ቀጣዩ የኢሕአዴግ ዒላማ ማኅበረ ቅዱሳን ይኾን?

FACT Weekily Magazine cover story

(ፋክት መጽሔት፤ ቅጽ 2 ቁጥር 14 መስከረም ፳፻፮ ዓ.ም.

ተመስገን ደሳለኝ

የኢሕአዴግ ታጋዮች የመንግሥት ‹‹ጠንካራ ይዞታ›› የሚባሉ ከተሞችን ሳይቀር መቆጣጠር ችለዋል፤ ወደ አዲስ አበባም የሚያደርጉት ግሥጋሴም ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ሳይቀር ዕንቅልፍ ነስቷል፡፡ በአንዳች ተኣምር ግሥጋሴውን መግታት ካልቻሉ በጥቂት ወራት ውስጥ ሁሉም ነገር ታሪክ እንደሚኾን በማወቃቸው መላ በማፈላለጉ ላይ ተጠምደዋል፡፡ በዚህን ጊዜ ነበር(የሐሳቡ አመንጪ ተለይቶ ባይታወቅም)፣ ‹‹ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አጭር ሥልጠና ሰጥቶ ከሀገሪቱ ሠራዊት ጎን ማሰለፍና የ‹ወንበዴውን ጦር› መድረሻ ማሳጣት›› የሚለው ሐሳብ እንደ መፍትሔ የተወሰደው፡፡

እናም መንግሥቱ ራሳቸው ተማሪዎቹን በዩኒቨርስቲ አዳራሽ ሰብስበው እንዲህ ሲሉ አፋጠጧቸው፡- ‹‹እነርሱ (ኢሕአዴግና ሻዕቢያን ማለታቸው ነው) ለእኵይ ዓላማቸው ከእረኛ እስከ ምሁር ሲያሰልፉ እናንተ ምንድን ነው የምትሠሩት? በሰላማዊ ሰልፍና በስብሰባ ብቻ መቃወም ወይስ ወንበዴዎቹ እንዳደረጉት ከአብዮታዊ ሠራዊታችነ ጎን ቆማችኹ የአገሪቱን ህልውና ታስከብራላችኹ?››

ይህን ጊዜም አስቀድሞ በተሰጣቸው መመሪያ ከተማሪው ጋራ ተመሳስለው በአዳራሹ የተገኙት የደኅንነት ሠራተኞችና የኢሠፓ ካድሬዎች ‹‹ዘምተን ከጠላት ጋራ መፋለም እንፈልጋለን›› ብለው በስሜትና በወኔ እየተናገሩ በሠሩት ‹ድራማ› ተማሪው ትምህርት አቋርጦ እንዲዘምት ተወሰነ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም ተዘጋ፤ ተማሪዎቹም ለወታደራዊ ሥልጠና ደቡብ ኢትዮጵያ ወደሚገኘው የብላቴ አየር ወለድ ማሠልጠኛ ከተቱ፡፡

ከመላው ዘማቾች [የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ የኾኑ ሠልጣኞች በማሠልጠኛው ባዶ ድንኳን] በየጊዜው እየተሰበሰቡና በመጨረሻም ካምፓቸው አቅራቢያ ወደሚገኘው ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ከመዐቱ ይታደጋቸው ዘንድ ፈጣሪያቸውን በጸሎት መማጠን የሕይወታቸው አካል አደረጉት፤ ከቀናት በኋላም በአንዱ ዕለት አንድም ለመታሰቢያና ለበረከት. ሁለትም ስብስቡ ሳይበተን ወደፊት እንዲቀጥል በሚል ዕሳቤ ‹‹ማኅበረ ሚካኤል›› ብለው የሠየሙትን የጽዋ ማኅበር መሠረቱ፡፡ . . . ይኹንና ከመካከላቸው አንዳቸውም እንኳ በ፲፱፻፸፯ ዓ.ም በፓዌ መተከል ዞን የተደረገውን የመልሶ ማቋቋም ሠፈራ ፕሮግራም እንዲያመቻቹ በዘመቱ ተማሪዎች ከተመሠረተውና ከተለያዩ የጽዋ ማኅበራት ጋራ በመዋሐድ የዛሬውን ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› እንደሚፈጥሩ መገመት የሚችሉበት የነቢይነት ጸጋ አልነበራቸውም፤ የኾነው ግን እንዲያ ነበር፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን

የ‹‹ማኅበረ ሚካኤል›› መሥራቾች ከተማሪ ጓደኞቻቸው ጋራ ‹‹ይለያል ዘንድሮ የወንበዴ ኑሮ››ን እየዘመሩ የገቡበት ወታደራዊ ሥልጠና ተጠናቅቆ ወደ ጦር ሜዳ ከመግባታቸው በፊት ዐማፅያኑ አሸንፈው የመንግሥት ለውጥ በመደረጉ ወደየመጡበት ተመለሱ፡፡ ኾኖም ለውጡ በተካሄደ በዓመቱ እነርሱን ጨምሮ በአምላካቸው፣ በጻድቃን፣ በሰማዕታትና በመላእክታት ስም የተመሠረቱ[ከአቡነ ጎርጎርዮስ ዘንድ ሲማሩ የቆዩ] የተለያዩ ማኅበራት ተሰባስበው ወደ አንድ እንዲመጡ መደረጉ ሊጠቀስ የሚገባ ልዩነት ባይፈጥርም ስያሜው ግን ብርቱ ክርክር አሥነሳ፤ አቡነ ገብርኤልም ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ብዬዋለኹ›› ብለው ውጥረቱን አረገቡት፡፡ ዕለቱም[ልደቱን የሚቆጥርበት] ግንቦት ፪ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. እንደነበር ተጽፏል፡፡

ዓላማው ምንድን ነው?

ማኅበረ ቅዱሳን ሲመሠረት ዓላማዬ ብሎ የተነሣበት መሠረታዊ ጉዳይ በተለያየ ጊዜ ለኅትመት ባበቃቸው ድርሳናቱ ተገልጧል፡፡ እርሱም፡- [የቤተ ክርስቲያኒቱ] ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት፣ ክርስቲያናዊ ትውፊትና ታሪክ ተጠብለትውልድ እንዲተላለ ማስቻል ነው፡፡

ማኅበሩ ከመሰሎቹ የተለየ ጥንካሬ እንዲኖረው ያስቻለው ዓላማውን ከግብ ለማድረስ በዋናነት በሀገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች የሚማሩ ተማሪዎችን አባል ማድረጉ ላይ ተግቶ መሥራቱ ነው፡፡ ዛሬም ድረስ መስፈርቱ እያገለገለ እንደኾነ ይታወቃል፤ ይህ ኹኔታም ይመስለኛል አንዳንድ ጸሐፍት ማኅበሩን ‹‹ቤተ ክርስቲያኗ በዩኒቨርስቲዎች ያላት እጅ›› እንዲሉት ያስገደዳቸው፡፡

የኾነው ኾኖ ማኅበሩ በምሥረታው ማግሥት በሃይማኖቱ የመጨረሻውን ሥልጣን በያዘው ቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና ተሰጥቶት በጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር እንዲኾን ተደረገ፡፡ በ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ደግሞ መተዳደርያ ደንቡን አጸደቀ፡፡

