የቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ለውጥ ጥናቶች የቅ/ሲኖዶሱን ሙሉ ድጋፍና ባለቤትነት አገኙ፤ በጥናቶቹ ቀጣይ አካሄድ ላይ ምልአተ ጉባኤው የአፈጻጸም አቅጣጫ ሰጥቷል፤ የምልአተ ጉባኤው ስብሰባ ዛሬ ያበቃል፤ መግለጫም ይኖራል

Holy SynodTikmit Meeting

  • በአገልግሎት ጥራት /በሰው ተኮር ነፍስ የማዳን አገልግሎት/ ምእመናንን ማብዛትና ማጽናት፣ ቤተ ክርስቲያንን ከባይተዋርነትና ጠባቂነት ወደነበራት ሚና መመለስ፣ አስተምህሮዋን ከማይቃረኑ ጋራ ዓለም አቀፍ አጋርነትን በማጠናከር የሰላምና አንድነት ተምሳሌት ማድረግ፣ ለሙስና ችግሮች በንስሐ መንገድ መፍትሔ ማበጀት የቤተ ክርስቲያናችን ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማሕቀፍና ቊልፍ ጉዳዮች ኾነዋል፡፡
  • በቡድን እየተደራጁ የመንግሥትን ወቅታዊ አጀንዳዎች በአሉታዊ መንገድ የሚጠቀሙ አሉባልተኞችና ሙሰኞች እንዲሁም በቤተ ክህነቱ ቢሮክራሲ ውስጥ የተሰገሰጉ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞች ዋነኛ የለውጡ ተግዳሮቶች እንደኾኑና እንደሚኾኑ ተጠቁሟል፡፡
  • የለውጥ አመራር መዋቅሩ፣ አደረጃጀቱና ዝርዝር አሠራሩ ሕገ ወጥ ጥቅምን የሚያስቀር ተገቢ ጥቅምን የሚያጎለብት፣ ማንኛውንም ሠራተኛና አገልጋይ ለለውጡ የሚያበቃ እንጂ የማያፈናቅል መኾኑ በቅ/ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤ ታምኖበታል፡፡ ካህናት፣ ባለሞያ ሠራተኞች፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ምእመናን የለውጡ ግንባር ቀደም አራማጆች ይኾናሉ፡፡
  • ተቋማዊ ለውጡን ለመተግበር÷ ነባሩ የሰው ኃይል የሚበቃበት አዲስ የሰው ኃይል የሚወጣበት የሥራ አመራር ማሠልጠኛ አካዳሚ/የሥልጠና ማእከል/ለመገንባት ጥናቱ ተጠናቆ ዝግጅቱ ተጀምሯል፤ ማእከሉ የድኩማን/አረጋውያን መጦርያና የነዳያን መልሶ ማቋቋሚያም ያካተተ ነው፡፡
  • በአ/አበባ ሀ/ስብከት ለተቋማዊ ለውጥ አመራር ጥናቱ ምቹ ኹኔታ የፈጠሩትና ያስቻሉት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አለጊዜውና አላግባብ በተደረጉ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎችና ሌሎች ሠራተኞች ዝውውሮች ቢገመገሙም ከምደባቸው የመነሣታቸው ዜና ከእውነት የራቀ ነው፡፡
  • በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት አዲስ የሙስና ኔትወርክ ዘርግተው ሕገ ወጥ ሲያጋብሱ በቆዩ ሦስት ሓላፊዎች ላይ ርምጃ ይወሰዳል፤ ሓላፊነታቸው ለቀው ወደ አሜሪካ በሄዱት የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ይልማ ቸርነት ምትክ አዲስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ይሾማል፤ ገለልተኝነታቸው፣ የትምህርት ዝግጅታቸውና አገልግሎታቸው የሚጠቀስላቸው የአራዳና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ታጋይ ታደለ ቀጣዩ ዋና ሥራ አስኪያጅ እንደሚኾኑ በስፋት እየተነገረ ነው፡፡
  • የገዳማት አጠቃላይ ወቅታዊ ይዞታና ሥርዐተ ምንኵስናው የሚገኝበትን ኹኔታ ተከታትሎ ለቋሚ ሲኖዶስ ሪፖርት የሚያቀርብ የሊቃነ ጳጳሳት ኮሚቴ በምልአተ ጉባኤው ተደራጀ፤ የዴር ሡልጣን ገዳምን ውዝግብ ለመፍታት ከኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋራ የሚደራደር በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የሚመራ ኮሚቴ እንዲቋቋም ምልአተ ጉባኤው መመሪያ ሰጥቷል፡፡
  • የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መተዳደርያ ደንብ በቅዱስ ሲኖዶሱ ጸድቋል፡፡ ደንቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕፃናትና ወጣቶች ጥራትና ወጥነት ባለው ሥርዐተ ትምህርት ተኮትኩተውና በሥነ ምግባር ታንጸው ተተኪዎች ለማድረግ የሚያስችል፣ ሁለገብ አገልግሎታቸውን ለማጠናከር የሚያግዝ እንደኾነ ተገልጧል፡፡ ሕገ ወጥ ሰባክያንን በመከላከል ስብከተ ወንጌልን በተለያዩ መንገዶች ለማስፋፋት ሰንበት ት/ቤቶችን በይበልጥ የማደራጀት ሥራ ትኩረት ይሰጠዋል
  • ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከነበራቸው የበላይ ሓላፊነት ተነሥተው በበላይ ጠባቂነት ተወስነው ይሠራሉ፤ በኮሌጁ አስተዳደራዊና የፋይናንስ እንቅስቀሴ ጉዳዮች ላይ የመወሰን ሥልጣን አይኖራቸውም፤ የኮሌጁ ዋና ዲን በግልጽ ማስታወቂያ በውድድር በሚካሄድ የቅጥር ሥርዐት ይመደባል፡፡
  • የካህናትና ምእመናን ምዝገባ/ቆጠራ/ ለማካሄድ የተያዘው ዕቅድ ተጨማሪ ዝርዝር ጥናት ያስፈልገዋል በሚል እንዲዘገይ ተደረገ፤ የመንግሥት ፈቃደኝነትና የበጀት አቅም እንደ ስጋት ቢጠቀስም የሊቃነ ጳጳሳት ደመወዝ በመቶ ፐርሰንት እንዲጨምር መወሰኑ አነጋጋሪ ኾኗል፡፡

