ሰበር ዜና – ማኅበረ ቅዱሳን ለአብነት መምህራን ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ታገደ

ማኅበረ ቅዱሳን

ማኅበረ ቅዱሳን

  • ከ200 በላይ የጉባኤው ተሳታፊ የአብነት መምህራን አዲስ አበባ ገብተው በማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጽ/ቤት ተሰብስበዋል፡፡ ፓትርያርኩ በአድራሻ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ የጻፉትን የእግድ ደብዳቤ የያዘው ፖሊስ፣ የማኅበሩ ጽ/ቤት ጉባኤተኞቹን ወደየመጡበት እንዲያሰናብት በማሳሰብ ላይ እንደኾነ ተነግሯል፡፡
  • በእግድ ርምጃው ምክንያት÷ ዛሬ፣ የካቲት ፯ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የአብነት መምህራኑ፣ የቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ሓላፊዎች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ምሁራን፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ የዓለም ባንክ፣ የወተር ኤይድ እና ዩኒሴፍ ተወካዮች በተገኙበት በግዮን ሆቴል ሊካሔድ የነበረው የሀገር አቀፉ የምክክር ጉባኤ መክፈቻ መርሐ ግብር ተስተጓጉሏል፡፡
  • ጉባኤተኞቹ፣ መርሐ ግብሩን ያስተጓጎለውን የእግድ ርምጃ አስመልክቶ በማኅበሩ አመራር ማብራሪያ ከተሰጣቸው በኋላ ርምጃው እንዲወሰድ ባነሣሱት የትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ላይ ቁጣቸው ነዷል!!!
  • ቀደም ሲል በአባ ሰረቀ ግፊት በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ ተላልፎ የነበረውን የእግድ ርምጃ በማንሣት የምክክር ጉባኤው እንዲካሔድ የፈቀዱት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ትላንት ከቀትር በኋላ በፓትርያርኩ የተጻፈውን የእግድ ርምጃ አልተቀበሉትም፡፡
  • የአብነት መምህራኑ÷ የእግድ ርምጃው እንዲወሰድ ባነሣሱት የትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ላይ መውሰድ ስለሚገባው የተባበረ አቋም በከፍተኛ ስሜት ሐሳብ በመለዋወጥ ላይ ናቸው!! ፓትርያርኩን እንደሚያነጋግሩ ይጠበቃል፡፡

*                         *                       *

  • በአኹኑ ሰዓት፣ ጉባኤያቸውን አጥፈው ለሀገር አቀፉ ስብሰባ ከኹሉም አህጉረ ስብከት የመጡ አካል ጉዳተኛና አቅመ ደካማ የኾኑ አዕይንተ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ሳይቀሩ ተሰብስበው ሲመካከሩ ከዋሉበት ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ጽ/ቤት በሰልፍ በመውጣት ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ አምርተዋል፡፡
  • የአብነት መምህራኑ፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ቅጽር ሲደርሱ በሀገር አቀፉ የምክክር ስብሰባ ላይ የተላለፈውን እግድ ለማስፈጸም ከተመደበው የፖሊስ ኃይል ጋራ ስለማንነታቸውና ስለመጡበት ኹኔታ ካስረዱ በኋላ ፍተሻ! እየተደረገባቸው ወደ ቅጽሩ ዘልቀዋል፤ በእግድ ርምጃውና በአባ ሰረቀ ጉዳይ ከፓትርያርኩ ጋራ ፊት ለፊት ለመነጋገር በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙም ተገልጧል፡፡

*                       *                       *

  • እንደ በጋሻው ደሳለኝ ‹መጋቤ ሐዲስ›ነት በዘፈቀደ የተለጠፈላቸው ጎጋ ምንደኞች ሳይገባቸው በሚወስዱት የሊቃውንት ሥያሜና የምስክር አሰጣጥ ላይ መወያየትና እነአባ ሰረቀ ሠርተው ባለማሠራት ጥፋት የፈረዱባቸው ቤተ ጉባኤያት ወቅታዊ ተቋማዊ ኹኔታ ከጉባኤው የመነጋገርያ አጀንዳዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡

*                       *                       *

ውን ሀገር አቀፍ የአብነት መምህራን የምክክር መድረክ ዝግጅትና አስፈላጊነት የተመለከ አጠቃላይ መረዎች

Ethiopian_Orthodox_Tewahedo_Church_Traditional_School_____

ባለንበት ወቅት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከ100‚000 በላይ ደቀ መዛሙርት፣ ከ6‚000 በላይ የአብነት መምህራንና ከ3‚000 የማያነሱ የአብነት ት/ቤቶች እንዳሉ ጉዳዩ ዙሪያ የወጡ ዘገባዎች ያስረዳሉ፡፡

በእግዚአብሔር ፈቃድ በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያና ደንብ ተሰጥቶት የተቋቋመው ማኅበረ ቅዱሳን÷ ገዳማት አንድነታቸው ተጠብቆ የጸሎት ቦታና የትምህርት ማእከል፣ በኢኮኖሚ ራሳቸውን ችለው የልማት ማሳያ እንዲኾኑ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችም ተቋማዊ በኾነ መልኩ ተጠናክረው የቤተ ክርስቲያኒቱ እምነትና ሥርዐት ለትውልድ እንዲሻገር የድርሻቸውን እንዲወጡ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ለቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ ዕድገት የሚበጁ በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ የሚገኘው ማኅበሩ፣ ስብከተ ወንጌል ባልተስፋፋባቸው በጠረፋማ አካባቢ ለሚኖሩ ወገኖችም ኅብረተሰቡን በቋንቋው የሚያገለግሉ ካህናትን በማፍራት በኩል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ የገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ የአብነት መምህራን በየዓመቱ የምክክር ጉባኤ እያደረጉ ችግሮቻቸውን የሚያነሡበትን፣ ልምድ የሚለዋወጡበትን፣ የመፍትሔ አቅጣጫ የሚጠቁሙበትን መድረክ በመፍጠር ለኹለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን ዕድገት አስተዋፅኦዋቸውን እንዲያበረክቱ ያግዛል፡፡

ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች÷ ለቅዱሳን መገኛ፣ ለሊቃውንት መፍለቂያ፣ ለተተኪ መምህራንና ለቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ብቸኛ ምንጭ በመኾናቸው እነርሱን ማእከል ባደረገ መልኩ በርካታ ሥራዎች ሊሠሩ ይገባል፡፡

???????????????????????????????

