በደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት በሥራ አስኪያጁ ላይ የተላለፈውን የማሰናበት ውሳኔ የተቃወሙ መላው የጽ/ቤት ሠራተኞች ሥራ አቆሙ፤ ሀ/ስብከቱ ‹‹የመንበረ ጵጵስና ልዩ ጽ/ቤት›› እስከ ማቋቋም በደረሱ ሙሰኞች እና ጠንቋዮች እየታወከ ነው

  • የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሥራ አስኪያጁ ላይ የተላለፈውን የስንብት ውሳኔ ውድቅ በማድረግ ወደ ሓላፊነታቸው እንዲመለሱ ለሊቀ ጳጳሱ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ ይኹንና ትእዛዙ በሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ ተፈጻሚ ባለመኾኑ የሀ/ስብከቱን ሥራ በማቆም የተወሰደው የመላው ሠራተኛ ርምጃ፣ በአሜሪካ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋራ በሐዋርያዊ ጉብኝት ላይ የሚገኙትን የብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስን መመለስ እየተጠባበቀ ነው፡፡
  • ራሳቸውን ‹‹የሊቀ ጳጳሱ የግል አማካሪ›› ብለው የሠየሙት ሙሰኞቹና ጠንቋዮቹ በሀ/ስብከቱና በሊቀ ጳጳሱ ስም ባስቀረፁት ማኅተምና ቲተር ጽ/ቤቱ የማያውቃቸውን ሕገ ወጥ ደብዳቤዎች ያዘጋጃሉ፡፡
  • ሥራ አስኪያጁ ከሓላፊነታቸው መሰናበታቸው የተገለጸው፣ ሊቀ ጳጳሱን የከበቡት ‹‹የሊቀ ጳጳሱ የግል አማካሪ›› ነን ባዮች በሐሰተኛ ማኅተምና ቲተር ባዘጋጁት ደብዳቤ ነው፡፡
  • በሀ/ስብከቱ በስምንት ዓመት ውስጥ 13 ሥራ አስኪያጆች ከሓላፊነታቸው መሰናበታቸው ሙሰኞች እና ጠንቋዮች በሊቀ ጳጳሱ ዙሪያ እየፈጠሩት ለሚገኙት ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳያ ኾኗል፡፡
Participants of the 32nd SGGA 02

አላግባብ ከሓላፊነታቸው የተሰናበቱት የደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ አፈ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌትነት በመ/ፓ/አጠ/ሰ/መ/ጉባኤ ፴፪ኛው ዓመታዊ ስብሰባ ወቅት በተሳትፎ ላይ

