የቅርስ ማጥፋትና ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀሎች ተጠርጣሪው አባ ገብረ ኢየሱስ መኰንን ከቅዱስ ላሊበላ ደብር መምህርነት ተነሥተው የእንጦጦ ማርያምን መልአከ ፀሐይነት ተሾሙ፤ በደብሩ ገንዘብ በሚገዛ የመኪና ‹‹ሽልማት›› ለማሰናበት የሚደረገው የጥቅመኞቻቸው ሽር ጉድ የላሊበላ ካህናትና ምእመናንን ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል፤ የመኪና ‹‹ሽልማት›› የሙሰኛ አስተዳዳሪዎች ዋነኛ መክበርያ እየኾነ ነው

Komos Aba Gebre Eyesus Mekonen

ለዘጠኝ ዓመታት በአስተዳዳሪነት ከቆዩበት የቅዱስ ላሊበላ ደብር መምህርነት በካህናትና ምእመናን ተቃውሞ ተነሥተው ወደ አዲስ አበባ – እንጦጦ ርእሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተዛወሩት ‹ተሸላሚው› መምህር ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ መኰንን

  • ከአስተዳዳሪው ጋራ የጥቅም ግንኙነት ያላቸው የቅ/ላሊበላ ደብር ሰበካ ጉባኤ አባላትና የአስተዳደር ሠራተኞች፣ ለመኪና ‹ሽልማቱ› ከግማሽ ሚልዮን ብር በላይ (በአንዳንድ ምንጮች መረጃ ከብር 800,000 – 1.5 ሚልዮን) ከደብሩ ካዝና ወጪ ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡ ለ‹ሽልማቱ› የሚገዛው ሞዴል ዶልፊን መኪና እንደ ኾነ ተጠቁሟል፡፡ ይህም በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት አንዳንድ አድባራት በሽኝት ስም በተፈጸሙ የመኪና ‹ሽልማቶች› ጋራ ተዳምሮ ሙሰኛ የአድባራት አስተዳዳሪዎች የመክበርያ መንገድ እየኾነ እንደ መጣ አመላካች ኾኗል፡፡
  • ‹‹መነኩሴ ቢሸለም መስቀል እንጂ መኪና ምን ያደርግለታል?›› የሚሉ የቅ/ላሊበላ ደብር ካህናትና ምእመናን፣ ‹‹አባ ገብረ ኢየሱስ በሕግ መጠየቅ እንጂ ሽልማት አይገባቸውም›› በሚል ኅዳር ፲፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ለከተማው ከንቲባ ምሬታቸውን ገልጠዋል፤ ፖሊስ ጣቢያውንም በአቤቱታ አጨናንቀው ውለዋል፡፡ ማኅበረ ካህናቱ እና ምእመናኑ አባ ገብረ ኢየሱስ የመኪና ‹ሽልማቱን› ለመቀበል አሁን ካሉበት አዲስ አበባ ወደ ላሊበላ ተመልሰው በሚገኙበት የሽኝት መርሐ ግብር ላይም ከፍተኛ ተቃውሟቸውን ለማሰማት ተዘጋጅተዋል፡፡ የሽኝት እና የ‹ሽልማት› መርሐ ግብሩን ከብዙኃኑ ካህንና ምእመን እይታ ውጭ በአዳራሽ /በደብሩ የአብርሃም ሆቴል/ለማድረግ ታስቧል፡፡
  • የመኪና ግዥው ሂደት ወደ አዲስ አበባ በተላኩ የአስተዳዳሪው ጥቅመኞች እንዲከናወን የተደረገው፣ አባ ገብረ ኢየሱስ የደብሩን ሰበካ ጉባኤና የአስተዳደር ሠራተኞች ሰብስበው ‹‹መሸኛ ይሰጠኝ›› በማለት የ‹መሸኛውን› ገንዘብ መጠን ጠቅሰው መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ይህንኑ ለማስፈጸም ‹‹የልደት በዓል አከባበርን በሚመለከት ለመወያየት›› በሚል ሰበብ በደብሩ ምክትል ሰብሳቢና ጸሐፊ አስተባባሪነት በተጠራ የካህናት ጉባኤ ላይ፣ ‹‹ከደብሩ ካዝና ገንዘብ ወጪ ተደርጎ እንድንሸኛቸው ብፁዕ አባታችን ፈቅደዋል›› እየተባለ የተሰበሰበ የተጭበረበረ የካህናት ፊርማ ለሀ/ስብከቱ መቅረቡ ተነግሯል፡፡
  • ሀ/ስብከቱ ቀደም ሲል በተፈጸሙ ምዝበራዎች ምክንያት አባ ገብረ ኢየሱስ የደብሩን ሒሳብ እንዳያንቀሳቅሱ አግዷቸው ሳለ፣ ለተባለው የ‹ሽልማት› መኪና ግዥ ከግማሽ ሚልዮን ብር በላይ ገንዘብ ወጪ እንዲኾን መፍቀዱ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱን በከፍተኛ ደረጃ እያስወቀሰ ነው፡፡ የሀ/ስብከቱ ጸሐፊ የተሰጠውን የግዥ ፈቃድ መቃወማቸው ተዘግቧል፡፡
  • የከተማው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት በደብሩ አብያተ መቅደስ ባካሄደው ድንገተኛ የቅርስ ቆጠራ÷ ቤተ መርቆሬዎስ በቅርስነት የተመዘገበው ጥንታዊ የብራና መጽሐፍ ከተመዘገበበት የተለየ ኾኖ ተገኝቷል፤ በቤተ ገብርኤል በቅርስነት የተመዘገበ ኵስኵስት በቦታው አልተገኘም፤ በዚኹ ቤተ መቅደስ የሚገኝ የወርቅ መስቀልም ስለ መቀየሩ እየተነገረ ነው፡፡ ጽ/ቤቱ ኹኔታውን ለሚመለከተው አካል በሪፖርቱ እንደሚያሳውቅ ተገልጦአል፡፡
  • ባለፈው ሳምንት እሑድ የላሊበላ ከተማ ፍትሕ ጽ/ቤት በቅርስ አጠባበቅ ሕግ ነክ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና ለመስጠት የደብሩን አስተዳደርና ካህናት በጠራበት ስብሰባ ላይ፣ ስለቅርስ ቆጠራና ርክክብ አስፈላጊነት ሐሳቦች በሚነሡበት ወቅት፣ አባ ገብረ ኢየሱስ አሠልጣኞቹን በተደጋጋሚ ተግሣጽ ለማሸማቀቅ ሲሞክሩ መስተዋላቸው ከጠፉትና ከተቀየሩት ቅርሶች ጋራ በተያያዘ ከፍተኛ የሕዝቡ ጥርጣሬ እንዲጠናከርባቸው አድርጓል፡፡ ወቅቱ አባ ገብረ ኢየሱስ ከሓላፊነታቸው ከመነሣታቸው ጋራ የተገናኘ ከመኾኑ አንጻር ተተኪው አለቃ ጽ/ቤቱን ተረክበው ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ጠቅላላ የቅርስ ቆጠራና የደብሩ ገቢዎችና ወጪዎች ኦዲት የማድረግ አስፈላጊነት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተጠየቀ ነው፡፡
  • ከቤተ ደናግል በፈለሰ የደንጊያ መንበር እና ከአብያተ መቅደሱ ጋራ በቅርስነት በተመዘገቡ ጎጆ ቤቶች ቃጠሎ ጋራ በተያያዘ የቅርስ ማውደም ከፍተኛ ወንጀል ተጠርጣሪ የኾኑት አባ ገብረ ኢየሱስ÷ በርካታ የልማት ሥራ እንዳከናወኑበት የሚናገሩለትን ደብር የቱሪዝምና ልማት ተቋማት ገቢዎች ግልጽነትና ተጠያቂነት በጎደለው አሠራር በመመዝበር ከባድ የእምነት ማጉደልና በሐሰተኛ ሰነድ ፈጠራ ከፍተኛ ወንጀሎችም ተጠርጣሪ ናቸው፡፡
  • ከሐሰተኛ ሰነድ ፈጠራ ጋራ በተያያዘ በተጠረጠሩበት ወንጀል የፖሊስ መጥሪያ የወጣባቸው አባ ገብረ ኢየሱስ፣ የተጠርጣሪነት ቃላቸውን የሰጡ ሲኾን ፖሊስ ምርመራውን አጠናቅቆና መዝገቡን አደራጅቶ ለከተማው ፍትሕ ጽ/ቤት ዐቃቤ ሕግ ማስተላለፉ ተዘግቧል፡፡ የተጣለባቸውን ሓላፊነት ወደ ጎን በመተው የቤተ ክርስቲያንን ሀብትና ንብረት በመመዝበርና ለግል መበልጸጊያ በማዋል በተጠረጠሩባቸው ከፍተኛ ወንጀሎች ጥፋተኛ ኾነው ከተገኙ ከ10 – 20 ዓመት የሚደርስ እስራትና ጽኑ እስራት ይጠብቃቸዋል፡፡
  • በቃለ ዐዋዲው የተወሰነውን የሥራ ዘመን በመፃረር ለስድስት ተከታታይ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው የደብሩ ሰበካ ጉባኤ (በተለይ ተተኪውን አስተዳዳሪ ተቀባይነት ለማሳጣት ከወዲኹ እያሳደሙና የሥነ ልቡና ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ክፉ ወሬዎችን እያስወሩ ናቸው የተባሉት የምክትል ሰብሳቢው ና ጸሐፊው) ኹኔታና ከአስተዳዳሪው ጋራ ከፍተኛ የጥቅም ግንኙነት ያላቸው የደብሩ ሠራተኞች አፈጻጸም በጥልቀት እንዲፈተሽ እየተጠየቀ ነው – ‹‹አዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ›› እንዳይኾን!
  • ተተኪው የደብሩ አለቃ (መምህር) እና በአዲስ መልክ መዋቀር የሚያስፈልገው የደብሩ አስተዳደር ሊፈጽሟቸው ስለሚገቡ ቀዳሚ የጥንቃቄና የእርምት ርምጃዎች የሚከተሉት ነጥቦች ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፡- 1) የቅርስ ቆጠራ፣ የገንዘብ እና ንብረት ወጪና ገቢ ኦዲት ተደርጎ ግኝቱ ይፋ እንዲደረግ፣ ጉድለቱ እንዲታወቅ በአያሌው ይጠበቃል፡፡ 2) በቤተ መዘክሩ ቅርሶች ከመጸዳጃ ቤት በታች በአልባሌ ኹኔታ እንደተቀመጡ ተገልጦአል፤ ይኸው ጉዳይ ትኩረት አግኝቶ የቅርሶቹ አቀማመጥ ብቻ ሳይኾን የቤተ መዘክሩ አስተዳደርም በተገቢው አሠራርና ባለሞያ ሊደገፍ ይገባል፡፡ 3) የሥራ ዘመኑን ጨርሶ ለተጨማሪ ሦስት ተከታታይ ዓመት በሥልጣን ላይ የሚገኘው ሰበካ ጉባኤ በቃለ ዐዋዲው የተፈቀደለት የሥራ ዘመን የተላለፈው በመኾኑ ከሓላፊነቱ ሊሰናበት ይገባል፤ የአስተዳደር ሠራተኞችም ከአባ ገብረ ኢየሱስ አስተዳደር ጋራ የነበራቸው የጥቅም ግንኙነት በጥልቀት እየተፈተሸ ተገቢው ርምጃ መወሰድ አለበት፡፡ 4) አብያተ መቅደሱን ለመጎብኘት የሚመጡ ቱሪስቶች ሚስተናገዱበት የትኬት ቢሮ በተሻለ የቋንቋ ክህሎት የሚግባባና በቱሪዝም ማኔጅመንት የሠለጠነ፣ ገቢውን ከመቆጣጠር አንጻርም ታማኝ በኾኑ ሠራተኞች የተደራጀ መኾን ይኖርበታል፤ በአዲስ አበባ ቱሪስቶችን አደራጅቶ ለመላክ በሚል የተከፈተው የጉዞና ጉብኝት ቢሮ በአባ ገብረ ኢየሱስ የጥቅመኝነት መረብ ውስጥ እንዳለ የሚጠረጠር በመኾኑ ለደብሩ ታማኝ በኾነ የሠለጠነ ባለሞያ እንዲንቀሳቀስ መደረግ ይኖርበታል፡፡ 5) የአስተዳደርና የቅጥር ሥርዐቱ ከመበላሸቱ የተነሣ በሠራተኞች ላይ ከፍተኛ አድልዎና በደል የተፈጸሙባቸው የደብሩ ሆቴሎች (ቤተ አብርሃም፣ ቤተ ይምርሓ፣ ሰባት ወይራ እና የእንግዳ ማረፊያው) አስተዳደርና የሠራተኞች ብቃት ከመልካም ገጽታ አንጻር ጥንቃቄ ሊደረግበት ያስፈልጋል፡፡
  • የላሊበላ ካህናትና ምእመናን በምሬት እንደገለጹት፣ መሸለም ሳይኾን በሕግ መጠየቅ ይገባቸዋል የሚባሉት አባ ገብረ ኢየሱስ ወደ አዲስ አበባ – እንጦጦ ርእሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ያደረጉት የእልቅና ዝውውር እርሳቸው እንደሚሉት ጠይቀው ሳይኾን ታዝዘው ያደረጉት ነው፡፡ ይኸውም ቢኾን ዝውውሩ በጸደቀበት የኅዳር ፲፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ‹‹ሕዝብ የተነሣበትንና ያባረረውን እንዴት እንመድባለን፤ ምደባው ቆይቶ መታየት ይኖርበታል›› በሚል በከፍተኛ ደረጃ አነጋግሮ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ የመሰል የሕግ ተጠያቂዎች ጉዳይ ግን ማነጋገር ብቻ ሳይኾን አስተማሪና ምሳሌያዊ የኾነ ርምጃ ይወሰድባቸው ዘንድ ከቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አመራር ይጠበቃል፡፡
  • በመጨረሻም፡- በአባ ገብረ ኢየሱስ መኰንን አስተዳደር የተመረረውና በቃሉም በሕይወቱም ምሳሌ ኾኖ የሚመራው አባት የናፈቀው የላሊበላ ካህንና ምእመናን አዲሱን የደብሩን ተተኪ መምህር (አስተዳዳሪ) በደማቅ አኳኋን ለመቀበል ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ መኾኑ ታውቋል፡፡ ወደ ቅ/ላሊበላ ደብር ተዛውረው የተመደቡት አዲሱ መምህር፣ የእንጦጦ ርእሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ከሁለት ዓመታት በላይ ያስተዳደሩት መልአከ ፀሐይ አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ ናቸው፡፡

