ለስሕተታቸው ሊቃነ ጳጳሳትን ይቅርታ የጠየቁ ግለሰቦች ጉዳይ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ቀኖና በጠበቀና ባገናዘበ መልኩ ሊወሰንበት ይገባል!

በቤተ ክርስቲያናችን ዐውደ ምሕረት ሰፍነውና በቢሮክራሲዋ ውስጥ ተሰግስገው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን ለሚያራምዱ ድርጅቶች ተልእኮ አስፈጻሚና የቅስቀሳ ኃይል የኾኑ ሕገ ወጥ ቡድኖችና ግለሰቦች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመመከት በኦርቶዶክሳዊ ቀናዒነትና በበጎ ፈቃድ ተሰባስቦ በጥቅምት ወር ፳፻፫ ዓ.ም አገልግሎቱን የጀመረው የፀረ – ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሰባክያንና ዘማርያን ጥምረት÷ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ወቅታዊ ጉዳዮችን የገመገመበትንና ቀጣይ የአገልግሎት አቅጣጫዎችን የተለመበትን የግማሽ ቀን ውይይት አካሂዷል፡፡

ከጥምረቱ መምህራን አንዱ የኾኑት መ/ር ያረጋል አበጋዝ÷ ‹‹ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የወጡ(ያፈነገጡ) ሰዎች የሚመለሱት እንዴት ነው?›› በሚል በመድረኩ ያቀረቡት ጽሑፍ የውይይቱ ዋነኛ መነሻ ነበር፡፡ የጽሑፉን ዋና ዋና ክፍሎችና ተያያዥ ሐሳቦች በማስቀደምና ሙሉ ይዘቱን በማስከተል አቅርበነዋል፡፡ እንዲመለከቱት ተጋብዘዋል፡፡

*             *           *

የቤተ ክርስቲያን የአንድነቷ መሠረት ሃይማኖት ነው፡፡ ይህ ሃይማኖት ደግሞ ከእግዚአብሔር የተሰጠ አንድና ብቸኛ እውነት ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ የሰጠውን የመዳን ጸጋ ሰዎች በሃይማኖት ዐውቀውና ተረድተው ይጠቀሙበት ዘንድ፡- የምሥራቹን ለዓለም ሁሉ የመናገር(የማስተማር፣ የመግለጥ)፤ ያመኑትን ምእመናን የመጠበቅና ምስጢራትን የመፈጸም፤ በራሳቸው ስንፍናና በመናፍቃን ቅሰጣ ከበረቷ የጠፉትን የመፈለግ፤ ኑፋቄ በተባለ የእምነት በሽታ የታመሙትንና የተለከፉትን የማከምና የማይድኑ ከኾነ ስለመንጋው ጤንነትና ስለ መናፍቁ በጎ ስትል እያዘነች በውግዘት የመለየት ተግባር አላት፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት ወካይና መገለጫ ናት፡፡ ስለዚህ በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ተቀላቅሎና ተመሳስሎ መግባት እንደሌለ ሁሉ በዚህ ዓለም ያለችው ቤተ ክርስቲያንም የዚያ ወካይና መገለጫ ናትና የእርሷ ወገኖች ያልኾኑትን ትለያቸዋለች እንጂ፣ ጭፍን የምድራዊ መንግሥት ካድሬዎችና በመንግሥት የፀረ – አክራሪነት አጀንዳ ስም ስሑታኑ ከእነ ኑፋቄያቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ተመልሰው እንዲገቡና የልዩ እምነት ፍላጎታቸው የኾነውን የቤተ ክርስቲያናችንን መዳከምና መከፈፋል እንዲያሳኩላቸው ‹‹የአስተምህሮ መቻቻል ዴሞክራሲ›› ከንቱ ፕሮፓጋንዳ እንደሚነዙት አንዳንድ ባለሥልጣናት በዝምታ ወይም በግዴለሽነት አታዝላቸውም!!!

አንድ ምእመን በቤተ ክርስቲያን የሚኖረው በእውነትና በሃይማኖት እስከተገኘ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ያን እምነትና እውነት ሲክድና ሌላ ባዕድ ነገር ውስጥ ሲገባ ግን ያንጊዜውኑ ከቤተ ክርስቲያን ራሱን በራሱ ያወጣል! በራሱ ድርጊት ራሱን ከድኅነት ውጭ ያደርጋል!! በመኾኑም በዚህ ዓለም ያለችው ቤተ ክርስቲያን አውግዛ የምትለየው ቀድሞውንም ራሱን በኑፋቄ አስተሳሰቡና ድርጊቱ ከቤተ ክርስቲያን የእውነት መሠረትና ዓምድ የለየውን ሰው ነው፡፡