ስለ መርሐ ግብሩ ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት

በዚኽም መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን፣ የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል በማዋቀር በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች በርካታ ጥናቶችን በማካሔድ ተስፋ ሰጭ ለውጦችን ማምጣት ችሏል፡፡

ይህ ዋና ክፍል እስከ አኹን ድረስ ከ180 በላይ ፕሮጀክቶችን በማጥናት በተለያዩ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ላይ ተግባራዊ ያደረገ ሲኾን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ድርሻቸው እንዲጎላ አድርጓል፡፡ የአብነት ት/ቤቶች ማጠናከርያና ማቋቋሚያ መርሐ ግብር(ፕሮግራም) በመንደፍ ላለፉት ዐሥር ዓመታት ባደረገው እንቅስቃሴ÷ የአብነት ት/ቤቶች እንዲጠበቁና እንዲጠናከሩ እንዲሁም በምሥራቅ፣ በምዕራብና በደቡብ የአገሪቱ ክፍልም አዳሪ የአብነት ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ተተኪ አገልጋዮች እንዲገኙ የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል፡፡

በ፳፻፭/፮ ዓ.ም. 150 በሚኾኑ የአብነት ት/ቤቶች መርሐ ግብሩን ተግባራዊ በማድረግ ለ171 መምህራንና ለ993 ተማሪዎች ከ2.8 ሚልዮን ብር በላይ በኾነ ዓመታዊ በጀት ወርኃዊ የገንዘብ ድጋፍ እንዲኹም ከ6‚000 በላይ ለሚኾኑ ተማሪዎች አስቸኳይ ቀለብና የአልባሳት ድጋፍ፣ የስብከተ ወንጌል ሥልጠናና የመማሪያ መጻሕፍት እገዛ፣ የጉባኤ ቤትና የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ያከናውናል፡፡ በዚኽም ከ5.5 ሚልዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ ከ7 ያላነሱ ፕሮጀክቶች ትግበራ እያካሔደ ይገኛል፡፡

ከዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት ጋራ ተያይዞ ወደ አብነት ትምህርቱ የሚመጣ ትውልድ እየታጣ በመሔዱ ቀጣዩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ችግር ላይ እንዳይወድቅ በማሰብ ትምህርቱ ቀጣይ ኾኖ እንዲቆይ ለመጪው ትውልድም እንዲተላለፍ የአብነት ትምህርቱን ከዘመናዊ ትምህርት ጋራ የሚያጣምር በኢትዮጵያዊው ሊቅ በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስም የተሰየመ ነጻ የዘመናዊ ትምህርት ዕድል በየደረጃው የአብነት መምህራንና ተማሪዎች እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

ማኅበሩ እነዚኽን ተግባራት ለማከናወን የሰንበት ት/ቤቶች፣ የማኅበራትና የበጎ አድራጊ ምእመናን ትብብርና ድጋፍ ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ ይታመናል፡፡

ክፍሉ በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. በርእሰ ገዳማት ወአድባራት ዳግሚት ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ባካሔደውና 45 መምህራን በተሳተፉበት የመጀመሪያው ዙር ሀገር አቀፍ የምክክር መርሐ ግብር፣ የአብነት ት/ቤቶችን ከኅብረተሰቡ ጋራ የማስተዋወቅና መምህራኑ አስታዋሽ እንዲያገኙ በማድረግ ላይ አተኩሮ ሠርቷል፡፡

በ፳፻፪ ዓ.ም ከ86 በላይ ሊቃውንት በተገኙበት በጠቅላይ ቤተ ክህነትና በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ባካሔደው ሁለተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ፣ የአብነት ትምህርቱን የትምህርት አሰጣጥ ጥራትና በተለይም እየጠፉ ባሉ የአቡ ሻህርና መጻሕፍተ መነኰሳት፣ እየተዳከሙ ባሉ የቅኔ ትምህርቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ጉባኤውን በስኬት አካሒዷል፡፡

ክፍሉ በተመሳሳይ አኳኋን በዚኽ ዓመት ሊያከናውናቸው ካሰባቸው ዓበይት ተግባራት ውስጥም እነኾ፣ ፫ው የአብነት መምህራን ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ነው፡፡ ለጉባኤው ዝግጅት ብር 627‚500.00 ጠቅላላ አማካይ ወጪ ታስቦለታል፡፡

  1. የአብነት መምህራን ሚና

የአብነት መምህራን÷ ተተኪ ሊቃውንትን፣ አገልጋዮችንና መሪዎችን በማፍራት የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ሥርዐትና ባህል ሳይበረዝ ተጠብቆ ለዘመናት እንዲሻገር በማድረግ በኩል ከፍተኛ ሚና ያላቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ወሳኝ አካላት ናቸው፡፡

    2. የጉባኤው አስፈላጊነት

  • የአብነት መምህራን በቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ድርሻ አስመልክቶ የጋራ ሐሳብ እንዲኖራቸው
  • የአብነት ትምህርት ቤቶችን ተቋማዊ አደረጃጀት አስመልክቶ ለመወያየት
  • በየቤተ ጉባኤያቸው ስላጋጠሟቸው ተግዳሮቶችና ስለተወሰዱ መፍትሔዎች ልምድ ለመለዋወጥ
  • የአብነት መምህራን አንድነት ምሥረታን አስመልክቶ ሐሳብ ለመለዋወጥና ለመሳሰሉት ይህ ጉባኤ አስፈላጊ ኾኗል፡

     3. የጉባኤው ግብ

  • በኹለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን ዕድገት የአብነት መምህራን ድርሻ ጎልቶ እንዲወጣ ማድረግ

     4. የጉባኤው ዓላማ

  • የማኅበረ ቅዱሳን የአብነት ት/ቤቶች ማቋቋሚያና ማጠናከርያ መርሐ ግብር የድጋፍ አፈጻጸም
  • የትርጓሜ መጻሕፍት/ሐተታ/ ሒደት ላይ መወያየት
  • የአብነት ት/ቤቶች የጤና ችግር ስለሚገኝበትና ወደፊቱም ሊኾን ስለሚገባው ኹኔታ መወያየት
  • መምህራንና ተማሪዎች የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነጻ የትምህርትና ሥልጠና ዕድል ተጠቃሚ በሚኾኑበት ኹኔታ ላይ መወያየት
  • ከምስክር ትምህርት ቤቶች የሚመረቁ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት አሰጣጥና ስለሚኖራቸው የአገልግሎት ኹኔታ
  • የሊቃውንት ስያሜ አሰጣጥ
  • የአብነት መምህራን አንድነት ጉባኤ ምሥረታን አስመልክቶ ውይይት ማድረ

     5. የጉባኤው ተሳታፊዎች

በዚኽ የ፫ው ሀገር አቀፍ የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ ከኹሉም አህጉረ ስብከት የተውጣጡ ከ200 በላይ የአብነት መምህራን ተሳታፊዎች ሲኾኑ ኹሉም የምስክር መምህራንና ጥሪ የተደረገላቸው ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ይሳተፋሉ፡፡

     6. ጉባኤው የሚደረግበት ቦታና ቀን

አዲስ አበባ የጠቅላይ ቤተ ክህነት መቀመጫው ከመኾኑ ባሻገር ለኹሉም አህጉረ ስብከት አማካይ በመኾኑ ጉባኤው በአዲስ አበባ ከየካቲት ፮ – ፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በግዮን ሆቴል እና በብሔራዊ ሙዝየም ትልቁ አዳራሽ ይደረጋል፡፡ በመጨረሻም እሐድ የካቲት ፱ ቀን ከ7፡30 ጀምሮ 6 ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ የባህል አዳራሽ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ መምህራኑና ምእመናኑ በተገኙበት ልዩ የመዝጊያ መርሐ ግብር ይካሔዳል፡፡

ምንጭ፡- ክፍሉ ለጉባኤው ዝግጅት ካሰራጫቸው ልዩ ልዩ ሰነዶች የተጠናቀረ

 

  

55 thoughts on “ሰበር ዜና – ማኅበረ ቅዱሳን ለአብነት መምህራን ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ታገደ

  1. baharu sisay February 14, 2014 at 5:35 am Reply

    weshaw lemn yechohal plc orthodox enenka anetegna zara yemenetegnabet seat adelem

  2. Anonymous February 14, 2014 at 6:54 am Reply

    dn begashaw is free

  3. Alehegn Adamu Yezengawe February 14, 2014 at 7:01 am Reply

    yas

  4. Deacon Samuel Ayalneh February 14, 2014 at 11:00 am Reply

    ከጉባኤ ቤት ያልመጡ ስለሆነ ድሮም ከእነሱ መልካም ነገር አይጠበቅም

  5. D ADUGNA February 14, 2014 at 11:05 am Reply

    እልልልልልል…………..!!!!!!!