የግጭት ጅማሬ

. . . አንዳንድ የኢሕአዴግ አመራሮች በብላቴ ከተመሠረተው ‹‹ማኅበረ ሚካኤል›› ጋራ በማያያዝ የማኅበሩን መሪዎች አልፎ አልፎ ‹‹ተረፈ ደርግ›› እና ‹‹መአሕድ›› እያሉ ከማሸማቀቅ ባለፈ ብዙም ጫና አያደርጉባቸውም ነበር፡፡ ዛሬ ማኅበሩን በመንግሥት ጥቁር መዝገብ በቁጥር አንድ ጠላትነት እንዲሰፍር ካደረጉት ልዩነቶች(ያለመግባባቶች) መካከል ዋናዎቹን በአዲስ መሥመር እጠቅሳለሁ፡፡

ኢሕአዴግ የአገሪቱን ምሥረታ ከዐፄ ምኒልክ ዘመን የሚጀምር የመቶ ዓመት ማድረጉ ማኅበሩ ዓላማዬ ከሚለው ‹‹ታሪክን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ›› ጋራ መታረቅ አለመቻሉ ያስከተለው ውጥረት የመጀመሪያው ነው፡፡ ማኅበሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ታሪክ 2000 ዓመት ወደኋላ ሄዶ ማስላቱ ብቻውን፣ ‹‹አንዲት ኢትዮጵያን በመፍጠር ስም ምኒልክና ተከታዮቹ ያስፈኑትን ጭቆና በጠመንጃ ለማስወገድ በረሓ ገባን›› ከሚሉት የህወሓት መሥራቾች ጋራ ሊያጋጨው መቻሉ የሚጠበቅ ነበር፡፡ ጉዳዩን ከለጠጥነው ደግሞ ‹‹ማኅበሩን በ1980ዎቹ አጋማሽ እንደ ስጋት ይመለከተው የነበረውን ‹የሸዋ ፊውዳል› ወደ ሥልጣን ለማምጣት ያደፈጠ ተቃናቃኝ አድርጎ ፈርጆት ነበር›› ወደሚል ጠርዝ ሊገፋን ይችላል፡፡ በነገራችን ላይ፣ በፖሊቲካው መንገድ ለሹመት የበቁት አቡነ ጳውሎስም እስከ ኅልፈታቸው ድረስ ማኅበሩ በሸዋ ተወላጅ ጳጳስ ሊተካቸው የሚያሤር ይመስላቸው እንደነበር ይነገራል፡፡

በጥቅሉ በኢሕአዴግና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል የርእዮተ ዓለም (በብሔር እና በኢትዮጵያዊነት ላይ የተመሠረተ) ልዩነት መኖሩ ላለመግባባቱ መነሾ ነው፡፡

ሌላው የቅራኔአቸው መንሥኤ፣ በወርኃ ሚያዝያ ፲፱፻፺፫ ዓ.ም ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያምና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋራ ሰብአዊ መብትንና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ባደረጉ ማግሥት፣ በዋናው ግቢ ከተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጋራ የሚያያዘው ኹነት ነው፡፡ በወቅቱ ተማሪዎቹ በሰላማዊ መንገድ ላቀረቡት ጥያቄ የጸጥታ አስከባሪዎች የኃይል ምላሽ መስጠታቸው ጉዳዩን ከቁጥጥር ውጭ አደረገው፡፡ ድብደባውና ማሠቃየቱ ከአቅም በላይ የኾነባቸው የተወሰኑ ተማሪዎችም ከመንበረ ፓትርያርኩ በአጥር ወደሚለየው ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሸሽተው ይገባሉ፡፡ በአካባቢው የነበሩ የጸጥታ ሠራተኞችም የግቢውን በር ይቆልፋሉ፤ ተማሪዎቹንም በኃይል አስወጥተው ደብድበው አሰሯቸው፤ ድርጊቱንም ማኅበረ ቅዱሳን በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ የቤተ ክርስቲያኗን ለሸሸ መጠለያነት ታሪክ አጣቅሶ አጠንክሮ መቃወሙ ከመንግሥት ጋራ በዐደባባይ ቅራኔ ውስጥ ከተተው፡፡

ሌላው ቅራኔአቸውን ያጦዘው ክሥተት ደግሞ በአቶ ተፈራ ዋልዋ በ፲፱፻፺፰ ዓ.ም ወርኃ ጥቅምት ‹‹መንግሥትና አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› በሚል ርእስ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሥልጠና በተሰጠበት ወቅት ኦርቶዶክስን ‹‹የነፍጠኞች ምሽግ››፣ ጥምቀቱንም ‹‹በውኃ መንቦጫረቅ›› ብሎ ማጣጣሉ ሲኖዶሱን ግድ ባይሰጠውም፣ ማኅበረ ቅዱሳንን አስቆጥቶ መልስ እንዲሰጥ ያደረገበት ኩነት መፈጠሩ ነበር፡፡

የመዋቅሩ ስፋትና የውጥረቶቹ ጡዘት

የማይቆጣጠረውን የተደራጀ ኃይል አጥብቆ ለሚፈራው ኢሕአዴግ፣ የማኅበሩ መዋቅር እየሰፋ መሄድ ስጋት ላይ ጥሎታል፡፡ አባላቱ የዩኒቨርስቲ ወይም ኮሌጅ ምሩቃን መኾናቸው ከገጠር እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ድረስ የራሱ ሰዎች እንዲኖሩት አድርጓል፡፡ የአገዛዙም ጭንቀት ‹‹ይህ ኃይል አንድ ቀን በተቃውሞ ፖሊቲካ ሊጠለፍ ይችላል›› የሚል ነው፡፡ ይህንንም የሚያረጋግጠው አቶ ኣባይ ፀሃየ መስከረም ፲፪ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. የማኅበሩን አመራር በሲኖዶስ ጽ/ቤት ባነጋገረበት ወቅት ‹‹ኢሕአዴግ ገለልተኛ የሚባል ነገር አይገባውም›› የሚል መኾኑን ስናስታውስ ነው፡፡

. . .በኢሕአዴግና በቅንጅት መካከል በድኅረ ምርጫ – 97 የተፈጠረውን አለመግባባት ቤተ ክርስቲያኗ የቄሣርን ለቄሣር ብላ ለማንም ሳትወግን ዕርቅ እንዲፈጠር መሸምገል እንዳለባት ማኅበሩ በልሳኖቹ መወትወቱ የተገላቢጦሽ አገዛዙን አስኮረፈው፡፡ በአናቱም ከአማራ ክልል የተላከው ሪፖርት፣ ‹‹በገጠር ያሉ የማኅበሩ አባላት ለተቃዋሚዎች ቀስቅሰዋል›› ማለቱ ውጥረቱን አንሮታል፡፡

በሌላ በኩል መንግሥት ለሦስተኛ ጊዜ ባካሄደው የሕዝብ ቆጠራ ‹‹የ[ኦርቶዶክስ]ክርስቲያኑ ብዛት 33 ሚልዮን ነው›› ማለቱ፣ ‹‹[የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያን መረጃ በመጥቀስ] 45 ሚልዮን ነው›› ከሚለው ማኅበረ ቅዱሳን ጋራ አለመግባባት ውስጥ ከቶት እንደነበር ይታወሳል፡፡