ከቤተ ክርስቲያን ትምህርት ግልጽ ተቃርኖ የያዘ ኑፋቄ ሁሉ በአጠቃላይ የተወገዘ ነው፡፡ የታወቀና የተወገዘ ኑፋቄ ይዘው የሚነሡ ሰዎች አዲስ ነገረ ሃይማኖታዊ ውይይት አያስፈልጋቸውም፤ በቀደመው ውግዘት እስከ ዕለተ ምጽአት የሚነሡት ሁሉ ተወግዘዋልና፡፡ ለእንዲህ ዐይነቱ ኑፋቄ የሚያስፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ እርሱም፡- ያን ኑፋቄ የሚያራምደው ግለሰብ በትክክል ያን ኑፋቄ መያዝ አለመያዙን፣ የሚመለስ መኾን አለመኾኑን ማረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ከተረጋገጠ በኋላ ያ ሰው ከቤተ ክርስቲያን መለየቱ(ማውገዙ) በአጥቢያ ሰበካ ጉባኤ ወይም በአገረ ስብከት ደረጃ ሊፈጸም ይችላል፡፡

ከቤተ ክርስቲያን በኑፋቄ ተወግዘው (ይፋዊ በኾነ ውግዘት ይኹን ራሳቸውን በኑፋቄ በመለየታቸው) የተለዩ ሰዎች የመመለሳቸው ዜና ታላቅ የምሥራች ነው!! ከኑፋቄያቸው እንዲመለሱ የቤተ ክርስቲያን ናፍቆቷና ምኞቷ ነው፡፡ ቀድሞም እንዲወገዙ የሚደረገው፣ ነፍሳቸው በምጽአት ቀን እንድትድን ራሳቸው ሰዎቹን ለመርዳት ሲባል እንጂ እንዲጠፉ አይደለም፡፡ ስለኾነም በኑፋቄያቸው ጠፍተው ሲባዝኑ የቆዩቱ ስሕተታቸውን በርግጥ አምነው ወደ እናት ቤተ ክርስቲያናቸው ከመመለሳቸው የበለጠ ደስታ የለም፡፡

ነገር ግን፣ መናፍቃን የነበሩ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንመለሳለን ሲሉ ሊደረጉ የሚገባቸው ዋና ዋና ጥንቃቄዎች እና ተግባራት አሉ፡፡ እኒህም፡-

  • እንመለሳለን የሚሉት ሰዎች በትክክል ከልባቸው ነው? ወይስ በንስሐ፣ ዕርቅና ይቅርታ ሰበብ እንደ ግብር አባቶቻቸው እንደ አርዮሳውያንና እንደ ሕንድ ማር ቶማ ቸርች ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ተገንጣዮች ውስጥ ገብተው ለመበጥበጥና ለመከፋፈል ነው? የሚለውን በሚገባ ማጤን ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ እያንዳንዱ ምእመን ሊያተኩርበትና ግዴታውን ሊወጣ ይገባል፡፡
  • የጅምላ ንስሐ የለም! እንመለሳለን የሚሉ ወገኖችን ጉዳያቸውን በየግለሰቡ/እያንዳንዱ ጥፋቱ ምን እንደነበር፣ ለምን እመለሳለሁ እንዳለ፣ ወዘተ በዝርዝር መለየት፣ ማጥናትና መወሰን ይገባል እንጂ በጅምላ ከዚህ ወዲያ ወይም ከዚያ መለስ ብሎ ማድረግ አይገባም፡፡ ይህ እንመለሳለን ለሚሉትም ሰዎች፣ ለማኅበረ ምእመናኑም ጠቃሚና አስፈላጊ ነው፡፡ ያን ኑፋቄ ዳግመኛ ሲያስተምሩ ቢገኙ ማንነታቸውን በግልጽ ለመለየት ይጠቅማል፡፡

    Yared Ademe

    በዘማሪት ወ/ሮ ፋንቱ ወልዴ አቅራቢነት መስከረም ፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ሉቃስንና ብፁዕ አቡነ ገብርኤልን በመኖርያ ቤቶቻቸው ተገኝቶ ይቅርታ የጠየቀውና ይቅርታ በመጠየቁ ይዞት ከወጣው ጠርዘኛ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኝ ቡድን በተነሣበት ተቃውሞ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ዲ/ን ያሬድ አደመ