5 thoughts on “የቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ለውጥ ጥናቶች የቅ/ሲኖዶሱን ሙሉ ድጋፍና ባለቤትነት አገኙ፤ በጥናቶቹ ቀጣይ አካሄድ ላይ ምልአተ ጉባኤው የአፈጻጸም አቅጣጫ ሰጥቷል፤ የምልአተ ጉባኤው ስብሰባ ዛሬ ያበቃል፤ መግለጫም ይኖራል

  1. Anonymous October 31, 2013 at 11:54 am Reply

    Abet!! Abet!! Abet!! Leras sikorsu ayasansu.??!!!

  2. Anonymous October 31, 2013 at 1:51 pm Reply

    I see the renaissance of the church in Ethiopia. I think time has come that the church leaders are standing to their church and the people they lead. It has been long the people ignored the roles of their leaders as they have no function than blessing (“Bemeskel mebarek”). Some of the church leaders were even reduced to the size of the pockets of the people they serve. Not only the church leaders but the country was reduced to the pockets of other countries. The notion that we can work maintain our physical, spiritual and emitional deginity have long been thrown to trash. When this is observed from the spiritual leaders, the depth and the width of our spiritual decay reflects on our never diminishing physical confrontation, hate, bitterness and crime. Currently, there seems a divine intervention is working. This is a country where religious fathers like Abune Petros gave their life to protect their people and the country. I hope the church leaders go beyond their comfort zone and indulge in apostolic mission of preaching love, peace and harmony. I hope they emerge as candle lights to recover the dignity and prosperity of the country. I hope they protect their sheep from injustice and suffering with dignity and love. It is an open secrete to all us and them several people were burnt, persecuted due to their religious orientation. Churches were burnt and constantly under attack. Overall, October will remain one of historical months of awakening of the orthodox church. I hope they maintain their missionary purposes with love, dignity, peace and decency to protect their sheep from physical and spiritual suffering under the hands of ignorant and unbelievers. I remember once a protestant preacher said, without Ethiopian orthodox church, Ethiopia would have been completely convert to Arabic culture.