  6. Anonymous February 14, 2014 at 11:29 am Reply

    ልቦናቸዉ በሰይጣናዊ አስተሳሰብ እያሰበ ለሚገኙ አባቶች እግዚአብሔር አምላክ አስተዋይ ልቦና ይስጣቸዉ ፤

  7. Abib February 14, 2014 at 1:07 pm Reply

    Heart Breaking New, let them give them the proper understanding view!
    We undestand had it been that was organized by external NGO I think nothing would have been happended.

  8. Anonymous February 14, 2014 at 1:12 pm Reply

    hulum ye abinet memihairan bemahiberu lay eyederese yalewun chana betegibar endiyayut hone. አባ ሰረቀ ሳይማር በአአ የመምሪያ ሀላፊ ሆኖ፣ ሊቃውንቱ ከ ገጠር ሢመጡበት ባይፈራ ላይፈራ ነው፡፡ ሊቃውንቱ ከተወያዩ፣ ከተመካከሩ ነገ እንደ … አይነቶቹ የኔ ቢጤ ለቦታው እንደማይመጥኑ ይነገራቸዋል፣ ስለዚህ በሩቁ መከላከል ይሻላቸዋል፡፡

  9. Anonymous February 14, 2014 at 1:28 pm Reply

    <>amekilawoch libonayestlin

  10. በአማን ነጸረ February 14, 2014 at 1:59 pm Reply

    1. የምትሰሩት ስራ መልካም እስከሆነ ድረስ እንደባእድ ተቁዋም አባቶች መርሃግብሮቻችሁን በየጋዜጣው እንዲያነቡ ከማድረግ አስቀድማችሁ ልታሳውቁዋቸው ይገባል!! ከቻሉ እነሱም ተገኝተው ስብሰባውን በቃለምዕዳን ይከፍታሉ!! ካልቻሉም ስለስብሰባው መኖር አስቀድሞ በግልባጭ እንዲያውቁት ቢደረግ ዓላማውን ተረድተው በጎ ፈቃዳቸውን ያሳያሉ!!
    2. ከበላይ አካላት ጋር ተናቦ መስራት ሁለት ጥቅም አለው (ሀ) መተማመንን ይገነባል፣ለሉዐላዊው የቤ/ክህነት የአስተዳደር አካል ያለንን አክብሮት ያሳያል፣ስርዐትም ነው (ለ) መንግስታዊ ከሆነ ወይም ካልሆነ አካል የሚመጣ ጫናን እንደማህበር ሳይሆን እንደሃይማኖት ተቁዋም ሆነን ሁላችንም በጋራ ለመቁዋቁዋምና ለማሳመን ይረዳናል-ጥቅሙ ለሁላችንም ነው!!አሁን ችግር እየፈጠረ ያለው የቤ/ክ አካል ሆኖ በአንድ ልብና በአንድ ሃሳብ ለመራመድ ከመሞከር ይልቅ በየአንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ከአካላቱ ተለይቶ እንደ ትርፍ ገላ በተቀጽላነት ጎልቶ ለመታየት የሚደረግ የተርእዮ አባዜ ነው!!
    3. የቤ/ክ ዜናዎች በየዓለማዊው ጋዜጣ ሲወጡ እናያለን!!! የኦኦተቤክ… እንዲህ ልታደርግ ነው… ይባላል!!ማን ነው ያለው ብለን ወደ ውስጥ ዘልቀን ስንገባ የመግለጫው ምንጭ የቤ/ክህነቱ ኦፊሴላዊ አስተዳደር ሳይሆን ንዑስ አካሉ የሆነው ማህበሩ ሆኖ ይገኛል!!!ማህበሩ አስቀድሞ ያላሳወቀውን ፕሮጀክት…. ቤ/ክ ይህን አስባለች… እያሉ ከአባቶች ቀድሞ መግለጫ መስጠት ትክክለኛ አካሄድ አይመስለኝም!!!የማህበሩን ደጋግ ስራዎችም የከንቱ ውዳሴ ያስመስልበታል!!!ማዕከላዊነትንም ይጻረራል!!!ሁዋላ ፕሮጀክቱ በቤተክህነቱ ተቀባይነት ባያገኝ ክፍተት ይፈጠራል!!የአባቶቻችንን ተዐማኒነትም ያላግባብ ጥይቄ ውስጥ ይከታል!!!እንደ ቤ/ክ ሀላፊነት ለመውሰድም ያስቸግራል!!!
    4. የአብነት መምህራኑ በማን ስልጣን፣ለምን ዓላማ እንደተጠሩና በስብሰባው የቤ/ክህነቱ አስተዳደር ስላለው ተሳትፎ በቂ ገለጻ ሳይደረግላቸው በየዋህነት መጥተው ከሆነ ያሳዝናል!!!ለደረሰባቸው መጉላላት ጥፋተኛ የሆነው አካል ተለይቶ ይቅርታ ሊጠየቁና የሞራል ማካካሻም ተደርጎላቸው ወደየጉባኤ ቤታቸው ሊሸኙ ይገባል!!ለወደፊቱም የበላዩ የቤ/ክህነት አስተዳደር ሀላፊነት በማይወስድበት ስብሰባ ለመሳተፍ ከመወሰናቸው በፊት በአካባቢያቸው ካለው የወረዳ ቤተክህነት ስለስብሰባው መረጃ እንዲጠይቁ ትምህርት ይሆናቸዋል!!!
    5. ስለ ቅዱስ ፓትርያርኩ፡ አንዴ በመዋቅር ጥናቱ፣ ሌላ ጊዜ በድሬዳዋው ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ግንባታ፣ አሁን ደግሞ ለምን እነ እከሌን አላወገዙም እያላችሁ የራሳችሁን ሀሳብ ብቻ በመንተራስ ተፈትነው ወደቁ ለማለት ስትፋጠኑ እያየን ነው!!!አንቸኩል!!!የአባቶቻችንን መለኪያ እናስተካክል!!! ሌሎቹን ‘የላም ውጊ’ የመሰሉ በስመ ‘ዘመቻ ተሃድሶን መጥረግ’ የሚካሄዱ ሀላፊነት የጎደላቸው ሂደቶቻችሁን ብዙ ብለንባቸዋል!! ላም እንደበሬ አይደለችም!!የተዋጋቸው እንስሳ አንዴ መሮጥ ከጀመረላት እንደበሬ ‘በቃ አሸንፌዋለሁ’ ብላ አትመለስም!!መድረሻ እስኪያጣ ማባረር ነው!!ማባረር ማባረር ማባረር ማባረር…..ይሄ የላም ውጊ(ያ) ይባላል!!
    6. በመጨረሻም፡ሁለት ጽንፎች ቅር ያሰኙኛል!!!አንዱ ማህበረ-ቅዱሳንን በፖለቲከኛነት ፈርጆ በመንግስት ለማስመታት የሚደረግ ዘመቻ ነው!!!ይሄን መቸም አልቀበለውም!!ፖለቲካ የሚያራምዱ አባላት ቢኖሩ እንኩዋ እነሱን በማስረጃ አንጥሮ ማውጣት እንጅ በፖለቲካ ሰበብ ሙሉውን ማህበርና የዋሃን አባላቱን አብሮ መኮነንን አልቀበለውም!!በማህበሩ በኩልም እንዲሁ!! በሲኖዶስ ያልተለዩና የስላሴ ልጅነታቸው ያልተነጠቀ ወገኖችን የቤ/ክ የበላይ የሆነው አካል መርምሮ ነጻ ካላቸው በሁዋላ ሳይቀር ባልተሰጠ ስልጣን ገዝቶ በአሉባልታ ማሸማቀቅን፣ማሳደድን፣ማባረርን እጸየፋለሁ!!በእዚህ ጸያፍ ድርጊት ከተሰማሩ ወገኖች ጎን አልቆምም!!!በዚህ ዙሪያ እሱ ቢፈቅድ ወደፊት የምለው ይኖረኛል!!!
    ከአባራሪነት ወደ ቅን ተባባሪነት ይመልሰን!!!ይቆየን!!