  • መናፍቃን ሲመለሱ በጓዳና ለሌሎች በማይታወቅ ኹኔታ ሳይኾን በግልጽ፣ ምእመናን ሁሉ በሚሰሙበትና በሚያውቁበት መድረክ በይፋ መኾን አለበት፡፡ በፊት የካዱት፣ ቤተ ክርስቲያንን ያሳጡትና የነቀፉት በይፋ እንደነበር ሁሉ ሲመለሱም በይፋ መኾን ይኖርበታል፡፡ መመለሳቸው በይፋ ከተደረገ፣ የቀድሞ ኑፋቄያቸውን እናስተምራለን ቢሉ እንኳ ‹‹ተመልሰናል ብላችሁ አልነበረምን? የቀድሞ ስሕተታችንን ትተናል ብላችሁ አልነበረምን?›› ብሎ ለመጠየቅና በቶሎ ማንነታቸውን ለማወቅ ይረዳል፡፡
  • የሚመለሱ መናፍቃን በእውነት ከመናፍቃን የተለዩና ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጋራ የተዋሐዱ ስለመኾናቸው አንዱ ምስክር የሚኾነው ከቀድሞ  ጀምሮ  የተነሡ  ዋና  ዋና  የኑፋቄ አመንጪዎችን  በይፋ  በማውገዛቸው  ነው፡፡ ስለኾነም በጥንቃቄ በተዘጋጀ የመናፍቃን ዝርዝር ላይ እነዚያን መናፍቃን ማውገዝና ለዚህም መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡ 
  • የሚመለሱ መናፍቃን እስከ ዛሬ ድረስ በስብከቶቻቸውና በመጻሕፍት ያስተማሯቸውንና የጻፏቸውን የኑፋቄ ትምህርቶች ሁሉ ቀድሞ ኑፋቄው ከተላለፈበት ልሳን (ሚዲያ) እና የሚዲያ ውጤቶች ዐይነትና ተደራሽነት ጋራ ተመጣጣኝ በኾነ መንገድ እንዲያወግዙና ስሕተት መፈጸማቸውን ተቀብለው ከአሁን በኋላ እንደዚያ ዐይነት የስሕተት ትምህርት እንደማያስተምሩ በጽሑፍ ቃል መግባት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም በተለያየ ጊዜና ቦታ በኑፋያሳሳቷቸው ሁሉ ስሕተታቸውን አምነው መመለሳቸውን እንዲረዱ፣ ወደ ስሕተታቸው ዳግመኛ በማይመለሱበትና በአስተማማኝ መልኩ ለመጥቀስና ምስክር ይኾንባቸ ዘንድ ነው፡፡
  • መናፍቃን ሲመለሱ በስሑት ትምህርታቸው የተነሣ ከእናት ቤተ ክርስቲያን ለመውጣታቸውና ለነፍሳቸው ጥፋት ምክንያት የኾኑባቸው ሰዎች እንዲመለሱ ጥረት ማድረግና መመለስ አለባቸው፡፡
  • የሚመለሱ መናፍቃን ከቀድሞ ጀምሮ የተነሡ ዋና ዋና የኑፋቄ አመንጪዎችን በይፋ እንዳወገዙ ሁሉ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተምህሮ የሚቀበሉ ስለመኾናቸውም ግልጽና ጠንቃቃ ቃለ ጉባኤ አዘጋጅቶ እንዲፈርሙ ማድረግ ይገባል፡፡
  • ፍትሐ ነገሥታችን ለሌላው ሰው ክሕደት ምክንያት የሚኾን ሰው ሲመለስ ቀኖናው ከበድ ያለ እንዲኾን ያዝዛል፡፡ ስለዚህ ተመላሾቹ ከበድ ያለ ቀኖና ተሰጥቷቸውና በነገረ ሃይማኖት የበሰሉ ሊቃውንት ተመድበውላቸው ከእነርሱ መማራቸው ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፡፡ ተመልሰናል የሚሉት ሰዎች መመለሳቸውና ንስሐቸው የእውነት መኾን አለመኾኑ የሚገለጥበትና የሚፈተንበት አንዱ መንገድም ይኽ ነው፤ የተመለሱት በእውነት ከኾነ ግድ እናስተምር፤ በመድረክ እንቀጥል አይሉም፤ ነገር ግን የተንኮልና የስልት ከኾነ መድረኩ ላይ ካልቀጠልን ብለው የሙጥኝ ይላሉ፡፡ እንመለስ የሚሉ ሰዎች ጭንቀታቸው መድረክ ላይ ስለ መዘመራቸውና ስለ መስበካቸው ከኾነ ጉዳዩ ዓላማን በውጭ ኾኖ ማስፈጸም ስለማይመች ወደ ውስጥ ገብቶ ተሐድሷዊውን ዓላማ ለማስፈጸም የአስገቡኝ ጥያቄ እንጂ የመመለስና የንስሐ ጥያቄ አይደለም ማለት ነው፡፡ ይኼ የድርድር እንጂ የንስሓ መንገድ አይደለም፡፡

    Begashaw Dessalegn

    በዘማሪት ወ/ሮ ፋንቱ ወልዴ አቅራቢነት መስከረም ፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ሉቃስንና ብፁዕ አቡነ ገብርኤልን በመኖርያ ቤቶቻቸው ተገኝቶ በግል ስላደረገባቸው መደፋፈር ይቅርታ የጠየቀውና ይቅርታ በመጠየቁ ይዞት ከወጣው ቡድን ጋራ ውዝግብ ውስጥ የገባው የቅ/ሲኖዶስ ፍርደኛ በጋሻው ደሳለኝ

