርዐቱን መረበሽ፤
  • በሃይማኖት ሽፋን ፖሊቲካዊ አቋም ማራመድ፤
  • የበላይነትን አጥተናልና ይህንኑ መመለስ ይገባናል፤
  • ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደሚመች እየጠቀሱ መተርጎም እና

የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እኒኽ አመለካከቶችና ድርጊቶች ግና የራሳቸውን አሳልፈው መስጠት ለማይወዱት፣ የሌላውንም ለማይሹት ኦርቶዶክሳውያን ጠባይ የማይስማሙ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ከተፈቀደውና ከታወጀው የማኅበረ ቅዱሳን ዓላማና ተልእኮ እንዲኹም ከእያንዳንዱ አባላቱ አስተሳሰብ አንፃርም ቢኾን ተቀባይነት የሌላቸው ከንቱ ውንጀላዎች ተደርገው ነው የተወሰዱት፡፡

mahibere kidusan meskel demera celebration at meskel squareበዚኹ ዐይን፣ በዩኒቨርስቲዎች የሚነሡ ሃይማኖት ነክ ጥያቄዎች ስለምን በወጣው የአምልኮ የአለባበስና የአመጋገብ መመሪያ መሠረት እንደማይስተናገዱ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹በትምህርት በተቋማቱ አካባቢ ከሚገኙ የአምልኮ ተቋማት ጋራ በመነጋገር ችግሩን ማስቀረት ያስፈልጋል፤›› በሚል የሰጡት ምላሽ አፈጻጸምም ማኅበሩ ሃይማኖቱን ያወቀ፣ በምግባሩ የተጠበቀና ሀገሩን የሚረከብ መልካም ዜጋ ለማፍራት ባደራጃቸው ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይኖረው በትኩረት ሊጤን እንደሚገባው ያስጠንቅቃሉ፤ ግቢ ጉባኤያት፣ በሥነ ምግባር የታነጸ ዜጋና የቤተ ክርስቲያንን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚያግዝ የአበው ተተኪ ትውልድ ማፍሪያ እንጂ ተንኰልና ክፋት በተጠናወተው አእምሮ እንደሚባለው ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት አስቀጣይ ኃይል መመልመያ መድረክ›› አይደሉምና፡፡

‹‹መንግሥት አክራሪዎችን ለምንድን ነው መቆጣጠር ያቃተው? ለምን ርምጃ አልወሰደባቸውም? የሃይማኖት አክራሪነትን የሚያስፋፉ ድረ ገጾችንስ ለምንድን ነው ማገድ ያልቻለው?›› ለሚለው የተሳታፊዎች ጥያቄ÷ ‹‹ወደ እያንዳንዱ ሰው መዝመት አዋጭ አይደለም፤ ዋናው የአመለካከትና የአስተሳሰብ ዝንባሌን ማስተካከል ነው፤ ሐሳብን በሐሳብ የማሸነፍ ስልት ነው የምንከተለው፤›› በማለት የሰጡትን ምላሽ በአዎንታ እንደሚቀበሉት አስተያየት ሰጭዎቹ አልሸሸጉም፡፡

yemeles-tirufatoch-on-dr-shiferaw-hubris011ነገር ግን፣ ቅ/ሲኖዶሱን ሳይቀር የእግራቸው መረገጫ እስከ ማድረግና በሃይማኖት ተቋማቱ ላይ የአብዮታዊ ዴሞክራሲን የበላይነት ለማስፈን እስከ መመኘት የናረ ለከት ያጣ ርእዮታዊ እና ምናልባትም ሃይማኖታዊ ጥላቻቸውን ጭምር በመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ፊት ለመናገር የቀለላቸው ሚ/ር ሺፈራው፣ በቃል የሚሉትን ያኽል በመረጃና በዕውቀት ላይ ለተመሠረተ ገንቢ የሐሳብ መተጋገል ብቃቱም ፍላጎቱም አላቸው ብለው አያምኑም፡፡

ከዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር አኳያ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር በሚል ለኢንዶክትሪኔሽን የተዘጋጁት የመንግሥት ጽሑፎች ሊታረሙና በአጽንዖት ሊመረመሩ የሚገባቸውን ጉዳዮች የያዙ ቢኾንም በአጻጻፍ ደረጃ እንኳ፡-

  • አክራሪነትን ለመዋጋትና ከምንጩ ለማድረቅ፣ ልማታዊ ባህሎችንና ሥነ ምግባሮችን ለማጎልበት ከእምነት ድርጅቶች ጋራ በነፃነት ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ መስተጋብር ሊኖረን ይገባል፤ በዴሞክራሲያዊ አኳኋንና የማንንም ወገን ነፃነት በማይነካ መልኩ መመካከር መቻል አለብን፡፡
  • የሃይማኖት ተቋሞች ከሃይማኖት እኩልነት፣ ከሕዝቦች መፈቃቀድ፣ ከሠርቶ መክበር ጋራ የተያያዙ የሞራል ትምህርት ማስተማር ከቻሉ ከዚያ በላይ እንዲሔዱ ማድረግ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል
  • ከእምነት ድርጅቶች በስተጀርባ አባሎቻችንን ጨምሮ ሰፊው ሕዝብ እንዳለ መገንዘብ ይገባናል፤

የሚሉ የጥንቃቄ አገላለጾችን በሚያሳዩበት ኹኔታ፣ የሚኒስትር ሺፈራው ጥናት የጎደለውና እርስ በርሱ የሚጋጭ የመድረክ አያያዝ በሰፊው አማኝ ሕዝብ ዘንድ ድርጅቱን እንዳስጠቆረው፣ በራሳቸው በሚኒስትሩም ላይ ከቅርብ የሥራ ባልደረቦቻቸው ጠንካራ ጥያቄ እንዳስነሣባቸውና በበላይ አለቆቻቸው ሳይቀር ክፉኛ እንዳስገመገማቸው መረጃው እንዳላቸው የስብሰባው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

በሴኩላሪዝም ሰበብ…

በታሪክ የአንድ ሃይማኖት መሠረታዊነት (hegemonic religion) በነበራቸው አገሮች የሚመሠረቱ ሴኩላር መንግሥታት ከሃይማኖት ተቋማት ጋራ ስለሚኖራቸው ግንኙነትና ስለሚከተሉት ሴኩላሪዝም “Secularism and State Policies towards Religion: The United States, France, and Turkey” በተሰኘው መጽሐፋቸው የተነተኑት የሳንዴያጎው ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር አኸመት ኩሩ፣ ከቀደሙት አገዛዞች ተጠቅሟል በሚባለው ነባር ሃይማኖት ላይ ጥላቻን ለማስፈን፣ አገራዊ ሚናውን ለመቀነስ ብሎም ከሕዝቡ ሕይወት ጨርሶ ለማጥፋትና በሴኩላሪዝም የበላይነት (the dominance of assertive secularism) ለመተካት መርሖውን በመሣርያነት የሚጠቀሙ ከልኩ ያለፉ ጠርዘኛ ዓለማዊ ኃይሎች (ultra-secularist circles) አይለው እንደሚታዩ የፈረንሳይንና የቱርክን ልምዶች በመጥቀስ አስረድተዋል፡፡

ከዚኽ በመነሣት ከኢትዮጵያ ታሪክና ወቅታዊ ኹኔታ እንዲኹም ከሃይማኖትና መንግሥት መለያየት ጋራ በተገናኘ፣ በአንዳንድ ሰሞናዊ የፖሊሲና ስትራተጂ ሥልጠና መድረኮች በጥንታዊት፣ ሐዋርያዊትና ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚሰነዘሩ ጽርፈቶች እምብዛም ባያስደንቁም ብዙኃኑን የሥልጠና ተሳታፊዎች ማሳዘናቸው እና በመድረኮቹ ዓላማና ግብ ላይም የብዙኃኑን ኦርቶዶክሳዊ ጥርጣሬ ማስነሣታቸው አልቀረም፡፡

የጽርፈቶቹ መግፍኤ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በመጽሐፋቸው ስለ ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር ሥሪት በውል እንዳስቀመጡት÷ ስሙ እንጂ ጥቅሙ የሌላ በነበረውና ለሕዝቡም ግልጥ ባልተደረገው ‘ሲሶ መንግሥት አላት’ አነጋገር ቤተ ክርስቲያናችን የንግድ ምልክት ኾና ለዘመናት ስትገፋ የኖረችበት ሥሪት አገሪቱንም ቤተ ክርስቲያኒቱንም የጎዳበትን አሠራር በውል አለመረዳት ብቻ አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በርስተ ጉልት የአድባራት አስተዳደር ካህናቷ ቶፋ በሚል ስመ ጽዕለት የነገሥታቱና የመሳፍንቱ ድርጎኛ ኾነው የአገልግሎታቸውን ዋጋ ያላገኙበት መኾኑን ያለመገንዘብ ብቻም አይደለም፡፡ በስመ ሴኩላሪዝም በአይዲዮሎጂ ላይ የተመረኮዘ ቤተ ክርስቲያናችንን የማጥላላትና ከሕዝቡ ነጥሎ የማዳከም ዝንባሌና የተግባር ውጣኔ እንጂ!