    • የሙ አትዬ February 14, 2014 at 6:27 pm Reply

      እግዚአብሔር ይስጥህ በረከቱን ያድልህ፡፡ ሐሳብህ በጣም ትክክልና መቶ በመቶ የምንቀበለው ነው፡፡

      • ገ/ሃና February 15, 2014 at 8:21 am

        midire ariwos

      • Anonymous February 15, 2014 at 8:25 am

        አሁንም ሊቃውንቱን ተዋቸው፣ ቤተ ክርስቲያን እንደነርሱ ላሉት ናትና፡፡ በጉባኤያቸው ተገኝቶ መወያየት፣ የጉባኤውን አጀንዳ አብሮ መቅረጽ፣ ጉባኤውን መምራት፣ አሠራሩን ማሳየት ይገባል፣ የአባትም ነው፡፡ የገዛ ሊቃውንቶቻችንን ግን አትሰብሰቡ፣ አትመካከሩ፣ አትወያዩ፣ ችግር አትፍቱ ብሎ ማገድ፣ እምቢ ካላችሁ ‹ለመንግሥት እነግርባችኋለሁ›› ብሎ መንግሥትን ማስፈራሪያ ማድረግ ሃይማኖታዊ አይደለም፡፡ ምነው በጎንደሩ የጥምቀት ኤግዚቢሽ የመንግሥት አካላት ሊቃውንቱን ሲያከብሩ ባየን፤ ይህቺ ቤተ ክርስቲያንኮ ያለ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት ኖራ ታውቃለች፣ ያለ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ግን የኖረችበት ዘመን የለም፣ አይኖርምም፡፡

    • ታዛቢው February 14, 2014 at 11:54 pm Reply

      በአማን ነፀረ! እግዚአብሔር ይባርክህ የብዙዎቻችንን ሀሳብ ነው በግልጽ ያስቀመጥከው።

    • Anonymous February 15, 2014 at 12:13 pm Reply

      ወንድሜ ጥሩ አስተያየት ነው ! ያቆይልን !

  11. The Angry Ethiopian(ቆሽቱ የበገነው) February 14, 2014 at 2:33 pm Reply

    ጳጳስ፣ ሲኖዶስ፣ ፓትሪያርክ የሚባል ነገር ስለሌለ የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ትርምስ ውስጥ መጓዝዋን እንደቀጠለች ነው።
    ዬኽ የአንጃ ግር ግር የሚያሳየው ቤተክርስትያኒቱ የበላይ ጠባቂ እንደሌላት ነው። በአንድ ወር ውስጥ እስከ ነፍስ ልጃቸው መልአከ ሞት የቀሰፋቸው የአሳማ ስጋ ሰልቃጩ ተሀድሶው ጳጳስ በስልጣናቸው ጊዜ ያላሸቁት ቤተክርስትያን አሁንም የባሰ ጉድ ውስጥ ላይ ነው ያለው። ጴንጤዎቹ ከውጭም ከውስጥም ቤትክርስትያናችንን እያቦረቦሩት ነው። ይሄ ሁሉ የሆነው ባለጊዜዎቹ ትግሬዎች ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት እስላምንና ጴንጤን ማጎልበት አንዱ ከውጭ የተሰጣቸው መርሃ ግብር ስለነበር ነው። ይኼ መንግስት እስካለ ድረስ ቤተክርስትያኒቱ ትርምሷን ትቀጥላለች። መንግስት ተብዬውም ተኖ ቢጠፋ፣ ትርምሱ ባንዴ የሚጠፋ አይደለም።

    • tezera February 15, 2014 at 9:21 am Reply

      are you a politician or religious. I think you are saying our savior blessed some ethnicity such as israel which can can not confirmed to our lord ”kal”. please wash out your dirty saying and believe.

      • The Angry Ethiopian(ቆሽቱ የበገነው) February 15, 2014 at 10:50 am

        እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ! ለዛውም ቆሽቱ የበገነ! አንተ ግን ቦለቲከኛ ትመስላለህ።

      • Anonymous February 17, 2014 at 8:06 am

        በጤና ነው ትንሽ አልበዛም

  12. አይይይ February 14, 2014 at 3:03 pm Reply

    አንድ ባለ ቅኔ ከሚከተለው ጉብኤ ቃና ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነገር በግምት ከ 50 አመት በፊት ተቀኝቶ ነበር።
    መላእክትሂ ቆሞሳት ሰረቀ ወኤልያስ ክልኤቱ
    ለሙሴ ቤተክህነት ቀበርዎ በሕይወቱ
    ለ Big Brother የሚጻፈው ግልባጭ ደግሞ የበለጠ ገራሚ ነው። ማኅበሩ የሚኖርበትን የእግር እሳት በጸሎት የሚያግዙ አባቶች ማወቃቸው ጥሩ ነው። ቢያንስ የሚጸለይለትንና የሚጸለይበትን ለይተው የሚሄዱ ይመስለኛል።

    • ገ/ሃና February 15, 2014 at 6:29 am Reply

      ማኅበሩ የሚኖርበትን የእግር እሳት በጸሎት የሚያግዙ አባቶች ማወቃቸው ጥሩ ነው። ቢያንስ የሚጸለይለትንና የሚጸለይበትን ለይተው የሚሄዱ ይመስለኛል።