የኢሕአዴግ ክሦች

ኢሕአዴግ በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም በጅማ ከአጋሮ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው በሻሻ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ካህናትና ምእመናን ‹‹የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው›› በተባሉ አንገታቸው በስለት ተቆርጦ መገደላቸውን የሚያሳየውን ፊልም በሲዲ አባዝቶ ያሰራጨውም ኾነ ከጭፍጨፋው ጀርባ የመንግሥት እጅ አለበት የሚል የስም ማጥፋት ዘመቻ የመራው ማኅበሩ ነው ብሎ ያምናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ‹‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት››፣ በጎንደር ‹‹ጎዶልያስ›› (የእግዚአብሔር ጦር) የሚል ጽሑፍ የታተሙባቸው ቲሸርቶች አዘጋጅቶ ያሰራጨው ማኅበረ ቅዱሳን ነው ሲል ይከሳል፡፡ በነሐሴ ወር ፳፻፭ ዓ.ም በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ስም ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎችና መፍትሔዎቻቸው›› በሚል ርእስ የተሰራጨው ሰነድ ክሡን፡- ‹‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ነች፤ አንድ አገር አንድ ሃይማኖት ወዘተ ጉዳዮችን በማቅረብ በአንድ በኩል የሃይማኖት ብዝኃነትን የሚፃረር፣ በሌላ በኩል ደግሞ አገራችን የሃይማኖት ብዝኃነት መኾኗን የሚቃወም አካሄድ ነው፤›› ሲል ያጠናክረዋል፡፡

የኦቦይ ስብሃት – ኩዴታ

በ፳፻፩ ዓ.ም ፓትርያርኩ አቡነ ጳውሎስ ከሲኖዶሱ ጠንካራ ተቃውሞ አጋጥሟቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይኹንና ከዚህ ንቅናቄ ጀርባ አቡነ ሳሙኤልና ሁለት የማኅበረ ቅዱሳን አመራር አባላትን የያዙት ኦቦይ ስብሃት ነጋ እንደነበሩበት ለጉዳዩ ቅርብ ከነበሩ ሰዎች አረጋግጫለኹ፡፡ አቦይ ስብሃት ‹‹አቡነ ጳውሎስ ለኢሕአዴግ ዕዳ ነው›› ብለው መደምደማቸው ለኩዴታ እንዳነሣሣቸው ይነገራል፡፡

. . .[በተቃውሞው] ውጤት ፓትርያርኩ አሸነፉ፡፡ በወቅቱ ማኅበሩ የእንቅስቃሴው ተቃዋሚ መኾኑን የተረዱት አቦይ ስብሃት ነጋ ጥርስ እንደነከሱበት ይነገራል፡፡ በነገራችን ላይ፣ የአቦይ ዕቅድ ቢሳካ ኖሮ ተያይዘው የሚነሡ አለመግባባቶችን በመጠቀም ማኅበሩን መምታትንም የሚያካትት ነበር፡፡

የዋልድባ ጉዳይ

በመንግሥትና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል የነበረውን አለመግባባት ወደላቀ ጠርዝ ያደረሰው በዋልድባ ገዳም አካባቢ ይቋቋማል የተባለው የስኳር ፋብሪካ ጉዳይ ነው፡፡ በገዳሙ የሚኖሩ ምእመናንን ጨምሮ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ያሰሙትን ተቃውሞ ችላ በማለት ወደ ሥራ ለመግባት በሞከረው መንግሥት ላይ የተነሣው ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጠለ፡፡ ይኹንና ሥርዐቱ ገዳሙ ላይ አልደርስም ብሎ ሲከራከር፣ ቤተ ክህነትም የማጣራት ሥራ መሥራቱን ገልጦ ‹‹ምንም ዐይነት ችግር የለም›› ብሎ ከመንግሥት ጎን ቆመ፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ጉዳዩን ቦታው ድረስ ሄዶ የሚያጣራ አምስት አባላት ያለው ቡድን ወደ ዋልድባ ላከ፡፡ ቡድኑ አጥንቶ ባቀረበው ሪፖርት፡- ‹‹16.6 ሄክታር መሬት ከገዳሙ ተወስዷል፤ ገዳሙን የውኃ መጥለቅለቅ ያሰጋዋል፤ . . .›› የሚል ሪፖርት ለመንግሥት አቅርቧል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የዶ/ር ሽፈራው ሰነድ የማኅበሩን ጥናት እንዲህ ሲል ኮንኖታል፡- ‹‹መንግሥት በሃይማኖታችን ጣልቃ ገብቷል በሚል ገሃድ ፍላጎትና ድብቅ አሠራር ካላቸው የውጭ ቡድኖች ጋራ በማበር ሰላምን አደጋ ውስጥ የማስገባት፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱን በሃይማኖት ሽፋን ለመናድ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በቅርብ በነበረው የፓትርያርክ ምርጫና በዋልድባ ገዳም ዙሪያ የተፈጠረው ዝንባሌ የነዚህ ፍላጎቶች ማሳያ ነው፡፡››

የፓትርያርኩ ኅልፈት

በ፳፻፬ ዓ.ም መጨረሻ አቡነ ጳውሎስ ማለፋቸው ሌላ ፍጥጫን አስከትሏል፡፡ ማኅበሩ ስደተኛውን ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስን ከአሜሪካ አምጥቶ ወይም እንዳሻው የሚያሽከረክረውን ጳጳስ መንበሩ ላይ ለማስቀመጥ ምርጫው በሚፈልገው መንገድ እንዲጠናቀቅ በርትቶ እየሠራ ነው የሚለው ወቀሳ የመንግሥት ቁጣን የበዛ አድርጎታል፡፡ የጠቀሱት ሰነድም ውንጀላውን በገደምዳሜ ገልጾታል፡- ‹‹በእስልምናም ይኹን በክርስትና ሃይማኖቶች ሽፋን የሚደረገው የአክራሪነት/ጽንፈኝነት እንቅስቃሴ በዋናነት እያነጣጠረ የሚገኘው የተቋማቱን የበላይ አመራር ዕርከኖች መቆጣጠር ነው፡፡››

ናዳው እየመጣ ነው?

ባለፉት ሁለት ዓመታት የእስልምና እምነት ተከታዮች ‹‹መንግሥት በሃይማኖታችን ጣልቃ አይግባ›› በሚል የጀመሩትን ትግል ተከትሎ አገዛዙ ማኅበረ ቅዱሳንንም ደርቦ የመምታት ዕቅድ እንዳለው የሚጠቁሙ ምልክቶች ታይተዋል፡፡ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትን በሚኒስትር ማዕርግ የሚመራው አቶ ሬድዋን ሑሴን፣ ‹‹መንግሥት ጉዳዩን በሰላም ቢጨርሰው የተሻለ ነው›› ሲሉ ምክር ለመለገሥ ለሞከሩ የምዕራብ አገሮች ዲፕሎማቶች፣ ‹‹የአወሊያን ቡድን በዚህ መልኩ ሳናበረክከው ቀርተን መጅሊሱን እንዲወስድ ብናደርግ፣ ነገ ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን ‹ሲኖዶሱን አምጡ› ቢለን ምን መለስ ይኖረናል?›› ሲል የሰጠው ምላሽ ይህንኑ የሚመለክት ነው፡፡