  • የጠፉትን መቀበል ተገቢና መልካም ቢኾንም በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ ሂደት የሚደረገው እያንዳንዱ ነገር ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ አርቆ ማየት ያስፈልጋል፤ የተመላሾቹን ጭምብሎቻቸውን ገልጦ ትክክለኛ ማንነታቸውንና አደጋውን መረዳትና መለየት ያስፈልጋል፡፡ ‹‹ሰላም ሰላም›› በሚል ቃል ብቻ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያንን ውሳጣዊ ሰላም፣ እንዲሁም ጊዜያዊ ችግር የፈታንና ያቃለልን ሲመስለን ለወደፊቱ ችግር እያወሳሰብንና እያቆላለፍን እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ በቅርብ ጊዜ ከስድስቱ አኃት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ በኾነችው በሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የኾነውን አሳዛኝ ነገር ልንረሳው አይገባንም፡፡
  • ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደተማርነው፣ እንመለሳለን ባይ መናፍቃን የፖለቲካ ሰዎችንና ባለሥልጣናትን በመዘወርና ከጎናቸው በማሰለፍ በኩል ይዋጣላቸዋል፡፡ በኒቅያ ጉባኤ በቅዱሳን አባቶች ተወግዞ የተለየው አርዮስና የኑፋቄ ጓደኞቹ የተለያዩ ሰዎችን በመላክና በውስጥ ለውስጥ በሠሩት የፕሮፓጋንዳ ሥራ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ አርዮስን ከፈረደበት ከግዞቱ እንዲወጣና ወደ ቤተ መንግሥቱ እንዲመጣ ካደረጉ በኋላ ቅዱስ አትናቴዎስን ጨምሮ ኦርቶዶክሳውያን ጳጳሳትንና ካህናትን ከየመናብርታቸውና አብያተ መቅደሳቸው እያሳደዱ ሲፈነጩባቸው ኖረዋል፡፡ ዛሬም እውነተኛ ዓላማቸው የተነቃባቸው እንመለሳለን ባይ መናፍቃን፣ ለቤተ ክርስቲያናቸው ቀናዒ የኾኑ አገልጋዮችንና ምእመናንን የመንግሥት የወቅቱ አጀንዳ በኾነው የፀረ አክራሪነት እንቅስቃሴ ተሸፍነው በጽንፈኝነት ውንጀላ ማሸማቀቃቸው የባሕርያቸው ነው፡፡
  • እንመለሳለን ለሚሉ ግለሰቦችና ቡድኖች በሽምግልና ይኹን በአጣሪነት ከሚሳተፉ ሰዎች አንዳንዶቹ፣ ‹‹ዕርቅን ማን ይጠላል? ይቅርታና ሰላም ምን ክፋት አለው›› በሚሉ መሸፈኛዎች ከመታለልና ከማታለል መጠበቅ ይገባቸዋል፡፡ ይልቁንስ ይቅርታ ጠያቂዎቹና እንመለሳለን ባዮቹ ከጠየቁት ጉዳይ ጋራ በተያያዘ ምን እያደረጉ እንደነበርና ምን በማድረግ ላይ እንደኾኑ ለመመርመር ብስለቱና ቅንነቱ ሊኖራቸው ያስፈልጋል፡፡
  • ራሳቸውን በአስታራቂነት ጎራ መድበው፣ እነርሱ ከሌሎቹ የተሻሉ አስተዋዮችና ያላከረሩ ብልሆች እንደኾኑ አድርገው ራሳቸውን የሚቆጥሩ ሰዎች÷ አስታረቁ ተብለው ስም ለማሰርና ጀብድ እንደሠሩ ለመቆጠር፣ በስሕተቱ ተለይቶ የወጣውን አካል በሽፍንፍን በመመለስ በሌሎች አጀንዳዎች ከተቀየሙት አካል በተፃራሪ በወደረኛነት በማሰለፍና ጎልቶ በመታየት እንበቀላለን ብለው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ይኸው ፍላጎታቸው ሊጋለጥ ደረጃቸውን ዐውቀው አድበው እንዲቀመጡ ሊደረግ ይገባል!!

38 thoughts on “ለስሕተታቸው ሊቃነ ጳጳሳትን ይቅርታ የጠየቁ ግለሰቦች ጉዳይ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ቀኖና በጠበቀና ባገናዘበ መልኩ ሊወሰንበት ይገባል!