31 thoughts on “የቅርስ ማጥፋትና ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀሎች ተጠርጣሪው አባ ገብረ ኢየሱስ መኰንን ከቅዱስ ላሊበላ ደብር መምህርነት ተነሥተው የእንጦጦ ማርያምን መልአከ ፀሐይነት ተሾሙ፤ በደብሩ ገንዘብ በሚገዛ የመኪና ‹‹ሽልማት›› ለማሰናበት የሚደረገው የጥቅመኞቻቸው ሽር ጉድ የላሊበላ ካህናትና ምእመናንን ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል፤ የመኪና ‹‹ሽልማት›› የሙሰኛ አስተዳዳሪዎች ዋነኛ መክበርያ እየኾነ ነው

  1. Anonymous November 29, 2013 at 6:28 pm Reply

    አህያውን ፈርቶ ዳውላውን አሉ ሐራ ተዋህዶዎች ትዝብት ላይ እየወደቃችሁ ነው ለዚህ ሁሉ ማን አለብኝነት ተጠያቂው ሊቀጳጳሱ ና የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር መሆኑን እያወቃችሁ ለምንድን ነው በገለሰቡ ላይ ብቻ የምትዘምቱት ያሳዝናል የሀገረስብከቱ ዋና ጸሐፊ የደብሩን ሀብት ሲመዘብርና አዲስ አበባ ውስጥ ከአንድ አይሉ ሁለት ቤት በደብሩ ሀብት ለገነባው ለአባ ገ/ኢየሱስ ሽልማት በሚል ሰበብ ከደብሩ ገንዘብ እንዳይወጣ ቢታገሉም ሰሚ አጥተዋል፡፡

  2. Anonymous November 29, 2013 at 7:32 pm Reply

    “•ሀ/ስብከቱ ቀደም ሲል በተፈጸሙ ምዝበራዎች ምክንያት አባ ገብረ ኢየሱስ የደብሩን ሒሳብ እንዳያንቀሳቅሱ አግዷቸው ሳለ፣ ለተባለው የ‹ሽልማት› መኪና ግዥ ከግማሽ ሚልዮን ብር በላይ ገንዘብ ወጪ እንዲኾን መፍቀዱ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱን በከፍተኛ ደረጃ እያስወቀሰ ነው፡፡”
    Why did not you mention the name of the Archbishop? Why do not you reveal his picture? but surely WE understand the reason why you did not do that. Because the arch bishop is the number one supporter of Mk. or the master key of Hara the tongue of Mk. So please be fair and say something fairly. Let us tell you the truth, we do know that Abune Cherlos is the lawyer of MK because of getting money from MK. But He is not a real supporter of MK.
    Look!! how the falls fathers playing a game in the church.