ጊዜ ተገኘ ተብሎ፣ ቤተ ክርስቲያናችን ከእርሷ በኋላ ለመጡ እምነቶች በሰላም አብሮ መኖር አንዳችም ሚና እንደሌላት ያኽል ‹‹መውጫ መግቢያ እንዳሳጣቻቸው››፤ አእላፍ ቅዱሳኗ በአራቱም የአገሪቱ ማእዝናት በሐዋርያዊ ትጋት አስተምረው ክርስትናን እንዳላስፋፉ ኹሉ ኦርቶዶክሳዊነት ‹በመንግሥት ሥልጣን ተደግፎ በሌሎች እምነቶች ላይ የተጫነ›› እንደኾነ፤ ከሐዋርያት ዘመን አንሥቶ የሚቆጠረው ታሪኳ ‹‹ረዥም ነው›› ማለታችንም ዕብለት እና የአክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌ እንደኾነ፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያበረከተቻቸውን የሥልጣኔ ስጦታዎች ሳይጨምር ትውልዱ ጀግንነትን፤ አገር ወዳድነትን፤ ለታሪክ፣ ለባህልና ለሃይማኖት ተቆርቋሪነትን ይዞ እንዲያድግ ማስተማሯንና ማበረታታቷን ከትምክህት ርእዮትና በዚኹ ርእዮት ላይ ይመሠረታል ከሚባለው አሸባሪነት ጋራ በማጃመል ከአገዛዞቹ ስሕተት ጋራ ተደርባና ተዳብላ እንደምትታይ፤…አፍ እንዳመጣ መለፈፍ በርግጥም በስመ ሴኩላሪዝም በአይዲዮሎጂ ላይ የተመረኮዘ የማጥላላትና ከሕዝቡ ነጥሎ የማዳከም ዝንባሌና የተግባር ውጣኔ እንጂ ሌላ ሊኾን አይችልም! ጥቂት በማይባሉ ወገኖች አረዳድም ዝንባሌውና የተግባር ውጣኔው መንግሥታዊ ሥልጣንን ተጥቅሞ ፕሮቴስታንታዊነትን በማንገሥ የራስን እምነት የበላይነት የማስፈን አካሔድ እንደኾነ በስፋት ከታመነበት ውሎ ያደረ ጉዳይ ኾኗል!!

yemeles-tirufatoch-on-dr-shiferaw-hubris02ቅ/ሲኖዶሱን የእግራቸው መረገጫ ለማድረግ የዛቱት ሚ/ር ሺፈራው፣ ‹‹በሃይማኖት ሽፋን የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር›› በሚል በሃይማኖት ተቋማቱ ላይ በምዝገባ መመሪያ በተደገፈ ጥብቅ ቁጥጥር ርእዮተ ዓለማዊ የበላይነትን ማስፈን የሚኒስቴራቸው ቁልፍ ሥራ እንደሚኾን፣ በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ፊት እንደተናገሩ የቀድሞው ሚ/ር ዴኤታ አቶ ኤርሚያስ በመጽሐፋቸው ያሰፈሩት ርግጥ ከኾነም መግፍኤው ከዚኽ ተለይቶ የሚታይ አይኾንም፡፡

ደጉ ነገር፣ የቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አመራር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ውሳኔው፣ በእነሚኒስትር ሺፈራው ሥልጠና ከትምክህት ርእዮትና ከአገዛዞች ስሕተት ጋራ ተዳብለን የተፈረጅንበት÷ የታሪካዊነታችንና የቀዳሚነታችን ጥሬ ሐቅ ኹሉም ሰው ሊጽፍበት የሚገባ እንደኾነ፤ ይኽን በመፃረር የሚነገረውና የሚጻፈው ኹሉ ደግሞ ‹‹እውነት ያልኾነና አስመሳይነት እንደኾነ›› በግልማስቀመጡ ነው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፤ እውነት ያልኾነው፣ በማስመሰል የሚነገረውና የሚጻፈው ታርሞና ተስተካክሎ እውነተኛውና ትክክለኛው ለሕዝብ፣ ለትውልደ ትውልድ መተላለፍ እንደሚገባው ምልዓተ ጉባኤው ጽኑ አቋም መያዙ ነው፡፡ ይህም እንዲፈጸም የሊቃውንት ጉባኤ፣ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊነትና ታሪካዊነት በጽሑፍ አብራርቶ፣ አስፍቶና አጉልቶ እንዲያቀርብ ቀን ቆርጦ መመሪያ መስጠቱ ነው፡፡ የአፈጻጸሙን ነገር አደራ እንጂ!

የሴኩላሪዝም መርሖ ምርጫ

ከአጠቃላይ ሕዝቡ ከ97 በመቶ ያላነሰው የአንዱ ወይም የሌላው እምነት ተከታይ በኾነባት አገራችን ከሃይማኖትና ሃይማኖተኝነት ጋራ የሚጫረቱ የሴኩላሪዝም ፈርጆች በጤናማ መርሖው ላይ የሰፊውን አማኝ ግንዛቤ በማዛባት ፍጥጫን እንዳያስከትሉ ጥንቃቄ እንደሚያሻው አስተያየት ሰጭዎቹ ያሳስባሉ፡፡

መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ እንደኾኑ የተደነገገበት ሕገ መንግሥታዊ አንቀጽ÷ አንዳቸው ከሌላቸው አሉታዊ ተጽዕኖ ተጠብቀው በየራሳቸው የሚጠናከሩበትንና እንዳስፈላጊነቱም የሚተባበሩበትን (the government and religion should not unduly influence each other) እንጂ ሃይማኖትና ሃይማኖተኝነት ከግለሰቡና ከሕዝቡ ሕይወት ጨርሶ የሚጠፋበት የሴኩላር አክራሪነት (secularist fundamentalism) አልያም መርሖውን መሣርያ አድርጎ ጥንታዊውን ሃይማኖትና ተቋማቱን በማዳከም ‹‹ሌላ ገጽታ ያለው የተዛባ የሃይማኖቶች ግንኙነት መፍጠር›› የሚደገፍበት እንዳልኾነ ይታመናል፡፡

በዚኽ ረገድ ከአጠቃላይ ሕዝባቸው የኖሩ ሃይማኖት ተከል – የማንነት ዕሴቶች ጋራ ያልተገናዘበ፣ ግልጽነት የጎደለው ኢ-ፍትሐዊና የማሰነ (unjust and corrupt) የሴኩላሪዝም መርሖ ማራመዳቸው ከስማዊ ልማትና የይስሙላ የሰላም ኹኔታቸው ጋራ ተደማምሮ በእርስ በርስ ግጭትና እምነት ወለድ ሽብር ዋጋ እየከፈሉ ካሉት እንደ ናይጄሪያና ሕንድ ካሉ አገሮች ትምህርት መውሰድ ይገባል፡፡

በፈረንሳይ ነበር-ካቶሊካዊነት እና በቱርክ ነበር-እስላማዊነት ላይ የገነገነው ሴኩላሪዝም (assertive secularist policies) በድጋፍና ተቃውሞ ባስከተለው ፖሊቲካዊና ማኅበራዊ ባላንጣነት ሳቢያ አገሮቹ ከኖሩባቸው ዕሴቶች ጋራ ተራርቆ ሊራመድ ወደሚችለው መርሖ (passive secularism) የመሸጋገር ርምጃዎች እያሳዩ እንደኾነ የሳንዴያጎው ዩኒቨርስቲ ምሁር ይገልጻሉ፡፡ አዎ! በሴኩላሪዝሙ ሃይማኖትና መንግሥት ተነጣጥለዋል፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፡፡ ሃይማኖትም በመንግሥት አስተዳደር ጉዳይ እጁን አያስገባም፡፡ እዚኽ ላይ ግልጽና የሠመረ ምላሽ የሚሻው ጥያቄ ግን መለያየቱና መነጣጠሉ እንዴትና በምን ደረጃ (the levels of the exclusion) ይኹን ነው፤ ይላሉ ምሁሩ፡፡

ሴኩላር ነው የሚባለው የአገራችን ሕገ መንግሥት ከሃይማኖት ጋራ ለተገናኙ ጉዳዮች የያዛቸው መሠረታዊ መርሖዎች÷ የእምነት ነፃነት እና እኩልነት ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና እንዳገኘ እንዲኹም መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ መኾናቸውን የሚደነግጉ ናቸው፡፡

ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ሲባረኩዜጎች የእምነት ነፃነት ተጎናጽፈዋል ሲባል የሚያምኑበትን ነገር በግልና በቡድን የመግለጽየማስተማርና የመተግበር መብቶችን ያካትታል፤ የአምልኮአቸውን አስተምህሮና አተገባበር ተቋማዊ መዋቅር በመዘርጋት የማደራጀት፣ የማስተዳደርና የማስፋፋት መብታቸው የተረጋገጠ ነው፤ የሕዝብ ደኅንነትና ሰላም፣ ጤናንና ትምህርት፣ የሞራል ኹኔታ፣ የሌሎችን መሠረታዊ መብቶችና ነፃነቶች የማይጋፉና የማይጎዱ እስከኾኑ ድረስ በኃይልና በሌላ መልኩ ሊገደብ አይችልም፡፡

ከዚኽ አኳያ ቤተ ክርስቲያናችን ሐዋርያዊ ተልእኮዋን ለማጠናከርና አስተምህሮዋን ለትውልድ ለማስተላለፍ የምእመኗን አቅም በማስተባበር ባቋቋመቻቸው የቴዎሎጂ ኮሌጆች ገብተው እንጀራዋን እየበሉ የሌላ እምነትና ባህል ለማስረግ ሲሞክሩ በማስረጃ በተረጋገጠባቸው ላይ ርምጃ እንዳትወስድ ጸጥታዊ ጫና ለመፍጠር፣ ከዚኽም አልፎ መምህራኑን ‹‹መናፍቅ አትበሉ፤ መናፍቃን እያላችኹ አታስተምሩ፤ አክራሪነትና ኋላቀርነት ነው›› ብሎ መመሪያ ለማውረድ የሚሞክሩ ግለሰብ ባለሥልጣናት በሕገ መንግሥታዊ መርሖው መሠረት በሕግ የሚያስጠይቅ የጣልቃ ገብነት ተግባር እየፈጸሙ መኾኑ ሊስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በኮሌጆቻችን ለሐዋርያዊ ተልእኳችን የምንፈልጋቸውን ምሁራን በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሯችን ብቻ የማሠልጠንና የአፈጻጸሙን አግባብነት የመቆጣጠር መብቱ የእኛው ነውና፡፡