  1. Birhan Bihil October 4, 2013 at 8:02 pm Reply

    ቤተክርስቲያንን የተዳፈረ የበደለ ይቅርታ መጠየቅ ያለበት በይፋ ቤተክርስቲያንዋን ነው ወይስ በአንድ ሰው አማላጅነት ሁለት አባቶችን ብቻ…. ነገሩ ወዴት ወዴት ነው…. በሃይማኖታችን እንዲህ ዓይነት ቀልድና ስላቅ ሰምተንም አናውቅም ..አስታራቂዋ እህታችን የቤተክርስቲያንዋ ሥርዓት ሳታውቀው ቀርታ ነው አባቶች መርጣ ወዳጆችዋን ይዛ በጓዳ የገባችው ርተኛ የምታስታርቅ መሰላት እንዴ
    .ስለዚህ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱንም ሆነ ሁሉንም የቤተክሲያንዋን መዋቅሮች ለምዳቸውን ለብሰው ሲያምሱት የኖሩትን አሁን የይቅርታ ልብ ይዘው ከመጡ አያጡትምና ሁሉም በሥርዓቱ ይሁን…. የጥፋታቸው አድማስ እኮ አንድ ቦታና ቤተክሲያን ብቻ አልነበረም ዓለም አቀፍ እንጂ… ሃራ…ምከሩዋቸው…እውነት ነው ሥርዓቱን ላያውቁት ይችላሉ ምክንያቱም ተኩላዎች እንጂ በጐች አልነበሩምና ተኩላ ደግሞ ሥርዓት እንዲያውቅ አይጠበቅበትምና …ሥርዓቱን የሚያቁትና ሥርዓቱን የሚያስፈጽሙት ግን በሃይማኖታችን ባይቀልዱ መልካም ነው እንላለን፡፡

  2. Birhan Bihil October 4, 2013 at 8:14 pm Reply

    የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ከፊት ይልቅ አሁን ልንተጋ ይገባናል!!…. አካሄዳቸው መግቢያ ቀዳዳ ፍለጋ ሊሆንም ይችላልና ምክንያቱም ከተለዩ በኋላ በቅርቡ እንደሰማናቸው አንዴ ጨለመብን አንዴ ዝክረ እንትና ወ እንትና እያሉ በቤተክሲያናችን ውስጥና በስሟ ተመሽገው ዓላማቸውን ሊያሳኩ ቢጥሩም ሳይሳካላቸው በመቅረቱ ይቅርታን እንደ አማራጭ ሊጠቀሙበት አስበው ሊሆን ስለሚችል መጠርጠሩ አይከፋም ….

    • Anonymous November 8, 2013 at 2:04 pm Reply

      ስለ እግዚአብሔር እስቲ እንንጋገር መናፍቅ ማለት እናንተ ናችሁ ወይስ በይፋ ለሕዝብ ወንጌል የሚያስተምሩ! መናፍቅ ማለት ተጠራጣሪ ማለት ከሆነ የጌታችንን የማዳን ስጦታና ለምኖ የመቀበል በረከት የምትክዱ፤ በቀጥታ በስሜ ለምኑ ይሰጣችሁዋል ስትባሉ ፍጡር ወይም መልአክ ካላማለደኝ ካንተ ጉዳይ የለኝም የሚል፤ ያጎረሰዉን እጅ የሚነክስ ከእናንተ ሌላ ማን ሊመጣ ነዉ፤ እባካችሁ እቤታችሁ ዉስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ደንገት ካለ በየቀኑ አንዳንዳንድ ዘለላ ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ ብታነቡ በእዉቀት ላይ ካልተመሰረተ ንትርክና ሃጢያት ዉስጥ ከመግባት ራሳችሁን አዉጡ፤ ይህንን ስል መልሳችሁ አንድና እንደ ነዉ፤ መናፍቅ

  3. Anonymous October 5, 2013 at 2:34 am Reply

    እነዚህ የሰይጣን ተላላኪዎች ዛሬ ደሞ በሌላ አሰመሳይ ለሰይጣን በሚሰራ በኩል መምጣታቸው ይገርማል የቤተክርስቲያን የሆነንን የሚጠላ እርሱ መናፈቅ ነው ስለዚህ የአስታራቂዎቹ ማንነትስ ቢፈተሽ ምን እንደሆነ ለማወቅ ያጉዋጉዋል::በጣም የሚያሳዝነው በአማላጅነት ለምን መምጣት አስፈለገ?መቶ በመቶ እርገጠኛ ሆኘ መናገር እችላለሁ ድጋሚ ቤተክርስቲያንን ለማመስ መሆኑን አልጠራጠርም ::ተኩላ መናፍቅ ሁላ

    እግዚአብሔር ሀገራችንንና ቤተክርስቲያንን ይጠብቅ ::አባቶቻችንንም ልቦና ይስጣችው ::

    • Anonymous October 8, 2013 at 8:34 am Reply

      ለጠላትህ እንኳ ይቅርታ ማድረግ አለብን አይደል እንደ! ምን ዓይነት ሰው ነህ አንተ! የሚሳደብ አፈፍ ይዘጋ!!