  3. Anonymous November 30, 2013 at 11:08 am Reply

    እጅግ የሚገርም ጉዳይ ነው፡፡ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ ከሊቀ ጳጳሰ የበለጠ ኃላፊነት አለው ማለት ነው? ይህ ፈጽሞ የማይታመን ጉዳይ ነው፡፡ ከመምህር ቆሞስ አባ ገ/ኢየሱስ መኮነን ሽራፊ ሳንቲም ሳይጣልለት ስለቀረ ብቻ አሁንም እኒህን አባት ማሳደዱን ቀጥሎአል፡፡ ይህ ግለሰብ እየሰራ ያለውን ተንኮል እያወቁ ብጽዕ አባታችን ለምን በዝምታ እንደሚያልፉት አይገባንም፡፡ ሀብት ለማጋበስ ሲል ብቻ የፈጠራ ወሬ እየፈበረከ በማያገባው ሁሉ እየገባ የሀገረ ስብከቱ የበላይ ኃላፊ አድረጎ እራሱን አስቀምጦአል፡፡

    ተራራ የሚያክል ወንጀሉን ደብቆ በልማት አርበኛው በአባ ገ/ኢየሱስ መኮነን ላይ ጣቱን ቀስሮ ማሳደድ መቀጠሉን ስናይ በጣም እናዝናለን፡፡ ካለፉት አስራ አምስት ቀናት በፊት በሀገረ ስብከቱ በነበረን አጠቃላይ ስብሰባ መምህር አባ ገ/ኢየሱስ አጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ ግለሰብ ራሱን ብቸኛው የሀገረ ስብከቱ ኃላፊ አድርጎ በማስቀመጡና ተው ባይ ያጣ በመሆኑ ለሥራ እንቅፋት መሆኑን ጠቁመው ማለፋቸውን እናስታውስለን፡፡ ስለዚህ ብጹዕ አባታችን ይደልዎ አስቦ ለዘይትቀነይ ነው ና ለመህምር አባ ገ/ኢየሱስ የሚገባቸውን ሽልማት እንዲሰጥ መወሰናቸውን እናደንቃለን ፡፡

  4. Anonymous November 30, 2013 at 3:07 pm Reply

    የሀገረ ስብከቱ ሀላፊዎችና ሊቀ ጳጳሱ ምነ አሉ? ይህን እብደት ዝም ብሎ ማለፍ በራሱ ለሌሎች በሀገረ ስብከቱ ውሥጥ ላሉ የደብር አስተዳዳሪዎች ሌላ ክፍተት መጣል ነው፡፡

  5. Anonymous November 30, 2013 at 3:15 pm Reply

    ከዚህም በላይ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ዘግተዋል ሰንበት ት/ቤት አዳከመዋል እንደውም ሰንበት ት/ቤት አያስፈልግም ብለው በአደባባይ የተነገሩ ሰው ናቸው መነኮሳትን አሳደዋል ( እንደ ቤተአማኑኤል የእናቶች ገዳም ) እንዲበተን ሲሰሩ የነበሩ ናቸው ትልልቅ የጉባኤ ቤት መምህራን ጉባኤአቸውን እንዲያጥፉ አድርገዋል የአብነት ተማሪዎች አያስፈልጉም አዋካቢ ናቸው ብለው ለፖሊስ አሳልፈው ሰጥተዋል

  6. Anonymous December 1, 2013 at 2:25 am Reply

    ቤተክርስቲያንን የሌባና የመናፍቃን መሽሸጊያ ለማድረግ መንቀሳቀስ እጅግ በጣም ክህደት ነው::እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ይጠብቅ :;

  7. Anonymous December 1, 2013 at 11:17 pm Reply

    ፈጣሪ ለሁሉም ፍርዱን ይሰጣል ሌባ ዱላ እንጅ ሽልማት አያስፈልገውም

  8. ሃይማኖት ርትእት December 2, 2013 at 5:23 am Reply

    ሙስናን ከመዋጋት በላይ እጅግ አንገብጋቢ የሆነውን የመናፍቃንን ወረራ እንዴት እያያችሁት ቢሆን ነው ዝምታን የመረጣችሁት? ከዚህ ቀደም ሐራ እንደዚህ ዓይነት መንፈስ የተላበሰች መስላኝ ደስ እያለኝ ነበር፡፡ በፍጥነት የሐዋሳ ጉዳይ በአደገኛ መንገድ እየተበላሸ ባለበት ሰዓት ዝምታው አልተዋጠልኝም፡፡
    እባክዎን በቶሎ ይናገሩ! ካልሆነ እንተዛዘባለን እንጂ እግዚአብሔር መንገድ አያጣም፡፡

  9. Anonymous December 2, 2013 at 12:34 pm Reply

    ለአባ ገብረ ኢየሱስ እንኳን መኪና አውሮፕላን ቢሸለም ቢያንሳቸው እነጂ የሚበዛባቸው አይደለም፡፡ ነገር ግን የአባገብረ ኢየሱስ መኪና መሸለም ያንገበገባቸው ሰዎች እነዳሉ ደርሰንበታል፡፡ ይህ የቅናት መንፈስ ከምን እንደ መጣ እናውቃለን ፡፡ለመሆኑ በአባ ገብረ ኢየሱስ ላይ ማን እንደዘመተባቸው ታውቃላችሁ? አባ ገብረ ኢየሱስ ላሊበላ እየጠሩ አበል ስላልሰጡት ያኮረፈ የግል ጥቅሙ የተነካ በቅዱስ ላሊበላ ባለ ሐብቶች እና ጋይዶች የገንዘብ ስጦታ የከበረ ሰው ነው ፡፡መኪና እንዲሸለሙ ማን እንደፈቀደ ማወቅ ካስፈለጋችሁ እወቁ?የደብሩ ካህናት በተወካዮቻቸው አማካኝነት ለዘመናችን ድንቅ እናብርቅ ታላቅ ሐዋርያ አቡነ ቄርሎስን አስፈቅደው እንዲያውም ከገዛችሁ አይቀር ደህና ነግር ግዙለት ብለው መመሪያ የሰጡበት እርሳቸው ናቸው፡፡ ሽልማቱን ማን እንደሚያስቀር እስቲ እናያለን፡፤
    ወሬ በማቀበል እና ሥራ ምሥራት ይለያያሉ ይህን ደግሞ እንኳን እኛ ብፁዕ አባታችን አቡነቄርሎስ የውቁታል፡፡እኛንም ሥራ አላሰራን ያለ ላሊበላ ላይ የተሰራውን ድራማ በብቃት የተወነ በስነ ምግባር የደከመ፡፡ ይህ ነው እንግዲህ የአባ ገብረ ኢየሱስ መኪና እንዳይሸለሙ ተቃዋሚ፡፡ለሁሉ ነገር ደስ አይበላችሁ አባ ባለመኪና ሆኑ፡፡

  10. Anonymous December 2, 2013 at 1:32 pm Reply

    እረ የአስተዳዳሪዎችን ምንፍቅና ለማ አቤት እነበል? ደግሞ ችግራቸው እንዲህ እታወቀ በሹመታቸው እነዲቀጥሉ ይደረጋል
    እረ ሰለ እግዚአብሔር የተሾማችሁበትን መንጋ አታማሩ አታሳዝኑ
    ሁሁሁሁሁ——–የፈጣሪ ያለህ

  11. Anonymous December 2, 2013 at 5:15 pm Reply

    yemetsefut neger kemekakelachu tilacha yalebet sew endale kulich adergo yasayal lemangnawum seweyew le hagerachen tilek seran yeseru yelimat arbegna nachew e/r edmena tena yestelen!

    1.keminim wode 4 hotel balebetinet yadresu,
    2. ke 2 mekina wode 5 mekina yasadegu,
    3. ke 2 dinamo wofcho wode 4 ye electric wofch yasedegu
    4. And kahin kneberwu ziktegna ye 5 birr demewez wode 1700 birr beamakai yaderesu,
    5. keminim mesebsebia adarash wode 3 tiratachewn yetebeku yiemesebsebia adarashoch menor yaschalu,
    6. memenanu keneberebet yebzu wochi yalemnim woch yefthat agelgilot endiagegn yaderegu,
    7.kahinatu hebtam woim dha sailu yaleminim felagi bete kristian zewetir tegegnitew memenanu agelgilot endiagegn yaderu,
    8.bete kristian bizu wochi yaswetu yeneberu ende teskar,arba,ametat yaskeru talak fana wogi abat mhonachewin lib lilu yishal.
    9.mengistinim kemedegefm anisar yiehbiret sira bemaderajet yegebya niretin lemekenes teff,zeit,sikuar bekelal waga endikefafel tedergual,eyaderegum yigegnalu,
    10.bemideregu yelimat wuchichiwoch kemanignawum tekuam bebelete ginibar kedem bemehon behuletu Yeashendyie lasta Lalibela bealoch layi ke tetesetut netsa 120 Yehotel kifiloch gar wode 600,000 birr bete kristian endilegis Adrgewal,
    11. Tmhirt betoch segenebu ke 300,000birr belay woch tedergo endisera yaderegu talak abat nachew,
    12. ye polis beuro sisera,ye techinch ena muya wode kollejinet lemiadergew shigigir,yefrdibet ginbata sijemer, ye meskel balin lemasamer kontainer sinesa,tmhirtawi guzo temariwoch ena memhiran sihedu ke 270,000birr belay woch tedergo lemahiberesebu endiwul yaderegu abat nachew.Lelochim tetekisew yemayalku zerfe bizu tegibaratin sertewal.
    Honom yihin menager Yemichalew chinkilatu lemiserana lemiyagenazib enji besigara,behashish,bemete,be chat aemrowun ladenezeze,chinkilatun befersle lemola bale mehonu hulunim letazabiwu etewewualehu!!!