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር መ/ቤት ባለፈው ዓመት ወርኃ የካቲት ‹‹ለሃይማኖት ተቋማት የተዘጋጀ›› ብሎ ያሰራጨው ሰነድ ማኅበረ ቅዱሳንና መብታቸው እየጠየቁ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታየች የጥቃቱ ዒላማ እንደኾኑ ያሳያል፡፡ ሂደቱን በመምራትም ኾነ በማስፈጸም ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ጀርባ ኾኖ በዋናነት የሚሠራው የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል እንደኾነ ይታወቃል፡፡ ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ‹‹የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፖሊቲካ ርብርብ ሜዳ አይኾኑም፤ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም ከማንኛውም ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ነጻ መኾን አለባቸው›› ያሉበት ዐውድ ‹‹በዩኒቨርስቲዎች የአካዳሚ ትምህርትን ተገን በማድረግ እምነትን ማስፋፋት አይቻልም›› በማለት ማኅበሩ እንደ ቀድሞው አባላቱን ለመሰብሰብና ለማስተማር የሚችልበትን ኹኔታ የሚያግድ ነው፡፡

በ፳፻፮ ዓ.ም በዩኒቨርስቲዎች ይተገበራል የሚባለው አለባበስንና አመጋገብን የሚመለከተው መመሪያም ራሱን የቻለ አደጋ አለው፡፡ እንዲሁም የሃይማኖት ማኅበራት ዓላማቸውን አሳውቀው እንዲመዘገቡ የሚያስገድደውን ሕግ በምክር ቤት ለማጸደቅ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡ መዝጋቢው ክፍል ማኅበራቱን በፍርድ ቤት ከማስቀጣት እስከ ማፍረስ የሚያደርስ ሥልጣን እንደሚሰጠው ምንጮቼ መረጃ አድርሰውኛል፡፡ ይበልጥ የንደነግጠው ደግሞ በዚህ መልክ ማኅበራቱን ከጠለፉ በኋላ ማንም ሰው ‹‹ቅዱስ ቃሉን›› ለመስበክ ፈቃድ ማግኘትን ግዴታ ለማድረግ መታቀዱን ስናነብ ነው፡-

‹‹የሰባክያን/ዳኢዎች ሚናን የበለጠ ለማጎልበትና የተጠያቂነት ሥርዐት ለመትከል እያንዳንዱ የሃይማኖት ተቋም የራሱን መምህራን የሚለይበትን የመታወቂያ ሥርዐት ሊያበጅና በዚህም የክትትል ሥራ እንዲሠሩ መደገፍ ይቻላል፡፡››

ሰነዱ ወደ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሚገቡ ተማሪዎችንም መልምሎ የሲኖዶሱን፣ የማኅበረ ቅዱሳንን፣ የመጅሊስን. . .አመራርነት የመያዝ ዕቅድ እንዳለው በዘወርዋራ ይጠቁማል፡፡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በ፳፻፬ ዓ.ም ባዘጋጀው የሥልጠና ማንዋል ላይም ‹‹በኦርቶዶክስ ክርስትና መድረክ አክራሪው ኃይል ማኅበረ ቅዱሳን ነው›› ሲል መፈረጁ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም የማኅበረ ቅዱሳንን ግቢ ጉባኤ በማዳከም፣ ከሰንበት ት/ቤቶች፣ ከሰበካ ጉባኤና ከሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ጋራ በማጋጨት፣ በካህናት በማስወገዝና በመሳሰሉት ተጠቅሞ ሊያፈርሰው እንደተዘጋጀ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በጥቅሉ ሰነዱ ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹በሃይማኖት ሽፋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መንግሥታዊ ሃይማኖት መኾን ይገባዋል በሚል በአቋራጭ የፖለቲካ መሣርያ ለማድረግ የሚንቀሳቀስ›› ሲል ይኮንነዋል፡፡ ‹‹የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ምንጩን ለማድረቅ እየተሠራ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሥራም ጎን ለጎን መፈጸም ያለበት ነው፤›› ሲል ጥቁምታ ይሰጣል፡፡

መፍትሔው ምንድን ነው?

ከላይ በጥቅሉ እንደጠቀስኩት የ22 ዓመታቱ ሂደት የሚያስረግጠው፣ የኢሕአዴግን ማንኛውም ዓለማዊም ኾነ ሃይማኖታዊ ተቋማት ነጻነት ያለማክበሩ ብቻም ሳይኾን ቀስ በቀስ ህልውናቸውን ለዘላለሙ ለማጥፋት በሙሉ ኃይሉ እየሠራ እንደኾነ ነው፡፡

የኾነው ኾኖ የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች ተቋማቸውን ለመከላከል . . .ሕዝበ ክርስቲያኑ ሕዝባዊ ንቅናቄ ፈጥሮ በመከራው ጊዜ የደረሰለትን ‹‹የእምነቱን ዘብ እንዲታደግ›› ጥሪ ማስተላለፍና ማነሣሣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

. . . ማኅበሩ ዝምታውን በመግራት የራሱን ህልውና እጅግ በፍጥነት ለመታደግ መሞከር ይኖርበታል፡፡ ከሥርዐቱ የፖሊቲካ ዘዬ እንደተረዳነው፣ ቀስ በቀስ እየጠበቀ በመጣው አፈና ላይ ማኅበሩ አንገቱን ቀብሮ፣ ጣልቃ ገብነቱን ቸል ብሎ የማንገራገሩ አካሄድ፣ በአንድ ክፉ ቀን በመጅሊሱ የተፈጸመው ታሪክ በራሱም ላይ መደገሙ አይቀሬ እንደኾነ ለመናገር ነቢይ መኾንን አይጠይቅም፡፡ የትምህርት ተቋማትን የረገጡ ከተሜ ወጣቶች በማኅበሩ ውስጥ መብዛታቸው የመውጫ መንገዱን በአመራሩ ላይ ይጥለዋል፤ ‹‹ለትላንት አናረፍድም፤ ለነገ አንዘገይም›› እንዲሉ የቤተ ክርስቲያኗ ሊቃውንት፡፡

ማስታወሻ፡- ጽሑፉ ከአንዳንድ መረጃውና ይዘቱ አንጻር መጠነኛ መስተካከል ተደርጎበት የቀረበ ነው፡፡

31 thoughts on “ቀጣዩ የኢሕአዴግ ዒላማ ማኅበረ ቅዱሳን ይኾን?

  1. Anonymous October 5, 2013 at 1:31 pm Reply

    ezay akum belut be enesu kemeta be haymanotachin mamtatu new eko!sirate b/k yitebek silalu new akrari yemibalut.EPRDF komeh asib.

  2. Anonymous October 5, 2013 at 2:05 pm Reply

    enkhuwa wayana dergem wadekhal gudgad setkofer atarekaw nage anthe letgababet tethlale

  3. Fikadu Worku October 5, 2013 at 7:18 pm Reply

    This is red line. Leading people to violence, no one predict the outcome. Better for gov’t to be wise no knock every silent door for violence.

  4. Anonymous October 5, 2013 at 8:12 pm Reply

    የማህበረ ቅዱሳን አገልግሎት ሰማያዊ ነውን ወይስ ምድራዊ? ግራ እኮ ነው

    • Anonymous October 6, 2013 at 3:27 am Reply

      ምኑ ነው ግራ የገባህ ወንድሜ ? ሰማያዊና ምድራዊ መለየት አልቻልክም ወይስ አንተ ራስህ ግራ የተጋባህ ነህ ?