  4. Befekadu October 5, 2013 at 5:21 am Reply

    Wisanew betkrstianin begudat yelebetim nisha kemer aydelem

  5. Mengaw October 5, 2013 at 6:08 am Reply

    መናፍቃን/ተሃድሶ መናፍቃን/ ብሎ መፈረጅ ያለበት መወሰን ያለበት ማን ነው ማቅ፤የፀረ – ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሰባክያንና ዘማርያን ጥምረት፤ሰ/ት/ቤቶች ወይም አባ ገብርኤልና አባ ሉቃስ /የማቅ አቀንቃኞቹ ይመስሉኛል ካልሆኑ ይቅረታ/ ናቸው። አይደሉም በበቂ ማስረጃና በቀኖና ቤተክርስቲያን መሰረት ቤተክርስቲያን የሚወክለው የበላዩ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው።እናንተ ታድያ ምን ባዮች ናችሁ ደግሞስ ቤተክርስቲያን መካፋፈል አይሆነባቹም ም/ቱም እነዚህ ሰዎች ማስረጃ ሳይቀርብባቸው፤ሰይጠየቁ፤ ሳይመከሩ፤ ሳይወሰንባቸው መናፍቃን ናቸው ብሎ መወሰን ያሰኬዳል አይመስለኝም። እነዚህ ሰዎች ብዙም አላውቃቸውም ግን በሚያቀጡት መዝሙርና በEBS አልፎ አልፎ አያቸዋሎሁ ሊቅ የመምሰል ድፍረት ካልሆነ በስተቀር የሃይማኖት ህጸጽ አላየሁባቸውም ካለ ግን ለግል ግንዘቤየ እንዲረዳኝ በEmail ብትልኩልኝ ደስ ይለኛል።በተረፈ ዘማሪዋ ተፈፀመችው የማስታረቅ ተግባር ያስመሰግናታል እንጂ አያስወቅሳትም።

    • Anonymous October 6, 2013 at 7:39 am Reply

      wondimachin… anbib, kuch bileh temar,,,, zim bilo mezelabed ke-Egziabhaire yileyhal…

      • ገ/ሚካኤል October 7, 2013 at 7:36 am

        andebetachihun teqotateru christianoch kehonachihu Yekrstina nigigire ena astesaseb yinurachihu.
        Erq yemitela Diablos bicha new.
        Kesash Diablos bicha new.
        Yesidib af Yetesetew le Diablos bicha new
        Feraj Egziabher bicha new.
        May The Almighty save our beloved EOTC from ignorants and enemies.

  6. Mengaw October 5, 2013 at 6:14 am Reply

    መናፍቃን/ተሃድሶ መናፍቃን/ ብሎ መፈረጅ ያለበት መወሰን ያለበት ማን ነው ማቅ፤የፀረ – ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሰባክያንና ዘማርያን ጥምረት፤ሰ/ት/ቤቶች ወይም አባ ገብርኤልና አባ ሉቃስ /የማቅ አቀንቃኞቹ ይመስሉኛል ካልሆኑ ይቅረታ/ ናቸው። አይደሉም በበቂ ማስረጃና በቀኖና ቤተክርስቲያን መሰረት ቤተክርስቲያን የሚወክለው የበላዩ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው።እናንተ ታድያ ምን ባዮች ናችሁ ደግሞስ ቤተክርስቲያን መከፋፈል አይሆነባቹም ም/ቱም እነዚህ ሰዎች ማስረጃ ሳይቀርብባቸው፤ሳይጠየቁ፤ ሳይመከሩ፤ ሳይወሰንባቸው መናፍቃን ናቸው ብሎ መወሰን ያሰኬዳል? አይመስለኝም። እነዚህ ሰዎች ብዙም አላውቃቸውም ግን በሚያቀጡት መዝሙርና በEBS አልፎ አልፎ አያቸዋሎሁ ሊቅ የመምሰል ድፍረት ካልሆነ በስተቀር የሃይማኖት ህጸጽ አላየሁባቸውም ካለ ግን ለግል ግንዘቤየ እንዲረዳኝ በEmail ብትልኩልኝ ደስ ይለኛል።በተረፈ ዘማሪዋ ተፈፀመችው የማስታረቅ ተግባር ያስመሰግናታል እንጂ አያስወቅሳትም።

  7. Anonymous October 5, 2013 at 7:21 am Reply

    to be seen carefully!!!