  13. Anonymous February 14, 2014 at 4:42 pm Reply

    ለበአማን ነጸረ ፤ እርግጥ መረጃው ከሌለህ አልፈርድብህም ሆኖም ግን ስለሰጠሀቸው አስተያቶች የማውቀውን ላካፍልህ
    1ኛ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ነበረባችሁ ብለሃል፣ ትክክል ነህ ሆኖም ማህበሩ ስለ ፕሮግራሙ ጠቅላይ ቤተ ክህነትን ፈቃድ ጠይቆ ጉባዔውን ማካሄድ እንደሚችል ደብዳቤ ተጽፎለታል፡፡
    2ኛ የቤ/ክ ዜናዎች በየዓለማዊው ጋዜጣ ሲወጡ እናያለን!!! ብለሀል፣ እዚህ ላይ አለማዊ ጋዜጦችን ይህን ዘግቡ ይህን አትዘግቡ ማለት አትችልም፣ እነሱ ያገኙትን መረጃ ለህዝብ ማቅረብ ስራቸው ነው፡፡ ዋናው መሆን ያለበት ጉዳይ ቤተክርስቲያናችን አካሄዳን በሙሉ ከህገ ቤተክርስቲያን አንፃር መሆን አለበት፣
    3ኛ የአብነት መምህራኑ በማን ስልጣን፣ለምን ዓላማ እንደተጠሩ… ስላልህው ዝርዝር አላማው እና ግቡ እኮ ይታዎቃል፣ በዝርዝርም ተገልፃል፡፡ በተጨማሪም ስል 3ኛው ምክክር ከዚህ በፊት በነበሩት 2ት ፕሮገራሞች ከመገለፁም መተጨማሪ መምህራኖቹም ከ ሶስት አመት በፊት በጋራ ያቀዱት ነው

  14. ገ/ሃና February 14, 2014 at 4:51 pm Reply

    ለበአማን ነጸረ ፤ እርግጥ መረጃው ከሌለህ አልፈርድብህም ሆኖም ግን ስለሰጠሀቸው አስተያቶች የማውቀውን ላካፍልህ
    1ኛ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ነበረባችሁ ብለሃል፣ ትክክል ነህ ሆኖም ማህበሩ ስለ ፕሮግራሙ ጠቅላይ ቤተ ክህነትን ፈቃድ ጠይቆ ጉባዔውን ማካሄድ እንደሚችል ደብዳቤ ተጽፎለታል፡፡
    2ኛ የቤ/ክ ዜናዎች በየዓለማዊው ጋዜጣ ሲወጡ እናያለን!!! ብለሀል፣ እዚህ ላይ አለማዊ ጋዜጦችን ይህን ዘግቡ ይህን አትዘግቡ ማለት አትችልም፣ እነሱ ያገኙትን መረጃ ለህዝብ ማቅረብ ስራቸው ነው፡፡ ዋናው መሆን ያለበት ጉዳይ ቤተክርስቲያናችን አካሄዳን በሙሉ ከህገ ቤተክርስቲያን አንፃር መሆን አለበት፣
    3ኛ የአብነት መምህራኑ በማን ስልጣን፣ለምን ዓላማ እንደተጠሩ… ስላልህው ዝርዝር አላማው እና ግቡ እኮ ይታዎቃል፣ በዝርዝርም ተገልፃል፡፡ በተጨማሪም ስል 3ኛው ምክክር ከዚህ በፊት በነበሩት 2ት ፕሮገራሞች ከመገለፁም መተጨማሪ መምህራኖቹም ከ ሶስት አመት በፊት በጋራ ያቀዱት ነው
    ዋናው ችግር ከዚህ በፊት ሰ/ትም/ ቤቶች መምሪያ ሃላፊ ሆነው ሲያደርጉት እንደነበረው ማህበሩ የሚሰራቸውን መልካም ስራዎች በዓላማ ለማሰናክል የሚጥሩት አባ ሰረቀ ናቸው፡፡ እርግጥ የእርሳቸው መምሪያ ስለ ጉባዓው የሚመለከተው ከሆነ ማህበሩ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ደብዳቤ ሲያስገባ ቤተ ክህነት ወደ አባ ሰረቀ መምራት ነበረበት እንጅ ማህበሩ ቀጥታ ለሳቸው መፃፍ ላይጠበቅብት ይችላል፡፡ ምንም ይሁን ምን በዓላማው ላይ ልዩነት ከሌለ መዋቅራዊውን ጉዳይ ከጉባዔው መልስ የሚመለካታቸው አካላት ተወያይተው ማስተካከል ይችሉ ነበር ፣ እውነት ለቤተ ክርሰተያን ቢቆረቆሩ፡፡

  15. Anonymous February 14, 2014 at 4:56 pm Reply

    Eski yiftaw!!!!!!!!!!

  16. Anonymous February 14, 2014 at 5:07 pm Reply

    Yibel new!!!!!!

  17. Anonymous February 14, 2014 at 5:53 pm Reply

    Egezabehr kaent gar yehun bartu

  18. Anonymous February 14, 2014 at 6:14 pm Reply

    Egezabehr kaent gar yehun bartu betam kaleb azegnlhugn ba gubaew matged gen Egezabehr lebona yestachw Betame yalasetawlut negar ya Ethiopia Orthodox tawhedo betkerstian machem behon fatena yegatmatal enej leyawkwt ytanasu hulu Bahilgnw ba Egezabehr kend wagachwen yagegnlu aikrem Mesrchw Ya Alem Madehanet Madehanetachn Eysuse Kerestos bademu yawjat naten wganoch Bahulum Egezabehr yerdachu

  19. Anonymous February 15, 2014 at 1:33 am Reply

    yigermal yemtadu eyale yenkbu tentata…..

  20. abebe February 15, 2014 at 2:45 am Reply

    Yh gubae endaykahed yetewsenew tqit seat siqerew now. Lemn?. Patriyarikus bemeweyayet amnalehu ylu alneber ende?, lemn slegudayu lelawn wegen qedmo lemamaker alfelegum? musegnochn lemegafet yaldefere halafinet lebetekrstiyan edget yemiteqmn gubae lemasqom wenew keyet meta????? , Ke egedaw jerbas eneman alu?? Dros lene Sereqe sltan seto betekrstiyann badebabay kemasdefer wedehuala kalale astedader mn ytebeqal. Le betekrstiyanua yemiqoreqoruna be ewnet yemiyageleglu discourage yemideregubet, musegnana tqmegna endihum alawaqiwoch yemiberetatubet Yetenkolegnoch mender mekam fre antebqm. Betekrstiyan badebabay stsedeb lemn endet yalale astedader mahberekidusan lay fetan ermja lemewsed fetan hone.Lemangawm, neger hulu lebego now blo meqebel now. LINEGA SIL YCHELMAL!!!!!

  21. WUBSET February 15, 2014 at 5:38 am Reply

    “YECHEW KIMIR SINAD BILT LIJ YALEKISAL MOGN GIN YISIKAL” YILALU ABATOCH. Silezih yalgebachew yidesetu yihonal hulum gin lezare yiker yihonal enji wedefit ayikerim.