    • Anonymous December 4, 2013 at 8:02 am Reply

      ሃራዎች በጣም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ እንደዚህ አይነቱ የበግ ለምድ ለባሽ ተኩላ በቤተክርስቲያናችን ገብቶ ሃይማኖታችን እየተፈታተናት ይገኛል፡፡በጣም ያሳዝናል አንድ የሃይማኖት አባት ልማት አለማ የሚባለው መጀመሪያ መስራት ያለበትን አለማቅ በጣም ይገርሞኛል፡፡ የሀይማኖት አባት የተቀመጠለትን ዋናውን ተግባር በህዝቡ ላይ የወንጌል ዘር ዘርቶ ተካታዮቹ ለሃይማኖታቸው ቀናኢ እንዲሆኑና ተከታዮቹን ማፍራት ከዛም አማኙ በማንኛውም መንገድ ቤተክርስቲያ በምትጠይቃቸው ተግባራት ሁሉ ተሳታፊ ሲሆኑ ልማት አለማ መባል ሲገባው አባ ገ/እየሱስ መኰንን የሚባለው ግን ፡
      1. የቅዱስ ላሊበላ ስራ ውጤቶች በመኞራቸው
      2. ይህንን ተከትሎ መንግስት ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ መሰረተ ልማቶች ውሀ፤ መብራት፤ስልክ የአየርና የየብስ ትራንስፖርት መኖር
      3. ከላይ የተጠቀሱት መሰረተ ልማቶች በመኖራቸው ለቱሪስቱ አመች የሆኑ ማረፊያ ሆቴሎች ባለሃብቶች በመስራታቸው
      4. መንግስትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅርሱን ማስተዋወቅ በመቻላቸው የእንግዳው /የጎብኝ / ፍሰት በመጨመሩ በቱሪስት መግቢያም ሆነ በሙዳየ መጽዋት የሚገባው ገቢ በመጨመሩ የቤተክርስቲያኒይቷ ገቢ ሊጨምር ችሏን፡፡ ከዚህ ላይ ልማቶቹ መለማታቸውን ማንም አይክድም ነገር ግን ከላይ በተገለጸው አግባብ አባ ገ/ዕየሱስ መኮነን ብዙዎች ያለ ደመወዝ መከራቸውን እያዩ ባቆዩትና አሁን ደግሞ እድላቸው ሆኖ ሳይለፉ መና በሚወርድበት ቦታ ላይ ተቀምጠው አለማሁ በሚል ስበብ ገንዘቡን እየዘረፉት ነው የሚገባው ገቢ ከዚህ በላይ በአምስት እጥፍ ማልማት የሚችል ገንዘብ እየተዘረፈ ነው፡፡ ገንዘቡ መዘረፉ ብቻ ሳይሆን ካህናት መነኮሳትና መእመናን ከቤ ክርስቲያን እተባረሩ ነው ምክንያቱም ብር ስላሰከራቸው ስካሩን መቋቋም አልቻሉምና ነው !የየትኛውም ሃይማኖት ምግባር የላቸውም ምንአልባትም የዳቢሎስ ይሆን!
      5. ወንድሜ ሌላው ድሆችን አሰባስበው በአንድ መጠለያ አድርገው እየረዱ ነው ብለሃን እነዚህን ድሆችና አረጋዊያን በመጀመሪያ እኛ አምናውቀው የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ና ባህል ቱሪዝም ፤ፖሊስ በመሆን ህዝቡን በማወያየት 60 አባላት ያሉት የኮሚቴ አባላት ተዋቅሮ ገንዘብ እዲሰባሰብ ተወስኖ ይህን ግን ማስተባበር ያለባት ከተልኮዋ አንጻር ቤተክርስቲያ ናት ብሎ ህዝቡ በፈጠረው ጫና መሰረት ህዝቡ ገንዘብ አዋቶ ክቡር የቀድሞው ፐሪዚዳንቱ ሳይቀሩ ድጋፍ አድርገው የውጭ ዜጎችም በቋሚነት በየወሩ 15ሺህ ብር እየተረዱ የሚገኙ ሲሆን ቤታቸውንም የከተማ አስተዳደሩ ወጩን ሸፍኖ የተሰራ ሁኖሳለ መነኩሴው እንደሳራ ተደርጎ መገለጹ ምንአለባትም ውሻ ፍርፋሪ ላገኘበት ቤት መጮሁ አይቀርምና እንዳይሆን! የሚገርመው የኮሚቴው ሰብሳቢ መነኩሴው ስለሆኑ የግል አድራሻ በመስጠት መለመኛ አድርገውታን ፡፡የነበሩትም ተረጂዎች ብዙዎቹ ሙተዋል ፤ተባረዋል፡፡ የነበረውን ስልሳ ኮሚቴዎች አባረው ህዝብ ያልመረጣቸውን ኮሚቴዎች በራሳቸው አዋቅረው የግል የልመናድርጂት ማድረጋቸው ነው የሚታወቀው፡፡
      በጣም የሚያሳዝነው የበሬን ምስጋና ወሰደው አህያ ነው የሆነብን መመስገን የሚገባቸው ቅዱስላሊበላ፤ይህን ቅርስ ያለደመወዝ ጠብቀው ያቆዩ አባቶች፤ አሁን ያለው መንግስት ለሰራቸው ስራዎች ሆነው ሳለ በዘረፋ ስራ የተሰማራው ሰውና ግብረ አበሮቹ አለሙ እየተባለ መወራቱ የሚገርም ነው ትንሸ እንቅስቃሴ ካልተደረገ እንዴት ገንዘብ መዝረፍ ይቻላል? ከሁሉም ነገር ከባዱ ፈተና በሃይማኖት በኩል ያለው እጸጽ ነው፡፡ ለመሆኑ ሀየ ባይ መንግስት ወይም የሃይማኖት አባት ማጣቱ የሚገርም ነው፡፡ በመጨረሻም ስለ ሰውየው ተነግሮ የሚያልቅ ስላልሆነ አጫፋሪዎችን ጨምሮ ልቦነ ይስጣችሁ ንስሃም ግቡ ቤተ ክርስቲያንን አታድሙዋት ፡፡
      መድሃኒት አለም እየሱስ ክርስቶስ ከነደዚህ አይነቶች አጨበርባሪዎች እኛንም ሆነ ቤተክርስቲያናችን ይጠብቅ!

  12. kereweyna eyassie December 2, 2013 at 5:23 pm Reply

    ebakachu hulunem le e/r enetew bene edme kayehuachew komosoch aba tiru sera yeseru ye lemat jegna nachew……
    1.keminim wode 4 hotel balebetinet yadresu,
    2. ke 2 mekina wode 5 mekina yasadegu,
    3. ke 2 dinamo wofcho wode 4 ye electric wofch yasedegu
    4. And kahin kneberwu ziktegna ye 5 birr demewez wode 1700 birr beamakai yaderesu,
    5. keminim mesebsebia adarash wode 3 tiratachewn yetebeku yiemesebsebia adarashoch menor yaschalu,
    6. memenanu keneberebet yebzu wochi yalemnim woch yefthat agelgilot endiagegn yaderegu,
    7.kahinatu hebtam woim dha sailu yaleminim felagi bete kristian zewetir tegegnitew memenanu agelgilot endiagegn yaderu,
    8.bete kristian bizu wochi yaswetu yeneberu ende teskar,arba,ametat yaskeru talak fana wogi abat mhonachewin lib lilu yishal.
    9.mengistinim kemedegefm anisar yiehbiret sira bemaderajet yegebya niretin lemekenes teff,zeit,sikuar bekelal waga endikefafel tedergual,eyaderegum yigegnalu,
    10.bemideregu yelimat wuchichiwoch kemanignawum tekuam bebelete ginibar kedem bemehon behuletu Yeashendyie lasta Lalibela bealoch layi ke tetesetut netsa 120 Yehotel kifiloch gar wode 600,000 birr bete kristian endilegis Adrgewal,
    11. Tmhirt betoch segenebu ke 300,000birr belay woch tedergo endisera yaderegu talak abat nachew,
    12. ye polis beuro sisera,ye techinch ena muya wode kollejinet lemiadergew shigigir,yefrdibet ginbata sijemer, ye meskel balin lemasamer kontainer sinesa,tmhirtawi guzo temariwoch ena memhiran sihedu ke 270,000birr belay woch tedergo lemahiberesebu endiwul yaderegu abat nachew.Lelochim tetekisew yemayalku zerfe bizu tegibaratin sertewal.
    Honom yihin menager Yemichalew chinkilatu lemiserana lemiyagenazib enji besigara,behashish,bemete,be chat aemrowun ladenezeze,chinkilatun befersle lemola bale mehonu hulunim letazabiwu etewewualehu!!!