  8. Selomie October 5, 2013 at 9:52 am Reply

    “ራሳቸውን በአስታራቂነት ጎራ መድበው፣ እነርሱ ከሌሎቹ የተሻሉ አስተዋዮችና ያላከረሩ ብልሆች እንደኾኑ አድርገው ራሳቸውን የሚቆጥሩ ሰዎች÷ አስታረቁ ተብለው ስም ለማሰርና ጀብድ እንደሠሩ ለመቆጠር፣ በስሕተቱ ተለይቶ የወጣውን አካል በሽፍንፍን በመመለስ በሌሎች አጀንዳዎች ከተቀየሙት አካል በተፃራሪ በወደረኛነት በማሰለፍና ጎልቶ በመታየት እንበቀላለን ብለው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ይኸው ፍላጎታቸው ሊጋለጥ፣ ደረጃቸውን ዐውቀውና አድበው እንዲቀመጡ ሊደረግ ይገባል!!”

  9. BB October 5, 2013 at 4:09 pm Reply

    seratun Yetbke geletse yehon yeyikerta sen serat medreg alebet!!

  10. Anonymous October 5, 2013 at 4:23 pm Reply

    Yikir mebabal tegebi new neger gin lenezih lijoch lela yemebetbet edili mestet tegebi ayidelemina tetenkekuachew

  11. Anonymous October 5, 2013 at 5:49 pm Reply

    ይቅርታ ማለታቸው ደስ የሚያሰኝ ሆኖ ሳለ ሂደቱ ግን የሲኖዶሱ ውሳኔ ከታወቀ ቦሃላ መሆን አለበት ፡፡ ይህ ክህደት ግለሰቦችን ማስቀየም ብቻ ሳይሆን የሀይማኖት ክህደት ስለሆነ እርቁ ቢፈቀድ እንክዋ የስርዐተ ቤተክርሰቲን ደንብ በተከተለ መልኩ ብቻ ሆኖ በቀኖና ቤተክርሰቲን እና ያጠፉትን ጥፋት አምነው የከፋፈሉትን ሕዝብ በይፋ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው ፡፡ ቢሆንም ግን እነዚህ ጡት ነካሾች / መናፍቃን የተመለሱት ጥቅማቸው ስለጎደለ /ለሌላ ነገር ሊሆን ስለሚችል የቤተክርቲያን አባቶች በየዋህነት ብቻ ሳይሆን በማስተዋል ጉዳዩን ሊያዩት ይገባል ፡፡ የተዘናጋ እረኛ በጎቹን ለተኩላ ያጋልጣልና እባካችሁን በሀላፊነት ያላችሁ አባቶች ለመንጋው ተጠንቀቁ ፡፡
    ነገር ግን ከእንግዲህ በየትኛውም መድረክ ልናያቸው አንፈልግም ፡፡
    በሀገር እና በሀይማኖት ቀልድ የለም !!!

  12. Yohanis October 5, 2013 at 6:00 pm Reply

    ይቅርታ ማለታቸው ደስ የሚያሰኝ ሆኖ ሳለ ሂደቱ ግን የሲኖዶሱ ውሳኔ ከታወቀ ቦሃላ መሆን አለበት ፡፡ ይህ ክህደት ግለሰቦችን ማስቀየም ብቻ ሳይሆን የሀይማኖት ክህደት ስለሆነ እርቁ ቢፈቀድ እንክዋ የስርዐተ ቤተክርሰቲን ደንብ በተከተለ መልኩ ብቻ ሆኖ በቀኖና ቤተክርሰቲን እና ያጠፉትን ጥፋት አምነው የከፋፈሉትን ሕዝብ በይፋ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው ፡፡ ቢሆንም ግን እነዚህ ጡት ነካሾች / መናፍቃን የተመለሱት ጥቅማቸው ስለጎደለ /ለሌላ ነገር ሊሆን ስለሚችል የቤተክርቲያን አባቶች በየዋህነት ብቻ ሳይሆን በማስተዋል ጉዳዩን ሊያዩት ይገባል ፡፡ የተዘናጋ እረኛ በጎቹን ለተኩላ ያጋልጣልና እባካችሁን በሀላፊነት ያላችሁ አባቶች ለመንጋው ተጠንቀቁ ፡፡
    ነገር ግን ከእንግዲህ በየትኛውም መድረክ ልናያቸው አንፈልግም ፡፡
    በሀገር እና በሀይማኖት ቀልድ የለም !!!