  22. Eden A,Mekbib February 15, 2014 at 5:56 am Reply

    ጳጳስ፣ ሲኖዶስ፣ ፓትሪያርክ የሚባል የለም እንበል ወይስ???……….. መንፈሳዊ ነገር ወዴት ነው አየወሰደን ያለው?? በአለማውም በመንፈሳዊውም የማውቀው የወረስነው አንድ አባት ልጆቹን ጠርቶ መምከር ነው እንጂ?? ልጆቼ እንዲህ ያሉ ናቸው ተብሎ አሳልፎ ለዓለም መስጠት በታም አሳፋሪ አና ለጆሮየሚቀፉ ነው !!! እንደው ትንሽ አይከብድም ከስንት መንገድ አቃርተው መተው ፣ምን አለ ትንሽ እንካን ፈርአ እግዚአብሔር ቢኖርን፣እንዲ ነው ግን አምላካችን ያስተማርን??እኔ ግን የምያሳዝነኝ ነግር ዓልም ስንት ነገር እያስጨነቀችን የእግዚአብሔር ማዳን,ተሰፋ,ፍቅር, የተጠማን ወገን እንዲእ ማወዛገብ ምን ይሉት ይሆን?በር መክፈት ነው የያዝነው ወገን?? እግዚአብሔር አምላክ ለሁላችንም መልካም ልብ ይስጥ ተስፍ በእግዚአብሔር ዘንድ አለኝ………… ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይታረቃት።

  23. gize February 15, 2014 at 6:39 am Reply

    hulum ye abinet memihairan bemahiberu lay eyederese yalewun chana betegibar endiyayut hone. አባ ሰረቀ ሳይማር በአአ የመምሪያ ሀላፊ ሆኖ፣ ሊቃውንቱ ከ ገጠር ሢመጡበት ባይፈራ ላይፈራ ነው፡፡ ሊቃውንቱ ከተወያዩ፣ ከተመካከሩ ነገ እንደ … አይነቶቹ የኔ ቢጤ ለቦታው እንደማይመጥኑ ይነገራቸዋል፣ ስለዚህ በሩቁ መከላከል ይሻላቸዋል፡፡

  24. Anonymous February 15, 2014 at 6:57 am Reply

    በቤተክህነቱ ውስጥ ለመልካም ነገር እንቅፋት የሆኑ ሰዎችስ ይህ አካሄዳቸው የት ያደርሳቸው ይሆን ?

  25. kinde February 15, 2014 at 6:59 am Reply

    በቤተክህነቱ ውስጥ ለመልካም ነገር እንቅፋት የሆኑ ሰዎችስ ይህ አካሄዳቸው የት ያደርሳቸው ይሆን ?

  26. kifie February 15, 2014 at 7:21 am Reply

    yih zemen negerochin bezimta yemnalfbet aydelem ewunetn ewunt malet alebin sile tsion zim anlm

  27. Anonymous February 15, 2014 at 8:09 am Reply

    በቤተክህነቱ ውስጥ ለመልካም ነገር እንቅፋት የሆኑ ሰዎችስ ይህ አካሄዳቸው የት ያደርሳቸው ይሆን ? aserate betekeretiyanen yastageselen medehanialem

  28. yikir belen February 15, 2014 at 8:26 am Reply

    የዛሬን አያድርገውና የፓትርያርክ ደብዳቤኮ የእምነት መግለጫ፣ የሚጠቀስ፣ በክብር የሚቀመጥ፣ በሃይማኖተ አበው መጽሐፍ ላይ የሚሠፍር ነበር፡፡ እንዲህ ጊዜ በሰጠ ቁጥር መዥለጥ እየተደረገ የሚጻፍ አልነበረም፡፡ ደግሞስ አንድ አባት ልጆቹን ጠርቶ መምከር እየቻለ ‹‹ልጆቼ እንዲህ ያሉ ናቸው›› ብሎ ለዓለም መንገር ከየት ያመጣነው ሥርዓት ነው? ዓለም ችግሯን ለቤተ ክርስቲያን ታቀርባለች እንጂ ቤተ ክርስቲያን ችግሯን እንዴት ለዓለም አቤት ትላለች?

  29. Solomawi February 15, 2014 at 4:42 pm Reply

    Protestant reformation advocates, they don’t want see real change in our church, because if our church respond appropriately to the current, social, religious, economical national and international challenges, the protestant group doesn’t get a chance to steal Christians.

  30. Estifanos February 15, 2014 at 8:30 pm Reply

    sile betekirstiyan kifuwua alsima. be’ewinet. le’andand agelgayochachinim fetari libinina mastewalin yistilin.

  31. tesfaye February 15, 2014 at 11:20 pm Reply

    እግዚአብሔር ለሥራ ጊዜ አለው፡፡…በእግዚአብሔር የምንጠየቀው የሚጠብቅብንን ሳንሠራ ስንቀር ነው::

  32. Anonymous February 16, 2014 at 10:58 am Reply

    beferisawuyan lay geta eyeferede new.betekiristianuan bebaed amiliko ena bahil yemolu gena yiketalu…yafiralu..kibir legeta yihun!!

  33. Anonymous February 16, 2014 at 12:45 pm Reply

    Fetena yelelew agelgilot agelgilot ayibalimina ayizoachihu yale new Egziabher Mahiberachinin yitebikilin, Mahiberun ye agelgilot mahiber yadirgilin.

  34. dirribaa February 16, 2014 at 3:29 pm Reply

    EGZIABIHER LE HULLACHIN ASTEWAY LIBONA YISTEN, ISU BE MENGEDU YIMRAN!!!

  35. አይይይ February 16, 2014 at 7:17 pm Reply

    1. ዕቅድ ከፎርማሊቲ ውጭ ያን ሁሉ ገጽ አንብቦ ይህን አንሳ ይህን ጣል የሚል የቤተክህነት ሃላፊ እንደሌለ እዬታወቀ አሳውቀናል የሚለውን መፎገሪያ ተውት። እንደ ጉዳዩ ክብደትና ለሰዎቹ ምክንያት ለማሳጣት ልዩ ደብዳቤ ሊጻፍላቸው ይገባ ነበር።(አራት ነጥብ)
    2. በቁጥር 1 ተማምነን ሊቃውንቱ ከመጡ በኋላ የተካሄደው ሸፍጥ ምን ያመለክታል ቢባል
    ሀ. አገልግሎት በሰዓትና በፊርማ የሚከፈሉበት ሞያ ብቻ ሆነ ብለን ስናዝን አባ ሰረቀ ይግረማችሁ ብለው ስልጣን እንዳደረጉት እሳቸውም አምባገነን ባለስልጣን እንደሆኑ አወቅን። የአምባገነንታቸውም ጥግ መንፈሳዊነቱን እርሱትና ሰብአዊነታቸው ተንጠፍጥፎ አልቆ ስንት ኪ.ሜ የተጓዙትን ሊቃውንት ለመበተን የሚጨክን ክፉ ልብ እንዳላቸው ተረዳን። ለዋልጌነታቸው ማስፈጸሚያ ህግ ወይም ቁጣ ሳይሆን ወደ ሕወሐት መራሹ መንግስት የሚያበሩት ደብዳቤ ካታች ያሉትን ብቻ ሳይሆን የሳቸው አለቆችን ስራስኪያጁንና ፓትርያርኩን ያስፈራራላቸዋል።
    ለ. አባ ማትያስ እውነት ነው አዲስ ናቸው። ይህን እውነት ግን ፍትሐዊነት የሚባል ከሚነበብ መመሪያ ውጭ የሆነ ሕገ ልቡና የሚባል ለዚህም የሚያግዝ አዕምሮ ግዕዛን የተሰጣቸው ሰው ሆነው ሳለ አልተጠቀሙበትም። በሰንበት ጭቃ ውስጥ የወደቀውን እንስሳ ከማውጣት ሰንበትን አክብር የሚለውን መመሪያ አከበሩ። እኒህን አምባገነን ማለት አልፈልግም። ነፍሳቸው አቅመ ቢስ ሆና አቤቱ ከእዚህ እሳት በፍጥነት ጥራኝ እያለች የምታሳስብ የተጨነቀች ሆና ነው የምትታየኝ። ይሄን ወስነው እንዴት ይተኛል?
    ሐ. የሥራ አስኪያጁና የማኅበረ ቅዱሳን ውሳኔ ተመሳሳይ ነው። ሁሉም ነገ ስለሚመጣው ብዙ አገልግሎት ሲሉ ዛሬን አንገትን ደፍቶ ማለፍ።
    ይሄን ፈቃደ እግዚአብሔር ነው እያለ በፍርሃትና ስንፍና ውስጥ የሚዋዥቅ አላዋቂ ሄዶ ሊቅውንቱን ይጠይቅ።