    • Anonymous December 4, 2013 at 7:22 am Reply

      ሃራዎች በጣም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ እንደዚህ አይነቱ የበግ ለምድ ለባሽ ተኩላ በቤተክርስቲያናችን ገብቶ ሃይማኖታችን እየተፈታተናት ይገኛል፡፡በጣም ያሳዝናል አንድ የሃይማኖት አባት ልማት አለማ የሚባለው መጀመሪያ መስራት ያለበትን አለማቅ በጣም ይገርሞኛል፡፡ የሀይማኖት አባት የተቀመጠለትን ዋናውን ተግባር በህዝቡ ላይ የወንጌል ዘር ዘርቶ ተካታዮቹ ለሃይማኖታቸው ቀናኢ እንዲሆኑና ተከታዮቹን ማፍራት ከዛም አማኙ በማንኛውም መንገድ ቤተክርስቲያ በምትጠይቃቸው ተግባራት ሁሉ ተሳታፊ ሲሆኑ ልማት አለማ መባል ሲገባው አባ ገ/እየሱስ መኰንን የሚባለው ግን ፡
      1. የቅዱስ ላሊበላ ስራ ውጤቶች በመኞራቸው
      2. ይህንን ተከትሎ መንግስት ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ መሰረተ ልማቶች ውሀ፤ መብራት፤ስልክ የአየርና የየብስ ትራንስፖርት መኖር
      3. ከላይ የተጠቀሱት መሰረተ ልማቶች በመኖራቸው ለቱሪስቱ አመች የሆኑ ማረፊያ ሆቴሎች ባለሃብቶች በመስራታቸው
      4. መንግስትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅርሱን ማስተዋወቅ በመቻላቸው የእንግዳው /የጎብኝ / ፍሰት በመጨመሩ በቱሪስት መግቢያም ሆነ በሙዳየ መጽዋት የሚገባው ገቢ በመጨመሩ የቤተክርስቲያኒይቷ ገቢ ሊጨምር ችሏን፡፡ ከዚህ ላይ ልማቶቹ መለማታቸውን ማንም አይክድም ነገር ግን ከላይ በተገለጸው አግባብ አባ ገ/ዕየሱስ መኮነን ብዙዎች ያለ ደመወዝ መከራቸውን እያዩ ባቆዩትና አሁን ደግሞ እድላቸው ሆኖ ሳይለፉ መና በሚወርድበት ቦታ ላይ ተቀምጠው አለማሁ በሚል ስበብ ገንዘቡን እየዘረፉት ነው የሚገባው ገቢ ከዚህ በላይ በአምስት እጥፍ ማልማት የሚችል ገንዘብ እየተዘረፈ ነው፡፡ ገንዘቡ መዘረፉ ብቻ ሳይሆን ካህናት መነኮሳትና መእመናን ከቤ ክርስቲያን እተባረሩ ነው ምክንያቱም ብር ስላሰከራቸው ስካሩን መቋቋም አልቻሉምና ነው !የየትኛውም ሃይማኖት ምግባር የላቸውም ምንአልባትም የዳቢሎስ ይሆን!
      5. ወንድሜ ሌላው ድሆችን አሰባስበው በአንድ መጠለያ አድርገው እየረዱ ነው ብለሃን እነዚህን ድሆችና አረጋዊያን በመጀመሪያ እኛ አምናውቀው የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ና ባህል ቱሪዝም ፤ፖሊስ በመሆን ህዝቡን በማወያየት 60 አባላት ያሉት የኮሚቴ አባላት ተዋቅሮ ገንዘብ እዲሰባሰብ ተወስኖ ይህን ግን ማስተባበር ያለባት ከተልኮዋ አንጻር ቤተክርስቲያ ናት ብሎ ህዝቡ በፈጠረው ጫና መሰረት ህዝቡ ገንዘብ አዋቶ ክቡር የቀድሞው ፐሪዚዳንቱ ሳይቀሩ ድጋፍ አድርገው የውጭ ዜጎችም በቋሚነት በየወሩ 15ሺህ ብር እየተረዱ የሚገኙ ሲሆን ቤታቸውንም የከተማ አስተዳደሩ ወጩን ሸፍኖ የተሰራ ሁኖሳለ መነኩሴው እንደሳራ ተደርጎ መገለጹ ምንአለባትም ውሻ ፍርፋሪ ላገኘበት ቤት መጮሁ አይቀርምና እንዳይሆን! የሚገርመው የኮሚቴው ሰብሳቢ መነኩሴው ስለሆኑ የግል አድራሻ በመስጠት መለመኛ አድርገውታን ፡፡የነበሩትም ተረጂዎች ብዙዎቹ ሙተዋል ፤ተባረዋል፡፡ የነበረውን ስልሳ ኮሚቴዎች አባረው ህዝብ ያልመረጣቸውን ኮሚቴዎች በራሳቸው አዋቅረው የግል የልመናድርጂት ማድረጋቸው ነው የሚታወቀው፡፡
      በጣም የሚያሳዝነው የበሬን ምስጋና ወሰደው አህያ ነው የሆነብን መመስገን የሚገባቸው ቅዱስላሊበላ፤ይህን ቅርስ ያለደመወዝ ጠብቀው ያቆዩ አባቶች፤ አሁን ያለው መንግስት ለሰራቸው ስራዎች ሆነው ሳለ በዘረፋ ስራ የተሰማራው ሰውና ግብረ አበሮቹ አለሙ እየተባለ መወራቱ የሚገርም ነው ትንሸ እንቅስቃሴ ካልተደረገ እንዴት ገንዘብ መዝረፍ ይቻላል? ከሁሉም ነገር ከባዱ ፈተና በሃይማኖት በኩል ያለው እጸጽ ነው፡፡ ለመሆኑ ሀየ ባይ መንግስት ወይም የሃይማኖት አባት ማጣቱ የሚገርም ነው፡፡ በመጨረሻም ስለ ሰውየው ተነግሮ የሚያልቅ ስላልሆነ አጫፋሪዎችን ጨምሮ ልቦነ ይስጣችሁ ንስሃም ግቡ ቤተ ክርስቲያንን አታድሙዋት ፡፡
      መድሃኒት አለም እየሱስ ክርስቶስ ከነደዚህ አይነቶች አጨበርባሪዎች እኛንም ሆነ ቤተክርስቲያናችን ይጠብቅ!

  13. ሃይማኖት ርትእት December 3, 2013 at 4:48 am Reply

    ውድ የሐራ አዘጋጅ!
    መልእክቴን በማየትዎ እና በአስተየየት መድረክ ስፍራ በመስጠትዎ እጅግ አመሰግናለሁ፡፡ ግን ውጤት እፈልጋለሁ፡፡ እግኢአብሔር ያመልክትዎ እነ አቶ በጋሻው እና አቶ ያሬድ በበር ሳይሆን በአጥር ሾልከው ወደ ቅጽረ ቤተክርስቲያን እየገቡ ነው፡፡ አሁን የፊታችን ቅዳሜ የእርቅ ጉባኤ በሚል ሰበብ ሰተት ብለው ሊገቡ ነው፡፡ እንደሰማነው ከሆነ ደግሞ በአነርሱ ኑፋቄ ተደልለው ግን ሳያውቁ ተከትለዋቸው ከመንጋው ተለየተው የነበሩትን የዋህ ምእመናን ወደቤተክርስቲያን እንመልስ በሚል ሰበብ የገበጣ ጨዋታ አደራዳሪ ሆነው መቅረባቸው ነው፡፡
    እውን እነርሱ ለአቅመ አደራዳሪነት የሚበቁ ሆነው ነውን? ሰው ጠፋ እንዴ? ምክንያቱስ? የእነርሱ ጉዳይስ? የተያዘው ማስረጃስ? ከሚመለሱት ሰዎች መካከል በተንኮል የሰለጠኑ ላለመኖራቸው ምን ማረጋገጫ አለ? የእነርሱ ተከታይ ሆነው የነበሩትስ ወደ እናት ቤተክርስቲያን ተቀላለቀሉ እነርሱስ? ጡት የምንጠባ አደረጉን እንዴ?
    አነዚህ እና ሌሎችም ጥያቄዎች መብራራትም ምላሽ ማግኘትም አለባቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ ሐራውያን የሠራሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ቀኑ እጅግ ከመቅረቡ የተነሣ ፍጥነት ያሻል፡፡

  14. Anonymous December 3, 2013 at 6:28 am Reply

    the corrupted man has a lots of experience and linking we christian are feeling sham. he had a lots of shocking activities which are not expected from a religious leader. where are they so called “Mahibere Kidusan”??? where are “Synodos???” for your surprise he was using ihone tablet during the Tisge ceremony whole other prists where praying.