  • ሥራ አስኪያጁ÷ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶችን ድጋፍ በማስተባበር በሚያዘጇቸው የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች፣ ከሌሎች አህጉረ ስብከት ጋራ በሚካሄዱ የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብሮች፣ በወቅታዊ ግምገማዎችና በግምገማዎቹ ላይ በተመሠረቱ የማስተካከያ ርምጃዎች በሀ/ስብከቱና በዐሥራ ሁለቱም የወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች የዘለቀ መልካም አስተዳደር በማስፈን፣ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታዎች የባለቤትነት መብት በሕግ አግባብ በፍትሕ አካል በማስከበር ሞያዊ ጥረታቸው ሀ/ስብከቱን በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ‹‹የአህጉረ ስብከት የሥራ ብቃት ዓመታዊ ውድድር›› ላይ ተሸላሚ በማድረግ ይታወቃሉ፡፡
  • በሕግ ዲፕሎማ ያላቸውና ለአንድ ዓመት ከዘጠኝ ወራት በሀ/ስብከቱ በሥራ አስኪያጅነት ሓላፊነት የቆዩት አፈ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌትነት፣ የመሬት ይዞታቸውን በሕገ ወጥ መንገድ የተነጠቁ የ12 አብያተ ክርስቲያንን የባለቤትነት መብቶች እንደጠበቃ በተለያዩ ፍ/ቤቶች በራሳቸው እየተሟገቱ አስመልሰዋል፡፡
  • ከእኒህም መካከል÷ በፎገራ ወረዳ መነጉዞር ኢየሱስ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ የታቀደበትና በሀገር በቀል ደን የተሸፈነ አራት ሄክታር መሬት፣ በሊቦ ከምከም የዋሻ ተክለ ሃይማኖት አራት ሄክታር መሬት፣ በደብረ ታቦር ፀጉር ኢየሱስ 2.5 ሄ/ር መሬት፣ በፋርጣ ወረዳ የሞክሼ መርቆሬዎስ 2 ሄ/ር መሬት እና በስምና ጊዮርጊስ አንድ ሄክታር መሬት እንዲሁም በደብረ ታቦር እና ላይ ጋይንት ከተሞች ስፋታቸው 7012 ካሬ ሜትር የኾኑ የሕፃናት ማሳደጊያዎች የይዞታ መብቶች መረጋገጥ ይገኙበታል፡፡ የሀ/ስብከቱ የ፳፻፭ ዓ.ም. ዓመታዊ ሪፖርት እንደሚያሳየው 623 አብያተ ክርስቲያን የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
  • በሥራ አስኪያጁ ላይ የተወሰደውን አላግባብ ከሓላፊነት የማሰናበት ርምጃ በመቃወም የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ሠራተኞች ከኅዳር ፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም አንሥቶ ሥራ በማቆማቸው ሳቢያ ከፍተኛ የባለጉዳዮች መጉላላት እየታየ ነው፡፡ በሥራ እንቅሰቃሴው እና የሠራተኞች ቁጥጥሩ ቀናት ይፈጁ የነበሩ ሥራዎችን በሰዓታት ያሳጠረው ሀ/ስብከቱ በጽ/ቤት ደረጃ የቅሬታ ሰሚ ሠራተኛ በመመደቡ ክፍተት የሚታይባቸው አስተዳደራዊ ውሳኔዎችና አሠራሮች በቅሬታ መልክ በድጋሚ ቀርበው አፋጣኝ መፍትሔ ያገኛሉ፡፡
  • የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ራሳቸውን ‹‹የሊቀ ጳጳሱ የግል አማካሪ›› ብለው በሠየሙና ለሥራ አስኪያጁ አላግባብ መታገድ ምክንያት ከኾኑ ግለሰቦች ውስጥ በሦስቱ ላይ ክሥ መሥርተዋል፡፡ ከእነርሱም መካከል በታች ጋይንት እና አዲስ ዘመን ከተሞች ሁለት ጊዜ በሥርዐተ ተክሊል ጋብቻ የፈጸመው የወረታ ወረዳ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል ሓላፊ መ/ር ዕንባቆም ዘርዐ ዳዊት ዋነኛው ሲኾን ካህናትንና ሊቃውንትን በመከፋፈልና በማጋጨት፣ የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤያትን በጣልቃ ገብነት በመበጥበጥና ከሰንበት ት/ቤቶች ጋራ በማጋጨት በሚገባ ይታወቃል፡፡
  • ሌላው አዋኪ፣ በፎገራ ወረዳ የደራ ቅ/ጊዮርጊስ አስተዳዳሪው መልአከ ሰላም አፈ ወርቅ ወንድማገኝ የሚባሉ ሲኾን በመጋቢት ወር ፳፻፭ ዓ.ም. ጀምሮ በከፍተኛ የገንዘብ ማጭበርበር ተከሠው የታሰሩና ከሓላፊነታቸው የታገዱ ናቸው፡፡ መሪጌታ መፍቀሬ ሰብእ መኰንን እና መሪጌታ ኅሩይ ደመወዝ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በደራ ወረዳ አንበሳሜ ከተማ እና በንፋስ መውጫ ቅድስት ሥላሴ በጥንቆላ ሥራ የሚተዳደሩ እንደኾኑ ተነግሯል፡፡
  • በሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያ ላይ የተላለፈው የማሰናበት ርምጃ አግባብነት የሌለው መኾኑን በመግለጽ ለሁለት ዓመታት ያህል ወደቆዩበት ሓላፊነታቸው እንዲመለሱ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ያስተላለፈውን ትእዛዝ ባለመቀበል ሁለተኛ የማሰናበት ደብዳቤ የጻፉት የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ÷ በአማካሪ ነን ባይ ነገረ ሠሪዎች ላይ እንዲያውቁባቸውና ሀ/ስብከቱን ‹‹መቋጫ ከሌለው መካሠሥና ከፋ ብጥብጥ›› እንዲታደጉት የሀ/ስብከቱ አካላት በመምከር ላይ ናቸው፡
  • ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በአንድ መልእክታቸው፣ ‹‹ሐላፊነት፣ ሐቀኝነትና ተጠያቂነት የተሞላበት መልካም አስተዳደር ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እስከ መንበረ ፓትርያርክ ድረስ እንዲሰፍን ማድረግ ተገቢነቱ አያጠያይቅም፡፡ መልካም አስተዳደር ከሌለ ሁሉም ነገር ከንቱ እንደኾነ እናምናለን›› እንዳሉት፣ በሥራ አስኪያጅነት በሚመሩት ሀ/ስብከት የመልካም አስተዳደር አብነት እንደኾኑ የሚነገርላቸው እንደ አፈ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌትነት ያሉ ሓላፊዎች በተቋማዊ ለውጥ አመራራቸው ይጎለብቱ ዘንድ ዕድል ሊሰጣቸውና አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡
  • ሀ/ስብከቱ÷ ባለፈው ዓመት መነሻቸውን አዲስ አበባ ባደረጉና ራሳቸውን ደቂቀ ኤልያስ በሚል ሲቀስጡ የተገኙ ሁለት ዲያቆናት ነን ባይ ግለሰቦችን ለፍትሕ አካል አቅርቦና እስከ ክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ ተከራክሮ በስድስት ወራት እስራት እንዳስቀጣው ሁሉ በቡድን ተደራጅተው አስተዳደሩንና መንፈሳዊ አገልግሎቱን በሚያውኩት ሙሰኞች እና ጠንቋዮች ላይም የሚወስደውን ርምጃ አጠናክሮ በመቀጠል ከመዋቅሩ ማጽዳት ይጠበቅበታል፡፡
  • የደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት የአራቱ የምስክር ጉባኤ ቤቶች መገኛ እንደመኾኑ መጠን የበርካታ ቋሚ መንፈሳዊ ት/ቤቶችና የአብነት ት/ቤቶች ምንጭ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ብዛታቸው 7,167 የኾነ የንባብ፣ የቅዳሴ፣ የቅኔ፣ የዝማሬና መዋስዕት፣ የድጓ፣ አቋቋምና የመጻሕፍት መምህራን እንዲሁም ከ27,928 በላይ ደቀ መዛሙርት እንደሚገኙበት የሀ/ስብከቱ ሪፖርት ያስረዳል፡፡ እኒህን የአብነት መምህራንና ደቀ መዛሙርት ለመደጎም በገቢ ምንጭነት የሚያገለግል ባለአራት ፎቅ ሁለገብ ሕንፃ በደብረ ታቦር ከተማ ለመገንባት ዲዛየኑ አልቆ፣ የመሠረት ደንጊያው ተጥሎ ወደ ግንባታ ሥራው በመግባት ላይ ይገኛል፡፡ የድጓ ምስክር የሚገኝበት የቅድስት ቤተ ልሔም ጉባኤ ቤት እና ሙዝየም በብፁዕ ሊቀ ጳጳ አቡነ እንድርያስ የቅርብ ክትትልና በማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናት መርጃና ማቋቋሚያ ድጋፍ ለፍጻሜ መብቃቱ ይታወሳል፡፡