    • Anonymous October 6, 2013 at 1:58 pm Reply

      ምኑ ግራ የገባህ ?ለጥያቄ ነው ወይስ አንተ ራስህ ግራ የተጋባህ መሆን ነህ? በግልፅ አቅዋሙ የሚታወቅ በቤተክርስቲያን ስር ያለ በቅዱስ ሲኖዶስ ድንብና መመሪያ ተዘጋጅቶለት ለቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት የሚለፋ ወይም የሚተጋ በተደጋጋሚ እንዲፈርስ በጠላት ስይጣንና አስፈፃሚዎች የሚሴርበት ነገር ግን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በፃድቃንና በቅዱሳን ፀሎትና ምልጃ በመላእክት ተራዳይነት በ እግዚአብሔር ፈቃድ የቆመ ፍፁም ሠላማዊና መንፈሳዊ ሥራ የሚሰራ ማኅበር ነው::አገልግሎቱም የሰማያዊውን መንገድ መጥረግ ነው ::ከዛ በተረፈ ግን ቤተክርስቲያን ውስጥ መሽገው የመናፈቃንን እና የ መንግስትን ጉዳይ እንደሚያስፈፅሙ የእናት ጡት ነካሽ አይደለም አላማው ሰማያዊ ስለሆነ ከነዚህም ውስጥ ግለፅልኝ ካልከኝ ልገልፅልህ እችላለሁ

  5. Anonymous October 6, 2013 at 6:41 am Reply

    YE ISRAEL AMLAK ZIM AYILIM. LEMIN SELAMIN SEBEKACHU NEW ?

  6. Getu October 6, 2013 at 9:25 am Reply

    “Teb yelesh Bedabo” let them try, Our church and our Association are in our heart! And I advise the reckless cadres of EPRDF to think twice! Is this Ethiopia or North Korea! No Return to the era of totaltorian communists! The law of the land has to emanate from the natuarl right of people and associated obligations ! not from the program of EPRDF! EPRDF always barks about the article in the constitution ” Separation of church and sate” But there is an urgent need to formulate longlasting policy. And as I suggested this policy has to allow people enjoy their freedom of worship at the right place and time. It has to also restrict pumping of money from abroad with intention of propagating religious ideology. I believe that MK can give gurantee for its indpendence as an association to EPRDF. MK is indpendent of any political activity not because EPRDF wants it! rather because it is neither the the purpose nor the desire of of MK.

  7. Anonymous October 6, 2013 at 12:26 pm Reply

    ማህበረ ቅዱሳን ኪራይ ሰብሳቢነትን ለማስቀረትና ፍትሀዊ አስተዳደር እንዲኖር ስነ ምግባርን ለትውልዱ ስለአስተማረ ይሆን? እነሱ እንደፈለጉ ቢአደርጉ ማን ይቃዎማል:: ትውልዱ ግን በፈርሀ እግዚአብሔር ቢኖር ክፋቱ ምን ይሆን? ሰላም የነሳቸው ምን ይሆን? አደለም ኢትዮጵያ ሶርያ: ሊቢያ: ግብጽና ሩሲያ የክርስቲያን ደሴት ሀገር ነበሩ አሁን ግን የት እንዳሉ ታሪክ ምስክር ነው:: ኢትዮጵያን እንደዚህ አገሮች እንዲትሆን የሚፈልግ ያለ አይመስልኝም:: ኢትዮጵያም የክርስቲያን ሀገር ብቻ መሆን አለባት የሚል ከርስቲያን የለም በፍቅር እና በሰላም መኖር እንጂ:: እግዚአብሔር ይችን ሀገር ይታደጋት:: ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። መዝሙረ ዳዊት 68:31

  8. Aregawi October 6, 2013 at 12:32 pm Reply

    የማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት በቅድስት ቤተክርስቲያን ጥላ ሥር በመሆን ለሰማያዊ ዜግነት ለመብቃት ምድራዊ ዝግጅቶችን በምድር ላይ የሚፈጸሙበት፤ መልካም አገልግሎት የሚፈጸምበት እና የቅዱሳን ምልጃ እና በረከት የሚገኝበት የአገልግሎት ማኅበር ነው፡፡ይህንን ደግሞ ላለፉት 22 ዓመታት በግልጽ አስመስክሮአል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ሆኖ ሰው የገደለበት ወይም ያስገደለበት ጊዜ የለም፡፡ ለወደፊትም አይኖርም፡፡ “ አስተዋዩና አርቆ አሳቢው” መሪያችን አቶ መለስና ቱልቱላ ተከታዮቻቸው አንድ አገርና አንድ ሃይማኖት እያሉ የሚጠቅሱት “ ማኅበሩንም ሆነ አንዳንድ አባላቱን” አይመለከትም ፡፡ ይህ ቃል “አስተዋዩ መሪያችን” እንደለመደባቸው አጣምመው መረዳትና መተርጎም ልማዳቸው ስለሆነ ነው እንጅ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁልጊዜ የምትሰብከው ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በላከው መልዕክቱ 4፥5 አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንድ ጥምቀት ብሎ እንደገለጸው፤ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር ፥ በአንድ ሃይማኖት ክርስትና እና በአንዲት የልጅነት ጥምቀት ማመን እንደሚገባ ያስተማረውን ስለምታስተምር ነው፡፡ ለነገሩ ነው እንጂ ሊበሏት ያሏትን ወፍ . . . አይደል የሚለው ያገሬ ሰው፡፡ ለነገሩ መለስ ዜናዊና አቦይ ስብሃት እንዲሁም ሌሎቹ የህወሓት መሪዎች አባይ ጸሐዬን ጨምሮ ነጻ እናወጣሃለን ያሉትን የትግራይ ህዝብን በአብይ አዲና ሐውዜን በቦምብ ያስደበደቡ የአገርንና የሕዝብ አንድነትን የሚሰብኩትን ማናቸውንም ሃይማኖታዊ ፥ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ አካላት ከማፈራረስ ወደኋላ እንደማይሉ የታመነ ነው፤ ሆኖም ግን እንዳለፉት መሪዎቻችን ሞታቸውንና ቅስፈታቸውን አንመኝላቸውም፤ የበደሉትን ሕዝብ ይቅርታ የሚጠይቁበትን እድሜ እንመኝላቸዋለን፡፡ የክርስትና መሠረቱ ፍቅርና ይቅርታ ነውና፡፡

  9. kebede October 6, 2013 at 12:38 pm Reply

    ማህበረ ቅዱሳን ኪራይ ሰብሳቢነትን ለማስቀረትና ፍትሀዊ አስተዳደር እንዲኖር ስነ ምግባርን ለትውልዱ ስለአስተማረ ይሆን? እነሱ እንደፈለጉ ቢአደርጉ ማን ይቃዎማል:: ትውልዱ ግን በፈርሀ እግዚአብሔር ቢኖር ክፋቱ ምን ይሆን? ሰላም የነሳቸው ምን ይሆን? አደለም ኢትዮጵያ ሶርያ: ሊቢያ: ግብጽና ሩሲያ የክርስቲያን ደሴት ሀገር ነበሩ አሁን ግን የት እንዳሉ ታሪክ ምስክር ነው:: ኢትዮጵያን እንደዚህ አገሮች እንዲትሆን የሚፈልግ ያለ አይመስልኝም:: ኢትዮጵያም የክርስቲያን ሀገር ብቻ መሆን አለባት የሚል ከርስቲያን የለም በፍቅር እና በሰላም መኖር እንጂ:: እግዚአብሔር ይችን ሀገር ይታደጋት:: ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። መዝሙረ ዳዊት 68:31