  36. Anonymous February 17, 2014 at 9:02 am Reply

    betam yigermal Egziabiher ayichekulem ande ken yifrdal እግዚአብሔር ለሥራ ጊዜ አለው፡፡

  37. Anonymous February 17, 2014 at 9:58 am Reply

    yelj tut nekash ……hone negeru!!

  38. Anonymous February 17, 2014 at 10:03 am Reply

    yeij tut nekash …….

  39. በአማን ነጸረ February 17, 2014 at 3:53 pm Reply

    በዲ/ዳንኤል ለተነሳውና ማህበረ-ቅዱሳን በጠራው ስብሰባ መሰረዝ ተጠቃሚው ማን ነው ለሚለው ጥያቄ ያለኝ መልስ…ሁሉም…ሁሉም ተጠቃሚ ነው የሚል ነው!!አዎ በድፍረት፣በጥብዐት፣ያለመሸማቀቅ እናገራለሁ!!ጥቅሙም….
    (1)ቤተክህነቱ….ስልጣኑን በአግባቡ በመጠቀም የቤ/ክ የበላይ እሱ እንጅ ማህበረቅዱሳን እንዳልሆነ በማሳየት፣ም/ቱም በወረቀት ተጠየቀ (ያውም ከ6 ወር በፊት ) ማለት ተፈቀደ ማለት አይደለምና፣
    (2)ማህበረቅዱሳንም…በዚህ እግድ በቤ/ክ ስር ያለ ንዑስ ክፍል እንጅ እንዳሻው የሚራመድ ማን ተናግሮኝ ባይ አካል እንዳልሆነ ይማራል-ከመከራው፣
    (3)መምህራንም….ማንም በአበል እያባበለ ከጉባኤያቸው እየነጠለ የሚያመጣቸው ሳይሆኑ በስርዐቱ በሀገረስብከታቸው በኩል ብቻ ሲጠሩ በመምጣት ክብራቸውን ማስጠበቅ እንዳለባቸው ይማራሉ፣
    (4)ቤተክርስቲያንም ሥርዐት ሲጠበቅ ትጠቀማለች እንጅ አትጎዳም!!ስለዚህ ተጠቃሚው ሁሉም ነው!!!
    (5)አሁንም የምናገረው ሊቃውንቱም ሆነ ቤ/ክርስቲያን ያለ ማህበረቅዱሳን ኖረው ያውቃሉ!!ሀቁ አንድ ነው!! እውነት እንናገር ከተባለ ቤ/ክ በማንም አለመኖር አትጠቀምም!! በሌላ በኩል ይሁን ግዴለም ህልውናን እናነጻጽር ከተባለ ግን እንደ ማህበረቅዱሳን አይነት 10….50….100… ማህበር መመስረት ይቻላል!! ሲኖዶስ ግን አንድ ነው!!
    (6)ሁሌ የሚገርመኝ ቤተክህነትና ማህበረቅዱሳን መሀል አለመግባባት ከተከሰተ ምንጊዜም ጥፋተኛው ቤተክህነቱ ነው!!ለዚህም ነው ቀ/ዶ/ር ሰሙ የኛን ቤት እንደምታውቁት….እያሉ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ሲናገሩ የተሰሙት-የተለመደ ነው በሚል የፍረጃ ስሜት!!ዲ/ን ብርሃኑ አበጋዝም እነእንትና ….ማህበሩን ሲፈትኑት ነው የኖሩት… እያለ ጣቱን ሲቀስር ሰማነው-ቆሞሱን ዲያቆኑ እንዲያስተሀቅር የትኛው ቀኖና እንደሚፈቅድ ባናውቅም!!ማህበሩ እየተፈተነ ያለው በራሱ የማንአለብኝነት አካሄድና ሁሌ አበሳውን ወደላይ አንጋጦ በማበስ ተግባሩ ጭምር ስለመሆኑ ለመረዳት የሚጎርፉለት ከንቱ ውዳሴዎች አውረውታል!!ስለሆነም ልብ እስኪገዛና ራሱን በአባቶች እግር ስር አድርጎ እስኪማር ድረስ ፈተናው መቀጠሉ አይቀሬ ነው!!!እርግጥ ነው ሚዲያውን ስለተቆጣጣረው በጥቂት አባቶች ላይ የሞራል ስብራት ለማድረስ መጣሩ አይቀርም!!ሆኖም ይህ አካሄድ እንደማያዋጣ በቀደመው ዘመን አስተውለናል!!አሁንም ወደራሳችሁ ወደውስጣችሁ ተመልከቱ!!ባጉዋጉል አካሄድ ከቤተክህነቱ ጋር በመጠላለፍ ከጳጳሳትና ከሲኖዶስ በላይ የኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖት ተቆርቁዋሪ ሆኖ በመቅረብ የፕሮሞሽን ስራ የሚሰራበት ዘመን አልፉዋል!!አበሳችሁን ሁሉ የምትጭኑባቸው አባትም አርፈዋል-እፎይ ብለዋል-ተገላግለዋል-ካህኑ ሁሉ እንደሚለው እግዚኦ አእርፍ ነፍሰ አቡነ ጳውሎስ እንላለን!!
    (7)የአብነት መምህራን በተለይ በገጠሩ ሰሜን ኢ/ያ ያሉት በደብር አስተዳዳሪነት ደረጃ ያሉ እንጅ ተራ ካህን ወይም በዳኒ አጠራር እነ ብሩ የሚያዙዋቸው አይደሉም!!ይብዛም ይነስም ካለው አገልጋይ የተሻለ ደሞዝና የሚያርሱት መሬት ከብዙ አክብሮትና መወደድ ጋር አላቸው!!እኔ በግሌም በኑሮ ረገድ አ/አ ከመኖር ይልቅ እዛው ገጠር መኖሩን እንደሚመርጡ የሚናገሩ መምህራንን አውቃለሁ!!በአ/አ ያሉትም ቢሆኑ በደሞዝ ካለቆች ቢያንሱም ከካህናቱ ቁንጮ ላይ ናቸው-ስኬላቸውም ይለያል!!ይሄን ሁሉ ብናገርም አሁንም የተሻለ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አምናለሁ!!ነገር ግን አፍንጫው ስር ካለው የሊቃውንት ጉባኤ ጋር ተስማምቶ ለመስራት ሲቸገር የምናየውና በአመራር ደረጃ ካሉ ሊቃውንት ጋር ማለትም ከአቁዋቁዋሙ ሊቅ ን/ዕድ ኤልያስ፣ከድጉዋው ሊቅ ሊ/ሊቃውንት እዝራ፣ድጉዋውን ቃኝተው፣ዝማሜውን ዘመው፣ቅኔውን ተቀኝተው፣ውዳሴ ማርያሙን ተርጉመው ሲያበቁ በስብከተ ወንጌላቸው ከሚያረሰርሱን እንደነ መ/ገነት ዘላለም አይነት አራት ዐይና ሊቃውንት ከመቀራረብ ይልቅ በሆነ ባልሆነው ሰበብ ስማቸውን በየኢንተርኔቱ ሲያስቦጭቅ የምናውቀው ማህበር ለጠረፎቹ የአዞ እንባ ማንባቱ ለማያውቁሽ ታጠኚ ያሰኛል!!ያስተዛዝባል!!
    (8)ዳኒም ያ ሁሉ ሊቅና ጳጳስ ከፓ/ኩ እስከ ቅ/ሲኖዶሱ ላለፉት ሃያ አመታት በየሚዲያው ሲቦጨቅና ያ ሁሉ ግዝት ዘበከንቱ ሲዥጎደጎድ እንዳላየህ ስታልፍ ኖረህ ማህበሩ ሲነካ ዘራፍ ማለትህ ጉዳዩን የመደብ ትግል አስመስለኸዋልና ቅር ብሎኛል!!
    (9)ቢሆንም….ቢሆንም አሁንም ልዩነቱ የአካሄድ እንጅ የአላማና የሃይማኖት እንዳልሆነ እረዳለሁ!!ስለሆነም ማህበሩ አካሄዱን የሚያርምበት ልቡና እንዲሰጠውና ከስሙ ይልቅ ስራው ገኖ ለቤ/ክ ከዚህም በላይ እንዲሰራ እጸልያለሁ!!