ሃይማኖት በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱ እምነቶችን የበላይና የበታች በማድረግ የዴሞክራሲን መሠረት መናድና ደብዛውን ማጥፋት እንደኾነ ከተገለጸ፣ በተመሳሳይ አኳኋን በአንዳንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ተማሪው – ምእመን በግሉ በሚፈጽመው ሥርዐተ እምነት ውስጥ ጥቂት ሓላፊዎች በራሳቸው አካሔድ ጣልቃ እየገቡ የሚወስኑበት ኹኔታ፣ ከተማሪው – ምእመን ሃይማኖታዊ መርሕ ጋራ የሚጋጭና የአንዱ ሃይማኖታዊ ትምህርትና ሥርዐት በሌላው ጫናው ውስጥ እንዲወድቅ የሚፈቅድ በመኾኑ የእምነት ነፃነታችን የሚሸራረፍበት አሠራር አስቸኳይ እርማት ሊደረግበት ይገባል፡፡

በተከታታይ ዘገባዎች እንደታየው፣ በጅማ ዩኒቨርስቲ አራቱም ካምፓሶች ባለፉት ሦስት ዓመታት በአጽዋማት ወቅት የምግብ ቤት አገልግሎቱ በሙስሊም እና በኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች መካከል የመስተንግዶ ልዩነት የሚታይበት መንሥኤ ምንድን ነው? ቤተ ክርስቲያናችን፣ ምእመናን ኹሉ ሰባት የዐዋጅ አጽዋማትን እንዲጾሙ ባዘዘችበት ኹኔታ ‹‹ኹለት አጽዋማትን ብቻ ነው የምናጾማችኹ፤ ሌላውን የማጾም ግዴታ የለብንም፤ የሐዋርያት ጾም የሚባል የምናውቀው የለም፤›› የሚለው የተማሪዎች ዲኑ ውሳኔ በየትኛው አሠራር የተደገፈ ይኾን? ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች የተመደበላቸውን በጀት በነፍስ ወከፍ ተጠቅመው ሥርዐተ አጽዋምን በየራሳቸው ማለትም በግላቸው ቢፈጽሙ በመንግሥት ጽሑፎች ከተገለጹልን የሴኩላሪዝም መርሖዎች የትኛውን ይጥሱ ይኾን?

የመንግሥትና የሕዝብ የትምህርት ተቋማት ከሃይማኖታዊ ትምህርትና ሥርዐት ተጽዕኖ ነፃ መኾናቸውን ለማረጋገጥ፣ አክራሪነትንና ጽንፈኝነትን የማስፋፋት ዕድል ለመገደብ በሚል የተቀመጠው ክልከላ በጥቅሉ የሚለው፣ ‹‹በትምህርት ተቋማት ውስጥ በቡድን መጸለይ፣ በቡድን መስበክ፣ በቡድን መዘመር፣ በቡድን መስገድ፣ በሃይማኖት አለባበስ ሽፋን ማንነትን ለመለየት የማያስችል አለባበስ የተከለከለ ነው፤›› ኾኖ ሳለ የዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ዲን ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎችን ለይተው ከትምህርት ገበታቸው እስከማሳገድ ድረስ የሚበድሉበት ‹የሴኔት ሕግና ፕሪንስፕል› ምን ይኾን? የጅማ ዩኒቨርስቲው አድልዎ ዐደባባይ መውጣቱን ተከትሎ በሌሎቹ ተቋማትም በኦርቶዶክሳውያንና በሥርዐተ እምነታቸው ላይ ያነጣጠሩ የሃይማኖታዊ መልካም አስተዳደር በደሎች እየተፈጸሙ ስለመኾኑ የሚያመላክቱ መረጃዎችና ሪፖርቶች እየወጡ ነው፡፡

የሴኩላሪዝማችን መርሖ÷ ‹‹የአስተሳሰብ ግልጽነትና የአፈጻጸም ወጥነት የጎደለው (vacuous secularism) ነው፤›› በሚል የሚተቸውና በሰበቡም አንዳንድ ባለሥልጣናት በጥንታዊት፣ ብሔራዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ርእዮታዊና ሃይማኖታዊ ጥላቻቸውን ለማስፋፋት፣ በፖሊሲዎችና በመዋቅራዊ አሠራሮች ተቋሞቿንና የተከታዮቿን ሃይማኖተኝነት ለማዳከምና ከተከታዮቿ ለመነጠል በመሣርያነት ይጠቀሙበታል፤ የምንለው እንዲኽ ባሉትና በመሰሏቸው ማሳያዎች አስረጅነት እንደኾነ ቢታወቅ መልካም ነው፡፡

ማዕተባችንን እናጠብቃለን፤ ግዴታችንም እንወጣለን

Amhara woman with traditional cross

ማዕተብ ከክርስቲያንነት መለዮነቱ (በአእምሮ ወንድማገኘኹ “The Ethiopian Orthodox Church” መጽሐፍ አገላለጽ ‘’badge of Christianity’’) አልፎ ማንነት እና ባህል እንደኾነ የሚኒስትር ሺፈራውን ‹‹ማተቡም ቢኾን የጊዜ ጉዳይ ነው፤ መውለቁ አይቀርም›› ማሳሰቢያን ተቃውመው አስተያየት የሰጡ የሥልጠናው ተሳታፊ ገልጸዋል፡፡

ማዕተብ ባህል ኾነ ሲባል በአባባል፣ በአነጋገር፣ በልማድ፣ በሕግ፣ በሥርዐት የእምነትና ክሕደት፣ የፍርድና ውሳኔ መግለጫነቱን ያሳያል፡፡ ማተበ ቢስ ማለት ማተቡን የማያስር ብቻ ሳይኾን ማተብ እያለው ሕገ ወጥ ሥራ የሚሠራ ሰው ማለት ነው፡፡ ማተብ የለሽ በአንገቱ ክር የሌለ፣ በሓላፊነቱ ያልታመነ ሰው ነው፡፡ ማተቡ ተያዘ ማለት የማይገባ ሥራ ስለሠራ ከክርስቲያን ተለየ ማለት ነው፡፡ ማተቡን በጠሰ ማለትም ክርስትናው ካደ ማለት ነው፡፡

በዚኽ ደረጃ ከእምነታችንና ማንነታችን ጋራ የተዋሐደ ይትበሃላችንን በመፃጉዕ አስተሳሰብና ተግባር ለማክሰም ከመጣጣር ይልቅ ሴኩላሪዝማችንን ቢያውደውኮ መርሖውን የፖሊቲካዊና ማኅበራዊ ባላንጣነት መንሥኤ ሳይኾን ሙሉዓ ዕሴት (value-laden) የኾነ የሰላምና የብሩህ ተስፋ ምንጭ ያደርገዋል፤ ሃይማኖት እና አዎንታዊው ሴኩላሪዝም ለሚጋሯቸው የነገረ ሰብእ እና ሞራላዊ ዕሴቶች ማበብም (development of humanistic and moral values) የበኩሉን ሚና ይጫወታል፡፡ ልማታዊነት የምንለውስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት ብቻ ከኾነና በሃይማኖተኝነትና ሞራላዊ ሥሡነት ካልታረቀ መጨረሻው ምን ሊኾን እንደሚችል ከኹላችን የተሰወረ ነውን?

የመንግሥት መካከለኛ አመራሮች ‹‹ሞተር ኃይል እና ቁልፍ ሚና ይዘው የሚንቀሳቀሱ›› እንደኾኑ በሥልጠናው መዝጊያ ላይ ከመገለጹ አንፃር፣ በዚኽ ደረጃ በሚገኘው አካል ዘንድ ‹‹ማተቡም ቢኾን የጊዜ ጉዳይ ነው፤ መውለቁ አይቀርም›› ዐይነት እምነትንና ማንነትን በቀጥታ የሚፃረር ድፍረት፣ ከአነጋገር ማዳጥ የተፈጠረ ‹‹የግለሰብ የአፈጻጸም ጉድለት›› ተብሎ ይታለፋል ወይስ በሴኩላሪዝሙ መርሖና በፖሊሲው የታዘለ ‹‹ሥርዐታዊ ጥሰት›› ተደርጎ ይወሰዳል!?

ክርስትናችን ‘የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጥ’ የሚል ሴኩላሪዝምን በአዎንታዊነትና በቀላሉ የሚገልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ያለው እንደኾነ የሥልጠናው ተካፋዮች ይገልጻሉ፡፡ የአገራችን የሴኩላሪዝም መርሖም ምእመኑን ለእምነቱ ለዘብተኛ በማድረግ በሒደት ወደ ሃይማኖት አልባነት የመምራት ተንኰል የተሸሸገበት ከሚያሰኝ አቀራረብ ሊጠበቅ እንደሚገባው ይመክራሉ፡፡

ክርስቲያንነታችንን በየራሳችን የምንመሰክርበት መለዮአችን ማዕተብ ለመንግሥት ሴኩላርነት ተፃራሪ እንደኾነና ሊከለከል እንደሚችል መናገር፣ የመንግሥትን የሴኩላሪዝም መርሖ በማማሰንና የተሳሳተ መልእክት በማስተላለፍ ሰፊውን አማኝ ፀረ – ሴኩላር የሚያደርግ፣ ሕዝቡንና መንግሥትንም ፊት ለፊት የሚያፋጥጥ እንዳይኾንም የሚኒስትር ሺፈራው አነጋገርና ጠቅላላ አካሔድ እርምትና ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚገባ ያስጠነቅቃሉ፡፡