  15. Anonymous December 3, 2013 at 11:51 am Reply

    የሚግረም ነገር ልንገራችሁ ሰሞኑን ከጠቅላይ ቤተክነት ሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ኦዲት ለማድረግ የመጡ ሰዎችን ከሊቀጳጳሱ ቀጭን ትዛዝ ደረሳቸው ኦዲት ማድረግ የመትችሉት ከቅር ጊዜ ወዲህ ያለውን እንጂ የቀድሞውን ማድረግ አተችሉም ብለዋል፡፡ ከዚህ በፊት ተገልብጣ ጠብልሽጽአደጋ የደረሰባትን መኪና ያለ ጨረታ ለዘመዳቸው ስለሸጧት ይህ እንዳይታወቅባቸው መሆኑን ደርሰንበታል፡፡
    ከዚህ በተጨማሪ አቃማቸውን ለይተው ቢያሳውቁን በአንድ በኩል ሀይማኖተኛ መሰለው ስለሃይማኖት ተቆርቋሪ ሆነው አናያቸዋለን በሌላበኩል ደግሞ የተቃዋሚ ድርጅቶችን የመሬት ፖሊሲ በሃይማኖት አጀንዳ ስም ሲያንፀባርቁ ምን እንበላቸው?::
    ገብረ ኢየሱስ ጋር ያገናኛቸው ይህ አቋማቸው ይሆናል ብየ እገምታለሁ፡፡

  16. Anonymous December 3, 2013 at 4:02 pm Reply

    የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር ፍጹም ኃይማኖታዊ መሆን ሲገባው ከዚህ በተቃራኒው ያለምንም ተቆጣጣሪ ና ተው ባይ እንደፈለጉ የሚያዙት ና የሚናዙት አባ ቄርሎስ ከፈለጉ አይደለም መኪና ሌላም ሌላም ሊሸልሙት ይችላሉ ለምን ቢባል
    በቃለ ዓዋዲው መሰረት ሌሎቹ ሀገረስብከቶች የሀገረስብከት ሰበካ ጉባኤ ሲኖራቸው አባ ቄርሎስ ግን ይህንን
    አይፈቅዱም ምክንያቱም የሚፈጽሙት ግፍ ታዛቢ ስለሚያገኝ በአደባባይ ተጋልጦ በቆብ የተሸፈነው ማንነታቸው
    ስለሚጋለጥ ነው፡፡

    በብዙዎች ዘንድ ወግተው ከያዙ አይመለሱ
    እየተባለ እንደ ጸጋ የሚነገርላቸው ጳጳስ በጠላትነት ነክሰው የያዙአቸውን ሰዎችን ራሳቸው አልያም መሰል ባህሪ
    ያለውን አጋራቸውን በማስተባበር ስለሚያሳድዱ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ትዳር ና ቤተሰብ እንዲበተን ምክንያት
    መሆናቸው በስፋት ይነገራል ራሳቸው በአንድ ሀገረስብከት ያንድ ጎልማሳ የዕድሜ ዘመን ላስቆጠረ ጊዜ ሳይዛወሩ
    መቀመጣቸውን ዘንግተው የጠሉትን ሁሉ ከቤተሰቡ እየለዩ እንዲዛወር ማድረግ የበቀል መወጫ ብቸኛ መንገዳቸው ነው
    የቀረውም የቤተክህነት ሰራተኛ ይህ እጣ ፈንታ እንዳያጋጥመው ምንም ሳይተነፍስ የታዘዘውን ብቻ በመፈጸም ለጥ ሰጥ
    ብሎ አንዲገዛ ተደርጎአል ፡፡ ያልተረጋገጠ ወሬ በመቀበል ና ምላስን መሰረት ባደረገ
    አሉባልታ አርምጃ በመውሰድ የሚታወቁት እኝህ ሰው በፍጹም ማን አለብኝ ባይነታቸው በጥቅምት ወር በተካሄደው
    አጠቀላይ የመንበረ ፓትርያርክ ሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉ ከጠቅላይ ቤተክህነት በተጻፈ ደብዳቤ ጥሪ
    የተደረገላቸውን የሀገረስብከቱ ስብከተ ወንጌል ኃላፊን በመተው ና የጠቅላይ ቤተክህነቱን የስብሰባ ጥሪ ደብዳቤ
    ከቁምነገር ባለመቁጠር ራሳቸው የፈለጉትን አስከትለው በመሄዳቸው የስብከተ ወንጌል ኃላፊው/የቅድስት ሥላሴ
    መንፈሳዊ ኮሌጅ የዲግሪ ምሩቅ ናቸው / በግላቸው ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት በመሄድ ስብሰባው እንዲሳተፉ ጥሪ
    የተደረገላቸው መሆኑን በቦታቸው ሌላ ሰው ተተክቶ የመጣ መሆኑን በማስረዳት ስብሰባውን እንዲካፈሉ ሊቀ ማዕምራን
    ፈንታሁን ሙጬን አናግረው ከጳጳሱ የተሰጠው መልስ አናውቀውም በመሆኑ በዘበኛ ከጠቅላ ቤተክህነት ግቢ እንዲባረሩ
    ተደርጎ በጳጳሱ ትዕዛዝ ፍትህ መፈለጋቸው እንደወንጀል ተቆጥሮ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የተጻፈባቸው በመሆኑ
    በያዝነው ወር ከሥራቸው እንዲሰናበቱ ተደረጎአል ፡፡ ከአጼው ዘመን ጀምሮ የሙጃ ማርያም ቤተክርስቲያን ሀብት
    የሆነ በቤተክርስቲያኑ የተቀመጠ 430 ጠገራ ብር የእጅ መስቀል ማሰሪያ በሚል ሰበብ ተወስዶ ተቀምተው የቀሩ
    በመሆናቸው ለመስቀል ማሰሪያው 5 ጠገራ ብር በቂ ነው ያለአግባብ የተወሰደው የቤተክርስቲያነቱ ኃብት አባቶቻችን
    ያስቀመጡልን ቅርስ በመሆኑ ይመለስልን በማለት የህዝቡ ተወካዮች ቢጠይቁም በር በላያቸው ላይ በመዝጋት ተባረዋል
    ይህንን የመሰለ የአመጽ ተግባር እየፈጸሙ ያሉት ጳጳስ የሚቆጣጠራቸው አካል ስሌለለ ለተዛወሩት የደብር አስተዳዳሪ
    መኪና ገዝተው መሸለማቸውን ሊየስቆም የሚችል አካል ስለመኖሩ እንጠራጠራለን ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አንድ አገልጋይ ‹‹ክብር አልሰጠኸኝም›› በሚል ከቆቦ ወደ ዓይና ቡግና ልከውት ልጁ ታሞ ማስታመም ሳይችል ለቀብር ተጠርቷል፡፡

    እንኪያስ በእርግና ላይ በሰው
    ድጋፍ ካልሆነ በስተቀር መንቀሳቀስ የማይችሉትን ጳጳስ በጡረታ ማግለል ተገቢ ሆኖ ሳለ እንደፈለጉ እንዲፈልጡ ና
    እንዲቆርጡ መተዋቸው ውሎ አድሮ ከቢተ ክርስቲያኒቱ እስከመለየት ድረስ አደጋ የሚያስከትል መሆኑ ይመለከተኛል የሚል
    ሁሉ ሊየስብበት ይገባል እንላለን፡፡

    • Anonymous December 4, 2013 at 8:19 am Reply

      Sorry about our Archbishop what he does? Because I know very well previously, he was very genius, kind and committed on religious duties and grateful father. But now, I think he missed all things. Why he missed? May be he intoxicated with money like his best friend Aba G/eyesus. Please come back to the normal behavior.