24 thoughts on “በደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት በሥራ አስኪያጁ ላይ የተላለፈውን የማሰናበት ውሳኔ የተቃወሙ መላው የጽ/ቤት ሠራተኞች ሥራ አቆሙ፤ ሀ/ስብከቱ ‹‹የመንበረ ጵጵስና ልዩ ጽ/ቤት›› እስከ ማቋቋም በደረሱ ሙሰኞች እና ጠንቋዮች እየታወከ ነው

  1. Anonymous November 17, 2013 at 11:28 pm Reply

    it is sham. as we know, his grace Abune Endriyas and Mahber have been working to gather for a long time and both of them stand against the truth. so what happened now:?
    who is አፈ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌትነት? and who is the reporter of this news? I think the answer is simple. The reporter of the is news is mahiber kindusan and aba Gebre Sllassie is one of the key supporters of mahiber kidusan. “ሙሰኞች እና ጠንቋዮች” my goodness! who are they? how do the association knows about them? if they are? why the association didn’t not say anything till now? anyway this is sham on them

  2. kk November 18, 2013 at 6:31 am Reply

    dear Hara Tewahdo, I always visit your blog to get updated on issues related with our church. Thanks for the information you supply us, but, please do not use unnecessary words like above to mention some people which you think are not right. “ሙሰኞች እና ጠንቋዮች” ….. This kind of expression is not good for the readers and may reduce the trust we have for your information. Thank you!!!