*መስቀል ስንል

Ethiopain Orthodox Church Hand Crosses‹‹መስቀልና ሃይማኖታዊ ይዘቱ›› በሚል ርእስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ ለመስቀል ደመራ ክብረ በዓል የተሰራጨው በራሪ ጽሑፍ፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ለማዳን የተሰቀለበት አራት ክንፍ ያለው መስቀል ስሙ ‹‹ሐዋርያ መስቀል››፤ ‹‹መጾር መስቀል›› እንደሚባል ይገልጻል፡፡ የመስቀልን ስያሜ አስመልክቶም መስቀል ጌታ በተሰቀለበት አምሳል ከዕንጨት፣ ከብረት፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከወርቅ፣ ከዕብነ በረድ ከሌላም የከበረ ማዕድን እየተሠራ ከአበው ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ቄሶች በሙሉ በእጃቸው የሚይዙት፣ ክርስቲያኖችም የሚሳለሙትና በአንገታቸውም የሚያስሩት፣ ሴቶችም በቀሚሳቸው የሚጠልፉት፣ በግንባራቸውም የሚነቀሱት ኹሉ ስያሜው መስቀል እንደኾነ ያትታል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው፣ የመስቀሉ አማናዊና ምስጢራዊ ኃይል በእምነት የደረሳቸው ምእመናን በክርስቶስ አምነው በመስቀል አማትበው ከኃጢአትና ከአምልኮ ጣዖት ድነዋል፤ አጋንንትን፣ መናፍቃንን ፍትወታት እኵያትን ድል ሲያደርጉ ኖረዋል፤ ይኖራሉም፡፡ ከዚኽ የተነሣ የክርስቲያኖች ኪነ ጥበብ ኹሉ ምልክቱ መስቀል ነው፡፡ በልብሳቸው፣ በመጽሐፋቸው፣ በቤት ዕቃቸው ኹሉ የመስቀል ምልክት አለበት፡፡

Ethiopian girl with a Coptic cross tattoo on her foreheadበብዙ አገሮች ይልቁንም በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ክርስቲያን መኾናቸው የሚታወቀው በክንዳቸው፣ በመዳፋቸው በሚጠቆሩት የመስቀል ቅርፅ እንደኾነና ክርስቲያን ነን ለማለት ሲፈልጉ ያን ብቅ አድርገው እንደሚያሳዩ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መጽሐፋቸው አስፍረዋል፡፡

በሀገራችንም ጥልፉ ዝምዝሙ፣ ጌጣ ጌጡ ሳይቀር ሴቶቹም በግንባራቸውና በሌላውም አካላቸው በመስቀል ቅርፅ ይጠቆራሉ፡፡ በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ብቻ ሳይኾን ከሞቱም በኋላ መስቀል ከምእመናን አይለይም፡፡ ዐፅማቸው በሚያርፍበት በመቃብራቸው ኹሉ የመስቀል ቅርፅ ከዕፅ ወይም ከደንጊያ ይሠራል፡፡ በመቃብራቸው ላይ መደረጉ፣ መስቀል የሞትና የመከራ ምሳሌ መኾኑ ቀርቶ የትንሣኤና የሕይወት ምልክት መኾኑን ለመግለጥ እንደኾነ ብፁዕነታቸው በመጽሐፋቸው አስረድተዋል፡፡


 *ማዕተብ – መከራ መስቀል

  • ‹‹ሦስት ፈትል አንድነት እየሸረቡ ለክርስትናው ሕይወት መግለጫ ማዕተብን በክርስትና ጊዜ አንገት ላይ ማሰር በቤተ ክርስቲያናችን የጸና ኾኖ ሲሠራበት ይኖራል፡፡››
/ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ እንዲጠበቁ ለማንቃት በሰኔ ወር ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ‹‹ተዐቀቡኬ እምሐሳውያን ነቢያት፤ ከሐሰተኞች መምህራን ተጠበቁ›› በሚል ርእስ ከተዘጋጀው መጽሐፍ/

ethiopian-orthodox-deacon-cherie-richardson
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ቤዛ የተቀበለው ጽኑ መከራ በማጠቃለል መከራ መስቀል ይባላል፤ ከመከራ መስቀሉም አንዱ አንገቱን በሐብለ ኀጺን (በብረት ገመድ) ታስሮ መጎተቱ ነው፡፡ ማዕተብ ‹‹ዐተበ፣ ባረከ›› ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲኾን መለያ፣ መታወቂያ ምልክት ማለት ነው፡፡ ይኸውም ያመኑትና የተጠመቁት ካላመኑትና ካልተጠመቁት የሚለዩበት የክርስቲያንነት መታወቂያ ነው፡፡ የዚኽም ምልክት መሠረቱ፣ ጌታችን መድኃኒታችን በዕለተ ዓርብ ከተቀበለው ጸዋትወ መከራ አንዱ የኾነው በገመድ ታስሮ መጎተቱ ነው፤ የማዕተብ ምሳሌነቱም ይህንኑ የሚያመለክት ነው፡፡ (ዮሐ. ፲፰÷፲፪ – ፳፬)፡፡

ይህንንም ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ኀደገ ለነ ማዕተቦ፤ ክርስቶስ ፍለጋውን ትከተሉ ዘንድ ምልክቱን ሊተውላችኹ ስለ እናንተ መከራ ተቀብሏል፡፡››(፩ኛጴጥ. ፪÷፳፩) ብሏል፡፡ ነቢዩ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ፤ ለሚፈሩኽ ምልክትን ሰጠኻቸው›› ብሎ የገለጸውን ቤተ ክርስቲያናችን ከትእምርተ መስቀሉ ጋራ በማገናዘብ የክርስትና ምልክት አድርጋ ትጠቀምበታለች፡፡ (መዝ.፶፱÷፬)፡፡

በዘመነ ሐዋርያት ማዕተብ/ማተብ የክርስቲያኖች መለያ ኾኖ ይሠራበት እንደነበርና በኋላም እነያዕቆብ ዘእልበረዳኢን የመሳሰሉ የቤተ ክርስቲያን አባቶች የአማንያንና የኢማንያን መለያ አድርገው ይሠሩበት እንደነበር የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይናገራል፡፡ በዚኹ ሥርዓትና ትውፊት መሠረት ሦስት ፈትል አንድነት እየሸረቡ ለክርስትናው ሕይወት መግለጫ ማዕተብን በክርስትና ጥምቀት ጊዜ አንገት ላይ ማሰር በቤተ ክርስቲያናችን የጸና ኾኖ ሲሠራበት ይኖራል፡፡


* *ማዕተበ ክርስትና የሚታሰርበት ሥርዐተ ጥምቀት እና ሥርዐተ ሜሮን

Infant Baptism in EOTC00

በልደተ ሥጋ ያገኘናት ልጅነት ከጥምቀት በምትገኝ ልጅነት (በሐዲስ ተፈጥሮ) ስትታደስ የአዲስ ሕይወት ባለቤቶች እንኾናለን፡፡ ይህም አዲስ ልደት በወልድ ውሉድ፣ በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ መኾን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐት ወንድ ልጅ በተወለደ በአርባ ቀኑ፣ ሴት ልጅ በተወለደች በሰማንያ ቀኗ ይጠመቃሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የተጠማቂውን መላ ሰውነት በውኃ ውስጥ በማጥለቅና ከራስ ጀምሮ በሰውነት ላይ በማፍሰስ ታጠምቃለች፤ የሥርዓቱ አፈጻጸም እንደሚከተለው ነው፡፡

ወላጆቹ የሚጠመቀውን ሕፃን ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን ይመጣሉ፡፡ ቄሱ ውኃውን በብርት አድርጎ ሥርዐተ ጸሎቱን ይጀምራል፡፡ የክርስትና እናት ወይም አባት ለመኾን የመጡት የሕፃኑን አውራ ጣት ይዘው ተጠማቂው ሊለው የሚገባውን ሦስት ጊዜ ‹‹እክሕደከ ሰይጣን›› እያሉ ሰይጣንን ያወግዛሉ፡፡ ሥርዐተ ጸሎቱ ተገባዶ ዲያቆኑ ‹‹ጸልዩ በእንተ ዛቲ ቤተ ክርስቲያን›› ሲል ተጠማቂው ካደገ ከተማረ በኋላ የመጣ እንደኾነ ራሱ፣ ሕፃን ከኾነ ግን የክርስትና አባት/እናት ጸሎተ ሃይማኖትን ይደግማሉ፡፡ ይህ ሲፈጸም የተጠማቂው ልብስ ይወልቃል፡፡

ተጠማቂው ሕፃን እንደኾነ ዲያቆኑ ተቀብሎ በኹለት እጁ ይይዘዋል፤ ዐዋቂ ከኾነ ግን ራሱን ስለቻለ ዲያቆኑ ይመራዋል እንጂ አይታቀፈውም፤ ማጥመቂያውን በአራቱ ማእዝን እያዞረ በምሥራቅ በምዕራብ በሰሜን በደቡብ ‹‹እሰግድ ለአብ እሰግድ ለወልድ እሰግድ ለመንፈስ ቅዱስ›› ይላል፡፡ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለኹ ማለት ነው፡፡ በዚኽ ጊዜ ቄሱ መስቀሉን በተጠማቂው ግንባር ላይ አድርጎ ‹‹ይኩን ስመከ እገሌ›› እያለ ስመ ጥምቀቱን ሦስት ጊዜ በመጥራት በክርስትና ስም ይሰይመዋል፡፡

ተጠማቂው የክርስትና ስም የሚወጣለት ቄሱ በሚያውቀው የዕለቱን በዓል ምክንያት አድርጎ ነው፡፡ ለምሳሌ በዓሉ የጌታ፣ የእመቤታችን እንደኾነ ገብረ መድኅን፣ ኃይለ ማርያም፤ የቅዱስ፣ የመልአክ እንደኾነ ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ወልደ ሚካኤል በሚል ስም ይሰይመዋል፡፡ ይህ ከተፈጸመ በኋላ አዳም ትእዛዘ እግዚአብሔርን ጥሶ ወደ ሲኦል መውረዱን ለማዘከር ተጠማቂው ፊቱን ወደ ምዕራብ ይመልሳል፡፡ በመቀጠል አዳም አባታችን የድኅነት ተስፋ መስማቱን ለማዘከር ተጠማቂው በማዩ አንፃር መቆም ይኖርበታል፤ ድኅነት በጥምቀት ነውና፡፡(ማር.፲፮÷፲፮)፡፡