  10. Anonymous October 6, 2013 at 1:30 pm Reply

    ቀደም ሲል አቡነ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለኔ ተገዙ እያሉ እንደሚያፈርሱት ሲዝቱ የት እንደገቡ ልብ እንበል፡፡ በየስብሳበው ላይም በጠላትነት ያዩት የት እንደገቡ ልብ እንበል፡፡ አሁን ደግሞ መሪና ተመሪ በማይታወቅበት ሃገር ስንኖር መናፍቃን በስልጣን ላይ ተሰግስገው ማህበሩን ለመምታት ሲያሴሩ ይታያል፡፡ እድሜ የሚኖራችሁ እንዳይመስላችሁ፡፡ ማህበሩን ሰው ያቁዋቁዋመው እንዳይመስላችሁ እግዚአብሔር እንጂ፡፡ በሰዎች የቆመ እንዳይመስላችሁ በቅዱሳን ጸሎት እንጂ፡፡ በየገዳማቱ መላው መኛኝ የሚያስበው ማህበር ነው፡፡ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማእታት ሁሌም ይራዱታል፡፡ መንግስት ይህንን ማህበር እነካለሁ ብሎ አይኑን እንደነካ ይቁጠረው፡፡ አሁን አሁን የአስተዳደር እድሜው ሲረዝም የሚያስተዳድረን ሳይሆን የፈጠረን መሰለው፡፡ እሳትን ላለመጨበጥ ብትሞክሩ ጥሩ ነው፡፡
    ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መንግስት ያስገባቸው ልጆች ምን እየሰሩ እንደሆነ ተብሎ ያለቀለት ነው፡፡ እራሱን መግዛት የማይችል በዝሙት የተለከፈ ትውልድ እያፈራ ትንሽም ቢሆን ማህበሩ ቃለ እግዚአብሔርን አካፍሎ ለሃገሩና ለወገኑ ስርዓት ያለው ትውልድ ከሙስናና ከሌብነት የጸዳ ትውልድ ቤተክርስቲያኑን አለሁልሽ የሚል ትውልድ ለመፍጠር እያደረገ ያለውን ነገር መቃወም ሌላ ጉዳ ነው፡፡ ማንም ስላለ ምንም አይፈጠርም እግዚአብሔር ካለ የሚሆነው ይሆናል፡፡ እድሜ ይስጠን እናንተ ቆማችሁ ማህበሩን የምትነኩ ከሆነ ታዩታላችሁ፡፡ ቀስ እያለ አምልኮታችሁ እኔን ይሁን እኔ ያልኩትን አድርጉ ሳይለን አይቀርም ምክንያቱም ቅዳሴ ተጉዋጉሎ ተቃውሞ ሰልፍ ውጡ ማለት ምን ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም እጃችሁን ከማህበሩ ላይ ሰብስቡ፡፡ የህልውና ጉዳይ ነውና በማህበሩ ውስጥም ሆነ ማህበሩን በጸሎት የሚራዱ ሁሉ አንድ ቀን ቢያዝኑ ችግሩ በራሳችሁ እንደሚሆን ልትረዱት ይገባል፡፡ አሁንም እስካሁንም በማህበሩ ላይ ባሳበችሁት እየተግደረደራችሁ እየኖራችሁ መሆኑን ማወቅ ይገባችሁዋል፡፡
    ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የራስዋ ደንብና ስርዓት ያላት በመሆኑ ሌላ መንግስታዊ መመሪያ አያስፈልጋትም፡፡ ቀደም ሲል አቡነ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለኔ ተገዙ እያሉ እንደሚያፈርሱት ሲዝቱ የት እንደገቡ ልብ እንበል፡፡ በየስብሳበው ላይም በጠላትነት ያዩት የት እንደገቡ ልብ እንበል፡፡ አሁን ደግሞ መሪና ተመሪ በማይታወቅበት ሃገር ስንኖር መናፍቃን በስልጣን ላይ ተሰግስገው ማህበሩን ለመምታት ሲያሴሩ ይታያል፡፡ እድሜ የሚኖራችሁ እንዳይመስላችሁ፡፡ ማህበሩን ሰው ያቁዋቁዋመው እንዳይመስላችሁ እግዚአብሔር እንጂ፡፡ በሰዎች የቆመ እንዳይመስላችሁ በቅዱሳን ጸሎት እንጂ፡፡ በየገዳማቱ መላው መኛኝ የሚያስበው ማህበር ነው፡፡ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማእታት ሁሌም ይራዱታል፡፡ መንግስት ይህንን ማህበር እነካለሁ ብሎ አይኑን እንደነካ ይቁጠረው፡፡ አሁን አሁን የአስተዳደር እድሜው ሲረዝም የሚያስተዳድረን ሳይሆን የፈጠረን መሰለው፡፡ እሳትን ላለመጨበጥ ብትሞክሩ ጥሩ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መንግስት ያስገባቸው ልጆች ምን እየሰሩ እንደሆነ ተብሎ ያለቀለት ነው፡፡ እራሱን መግዛት የማይችል በዝሙት የተለከፈ ትውልድ እያፈራ ትንሽም ቢሆን ማህበሩ ቃለ እግዚአብሔርን አካፍሎ ለሃገሩና ለወገኑ ስርዓት ያለው ትውልድ ከሙስናና ከሌብነት የጸዳ ትውልድ ቤተክርስቲያኑን አለሁልሽ የሚል ትውልድ ለመፍጠር እያደረገ ያለውን ነገር መቃወም ሌላ ጉዳ ነው፡፡ ማንም ስላለ ምንም አይፈጠርም እግዚአብሔር ካለ የሚሆነው ይሆናል፡፡ እድሜ ይስጠን እናንተ ቆማችሁ ማህበሩን የምትነኩ ከሆነ ታዩታላችሁ፡፡ ቀስ እያለ አምልኮታችሁ እኔን ይሁን እኔ ያልኩትን አድርጉ ሳይለን አይቀርም ምክንያቱም ቅዳሴ ተጉዋጉሎ ተቃውሞ ሰልፍ ውጡ ማለት ምን ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም እጃችሁን ከማህበሩ ላይ ሰብስቡ፡፡ የህልውና ጉዳይ ነውና በማህበሩ ውስጥም ሆነ ማህበሩን በጸሎት የሚራዱ ሁሉ አንድ ቀን ቢያዝኑ ችግሩ በራሳችሁ እንደሚሆን ልትረዱት ይገባል፡፡ አሁንም እስካሁንም በማህበሩ ላይ ባሳበችሁት እየተግደረደራችሁ እየኖራችሁ መሆኑን ማወቅ ይገባችሁዋል፡፡ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የራስዋ ደንብና ስርዓት ያላት በመሆኑ ሌላ መንግስታዊ መመሪያ አያስፈልጋትም፡፡

  11. tazabi October 6, 2013 at 10:11 pm Reply

    One of eprdf’s usual delusional behavior. i remember having this discussion with my elder bro before a year on one of the holidays. he already knew that a time will come for eprdf to rage war on orthodox and he argued that” we are just watching the Muslims claim of freedom from government and furthermore, we joined the govt in labeling them as a terrorist while in reality they were just asking the ruling party to leave their religion for them selves. he added just shortly they will come to us and i will see u barking about it” as i was negligent to the case of the Muslims. now i realized he was right, right now what we need is to stick together. avoid our internal blame games of menafik kidus bla bla bla and find a way to tackle the upcoming disaster to save our church. if we keep on this internal blame game and power struggle then aboy sibhat and buchelochu will win the game with out tossing a single dime. i dont expect anything from the so called sinod or papal palace as they r just bystanders if not dengay akebay le eprdf. Egziabher Amlak Ethiopian ena betekrstiyanachenen yetebek.