  3. Anonymous November 18, 2013 at 7:58 am Reply

    WESHETAMOCH

  4. Anonymous November 18, 2013 at 8:05 am Reply

    O! We know Enibakom , he is the right hand and the agent of Tehadiso Protestants. I think Abune endiriyas may not know his mission of challenging and disturbing the churches. Belive me he is relay protestant.

  5. Anonymous November 18, 2013 at 9:38 am Reply

    እናንተ ሐራ ተዋሕዶ ለምንድን ነዉ እንዲህ ያለ የማይረባ ነገር የምትዘግቡት ገብረ ሥላሴ እኮ መነኩሴ አይደለም የሚሠራዉን ሁሉ እናዉቃለን አንድ አቡነ እንድርያስ ተገኝተዉ ይሕን ያክል ገብረ ሥላሴ ሳይሆን ገብረ ሰይጣን ነዉ ጮሌ አፍ ስላለዉ ብቻ ስለሚያስመስል ነዉ የሚሠራዉን ሁሉ እኛ ለጠቅላይ ቤተ ክሕነት እናቀርበዋለን. . .የጻፈዉን ሜሴጅ እንዳለ በሙሉ ይዘነዋል

  6. Anonymous November 18, 2013 at 10:13 am Reply

    ገብረ ሥላሴ. . .? ለማይረባ ሰዉ ለምን ቤተ ክርስቲያን ትረበሻለች ሀ ቢሉት ሁ የማይል አፈ ጮሌ

  7. Anonymous November 18, 2013 at 11:41 am Reply

    How do you Know “the reportor is mahiber kidusan”
    Who is mahiber kidusan???????????Do you know about mahiber kidusan????????

  8. Anonymous November 18, 2013 at 1:31 pm Reply

    my friend maybe Aba Gebresllasie is a hard worker Monk and he has a great vision for the church. the problem of Aba Geresilasie is unknowing the enemy of our church which is the association ( Mahbere Kidusan) he works with his enemy Mk and supports them for a long time. as we know, Aba Gebreslasie a creative and clever person, so this is my advice to him!! Dear Aba G. keep going with it, fight against the enemy. You understand now who your enemy is. I am sure. the Head Office of the Ethiopian Orthodox Tewahdo is with you. most of us really know about the bishop and what the bishop Endriyas has been doing . yes. he knows the word of God but he does not abide by it. he does not have enough faith.
    may the blessing of the Almighty God be unto you.

  9. Anonymous November 18, 2013 at 3:26 pm Reply

    The decision made by Abune Enderyas is not right. It is known that Aba Gebere Sellase is a young guy who do have problems. But I found no problem with his religion. He is fighting with TEHADISO groups, not only in South Gondar but also in some other places like Gondar and Bahir dar.

    I am not denying that he does have some problems related to canonical issues (personally) but he is devoted to his church. He himself even believe that he is not a good monk (like those who are living saints in monasteries), but wants to be scarified to his church.

    What I want to say about Enbakom is different. He is a Tehadiso memeber. I know him very well. While he was in Addis Ababa St.Paul spiritual school, he has been attending “tekuando” training. He used to say that he graduated from St.Trininty college at Addis abab. In addition to this he mystify for the people of Addis Zemen that he went to Korea and South Africa for he scored excellent grade while he was in the college.

    Finally we found that he is a grade four student at elementary school. But he vowed to his “wife”, now divorced him, that he completed grade 12. Finally she found him attending elementary school and decided to divorce. In addition to this, Dera Christians, he married a woman in South Gondar, with vow at church. Teklil, two times?

    To conclude my ideas, the two guys are not comparable. Aba Gebre Sellasie is a devoted manager of the diocese. What he needs is support from fathers to improve his spiritual life. As his status in spiritual life moves forward, there shall be further advices and prayers to him so that he could improve and stand for the church.