ይህ ሲፈጸም ቄሱ ማዩን ‹‹ቡሩክ›› ብሎ ባርኮ ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ካለ በኋላ ‹‹አጠምቀከ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ›› እያለ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አድርጎ ያጠምቀዋል፡፡ ቄሱም የተጠማቂውን እጁን ይዞ ወደ ምሥራቅ ፊቱን ይመልሰዋል፡፡ ይህም ጌታ በጥምቀት ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት እንደመለሰን ያስረዳል፡፡ (ዘፍጥ.፪÷፰፤ ሕዝ.፵፬÷፩ – ፱፤ ዮሐ.፫÷፭)፡፡

ስያሜውና ጥምቀቱ ሲያበቃ ካህኑ በተጠማቂው ፊት ላይ ‹‹ንሣዕ መንፈሰ ቅዱሰ፤ መንፈስ ቅዱስን ተቀበል›› እያለ እፍ ይልበታል፡፡ ቀጥሎ ቅብዐ ሜሮን ይቀባዋል፡፡ ሦስት ኅብረ ቀለማት ያሉት ፈትል ተገምዶ በአንገቱ ይታሰርለታል፡፡ ይህም በግእዝ ማዕተብ፣ በአማርኛ ማተብ ይባላል፡፡ ቀለሙ ሦስት ዓይነት ነው፡፡ ሦስት መኾኑ የሥላሴ ሦስትነት፣ አንድ ኾኖ መገመዱ የአንድ አምላክ ምሳሌ ነው፡፡

ሕፃኑ ልብሱን ከመልበሱ በፊት ቄሱ ሕፃኑን እንደገና ተቀብሎ በኹለት እጁ ከፍ አድርጎ ይዞ ‹‹ይባዕ መንፈስ ቅዱስ›› እያለ እፍ ይልበታል፡፡ ለክርስትና አባት፣ እናት ያስረክበዋል፤ ከልጅኽ፣ ከልጅሽ የማትለየው፣ የማትለይው፤ በክርስቲያናዊ ሃይማኖትና ምግባር የምታሳድገው፣ የምታሳድጊው እያለ፡፡ የክርስትና አባትም ወይም እናትም እሺ፣ አዎ እያለ/ች ይቀበላል/ትቀበላለች፡፡ ከዚኽ በኋላ ተጠማቂው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ይቆርባል፤ የጥምቀት ሥርዓት የሚፈጸመው ተጠማቂው ሲቆርብ ነውና፡፡

ምንጭ፡-
  • ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን
  • ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት
  • መራሔ ድኅነት

61 thoughts on “ሚኒስትር ሺፈራው: በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የክርስቲያንነት መታወቂያችንን ማዕተብ ከማሰር እንደምንከለከል አስታወቁ፤ ማዕተባችንን እናጥብቅ!

  1. Anonymous October 5, 2014 at 3:45 am Reply

    ያበደ ውሻን ካልተከላከሉት ሁሉንም ነክሶ ይጨርሳል!

  2. Anonymous October 5, 2014 at 4:15 am Reply

    ግቢ ጉባኤያት፣ በሥነ ምግባር የታነጸ ዜጋና የቤተ ክርስቲያንን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚያግዝ የአበው ተተኪ ትውልድ ማፍሪያ እንጂ ተንኰልና ክፋት በተጠናወተው አእምሮ እንደሚባለው ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት አስቀጣይ ኃይል መመልመያ መድረክ›› አይደሉም

    • Anonymous October 6, 2014 at 7:06 am Reply

      ግቢ ጉባኤያት፣ በሥነ ምግባር የታነጸ ዜጋና የቤተ ክርስቲያንን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚያግዝ የአበው ተተኪ ትውልድ ማፍሪያ እንጂ ተንኰልና ክፋት በተጠናወተው አእምሮ እንደሚባለው ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት አስቀጣይ ኃይል መመልመያ መድረክ›› አይደሉም

  3. admasu demeke October 5, 2014 at 6:32 am Reply

    bakachihu tewign hulum yerasu haymanot lay akrari nw. degreew yileyayinji.haymanot ina mengist yeteleyaye nw ketebale ante haymanotawi megelechawochin bemengist bet sitakenawin nw irasin meteyek yemigebah weyis lemitefestimew sihitet mengist talka megibatun metechet nw sihitet lhon yemigebaw tilaleh/ yihen balenibet kom bilen linatenew yigebal yemil imnet alegn. state and religion is separate. article 11 of theFDRE constitution. haymanotawi nestanet ikulinet ina mesel hunetawochin article 27 liteqis zirzir higochin memelik beki yihonal yemil imnet alegn.mengist sihetetochin yemarem hige mengestawi mebt indalew mawek degmo tegebi yihonal yemil imnet alegn bechifin metechet ina bechifin mamoges tiru aydelem

    • Anonymous October 6, 2014 at 7:13 am Reply

      Article <<<<<<< the holly BIBLE

  4. Fetsum Berhane October 5, 2014 at 1:23 pm Reply

    what does “ብሔራዊትቤተ ክርስቲያናችን” mean? you are boko haram

    • ተስፋዬ October 6, 2014 at 4:36 am Reply

      ወፈፌ ካድሬ ቱልቱልን ንፋ !!!

    • Anonymous October 6, 2014 at 7:11 am Reply

      Ahiya silehonk ayigebahim

    • Teklay October 6, 2014 at 5:48 pm Reply

      To Fetsum Berhane
      You are banda who brays your mother Ethiopia and you are someone who does not have faith and believe, you mentality is evil and wild. There was no time that Ethiopian Orthodox was behind any destruction rather teaches love, unity and way of salvation to Christian, further more teach us even to love our enemies. So where did you get Boku Haram.
      Yes, you are saying what you thing in your mind waiting a day to butcher Orthodox Christian believer, it will never happen, You are banda and evil the son of Satan who teaches you all evils and haterate.

    • wen October 7, 2014 at 5:11 am Reply

      Ante fitsum dedeb sew neh leka,,,,,,,,, boku haram eko sew yemiard neft yanesa,,,,,, geday budin new. yeneman jele. neh.,,,,,,, leloch silaweru bicha mawrat yastezazibal

  5. engida kelecha October 5, 2014 at 5:58 pm Reply
    • Teklay October 6, 2014 at 5:57 pm Reply

      Minister Shiferaw T/Marian is the delegate of evil, the messenger of Satan or Diablos, who does not have believe and faith. Please make sure you should not play with fire. You might have seen some fathers or priests who are weaken of pray and fasting, and think that you want to varnish them and put instead you satanic ideology protestant, that is dream which Italy and some other European powers tried in 1890s and fail to do and you are the son of bitch

  6. Anonymous October 5, 2014 at 10:03 pm Reply

    Fitsum EOTC is ብሔራዊትቤተ ክርስቲያናችን” Don’t be surprised. This is because the church is ancient and could creat Ethiopia itself.

  7. […] ሚኒስትር ሺፈራው: በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የክርስቲያንነት መታወቂያችንን ማዕተብ ከማሰር እንደምንከለከል አስታወቁ፤ ማዕተባችንን እናጥብቅ!ምንጭ – ሐራ ዘተዋሕዶ […]

  8. sami October 6, 2014 at 5:48 am Reply

    @fetsum berhane የኢትዪጵያዊነት መሰረት የተጣለባት ስልሆነች ብሔራዊትቤተ ክርስቲያናችን ተብላለች የኢትዪጵያ ታሪክ ማለት የቤተክርሰቲያን ታሪክ ማለት ነው ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናችው፡፡ ካልገባህ ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ እንኳን ሊገባህ ይገባል ፡፡
    እንኳን ዛሬ የተነሱ የምዕራብያዊያ ቡችሎች ይቅርና የሲዖል ደጆች የማይችሉዋት ቤተክርሰቲያን ናት ያለችን ሚኒስትር ተብየው እንዲህ ስላለ የምንረበሽ ባንሆንም የበለጠ እንድንጠነክር ግን የሚያደርገን ነው፡፡
    በቅዱሳኑ ስም የተሰየማችው እናንት የቤ/ክ አርበኞች የጥንት ጠላታችን ፍላፃው የተለያ ስለሆነ በዚህ የምትረበሹ አይመስለኝም ጌታችንስ የተለያየ ስም ተሰጥቶት አልነበር …እኛም የአባታችን ልጆች ነን በሉሲፈር ልጆች የማንወደድ
    ቤተክርሰቲያናችንን(አገራችንን) ፈጣሪያችን ይጠብቅልን!

  9. Anonymous October 6, 2014 at 5:59 am Reply

    minm ayametam. dirom sew eminet kata/kelelew letifat enji ……………………lebego yemiyasbibet hilina yelewm miknyatum ye abatu lij newna
    …………..

  10. Anonymous October 6, 2014 at 7:10 am Reply

    ማዕተቤ የሥጋዬ አካል ናት፤ስትበጠስ ያመኛል፤በሠማይ ካለችው ሀገሬ ከክርስቶስ መንግስት ይለየኛል፤ነፍሴ ያለችው በማዕተቤ ላይ ነው፤የመንግስተ ሰማያት ዜጋ መሆኔን የምታስረግጥ መታወቂያየ ናት፤ ይህችን መታወቂያዬን ምንም ሊበጥሳት ቢሞክር ስለ እርሷ ነፍሴን አሳልፌ እሰጣለሁ፡፡ ስለ ማዕተቤ በብዙ ሽህ የሚቆጠር ሰራዊት ዙሪያየን ቢከበኝ ልቤ አይፈራም፤ ከቶውንም ከመንገዴ ፈቀቅ አልልም፡፡ስለ ማዕተቤ ብዙ መከራን የማሸንፍበት የክርስቶስ ኃይል ከኔ ጋር ነው፡፡

  11. ye October 6, 2014 at 7:10 am Reply

    ግቢ ጉባኤያት፣ በሥነ ምግባር የታነጸ ዜጋና የቤተ ክርስቲያንን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚያግዝ የአበው ተተኪ ትውልድ ማፍሪያ እንጂ ተንኰልና ክፋት በተጠናወተው አእምሮ እንደሚባለው ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት አስቀጣይ ኃይል መመልመያ መድረክ›› አይደሉም

  12. Anonymous October 6, 2014 at 7:37 am Reply

    Hitting the load instead of the donkey!!