  12. Mengaw October 7, 2013 at 6:35 am Reply

    “ቀደም ሲል አቡነ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለኔ ተገዙ እያሉ እንደሚያፈርሱት ሲዝቱ የት እንደገቡ ልብ እንበል” ትላለህ ?አቶ Anonymous ምን ማለት ነው ማቅ ላይ ስለፎከሩ ተቀዘፉ እያልከን ነው ? እግዚኦ የግብፆችና የአባትህ ንጉስ ዘርዓያዕቆብ አባባል አስታወስከኝ ግብፆች ኢትዮጵያውያን ከራሳቸው ለቃውንት ጳጳት እንሾማለን በማለታችው እግዚአብሔር ተቆጥቶባቸው ዝናብ ከለከላቸው ብለው በስንክሳር ፃፉ እንዳንተ አይነቶቹ አሁን ድረስ ያነቡታል።አባትህ ዘርዓያዕቆብ ደቂቀ እስጢፋኖስ እውነቱን ሰናገሩት ጊዜ በሞት ቀጣቸው/ጨፈጨፋቸው/ና በመፃህፍቱ ሰው በመግደሉ ከሰማይ ብርሃን ወረደ አስብሎ አፃፈ። አሁን ደግሞ አንተ እንደ አባቶችህ ቅዱስ አባታችን አቡነ ጳውሎስ ማቅን ስላስፈራሩ ተቀዘፉ ብለህ ፃፍክ። መፃፍና ማንበብ በመቻልህ ብቻ እንዲህ ታስነብበን? ወሬኛ።

  13. annonymus October 7, 2013 at 8:29 am Reply

    በእኔ ግንዛቤ የእነ አቦይ ስብሀትም ሆነ ዶ/ር ሽፈራው ስጋት በአብዛኛው ከሀገር ደህንነት ጋር ሳይሆን ከራሳቸው የፖለቲካ ድርጅት ደህንነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ማህበሩም ላይ ያላቸው ስጋት ይሄው ሊሆን ይችላል፡፡ ማህበሩ እንደ ማህበር በፖለቲካ ጉዳይ ገለልተኛ የመሆን ግዴታ እንዳለበት ይታወቃል እስካሁንም እዚህ ጋር የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት አሳይቷል ተብሎ ሊወቀስበት የሚችል ክስተት ለመኖሩ ማስረጃ የሚቀርብበት አይመስለኝም፡፡ ሆኖም የማህበሩ አባላት እንደማንኛውም ግለሰብ የየራሳቸው የፖለቲካ ዝንባሌና ድጋፍ ሊኖራቸው ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይሄ ደግሞ ትክክልም ነው፡፡ ቢቻላቸው ግን ስለማህበሩ ሲባል አባላቱም በተለይ ወሳኝ አባላት ከፖለቲካ ገለልተኛ ቢሆኑ ይመረጣል፡፡ በየትኛውም አግባብ ግን ማህበሩን የትኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ ለመደገፍም ሆን ለመቃወም የመጠቀም መብት የላቸውም፡፡
    ማህበሩ ለአለፉት በርካታ ዓመታት ቤተክርስቲያኗን በተለያየ መልኩ ሲያግዝና በተለይም ቁልፍ የመረጃ ምንጭ በመሆን ሲያገለግል መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን ግድፈቶች እየተነበቡበት በሕዝብም ዘንድ ጥራጣሬን እያሳደረ መጥቷል፡፡ ማህበሩ ከአለው የአለውን ተቀባይነት ወደ ትምክህት እነዳለወጠውም ስጋት አለ፡፡ ማህበሩ አጠፋህ የሚለውን የመቀበል አቅሙ እየደከመ ማንም አያርመኝም አይነት አዝማሚያም ይታይበታል፡፡ በአንጻሩ ግን ብዙ ግድፈቶችን ሲሰራ ይታያል፡፡ ቤተክርስቲያኗን ከጎደፈ እምነት አራማጆች ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረትም የተሳሳቱ ግለሰቦችን ለማረም ከሚጋብዙ ይልቅ የሚገፉ አሰራሮችን እንደሚሰራ ማህበሩ ይወቀሳል፡፡ አንዳንዴም ራሱ ተሳስቶ ምንም ስህተት የሌለባቸውን እንደገፋ ጭምር፡፡ በዚህም የተነሳ ከዚህስ ቢቀር ሲሉ እምነታቸውን ሳይቀር ያጡ ወገኖች እነዳሉ ይነገራል፡፡ ይህ ደግሞ ከስህተቶች ሁሉ ስህተት ነው፡፡ የባስ በእምነቱ ባለቸው ጥንካሬ ከልዑል አምላክ የተሰጣቸውን አባቶች ፀጋ ሲያቃልልና በተቃራኒው ማህበሩ ይደግፉኛል የሚላቸውን እምነትን ሳይሆን ዘመናውነትን ለሚኖሩ አባት ተብዬዎች ሲያካብድ ይታያል፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ በዘመናችን የልዑል አማላክን ኃይልና የክፉ መናፍስትን ሴራ ገሃድ ያወጡትን መ/ር ግርማ ወንድሙ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አግባብ ባልሆነ መልኩ ሲታገዱ ማህበሩ ቀዳሚ ደጋፊ ሆኖ የምስራች ያህል ነበር ክስተቱን የዘገበው፡፡ በዚህ ምክነያት ብዙ የእምነቱ ተከታይ ደጋፊዎቹን እንዳጣ ይገባኛል፡፡ ለማህበሩ መንፈሳዊነት ሆያ ሆዬ ባህልን ከእምነት ያለየ አይነት አምልኮ እንጂ እውነተኛው አምልኮ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው አጠያያቂ ሆኗል፡፡
    ሌላው ማህበሩ ራሱ የሚደገፋቸውን የሀይማኖት አባቶች ይክባል ሌሎችን ደግሞ በተለያዩ የመረጃ ምንጮች ብዙም ጊዜ በአልታረሙ ቃላት ጭምር እየኮነነ በቤተክርስቲያኗ ሰላም እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ በተለይም ከቅርብ ጊዜ በኋላ በአንዳንድ የማህበሩ ናቸው ተብለው በሚታሙ ደህረገጾች የሚወጡ ጉዳዮች ፍጹም የቤተክርስቲያኗን ስነምግባር ያልተከተሉ መሆናቸው በግልጽ ይታያል፡፡ ሲጀምር የቤተክርስቲያኗን የውስጥ ጉዳይ (ችግር ቢኖር እንኳን) ሚዲያ ስላመቸ ብቻ ለሕዝብ ማውጣት ትክክል ነው ብዬ አላምንም፡፡ ሲቀጥል ግን አብዛኛዎቹ የማህበሩ ናቸው ተብሎ በሚገመቱት ድረ-ገጾች የሚወጡ መረጃዎች በጣም የወረዱና ገለልተኛ ያልሆኑ ናቸው፡፡ እንዲህ ያለው አዘጋገብ በአለማውያኑ ዘጋቢዎች አይታይም፡፡ አባቶችን በዝለፍ፣ ጉዳዮችን ወደ ራስ ብቻ ጽንፍ እንዲታዩ መሞከር፣ ሌሎችም ችግሮች በግልጽ ይነበባሉ፡፡ ከዚህ አንጻር በሌሎች የፖለቲካ ጉዳዮች ሳይቀር ላለመተላለፉ ዋስትና ሊኖር አይችልም፡፡
    በአጠቃላይ ብዙ አስተያየት ሰጭዎች እንደገለጻችሁት የማህበሩ መነካት እናንተ እንደምታስቡት የቤተክርስቲያኗ ወይም የአማኞቿ መነካት ሳይሆን አሁን የራሱና የደጋፊዎቹ መነካት ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡ ሕዝብ ማህበሩን ድሮ እንደሚያምነው አሁን እያመነው ለመሆኑ እጠራጠራለሁ፡፡ ጥንቃቄ ያለበት አካሂድ ሊጓዝ ይገባዋል እላለሁ፡፡ ማህበሩ በቤተክርስቲያኗ በሚፈጠሩ ችግሮች መፍትህ እንጂ የችግር አባባሽ ሆኖ አለመግባባቶች እንዲጎሉ ማድረግ የለበትም፡፡ ራሱንም ከሲኖዶስ ሳይቀር አስቀድሞ መገኘት የለበትም፡፡ የቤትክርስቲያን የተባሉ ሚዲያዎችም ስነምግባርን የተላበሱ ዘገባዎችን እንዲያቀርቡ፣ በሚስጢር መያዝ የሚገባቸውን ጉዳየዮች በሚስጢር እንዲይዙ አስፈላጊ ሲሆን አግባብ ባለው ሁኔታ በብልህ አቀራረብ እንዲያቀርቡ ማድረግ ቢችል ጥሩ ነው፡፡
    ቸር ያሰማን