  10. Anonymous November 18, 2013 at 7:18 pm Reply

    በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለውን ህጋዊ አሰራር በቂ የአስተዳደር ትምህርት ሣይኖራቸው በጸሎት እና በምህላ ተወስነው መኖር ሲገባቸው ጳጳሳቱ በወንጌል የተጻፈውን ህግ በመጣስ ምለስኛና ሰላይ በማስቀመጥ ዘመዶቻቸውንና የትውልድ ጎጣቸውን ሰዎች ቀጥረው በዙሪያቸው በማስቀመጥ የንጹሀኑን የቤተ ክህነት ሰራተኛ ከነቤተሰቡ ኑሮውን እያመሳቀሉ ያሉ ሰለ መሆናቸው በእግዚአብሄርም በሰውም ፊት የተረዳ ግልጥ ነገር ነው በመሆኑም የጵጵስነ ስልጣን የተገባው ሁሉንም በእኩል እይን በማየት ምላስ ተቀብሎ ሰውን ከማሳደድ በቆመጠብ ዘመድ አዝማዶቻቸውን ህግን በመጣስ ሃጢአትን ባለመጠየፍ ከመቀጥር ሊርቁ ለተቻላቸው በመሆኑ ሃራ ተዋህዶዎች እንዲህ አይነቱን በቤተክርስቲያኒቱ ላይ በጵጵስና ስም እየተሰራ ያለ ግፍ በየሀገረስብከቱ ሞልቶ እየፈሰሰ ነውና ያለው ተከታትላችሁ ገሀድ በማውጣት ወደ ትክክለኛው የእምነት መስመር መመለስ ሃይማኖታዊ ግዴታችሁ በመሆኑ ልትበረቱ ይገባል

    በጳጳሳቱ ዙሪያ ከበው የሚገኙት ጥቅመኞች የሀሰት መፍለቂያዎች በመሆናቸው የሚቀባጥሩትን የሚያዳምጥ የለም አባ እንድርያስ በቂመኝነታቸው የሚታወቁ በዚሁ ባህሪአቸው ዝውውር ሲደረግላቸው የኖሩ እንደመሰሎቻቸው ተንኮለኛ መሆናቸው ይታወቀል በጵጵስና ማዕረግ ላይ ተቀምጦ ምላስ በመስማት የጠሉትን ከመበቀል የበለጠ ሀጢአትና ወንጀል የለም ጵጵስና ስለ ሀገር ስለ ህዝብ ስለቤተክርስቲን ወደ እግዚአብሄር በንጹህ ልብ በመጸለይና በመማለድ ስርየት የሚያመጣ የብርሃን ስልጣን እንጅ በማያውቅትና ፈጽመው ባልተማሩት የአስተዳደር ሥራ ውስጥ በመዳከር እግዚአብሄርንም ሰውንም የሚያሳዙንበት የሚያሳዳዱበት የአመጽ ጠበንጃ አይደለም

    ጳጳሳቱ ለሀገርና ለሀዝብ ከመጸለይ ባሻገር በአሁኑ ጊዜ የተጠሩበትን ተግባር ወደ ጎን በመተው በማያገባቸው የአስተዳደር ስራ በመግባት እየፈጠሩት ያለውን ግፍና አመፃ ማስቆም ካልተቻለ ምዕመኑ የክፋት ተግባራቸውን በተረዳ ጊዜ የመበታተን ጉዳይ ስለሚያጋጥም ቤተ ክርስቲያናችንን ልንታደግ ይገባል ይሄ የቲፎዞ ጉዳይ አይደለም የጵጵስና ሥልጣን ለጸሎት ወይስ ለአስተዳደር ይህንን የመመለስ ጉዳይ ብቻ ነው::

  11. Samson November 18, 2013 at 8:57 pm Reply

    Yemigermew enante sile gileseb ena girupoch sititsifu le seaw kalachu niket yehun simetawi kemehon yetekesetewn endewerede kemakireb wesnachu! Simet yetekelakelebet wegentegninet yemitaybet.. Seaw endemiastewl, enditazebm asibubet… Mizan(akerareb lay)!