    ወነአምን በአሀቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት!!

  40. ግበምድር February 19, 2014 at 10:09 am Reply

    የዘመኑ አርዮስ፣ የማርቲን ተከተታየይ የ “አባ” ሰረቀና ግብር አበሮቹ” ምንፍቅና የ100 ዓመት እስትራቴጂ ዕቅድ ውጤት ነው፡፡

    ይህ ሰው ፓስተር ሰረቀ ከነተከታዮቹ እኮ ተረፈ አሪዎሳዊ ነው፡፡ ‹‹ስም አልባው›› … አናንተንም ጨምሮ!!! ስለዚህ በኒቂያ፣ በኤፌሶን .. ጉባኤ ተለይተው እደተወገዙት አሪዎሳውያን ወይ ከነ ግብር አበሮቻችሁ ተወግዛችሁ ትለያላችሁ ወይም ስጋችሁ ተጎትቶ ከቤተክህነቱ፣ ከጉልላቱ ይወጣል…፡፡ ይህንን ደግሞ ጊዜ ይፈጅ ይሆናል እንጂ እናንተ አሪዎሳውያን በአይናችሁ ታዩታላችሁ፣ በጆሮዋችሁ ትሰሙታላችሁ፤
    ምክንያቱ ‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም!!!›› የተመሰረተችው በክርስቶስ ደም ነውና!!
    ምክንያቱ ‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም!!!›› የተመሰረተችው በክርስቶስ ደም ነውና!!

    1ኛ. ‹‹በቤተክርስቲያናችን በአውደ ምህረቱ በአደባባይ ላይ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በአማላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በንጽህተ ንጹሀን በቅድስት ድንግል ማርያም፣ በቅዱሳኑ፣… ላይ የሚነዛው የአሪዎሳዊ፣ የማርቲን … የምንፍቅና፣ የክህደት ትምህርት ዋና ምንጩ የቤተክህነቱ የውስጥ ፓስተር ጉዳይ አስፈጻሚ እኮ ሰረቀ፣‹‹ስም አልባው››ና … ሌሎች ብዙ መሰሎቻችሁ ናችሁ!››

    2ኛ. የዚህች ቤተክርስቲያን ልዕልና መደፈር፣ የቤተክህነቱ የሙስናው፣ የዘረኝነቱ፣ የአድልዎ ቅጥሩ፣ የሙዳይ ምጽዋቱ ሰበራው፣ የነፈፍስ ግድያው …. የእናንተ አይን አያይም፣ ጆሮ አይሰማም፣ … ለነገሩ ዓላማችሁ ይህ ነውና፣ …

    3ኛ. በዚህ 10 እና 15 ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ እንኳን ከ10 ሚሊዮን በላይ ኦርቶዶክሳዊ የተዋህዶ ልጅ መናፍቅ መሆኑ፣ ከእና ቤ/ክ መኮብሉ የማን ደባና ስራና ይሆን? የፓስተር ሰረቀ፣ … እና መሰሎቻቸው የ100 ዓመት እስትራቴጂ ዕቅድ ነው፡፡ ኩሎ ለጊዜ!!!

    ‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም!!!››

  41. Anonymous February 19, 2014 at 12:49 pm Reply

    ene yegeremegn mahiberu lesibsebaw be baner lay yawetaw meri kal new ”ye akababi na yegil nitsihina bemetebek rasachinini kebeshita enikelakel ylal” yemahiberu arma na maninetunim kebeachu sifual. yigermachuhal yihen saneb ye andegna kifil duro yetemarkubet ye science metsehaf new tiz yalegn. ahun yihe ye tena minister melikit weyis ye betekirstian. gena fund agegnalehu mengist des yisegnibetal tebilo yihen mastelalefu endene agibab ayidelem. lemehonu yegedamat chigir nitsihina metebek new. yeduro abatochachin yan hulu egadilo yetegadelut na yeteleye tsegan yagegnut enante endemitilu sile sigawi nitsihina techenkew sayihon sile menfesawi nitsihinachew bemechenek new . any way am not happy with that!

  42. Anonymous February 23, 2014 at 8:54 pm Reply

    yasazinal yemelkam neger tekarani yehonew aba sereke emnetu yemaytawek sew eyeteshome new eminetachin eyeberze yalew

  43. Anonymous March 14, 2014 at 9:09 am Reply

    kirsitian

    Sew yezrawen yachidal!

  44. ገ/ስላሴ March 18, 2014 at 12:14 pm Reply

    ‹‹ማንኛዉንም ሰዉ ክፉ ሃሳብ እንዲያስብ ፣እንዲናገር፣እንዲሰራ የሚያደርግ ቅድመ ጠላታችን ሳይጣን ነዉና እግዚአብሄር ይህን ሳይጣን ያርቅል ዘንድ እባካችሁ አንዳችን ለአንዳችን እንፀልይ›› እግዚአብሄር ሆይ ይቅር በለን

  45. ዘውዱ አስጨነቅ April 5, 2016 at 7:42 pm Reply

    ለበጎ ነው

  46. kal fisha February 4, 2018 at 11:39 am Reply

    best

Leave a comment