    My today’s point was though the following one. Ethiopia have several famous theological centers in the country which could be viable theological centers not only to Ethiopia but also to Eastern orthodox churches. Egyptians, Syrians, Indians and other scholars could come and study Ethiopian and international orthodoxy. However, this centers are in dire conditions and deteriorating. I suggest the church work to consider converting these old and famous religious schools such as Washera, Dima, etc into modern theological institutions. Spirituality grows in seclusion not in the detractive city life. I mentioned some of the places but I suppose there are hundreds of famous theological centers in the country. That is where the church should invest and capitalize. I hope any people will feel the same way as me.

  3. Anonymous November 1, 2013 at 8:59 am Reply

    abtohahene yabretahehu manegadahenene asetakakelu manegadune tergulene egame kagonhehu nane egzabhare kanga gare yehune malkmu kane lemta yemselale enafekwalane

  4. Adis Amet November 1, 2013 at 3:23 pm Reply

    እናንተ ለቤተክርስቲያን እድገት ባላችሁ እውቀትና ጉልበት እያገለገላችሁ ለመሆኑ ምስክራችሁ ነኘ
    ግን አንድ ቅር የመለኝ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከነበረበት ክፉ ስም ይወጣል ተብሎ በቅዱስ ሲኖዶስ በ7 ክፍል ከተማዎች መዋቀሩ ቢያንስ በየክፍለ ከተማው 3 ሌቦችን ፈጥረዋል በሀረ ስብከቱ የነበሩት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለቢሮ ሳይሆን ለማእድ ቤት የሚያበቃ የሥራ እውቀት ሳይኖራቸው በቲፎዞ በመመደባቸውና ቀጥሎም በተጭበረበረ የትምህርት ማስረጃ የተመደቡት ወጠጤ እንዲሁሙ በሙሰኛነታቸው ወደር የማይገኝላቸው መልአከ ሰላ ዳዊት ያድ ባለው ዘመን የሰሜን አዲስ አባበ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የአበላል ምክር ሰጭነት ያለ ፈተና ያለ ማስታወቂያ በበኣላት ቀናት በቅዳሜና በእሁድ በስብሰባ ቀናት ጭምር በፈጸሙት የሻሞ ቅጥርና ዝውውር አብያተክርስቲያናቱ ለክስና እንግልት ሲዳረጉ አንዳንድ ገንዘብ ከፍለው ቅጥርቸው በአድባራቱ ተቀባይነት ያጡ ዜጎች ደግሞ ለቅሶ ላይ ናቸው እውነት ግን ሊቀጳጳሱ ለለውጥ የተዘጋጁ ናቸው ቢሆኑ ኖሮ ከሌቦች ባላበሩ እርግጥ እንደአባትነታቸው ከሁሉም አይነት ሰው መዋል ግድ ይላቸዋል ግን አብዝተው የሚጠጉት/ያሚያስጠጉት ሌቦችን አላዋቂዎችን ጫት ቃሚዎችን በቀን ጠጭዎችን በመሆናው እንጠራጠራቸዋለንና ቢነገራቸው; የሚያወራላቸው እንጂ የሚሰራ ለይተው አያዩም እርግጥ ይጥራሉ ግን ከነማን ከአህያ ጋር ያዋለች ጊደር ምን ተማረች ቤተክርስቲያኒትዋ ብዙ ለለውጡ የተዘጋጁ ባለሙያዋች ያሉዋት ቢሆንም እሳቸው ግን ከመናገር አልፎ ሥራ ከማያውቁ ሆዳሞች ተከበው መዋላቸው ቢያስቡበት ድሮ የድራፍት ብዱን አሁን የጫ ብዱን ለምን አባታችን;

  5. elias November 9, 2013 at 4:18 am Reply

    hulgize yeadihari astesaseb maramed yiqir lemin wetat beayinachin ayen lemin ke tigire wichi sew meta demos ye hasetegna ye timihirt masreja kehone lemin atagalitum alasibela silalwachihu new keep it up MK !!!!!!!!

Leave a comment