    • ገ/ሚካኤል October 8, 2013 at 8:17 am Reply

      Thank you @annonymus October 7, 2013 at 8:29 am.
      Though i can say nothing regarding “Memhir Girma”
      I agree with all the rest facts.
      Almost more than half members narrow minded and MK-directed rather than EOTC-oriented.
      BUt I believe the importance of MK is only for the sake of empowering the church(as the objective of MK) not substituting it(as the real fact.)
      MAy the almighty blessed our beloved EOTChurch.

  14. Tesfaye October 7, 2013 at 10:35 am Reply

    GOD IS WITH US!

  15. Anonymous October 7, 2013 at 10:49 am Reply

    The move by the Government would be very destructive for both the Church and the Government. In this time, it has high value to be proactive than reactive. For the time being, I propose the following two measures to be taken by Mahibere Kidusan.

    1. Lobbying the Holy Synod to change the stand and move of the Government against Mahibere Kidusan. This may be made by a group of individuals from Mahibere Kidusan, Hagere Sibkets, scholars and other renowned individuals.

    2. If the government is able to silence the Holy Synod and the measures become inevitable, Mahibere Kidusan shall immediately look the opportunities to move its head Office and assets to Europe or America. I think, there will be a chance to work for the church by reestablishing itself in foreign country. Internet based communication can be a means to contact with its members herein Ethiopia.

    • Anonymous October 8, 2013 at 2:10 am Reply

      ቱልቱላ መናፈቅ

      • Anonymous October 16, 2013 at 7:38 am

        What do you mean by tultula menahiq? I guess you are one of those morons who work day and night to destruct th church and Mahibere Kidusan….

  16. Anonymous October 8, 2013 at 10:34 am Reply

    ብስልጣን ላይ ያለው ስብስብ በመሰረቱ ኢትዮጲያዊነትን የተላበሰ አይደለም። ሃይማኖቱም ስልጣንና ገንዘብ ነው። በሚያራሚደው በማር የተለወሰ ጸረ ኢትዮጲያ አቁዋም ካልተጠመክና ከጸበሉ ካልተጎነጨህ፣ አንተ ሽብርተኛ ነህ። እኔን እስካልነካ የሚል የጨዋታ ስሌት በዚህ የስልጣን ስብስብ አይሰራም። በ ፳፪ ዓመት የሥልጣን ዘመኑ ያየነውም የሁሉንም ቤት ሲደፍር፣ሲያዋርድ፣ሲያስርና ሲገድል ነው። በኣገራችን ብሎም በዕምነታችን እንድንኖር በኣሁን ጊዜ ያለው ብቸኛው መፍትሔ በስልጣን ላይ ያለውን ስብስብ በቃህ ማለት ብቻ ነው። ምንም ደም ሳይፍስ ይህንን በስልጣን ላይ ያለ ስብስብ ለማስወገድ ህቡ ተደራጅቶ መታገል ነው።

  17. Seyoume October 8, 2013 at 10:36 am Reply

    ብስልጣን ላይ ያለው ስብስብ በመሰረቱ ኢትዮጲያዊነትን የተላበሰ አይደለም። ሃይማኖቱም ስልጣንና ገንዘብ ነው። በሚያራሚደው በማር የተለወሰ ጸረ ኢትዮጲያ አቁዋም ካልተጠመክና ከጸበሉ ካልተጎነጨህ፣ አንተ ሽብርተኛ ነህ። እኔን እስካልነካ የሚል የጨዋታ ስሌት በዚህ የስልጣን ስብስብ አይሰራም። በ ፳፪ ዓመት የሥልጣን ዘመኑ ያየነውም የሁሉንም ቤት ሲደፍር፣ሲያዋርድ፣ሲያስርና ሲገድል ነው። በኣገራችን ብሎም በዕምነታችን እንድንኖር በኣሁን ጊዜ ያለው ብቸኛው መፍትሔ በስልጣን ላይ ያለውን ስብስብ በቃህ ማለት ብቻ ነው። ምንም ደም ሳይፍስ ይህንን በስልጣን ላይ ያለ ስብስብ ለማስወገድ ህቡ ተደራጅቶ መታገል ነው።

  18. Anonymous October 8, 2013 at 12:59 pm Reply

    egziabehre meftehewen yametalen

  19. Anonymous October 8, 2013 at 1:03 pm Reply

    Geta yawkal

  20. Mulugeta B October 10, 2013 at 8:16 am Reply

    ምን እናድርግ

  21. Anon October 15, 2013 at 3:04 am Reply

    MK IS THE ORTHODOX VERSION OF EXTREMISM IT SHOULD BE DISMANTLED

  22. Anonymous October 16, 2013 at 5:53 am Reply

    How can u dismantel this organization(MK) which stands with the help of GOD. Pls don’t try or don’t play with fire.

  23. Anonymous October 19, 2013 at 7:55 am Reply

    ምኑ ግራ የገባህ ?ለጥያቄ ነው ወይስ አንተ ራስህ ግራ የተጋባህ መሆን ነህ? በግልፅ አቅዋሙ የሚታወቅ በቤተክርስቲያን ስር ያለ በቅዱስ ሲኖዶስ ድንብና መመሪያ ተዘጋጅቶለት ለቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት የሚለፋ ወይም የሚተጋ በተደጋጋሚ እንዲፈርስ በጠላት ስይጣንና አስፈፃሚዎች የሚሴርበት ነገር ግን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በፃድቃንና በቅዱሳን ፀሎትና ምልጃ በመላእክት ተራዳይነት በ እግዚአብሔር ፈቃድ የቆመ ፍፁም ሠላማዊና መንፈሳዊ ሥራ የሚሰራ ማኅበር ነው

  24. Anonymous February 2, 2014 at 3:12 pm Reply

    Ke Egziabher Serawit gar man tewagito Yashenifal!!…Esu Sile Kidus Simu Yiwagalna!!
    “””Egziabher Hagerachinina Mahibere Kidusanin Yitebikiln”””

Leave a comment