  12. Anonymous November 18, 2013 at 10:41 pm Reply

    Hara and saudi Arabia are the same

  13. seyum maru November 19, 2013 at 6:05 am Reply

    እናንተ ግን በቃ ማኅበረ ቅዱሳን ወይም ሞት አላችሁ አይደል ለማኅበሩ ከጠቀመ ሠይጣንም ቢሆን ስልጣን ቢይዝ ጽድቁን ታወራላችሁ፡፡ ማቅን ካልደገፈ ደግሞ መልአክም ቢሆን የሲኦል እንደራሴ ነው ትላላችሁ፡፡ አረ ተዉ አንደንዴ ለእውነት ሥሩ ፡፡ይሉኝታም ይግባችሁ፡፡ በጣም ነው የምታሳዝኑት፡፡

  14. Anonymous November 19, 2013 at 7:00 am Reply

    You are simply empty vessel what does it signify hara And Saudi Arabia is the same shame on you
    Not only aba endriase most of the archbishops valued being dictators and revenge packages No one shorn of this

  15. Anonymous November 19, 2013 at 7:13 am Reply

    let us speak true do we have honest archbishop most of them are personal interest hunter , slaughterer who spoiled life of a lots they comes across to this church position not by their spiritual competence but by gossip and bribe no one expects truth from theme

  16. Anonymous November 19, 2013 at 7:24 am Reply

    ስለ ጳጳሳቶቹ ጉድ የተነካ ነገር የለም ሁሉም ነገር ገሀድ መውጣት አለበት ምክንያቱም አድሮ ውሎ ተጎጀዎቹ ቤተክርስቲያንና ምእመናኖቹ ናቸው ና ስለ ቂመኝነታቸው ስለ አሳዳጅነታቸው ስለጉቦ ወዳድነታቸው ስለ ስጋ ዘመዶቻቸው ደጀንነታቸው ስለ ዝሙት ልጆቻቸው ብዙ ማለት ይቻላል ማለትም ይገባናል ሃራ ተዋህዶ በርቱ ውይይቱ ሊቀጥል ይገባዋል ቅዱሳን በነበሩ አባቶቻችን መንበር ላይ ተቀምጠው ሰይጣናዊ ተግባር የሚፈጽሙት ጳጳሳት ነን ባዮች ተግባራቸው በአደባባይ ለህዝብ ሊቀርብ ይገባዋል

  17. Anonymous November 19, 2013 at 7:24 am Reply

    egeziabeher becha huluneme yawukal yasetekakilewalem!!!we pray

  18. s/g November 19, 2013 at 12:06 pm Reply

    before you give comment know what is happening at the church.

  19. kebede November 19, 2013 at 7:24 pm Reply

    Nefas Mewucha yeteniqola bet honechi maleti newu? Where is Sunday school?

  20. Anonymous November 20, 2013 at 9:08 am Reply

    we know all about what is happeing in the church corruption

  21. Anonymous November 20, 2013 at 11:08 pm Reply

    “መሪጌታ መፍቀሬ ሰብእ መኰንን እና መሪጌታ ኅሩይ ደመወዝ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በደራ ወረዳ አንበሳሜ ከተማ እና በንፋስ መውጫ ቅድስት ሥላሴ በጥንቆላ ሥራ የሚተዳደሩ እንደኾኑ ተነግሯል፡፡” what happened to you Hara? don’t you know the meaning of Hara? why don’t you go and arrest them? because you are Hara. Or are you afraid of them? By the way, Do you know the meaning of Merijeta? Or Debtera? I think you don’t .Debtera and Merijeta are never being called Tnquay” Merijeta or Debtera is a highly educated or scholar person. please think first before you speak

  22. Anonymous November 21, 2013 at 9:11 am Reply

    that is true most of the archbishops are revenger though our church is distracted by this collection please let us stand to protect our religion by forwarding truthly waht those peoples doing MAHBER KIDUSAN you are the most expected to coming front and to stand for the church & clear out.

  23. Anonymous November 22, 2013 at 1:15 pm Reply

    Talking with person who are already passed away. please give us a break!!
    stop talking with dead body. Mahbere Kidusan is just like that
    but all the followers of the Church which are all of us, we can save our church from the evil one.

  24. Anonymous November 22, 2013 at 8:13 pm Reply

    my brother we are not talking about the passed away. but the existance once they should be screen out either they are on the right direction or not . so we shall forward based on evidence and fact withn each of us district.

Leave a comment