  17. የሰለቸው December 4, 2013 at 9:53 am Reply

    እናንት ለአፎቻችሁ ለከት የሌላችሁ የስድብ አፍ የተሰጣችሁ ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ አንደበታችሁን እንዲፈውስላችሁ ሊጸለይላችሁ ይገባል፡፡ ራሳችሁ እንኳን ያልተገለጠ ስንት ርኩሰት አድርጋችኋል፡፡ ከባቴ አበሳ መድኃኔዓለም ሸፈነላችሁ እንጂ! እባካችሁ አባቶችን አትዝለፉ፣ አታዋርዱ፣ ስድባችሁን የክርስትና ወግ አታስመስሉት፡፡ አቅም ካላችሁ ጸልዩ ያለበለዚያ እንደ አባ ቄርሎስ የመሰሉ አባቶችን በመሳደብ ሥራ ፈታችሁ ትቀራላችሁ፡፡ እስኪ ከእናንት መካከል ኃጢአት የሌለበት ድንጋይ አንስቶ ይውገራት ያለውን አስቡ፡፡ ስድባችሁ ሰለቸን፡፡ ይህ መነኮስ ስሙ በተነሣ ቁጥር አባ ቄርሎስን የመደብደብ ተልእኮ ምን የሚሉት ነው፡፡ ጥቡዕ ሐዋርያ ፊት ለፊት ለቤተክርስቲያን ዘብ ቆመው ዋሉ ተብሎ በዚሁ ብሎግ የተወደሱትን ሺ ጊዜ ብትሳደቡ ስድቡ ወደ እናንተ ቢመለስ እንጂ የሚሰማችሁ የለም፡፡ እንዲያውም ሰለቻችሁን፡፡

  18. የሰለቸው December 4, 2013 at 9:54 am Reply

    እጅ እጅ አላችሁ! የሚል ጨምሩልኝ

  19. Anonymous December 4, 2013 at 3:14 pm Reply

    It is not appropriate to reward car for monk except giving some spiritual things and prayer.

  20. Anonymous December 5, 2013 at 5:25 pm Reply

    ሃራ ተዋህዶች፣ አውነቱን ና ሃቁን በመዘገባችሁ ልትመሰገኑ ይገባችሁአል፡፡ አሰለቻችሁን በሚል ርዕስ የጻፉትን ለአፋቸው ለከት የሌለውን አስተያየት ሰጭ እና የአባ ቄርሎስን ጠበቃ ጉንጭ አልፋ ልንላቸው እንወዳለን፡፡ ከእኝህን ግለሰብ ውቅያኖስ የሚያክል ጉድ ሀጢአትና ወንጀል ውስጥ አስተያየት ሰጭው በጣት ቀንጨብ አድርገው ማቅረባቸው ነው ገና ያልተናካ ብዙ እጅግ ብዙ ጉድ አለ፡፡

    ጥቡዕ ሐዋርያ አልካቸው ወሬኛ ነህ ወጣቱ ሰባኪ መምህር አስነቀ አለሙ የየጁ ተወላጅ በመሆኑ የተፈጸመበት ግፍ ውሸት ነው??? ወይስ የሙጃ ማርያም ጠገራ ብር በጳጳሱ አልተዘረፈም ነው??? ምንድነው ሃሰቱ ያስረዱን በጥላቻ የተነከሱት የወረዳ ቤተ ክህነት ሊቀነ ካህናቶች ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ሥራን ሳሆን ጥላቻን መሰረት ባደረገ አልተዛወሩም ወይ? እውነተ ወይስ ሀሰት?

    ለነገሩ ይህ የክርስትና ጉዞ በመሆኑ የፍረዱ ባልተቤት የአንተን መሰል ጭፍን ደጋፊ ምስክርነት የማይፈልግ ጳጳሱ የሰሩትን ና እየሰሩት ያለውን ጽድቅም ሆነ ግፍ ና ኃጢአት የሚያውቅ ኃያሉ እግዚአብሄር በመሆኑ አሁንም ሣይዘገይ ፍረዱን ይስጥ እንላለን፡፡

  21. Anonymous December 5, 2013 at 5:25 pm Reply

  22. Anonymous December 6, 2013 at 7:36 am Reply

    አሁን በግልጽ ንስሐ ልግባ ለገብረ ኢየሱስ ልጆች ማሳደጊያ ገንዘብ ታዝዤ ስልክ የኖሩኩ እኔ ነኝ ስሜን የማታወጡ ከሆነ የላኩባቸውን ደረሰኞች እስካን አድርጌ በኢሜላችሁ ልላክላችሁ ግን አደራ ስሜን የምታወጡብኝ ከሆነ አባ ቄርሎስ አሁንም ቀኝ እጁ ስለሆኑ ይበቀሉኛን አደራ አደራ፡፡

  23. Anonymous December 6, 2013 at 10:49 am Reply

    ማስተካከያ የተገለበጠች መኪና ሳትሆን ከዚህ በፊት በልማት ኮሚሽን በኩል ሰሜን ወሎ ውስጥ ተከስቶ በነበረው ርሃብ ምክንያት የተላከው የዕርዳታ እና ዘይት መያዢያ በሚል የተሠበሰበው ከረጢት የተገዛች ባለ 4 በር ቶዮታ መኪና፡፡ ይህቺን መኪና አባ ቅርሎስ ከእኔ ጋር መስዋዕትነት የተቀበለች ሰማዕት መኪና እያሉ የሚጠሯት ሲሆን መኪናዋም የተመታቺበት ምክንያት አቡነ ቄርሎስ ስለ ሰበካ ጉባኤ ይግባ ሕዝቡን እና ካህናቱን በመዋሸታቸው የደረሰባቸው ውርደተ ነው፡፡ እንግዲህ ይህችን መኪና ነው አባ ቄርሎስ የለምንም ጫረታ የሀገረስብከቱን ሠራተኞች በጉልበት አስገድደው ቃለጉበኤ ያዙ ተብለው በዚህ ብቻ ለቅርብ ወዳጃቸው በ 40000(አርባ ሺ ብር)ለቅርብ ወዳጃቸው የተሸጠችው፡፡ የሚገርመው ነገር ብሩም ለሀገረ ስብከቱ ካዝና ያልገባ ሲሆን ጳጳሱ በግል አካውንታቸው እንደ አስገቡት የሂሳብ ሰራተኛ በነበርኩበት ዘመን አረጋግጫለሁ፡፡

  24. Anonymous December 8, 2013 at 9:33 am Reply

    በእውነቱ ልንገራችሁ፡- አባ ቄርሎስን የማውቃቸው በበአላት ላይ ሲያስተምሩ ነው:: የስነ ቃል ምሩቅ በመሆኔም የሚደርጉትን ንግግር ስመዝን ጥሩ ተናጋሪ መሆናቸውን ለመገንዘብ ጊዜ አልወሰደብኝም:: በሚናገሩት ልክ ምግባራቸውም እንደዚያው ነው የሚል ግምት ስለነበረኝ በሚያስተምሩበት ቦታ ሁሉ እገኛለሁ:: ከተወሰኑ ሰዎችም መነኩሴ ሆነው ሳለ ለሥጋ ዘመዶቻቸውና ለጎጣቸው ሰዎች የሚያዳሉ ሥራ የሚስይዙ መሆናቸው እሰማ ነበር:: በተዋበ ቃለት የሚደርጉትን ስብከት ወይም ንግግር ማዳመጥ ብቻ ሳይሆን የኑሮ መመሪያም ጭምር አድርጊ በመያዜ የሚነገርባቸውን ሁሉ አሉባልታ አድርጌ እወስድ ነበር::

    ባሰላፍነው የክረምት ወራት የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ካህናት የቤተ ክርስቲያኑ አለቃ ኑፋቄ እያራመደ በማግኘታቸው ከቦታው እንዲነሳለቸው ካልሆነ ግን ከዚህ ግለሰብ ጋር አናገለግለም ብለው አም በመውሰዳቸው ምክንያት ጳጳሱ በቀለኛ በመሆናቸው ጠቅላላ የደብሩን ካህናት ወደተለያዩ ቤተ ክርስቲያኖች እንዲዛወሩ በማድረግ በወሰዱት እርምጃ ህዘቡ ከዳር አስከዳር በመነቃነቁ በሀገረ ስብከቱ ጸሐፊ ጥረት ዘውውሩ መቆሙን ስረዳ ስለ ጳጳሱ የሚነገረው ሁሉ እውነት መሆኑን በማረጋገጤ እጅግ አዘኜአለሁ::

    ግን ለምንደን ነው በዚህ ወደ ሞት በሚጠሩበት የዕድሜ ዘመናቸው ሁሉም ይቅርብኝ ብለው ገዳም የማይገቡት ???????????

  25. Anonymous December 9, 2013 at 9:44 am Reply

    ወንድሜ የወልዲያ መድኃኔዓለምን መላ ካህናት ዝውውር በጳጳሱ ቀጭን ትዕዛዝ በሀገረ ሥብከቱ ሥራ አስኪያጅ ፊርማ ወጭ ሆኖ ለተወሰኑ ካህናት በየቀኑ ከታደለ በኆላ ሕዝቡ በቁጣ በመነሳቱና ዝውውሩ መሰረዙን እኔም ምስክር ነኝ::

    የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ የራሱን ጥቅም ብቻ የሚያይ፣ አድርግ የተባለውን ብቻ የሚፈጽም ሰው በመሆኑ ጳጳሱ የሚበቀሉትን ሠራተኛ በፊርማው ወጭ እያደረገ ስንቱን የቤተሰብ ኃላፊዎች ከቤተሰቦቻቸው እንደለየ ምስክሮች ነን:: በያዘው የስልጣን ወንበር ለመቆየትም ይህንኑ ተግባሩን እየፈጸመ መኖር ይፈልጋል:: ስለመብቱ ህጋዊ ጥያቄ ያቀረበውን የሀገረ ስብከቱን ሥብከተ ወንጌል ኃላፊ ሁለት ገጽ ሙሉ ማስጠንቀቂያ ጽፎ ተወደጁን የወንጌል መምህር አስናቀ ዓለሙ ሥራውን በፈቃዱ በማመልከቻ ለቆ የተረከበውን ንብረት አስረክቦ መሄዱን እያወቀ ይህው ሥራ አስኪያጅ የጥሪ ማስታወቂያ አውጥቶበታል::

    እንግዲህ እንዲህ አይነቶቹን ኃላፊዎች መድበው ነው ጳጳሱ ሀገረ ስብከቱን መጫዎቻ ያደረጉት:: በየትኛው አሰራር ነው ማመልከቻ ጽፎ ንብርት አስረክቦ የተሰናበተ ሠራተኛ የጥሪ ማስታዎቂያ የሚወጣበት?