  13. Anonymous October 6, 2014 at 7:41 am Reply

    ወያኔ ዝም ከተባለ ገና ታሪክ ያበላሻል
    የታሪክ አተላወች

  14. Anonymous October 6, 2014 at 9:03 am Reply

    ene eko yemigermegn mengist yihin yahil sayawkew kerto yihon woise mengistm alamaw mateb masfetat new .kehone yemengistnet terzu mn lay endhone yetfabet aymeslachihum

  15. selam October 6, 2014 at 9:23 am Reply

    My comment

    Esu mateb lemebetes semoker yesewuyewun anget beteso metal new. Negeru tebekay Egzeabher wagawun yekeflewal metebek new yehe menafk

  16. anonymous October 6, 2014 at 9:31 am Reply

    Anten belo demo heg dengagi beteso yetalke bel mokera demo sele mateb men agebak kalamenkew zem belek be megeset bet eyezerefk bela

  17. Anonymous October 6, 2014 at 4:50 pm Reply

    PASTOR sHIFERAW tEKLEMARIAM(DR) IS TRYING TO DEMOLISH OUR CHURCH BUT IT IS TRIAL LIKE WHAT HAS BEEN DONE BY HIS BROTHERS (MENAFIQAN) IN THE PAST. HE SHOULDN’T TRRADE WITH HIS GOVERMENTAL AUTHORITY TO PREACH OTHERS. IT IS A TYPICAL CRIME AND HE WILL PAY THE PRICE ONE DAY.

  18. Anonymous October 6, 2014 at 5:12 pm Reply

    “የማህበረ ቅ. አባላት እዚህ ውስጥ አላችሁ፣የድርጅትም/የፖለቲካ/
    አባል ናችሁ ” ሰውየው እውነት አለው። አንዲት ቅ.ቤ/ክ ማኅበረ ምዕመናን ናት
    እናንተ ግን ውስጥ ገብታችሁ ሸመቃችሁባት፨ ብዙ የዋሃንን አሳታችሁ ፦ ከቤቱ
    ይልቅ” ማኅበሬ” እንዲል አደረጋችሁት ሰንበት ተማሪውን መለመላችሁት
    ለቅ. ቤ/ክ የሚገውን አሥራት ከውስጥም ከአገር ውጭም ወደ ካዝናችሁ አስገባችሁ፣
    ሌላም ብዙ ግፍ አደረጋችሁ ።ለሽፋን/ under cover/ ለማስመሰል የምታደርጉት እንዳለ ሆኖ።
    “mahbere kdusan weys mahbere seytan” ለማንኛውም የሁሉም ፍጻሜ ርኁቅ አይደለም።

  19. serawit Debebe October 6, 2014 at 6:21 pm Reply

    EGZIABIHER haymanotachini yixebqilin !!!

  20. abebe tassew October 7, 2014 at 4:08 am Reply

    Bekresitna menor kefitena gar abro eskehelfet monorenew ena eninoralen

  21. Arbagashaw Maru October 7, 2014 at 4:20 am Reply

    ‘እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል’፡፡
    ሮሜ 8፥31

    • miki October 18, 2014 at 4:36 pm Reply

      right right no body no body
      …….n amen .

  22. Anonymous October 7, 2014 at 4:39 am Reply

    Ybasa. Atmita. Malit.new.egzabhir.mastwaline.ystike.ortodoxtawahdo.la.zalalime.tenur. Gin. Yeh.saw.emnatu.mindin.new???.ersu une. End.tarara.yakimra.end.dingay.yakbida.ersu
    ma new.wagnocha.egzabhir.yfrdale.batgesit.tabku.

  23. mesfin atnaf October 7, 2014 at 5:08 am Reply

    YEBRLAY AMERAROCH LEMEN ZIM ENDEMILU ALIGEBAGNIM? ANDEGNA DIRIJITUN ENA HIZIBIN EYARARAKE NEW, BITEKIRSTIAN EGIZIABIHIR YITEBIKATA ፣

  24. Anonymous October 7, 2014 at 6:35 am Reply

    Balebetune Kalenaku Aterune Aynekeneku

  25. Anonymous October 7, 2014 at 7:23 am Reply

    anedanede be betekeresetiyane wesete tedebekewe yeminoru ye lela hayemanote teketayoche nachewe enedihe ayenetune deregite yemfetsemute selezihe hezebe keresetiyanu betefeterewe ye hasete were bezume sayedenagere ewenetawene enedihe maweku dese yemile negere newe negere gene enezihene sewoch ahuneme lenetenekekachewe yegebale egziabhere Ethiopiane ena Hezebochuane yebareke.

  26. Anonymous October 7, 2014 at 8:15 am Reply

    እንግዲህ የማህበረ ቅዱሳን 3ኛው ገጽ ሲገለጥ እንዲህ ይነበባል 1ኛው እውነተኛውን ለሐይማኖቱ ትክክለኝነት የቆሙ እና የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብለው የሚጸልዩ እንጂ ቢደርሱባቸው እንኳን ሦስተኛው ወገን ደጅ መድረስ አይፈልጉም 2ኛዎቹ ቢዝነስ አሳዳጆች በመንፈሳዊ ጉዞ በሲዲ በካሴትና በመጽሐፍት ሽያጭ ናላቸው የዞረ ሐይማኖቱን የቢዝነስ ሴንተር ያደረጉ ገበያቸው ሲቀዘቅዝ ከ3ኛዎቹ ጋር የሚያብሩ ናቸው ለዛሬው አስተያየቴ መነሻ የሆኑት ፖለቲከኞቹ እና ሐይማኖቱን እንደሽፋን የሚጠቀሙት ናቸው እነዚህ ሲያሻቸው ቤተ እምነቱ ውስጥ ሰርገው ገብተው የሚያምሱ ሲያሰኛቸው ህዝበ ክርስቲያኑን ከመንግስት ጋር ለማጋጨት አልያም ምዕመናኑ ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር የከረረ ጸብ ውስጥ እንዲገባ የሚተጉ ናቸው ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ ፖለቲካውን የሚያላቁጡ ናቸው በየቢሮው ሰርገውም መንግስት ለስራ በሰጣቸው ኮምፒዩተሮች የፊት ገጽ ላይ የተለያዩ ሐይማኖታዊ ስዕሎች እና ጥቅሶች በማስቀመጥ ከሌሎች ዕምነት ተከታዮች ጋር ያልሆነ ፉክክር እና እሰጥ አገባ በመፍጠር ድብቁን የፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃ ለማድረግ በየጊዜው ይሞክራሉ ይህንን የመከላከል እና የመንግስት የስራ መሳሪያዎች ለመንግስታዊ ስራ ብቻ እንዲውል የማድረግ ግዴታ አለበት ታዲያ በዚህ ወቅት ነው በማህበረ ቅዱሳን ስም ጫጫታ ማስነሳት የሚፈልጉት ማንም ኢትዮያዊ የግል እምነቱን በተገቢው ቦታ የማራመድ ህገመንግስታዊ መብት እንዳለው ይታወቃል ይሁን እንጂ ባልተገባ ቦታ እና ጊዜ እንጠቀም ሲሉ በቃችሁ ስባሉ ያልተባለ እና ያልተደረገ አሉባልታ መንዛት ቀዳሚ ተግባራቸው ነው መንግስት ለስራ በሰጠህ መሳሪያ ላይ የግልህን ሐይማኖታዊ ድርጊት አትፈጽም ማለት አንገትህ ላይ ያለውን መስቀል አውልቀህ ጣል ማለት አይደለም ስለዚህ ሐይማኖቱን የፖለቲካ እና የጥላቻ መጠቀምያ ከማድረግ እንዲቆጠቡ የሁላችንም የዕምነቱ ተከታዮች ሃላፊነት ነው

    • Anonymous October 11, 2014 at 5:00 pm Reply

      ስለ መንግስት ሀብት አጠቃቀም ለመምከር የሞከርሀው ጥሩ ነው፡፡ይሁን እንጅ መንፈሳዊ ህይወትን፣ፈሪሃ እግዚአብሔርን የተለማመዱ፣ለዚያውም በአለም እውቀት የበለጸጉ ምሁራንን ስለ ሪሶርስ ሞቢላይዜሽን መምከር ሞኝነት ይመስለኛል፡፡

  27. Kidus October 7, 2014 at 11:01 am Reply

    Wa Shiferaw!!!!!!!! You were not born be derg zemen?
    <>

  28. Anonymous October 7, 2014 at 11:05 am Reply

    Kes bileh degmo yetenekesachihu yeMengist serategna mehon atichilum bela

  29. Enbakob October 7, 2014 at 11:30 am Reply

    ይኽ ዝም ከተባለ ያማኙን ልብ ያውካል
    ጥንታዊ የሆነችውን ማጥፋት ይሆናል

  30. Anonymous October 7, 2014 at 11:36 am Reply

    aste zeraicob and minilk bisemu mn yilu?

  31. Anonymous October 7, 2014 at 1:29 pm Reply

    kerfafa kabine .timihirt begolmasa yeceresew yibeltewal

  32. Anonymous October 7, 2014 at 5:42 pm Reply

    men al arfew bikemtu sew endeat be esat yechawetal ke maychelew gar lemen yetagelalu. mahetem yelelewen werket yefedral gudayoch minster yekebelal endea?egnam tewahedo yatemecheben mahetemachen new.awo egnan yangelatun yehonal hayal kendun gen aychelutem yemokerut.ahzab ena menafk mechem menem ayametum.esatun defro yenka hulu yekatelal.