    ሌላም ጉድ አለ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ሀገረ ስብከቶች ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ለብቻው ተለይቶ የጉዞ ፈትሃት የተከለከለበት፣ በጽጌ ጾም በጠዋት የሚቀደስብት ለክርስትናና ለፍትሃት ለካህንቱ የሚቀርበው እህልና ውሃ ተከልክሎ በገንዘብ ክፍያ እንዲሆን የተወሰነበት ለምን የሚል ጥያቄ ሲቀርብም ‹‹ለካህናቱ ገንዘቡ ደመዎዘቸው ላይ ተጨምሮ ቢከፈላቸው ይሻላል›› የሚል መልስ ሰጥተው ነገር ግን ለክርስትናና ለፍትሃት የሚከፈለውን ገንዘብ በፐርሰንት እየቆረጡ የሚወሰድበት እህልና ውሃ እንደቀድሞው ቢዘጋጅ ኖሮ በፐርሰንት ሊወሰድ ነበር ማለት ነው::

    ይባስ ብለው ከቅርብ ጊዚአት ወዲህ ለክርስትናና ለፍትሃት ይከፈል የነበረውን ገንዘብ መጠን ህዝቡን ሳያወያዩና ይሁንታ ሳያገኙ ጨምረው እያስከፈሉ ነው፡፡ ምንድን ነው ይህ ሁሉ ግፍ ሰሜን ወሎ ላይ ብቻ እምነታችንን እስክንጠራጠር ድረስ እየተፈጸመ ያለው? ሰው ዝም ብሎ ሰለተመለከተ ብቻ ንቀት ነው?

    የሚያሳዝነው ጉዳይ እንዲህ አይነት መልዕክት ሲተላለፍ ስህተታቸውን እንደማረም ማነው የጻፈው የሚል ጥያቄ ማንሳት ነው የሚቀላቸው፡፡ ይህ አያዋጣም እውንት ወይስ ሀሰት ማለት ነው የሚገባው፡፡ ተወደደም ተጠላም እየተሰራ ያለውን በደል ህዝቡ እያወቀ የመጣ መሆኑን መረዳት ነው የሚገባው፡፡

  26. Anonymous December 12, 2013 at 8:12 am Reply

    አንድ ነገር ታየኝ እውነቴን ነው የምላችሁ የገና ላሊበላ ለሚመጣው ሰው ሁሉ በአቡነቄርሎስ ላይ የተሰጡትን አስተያየቶች በሙሉ
    ኮፒ አድርጌ በራሴ ወጭ አሰራጫለሁ ደግሞ ይገርማሉ ቆመው ለዚያ ወንበዴ መኪና ሸልሙልኝ ብለው ሲለምኑ አለማፈራቸው፡፡
    ከዚህ ቡኋላ የማያርፉ ከሆነ ፊርማችን አሰባስበን ጳጳስ ይመደብልን ብለን ወደ ፓትርያርኩ መሄዳችን አይቀሬ ነው ቢያስቡበት ይበጃል ፡፡

  27. Anonymous December 13, 2013 at 6:57 pm Reply

    የያዙትን መንፈሳዊ ስልጣን በጠበንጃ አፈሙዝ እንደሚገዛ አምባገነን መሪ ሲጠቀሙበት የቆዩት የአባ ቄርሎስ ጉድ ላሊበላ ከተማ ላይ በነረው ስብሰባ ተጋልጦ መባረራቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም

    ከዚህ በፊት መኪናቸው ተደብድቦ ማምለጣቸው ይታወሳል አሁን ደግሞ ይህ አምባገነን ሰው ከውስጥ ወደ ውጭ እንጅ ከውጭ ወደ ውስጥ በማያሳይ ፕልስቲክ የመኪናቸውን መስታዎት አሳሽገው ላሊበላ ሲመጡ ፍጹም የለየላቸው አምባገነን ባልስጣን የመሆን ፍላጎታቸው በአደባባይ ገሀድ መውጣቱን ስንገነዘብ ከዚህ ሰው ጋር የምናደርገው ስብሰባ ዋጋቢስ መሆኑኑን ተረድተናል

    እግዚአብሄር ያሳያችሁ ቆብ ለአጠለቀ መነኩሴ ነኝ ባይ ከማን ለመሰወር ነው የመኪናውን መስታዎት በማያሳይ ፕላስቲክ መሸፈኑ ምንችግር አለ
    እንጨት ሽጣ ከጉሮሮዋ ነጥቃ ይቅርብኝ ለቤተክርስቲያን አስራት የምተሰጠው የደሀዋ ሳንቲም ሳይቀር ስልተጠራቀመ የመኪና መስተዎት ቀርቶ ቤታቸውን በወርቅ ቢያስለብጡ ይቻላቸዋል ይባስ የሚገርመው ደግሞ ተከትሎ የመጣው ሥራ አስኪያጃቸው አባ ቄርሎስ ያሉትን ካልፈጸማችሁ ትረገማላችሁ ብሎ በሙሉ አፉ ደፍሮ መናገሩ ነው

    እኛ እኮ እርግማናችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የታጠበልን የቅዱስ ላሊበላ ልጆችነን የምታስፈራራውን አስፈራራ ማን ረጋሚ ማን ተረጋሚ የምታሳዝን ፍጡር ነህ አንተ ምን ታደርግ የአካባቢአቸው ሰው በመሆንህ ዋና ጸሀፊው እየለፋ ችሎታ ስሌለለህ ተቀምጠህ ትበላ የለም አንተ ምንቸገረህ ለማንኛውም የስብሰባውን ይዘት ና አባ ቄርሎስ እየሰሩ ያሉትን ጉድ ለገና በዓል ለሚሰበሰበው ምዕመን በሙሉ አባዝተን እናድላለን

    አባ ቄርሎስ ጡረታዎን ጠይቀው ቀሪ ዘመነዎን አስከዛሬ ድረስ ስለሰሩት ኃጢአት ቢያለቅሱ ይሻለዎታል እኛ እንደ አክሱም ማርያም ለራሳችን ጳጳስ እንፈልጋን ይብቃዎት ይብቃዎት ይብቃዎት .፡፡

  28. Anonymous December 14, 2013 at 5:24 pm Reply

    የተንኮለኛውን ና የክፉውን የአባ ቄርሎስን ጉድ ላሊበላ ያለችሁ ወንድሞቻችን ለአደባባይ ስለ አበቃችሁት ልትመሰገኑ ይገባል ለካስ የክፉ ሰው ሥራ መገለጡ አይቀርም ተመስገን ነው የሚያሰኘው

    ሰውየው በተፈጥሮ አንደበተ ርቱዕ በመሆናቸው ሰው ሁል ንግግራቸውን እያዳመጠ ፍጹም መንፈሳዊ መሪ አድርጎ ስለሚቆጥራቸው አንድም ቀን ስለክፋታቸው ተነግሮ አያውቅም አልፎ አልፎ የስጋ ዘመዶቻቸውንና የአገራቸውን ሰዎች ስራ መቅጠራቸው ከናሚነገር በቀር ስለ ሌላው ጉዳቸው ተነግሮ አያውቅም ነበር የስንቱን ቤትና ትዳር አንደበተኑ እነ አለቃ መንበሩ ምስክር ናቸው

    ይህ ሰውየ እግዚአብሄርን የማይፈሩ በመሆናቸው ጡረታ ልውጣ ብለው የሚጠይቁም አይደሉም ለምን ቢባል በሀገረ ስብከቱ ያስጠጉአቸው ዘመዶቻቸው እጣ ፈንታ ስለሚያሳስባቸው ነው እርሳቸው በሰው ላይ የሚፈጽሙትን ግፍ ስለሚያውቁ ስለዘመዶቻቸው በወንበራቸው ላይ ሞተው መገኘትን ነው የሚመርጡት አይ መንፈሳዊ መሪ ሰው ሁሉ እንደጠላቸው አያውቁም ቢውያቁም ግድየላቸውም እንዲህ ነው ጻድቅ፡፡

Leave a comment