  33. Anonymous October 7, 2014 at 6:21 pm Reply

    albezam

  34. rohama October 7, 2014 at 8:29 pm Reply

    Mahetabane!!! Alebeteseme!tenoraleche lezelzlem!!!!!!!!

  35. Anonymous October 7, 2014 at 9:00 pm Reply

    Albezam woyi mefazezu Dinizazew.

  36. Matebe Belete October 8, 2014 at 2:15 am Reply

    “ፎገራ አሳለፊ ደምቢያ እንጀራ ጣይ
    ተበላህ ጐንደሬ አትነሳም ወይ!”

    የተባለውኮ አፄ ×ሐንስ መተማ ላይ ተሰውተው ደርቡሽ ጐንደር ድረስ ዘልቆ ምዕመናኑን እያረደ ቤተክርስቲያኑን ባቃጠለበት ዘመን ነው፡፡ ይህ ከሆነ ወደ 13ዐ ዓመታት ያህል ተቆጥረዋል፡፡ እንግዲህ ይህ የመከራ ዘመን በተለይ በሰሜን ኢት×ጵያ ላይ ለዚያውም ለጥቂት ወራት ብቻ የዘለቀ ቢሆንም፣ ባለûት መቶዎች አመታት በ×ዲት ጉዲትና ግራኝ መሀመድ ዘመን በእናት ቤተክርስቲያናችን ላይ የተፈጽመውን ውድመትና ከጥቂት አስርት አመታት በፊት በጣልያን የተፈጸመውን “የማተብህን ፍታ” እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን እምነትና ቤተ እምነት የማውደም ዘመን ክርስቲያኑም ሆነ ሌላው ክርስቲያን ያልሆነው የሚረሳው አይደለም፡፡ ይኸውና አሁንም “የማተብህን በጥስ” ዘመን እየመጣ ነው፡፡ ሚኒስትራችን ማንንም ሳይፈ„ የመንግስታቸውን አÌም ነግረውናል፡፡ ይህ መጭው የምርጫ ዘመን ቢሆንም የህዝብ ደምፅ በማይከበርበት ሀገር ምንም ሊጠቅም አይችል ይሆናል፡፡ የሆነው ሆኖ ግን ይህን አጀንዳ በየሰበካ ቤተክርስቲያናችን ልንነጋርበት የሚገባ ነው፡፡ “ብዙሀን የመውዑ” ማለት ብዙሀን ይወስኑ፣ ይግዙ፤ ማለት ይመስለኛል፡፡ ጐበዝ፣ ማተባችንን አጥብቀን ቤተክርስቲያናችንን እንታደግ! ለመሆኑ እየተጠራ„ የሚሻ*ሻ*ሙት ፕሮቴስታንቶች መሆናቸውን ልብ ልንል ይገባል፡፡ በእውነቱ መንግስት ያለ ኦርቶዶክስ አማኙ ድጋፍ በመንግስትነቱ ሊቆምም ሆነ ሊዘልቅ እንደማይችል አÌም ይዘን ልንንነግረው የሚገባበት ጊዜው ዛሬ ነው፡፡
    እግዚአብሔር ሁለት ሽህ ዘመናት ወንጌል የሰበከች ጥንታዊት ቤተክርስቴያናችንን ይጠብቅልን፤ አሜን!!!

  37. Rahel October 8, 2014 at 1:44 pm Reply

    lots of white lies

    • Lafo October 21, 2014 at 7:15 am Reply

      ፕሮቴስታንትን ለቀቅ እናድርገውና ይልቁንስ በዚህ በተጋረጠው አደጋ ላይ አብረን በመነሳት ለክርስትና ሃይማኖት ዘብ መቆም ይገባናል:: የፕሮቴስታንት ተጽእኖ እንደሆነ የምናስብ ከሆነ ተለያይተን መበታተናችን ነውና ፀረ እምነት የሆነውን ይህን አመለካከት ማስቆም ይኖርብናል::

  38. Anonymous October 8, 2014 at 11:43 pm Reply

    @ Matebe …yihen hulu zemen wonge/meklit yekeberech …..Betekiristianachin 2000 amet yesebekechiw wongel lemin wonz meshager akatew?kiristos “bemelaw alem wongel yisebekal yanem mechereshaw yimetal blual.”yih memeria mefefetsemu gid naw demom iyetefetsemem naw. ignan leAfricawian hawariat adrgo bishomenim 1400 amet mulu wondimochachinin sanmesekirilachew,haymanot sinarakik yegilachin abeshawi kiristina fetren yihew zare betekiristianachin meimen sechi inji meimen tekebay mehon tesinuatal.memeriaw begna alseram. amarigna yemayawuk kes mefter alchalnim.kidase besumalegna yelem…lelam lelam…. ere bizu naw.lelelaw mabrat alchalnim… teklehaymanot ,abuye iyalin inkuwan keniya, sudan linders oromian inkua be hizbu language sebken badaresin. yegna 2000 ametat yaterefelin 1000 kesawust balubet mender 1000 Demelash yetebalu yekes lijoch mafrat naw.Minjar yenorku saw nagn yihe gilts naw.INA MEKISES MEKASES TITEN KALUN INIKETEL !!!!!!We need tehadiso..tehadeso ….tehadeso like the ancient korontos.Kalun yabiralin!!

  39. Anonymous October 9, 2014 at 9:04 am Reply

    wey gud mewidekiachew sifetin endih aregachew

  40. Anonymous October 9, 2014 at 1:24 pm Reply

    Igziabiher asteway libona indisetew tseliyu.

  41. abel akalemariam October 10, 2014 at 5:08 pm Reply

    tiru new

  42. Anonymous October 11, 2014 at 5:21 pm Reply

    yichinat chaweta man komo yiteyayal

  43. Anonymous October 14, 2014 at 1:16 pm Reply

    በርግጥም ይሄ አባባል ከፓርቲው ጀርባ የተሰጣቸው የቸርች ተልዕኮ እንደነበረ በደንብ ይታወቀል ለምን ቢባል ባለቤታን የምትተማመን እንደሚባለው በአሁኑ ሰአት በትክክለኛው እንደ ቤተክርሰቲያን የተበደለች በተቃራኒው ደግሞ እንደ ፐሮቴሰታነቱ ባለግዜ የለም ሌሎች እምነቶች በአምላክ ቸርነት እየቀጠሉ ቢሆንም እነሱ ግን እንደፈለጉ ነው፡፡ለምሳሌ የሙስሊም ወንዲሞቻችን የኢ.ኦ.ተ ስርዓተ አምልኮ ሰዓት ቦታ ወቅት የገደባቸውና ጥራዝ ነጠቅ ያልሆነ ሲሆን በስመ ቸርች ግን በየስርቻውና በየመኖርያ ቤቱ ሁሉ ሁካታና ግርግር ማብዛቱ በጣም ከሚፈለገው በላይ በዝተዋል፡፡ለዚህም ማሳያ የሚሆን በየመቶ ሜትሩ ቸርች እየተባለ አዛውንት በሽተኛ ሰዎች ቀን ሰርተው ማታ ለማረፍ በሚዘጋጁበት ወቅት በሁካታ ለበሸታ የተዳረጉትን መንግስት ዝም ያላቸውን የፈጣሪን ፍርድ የሚጠብቁ ቤት ይቁጠራቸው ምክንያቱም ወቅት ግዜ ቦታ ያለገናዘበ አምለኮ ስርዓትን ስለሚከተሉ፡፡ለማንኛውም አንድ ማሳያ ልንገራችሁና ነገሬን ልጠቅልል ጅማ ከተማ ከሚገኙ ሳር ሰፈር በሚባለው ከፈረንጅ አራዳ ከሚባለው እስከ እርሻ ኮሌጅ ድረስ ባልው ቦታ ከ 20-25 የሚደርሱ ቸርቾች አሉ ያለማጋነን በየ 100 ሜትሩ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡

    • Lafo October 21, 2014 at 7:12 am Reply

      ወንድሜ እዚህ ጋ ትንሽ ማስተካከያ ልስጥህ:: በየ100 ሜትር ቸርች ተሰጥቶ ከሆነ ለማመን ይከብዳል:: ሆኖ ከሆነ ደግሞ ከተማ ውስጥ ሊሰጧቸው ስላልፈለጉ ለተለያዩ ቸርቾች ከከተማ ውጪ በተመሳሳይ ሰፈር አካባቢ ሰጥተዋቸው ሊሆን ይችላል:: የድምጽ ረብሻ ካልከው ነጥብ ጋር በደንድ ነው ካንተ ጋር እምስማማው:: ይህ መስተካከል ያለበት ነው:: ሰዎች በቤታቸው የማረፍ መብት አላቸውና:: በሌላ በኩል ግን ሁላችንም ወደየራሳችን ስለምናዘነብል ነው እንጂ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ባለበት አካባቢም እኮ በማይክራፎን የሚለቀቀው ድምጽ ሌሊት ሌሊት የሰፈሩን ሰዎች ዕረፍት ይነሳል:: መስጊድ ባለበት አካባቢ ያሉትስ ወገኖች በየስንት ሰዓቱ ነው ሌሊትም ቀንም ዕረፍት የሚያጡት (በማይክራፎን ድምጹን ስለሚለቁት):: ይህ ሁሉንም የሚመለከት ከተስተካከለም መስተካከል ያለበት ነጥብ ነው:: የኦርቶዶክስንና የሙስሊሙን የለመድነው ድምጽ ስለሆነ ችግር የለውም: የቸርቹ ግን ይታገድልን የሚል አንድምታ መኖር የለበትም:: እንደኔ እነደኔ ከተቻለ ሁሉም ድምጻቸውን እዛው የአምልኮ ቦታ ውስጥ ላለው ህዝብ ብቻ ቢያደርጉትና ከግቢው ውጪ ያለውን ህዝብ ለቀቅ ቢያደርጉት መልካም ነው:: ይህ እስኪስተካከል ድረስ ግን እኛ ነን መታገስ ያለብን::
      ወደ ሁለተኛው ነጥብ ስመጣ ይህ የአሁኑ የመስቀልና የማተብ ጉዳይ ግን ሁሉንም የክርስተና ክፍሎች ማለትም የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር አባላት የሆኑትን (ኦርቶዶክስ: ካቶሊክና ፕሮቴስታንትን) የሚመለከት ነው እንጂ ኦርቶዶክስ ላይ ብቻ ያነጣጠረ አደጋ አድርገን መመልከት የብንም:: በዚህ ወሳኝ ሰዓት ፕሮቴስታንቱን ወይም ካቶሊኩን እንደ ልዩ ተጠቃሚ በመቁጠር ኦርቶዶክስ ላይ ነው የተነሱብን የሚል አመለካከት የሚይዝ ሰው ካለ ለክርስትና ሃይማኖት መዳከም አስተዋጽኦ ማድረጉ እንደ ሆነ ማወቅ አለበት:: በጽሑፍህ ላይ የሙስሊም ወንድሞቻችን ስርዓት የጠበቀ……..ስትል ስሜትህ በፕሮቴስታንት እንደተጎዳ እንጂ በክርስትና ሃይማኖት አደጋ ላይ መሆኑ የተሰማህ አትመስልም:: በሌላ አነጋገር በዚች ሃገርም ሆነ በሌላም ዓለም የሃይማኖት አደጋ አለ ቢባል ፕሮቴስታንትም ሆነ ሌላው የክርስትና ክፍል አደጋ የሆነበት ምድር የለም ማለት ይቻላል:: ይልቁንም የእስልምና ጽንፈኝነት ግን ትልቁ አደጋ ነው:: የአሁኑ አደጋ ግን በክርስቲያኖች ላይ የተነሳ አደጋ በመሆኑ ሙስሊምን ወደድኩ ፕሮቴስታንትን ጠላሁ የሚባልበት ሰዓት እንዳልሆነ መገንዘብ አለብን::

      ምናልባት የጠቅላይ ሚኒስቲሩ ሃይማኖት ለፕሮቴስታንት መልካም በር እንደከፈተ ተቆጥሮ ከሆነ ትክክል አይመስለኝም:: የአሁኑ የመስቀልና የማተብ ጉዳይ ከእሳቸው ጋርም በፍጹም የሚገናኝ አይመስለኝም:: ትልቁ አደጋ የሴኩላሪዝም ርእዮት ሚዛናዊነት የማጣቱ ጉዳይ ነው ብዬ ነው እማስበው:: እነ ዶክተር ሺፈራው ሴኩላሪዝም ማለት ሃይማኖትን ማጥፋት እንዳልሆነ አልገባቸውም:: ሴኩላሪዝም ከየትኛውም የሃይማኖት ወገንተኝነት ነፃ መሆን እንጂ ሃይማኖትን መቃወም ማለት አይደለም:: እንዲያዉም አንድ ሰው አጥባቂ ሃይማኖተኛ ሆኖም ሴኩላሪዝምን ማስኬድ ይችላል የሚል ግምት አለኝ:: ምክንያቱም ሴኩላሪዝም ሁሉንም ሃይማኖቶች እኩል በማየት ይሠራል እንጂ ሃይማኖትን አይከለክልም:: ሴኩላሪዝም ከሃይማኖት ስፍራዎች ውጪ (በሥራ ቦታ: በትምህርት ቤት:የህዝብ የጋራ መገልገያ በሆኑ አካባቢዎች ሁሉ) የየትኛውም ሃይማኖት አመለካከት እንዳይሰበክ ሊከላከል ይችላል እንጂ ሃይማኖተኝነትን ግን ሊቃወም አይችልም:: በተግባር ግን በሰብአዊ መብት ሰበብ ሃይማኖተኞች ላይ አደጋ ሊጥል እንደሚችል የታወቀ ነው::

      ያም ሆነ ይህ ወቅቱ አንድ ላይ ሆነን የምንነሳበት ወቅት ነው እንጂ እርስ በራሳችን የምንነካከስበት ወቅት አይደለምና እየተለያየንና እየተበታተንን ለአውሬ ራሳችንን አናመቻች እላለሁ!!!!

  44. Anonymous October 15, 2014 at 10:24 am Reply

    Ayi yekidusan amilak eski yederesebinin temeliket!!! Ene yemilew ministiru lela siru atu malet new?

  45. Anonymous October 16, 2014 at 9:40 am Reply

    I don’t think they know what they are doing. They could be Satan. Let us pray for GOD.

  46. Lafo October 21, 2014 at 6:42 am Reply

    ሠላም ለእናንተ ይሁን!
    እኔ የኦርቶዶክስ ተከታይ አይደለሁም – የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አባል እንጂ! ይሁን እንጂ ይህ ያነሳችሁት ጉዳይ ኦርቶዶክስን ወይም ማኅበረ ቅዱሳንን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን በዋናነት በክርስትና ላይ የተነሳ ጥላቻ ነው:: ምንም እንኳን በእግዚአብሔር ማመንን (ሃይማኖትን) በአጠቃላይ አደጋ ላይ የሚጥል ቢሆንም በተለይ ግን በክርስትና ላይ ያነጣጠረ አካሄድ ነው:: ስለዚህ ኦርቶዶክስ: ካቶሊክ: ፕሮቴስታንት ሳይባል የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር አባል የሆኑ ሁሉ በአንድነት ተነስተው ድምጻቸውን ሊያሰሙና ተቃውሞአቸውን ሊገልጹ ይገባል:: ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን ሁሉም በተናጠል ለመሮጥ የሚሞክሩ ከሆነ አንድ በአንድ እየጣሉ ለማዳከም እንዲችሉ ያመቻል:: ስለዚህ ፕሮቴስታንቱ ዛሬ የተነሳውን የማተብን ጉዳይ አይመለከተኝም ቢል ነገ እሱም እንደማይቀርለት በማወቅ መተባበር ይኖርበታል::
    በጽሑፋችሁ ሙሉ በሙሉ ደስተኛ ነኝ ማለት እችላለሁ:: አንድ ነጥብ ላይ ግን አልስማማም:: ፕሮቴስታንት ሊያደርጉን ነው እንዴ? በሚል መልኩ ከተገለፀው ሐሳብ ጋር በፍፁም አልስማማም:: አንድም ይህ አደጋ ፕሮቴስታንትን ችላ የሚል አደጋ አይደለም:: ሁለተኛ የኦርተዶክስ አደጋ ላይ መውደቅ የሌላውም የክርስትና ክፍል አደጋ ላይ መውደቅ ነው:: ሶስተኛው ደግሞ መስቀል ላይ ያነጣጠረው አደጋ የኦርቶዶክሶች ብቻ አይደለም:: ምናልባት ፕሮቴስታንቶች መስቀልን አያምኑም ከሚል የተሳሳተ ግምት የመነጨ ነው ብዬ ነው እማስበው::
    ስለዚህ ይህን በእግዚአብሔር አማኝነት ላይ የተነጣጠረውን አደጋ አብረን ለመመከት መመካከር አለብን እንጂ ይህ እኛን: እነሱን የሚለው አስተያየት አንድነታችንን በማዳከም ኢ አማኒነትን አሸናፊ እንዲሆን በር ከመክፈት ያለፈ ፋይዳ የለውምና ዛሬውኑ ነቅተን እንዘጋጅ::
    ማኅበረ ቅዱሳንም ቢሆን የኦርቶዶክስ አንድ ማህበር እንጂ ራሱን የቻለ ሌላ የሃይማኖት ድርጅት እስካልሆነ ድረስ ራሱን በመነጠል ሳይሆን ከእናት ቤተክርስቲያንንና ከሌሎቹም ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመተባበር መስራት ይጠበቅበታል::

    ጊዜው በማኅበር: ቤክርስትና ክፍልና በሌላም ልዩነት የምንለያይበት ወቅት ሳይሆን የእግዚአብሔር አማኞች ሁሉ በተለይም የሥላሴ አማኝ ወገኖች ሁሉ የምንተባበርበት ወሳኝ ወቅት ነው:: አለበለዚያ ስንለያይ ተበታትነን እንዳንቀር::
    በኔ በኩል ማተብም ሆነ የመስቀል ምልክት በየትኛውም የወስነት ክፍሉም ሆነ የግሉ ንብረት በሆነ ነገር ላይ ማድረጉ ስህተት የለውም ባይ ነኝ:: ይልቁንም መስቀልንና ማተብን ወደ ባህል ደረጃ ዝቅ ማድረጉ ደካማ የመከራከሪያ ነጥብ እንዳይሆን የሚል ስጋት አለኝ::
    በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ሃይማኖት አትስበኩ ቢሉን ግቢው የጋራ ነውና እሺ ልንላቸው እንችላለን:: የግል ደብተርህ ላይ ይህን አታድርግ ሲሉን ግን ለመስማት ያስቸግረናል::
    ስለዚህ አብረን በመቆም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የተቀበልነውን የክርስትናን እምነታችንን ጠብቀን ለመኖር መነሳት ይኖርብናል:: ከዚህ በኋላ ሌላ ሃይማኖት አይሰጠንምና!

  47. tewolde medihine October 30, 2014 at 2:15 pm Reply

    Just you made good I were abinet temari of Haddis kidan and kidassie but You have done what is wonder ful Do not retun to the back’libu letsadik wukul kem anbessa.’

  48. Anonymous February 9, 2015 at 1:37 pm Reply

    Tizibt new enji Egziabher Betun Aytewm……Yetelemede fetena new .

  49. Anonymous May 17, 2016 at 1:10 pm Reply

    ISKI TOWUT YEMOKIR NABUKADANSTOR SAR INDABALA ISU DAGMO BA WUSHA YIBALAL

Leave a comment