  13. Anonymous October 5, 2013 at 6:06 pm Reply

    በጣም መታሰብ አለበት ቢመጡም ለቤተክርስቲያን ምንም አይጠቅሙም ፡፡ የበሉት ይበቃል ሳያውቁ አዋቂ ያደረግናቸው እኛ ነን መድረኩን ሰጠናቸው እንደፈለጉ አደረጉት ነገር ግን ያሰቡትን ያህል ሰው ስላላገኙ በይቅርታ ሽፋን ተመልሰናል ብለው እራሳቸውን ደብቀው ከውስጥ ለመበጥበጥ ነው ፡፡ በቀላሉ ቅዱስ ዬሴፍ ቤተክርስቲን እስካሁን መፍትሔ ሳይሰጠው ያለ ጉዳይ ነው ሲኖዶሱ እርሱን ቢያስተካክል ይበጃል፡፡

  14. Anonymous October 5, 2013 at 7:05 pm Reply

    ማንም የማንንም መጥፋት የሚፈልግ የለም፡፡ ነገር ግን ፍትህ መንፈሳዊ አለና ሊቀጡ ይገባል፡፡ አንድ ሰው በንግግሩ ማፈንገጡ ይታወቀል፡፡ ሲመከር ካልሰማ ከአውደ ምህረት እንዲርቅ ይደረጋል፡፡ ራሱን ከለየ ለየ ካለየና በአውደ ምህረት መቆም አለብኝ ብሎ ተከታዮቹን ቢያሳምጽ ጉዳዩ እስከ ላይ ሄዶ ሊታይ ይችላል፡፡ የነዚህ ሰዎች ጉዳይ ሲኖዶስ አይደለም ያየና የሰማም ሰው ይፈርድባቸዋል፡፡ በተለያየ ሚዲያ የሚናገሩትም ምስክር ነው፡፡ አሁን በጣም ሃብታም ሆነዋል፡፡ ቤተ ክርስቲናቸውን ተጠቅመውባት የተለዩ ሆነዋል፡፡
    በመናፍቃን እርዳታ በኢቢኤስ ፕሮግራም አላቸው እዚህ ግን ባስተማሩና በዘመሩ ቁጥር ቀለቀል ብር አይጠይቁም፡፡ የተለያዩ ካሴቶችን መጽሄቶችን ሳያስመረምሩ ከነኑፋቄያቸው ሰዎች እጅ ገብቶዋል፡፡ እነዚህን ነገሮች በሊቃውንት ጉባኤ ታይተው እንዲገመገሙ ችግራቸውም እንዲነቀስ ተደርጎ ማስተባበያ በሚጠቀሙበት ካሴት በኢቢኤስ ቲቪ በጋዜጣ (በዜና ቤተክርስቲያን በመሰሉ) እራሳቸው እንዲያስተባበሉ ማድረግ፡፡ ከዚህ በሁዋላ የሚሰሩትን የግሩፕ ስራ እንዲቀር ማድረግ፡፡ ለአገልግሎትም መንቀሳቀስ እንዳይችሉ ቢያንስ ቀኖና እንዲወስዱ በግል ስራ ላይም ቢሰማሩ መልካም ነው፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በሁዋላ አውደምህረት ላይ ለመቆም ሞራሉም የላቸውም፡፡ እንደማንኛውም ሰው መገልገል እንዲችሉ ቢደረግ፡፡
    ቤተክርስቲያናችን አሁን ይዛው ያለውን ሰላም ይዛ እንድትቀጥል ቢደረግ ጥሩ ነው፡፡ መናፍቃን እድላቸውን የሚያጡበት ስለሚሆን ሊናደዱ ይችላሉ፡፡ በተለይ ማህበረ ቅዱሳን ላይ እጃቸውን ሲቀስሩ ይታያል፡፡ እነዚህ ሰዎች ዝም ተብለው ቢታዩና ምንም እርምጃ ባይወሰድ ኖሮ ይችን ቤተክርስቲያን ከመበታተን ወደ ሁዋላ አይሉም ነበር፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ ታወቀባቸው፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ በሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ጥረት ነው እንጂ በግለሰብና በማህበር አይደለም፡፡ ማህበሩ ቤተክርስቲያንዋ ይዛው ልትኖር የሚገባውን ነገር እንድትይዝ ለማድረግ የተቁዋቁዋመ በመሆኑ ማንም ከዚህ ሊገታው አይችልም፡፡ ድጋፍ በጭፍን አይሆንም ማህበሩን ሊያስመሰግን የሚችል አንዱ ድሉ ይህ ነው፡፡
    አንድ አንዱ ዘማርያን አሜሪካን በመሄድ ኑሮዋቸውን እያደላደሉ ናቸው፡፡ ቤተክርስቲን ግን የምታበራው ጡዋፍ በየገጠሩ እያጣች ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ በሁዋላ ቤተክርስቲያንን መጠቀሚያ መሆንዋ እንዲቀር መሆን አለበት፡፡ የነሱ ዘማርያን እኮ ጌታን በብር ነው የሚያመሰግኑት ለምን ቢባል ስብከቱም ዝማሬውም በክፍያ ነውና፡፡ እያንዳንዱ ዘማሪ በየትኛውም ቦታ ተከፍሎት እንደሚመጣ ልናውቅ ይገባል ያውም ለአንድ የገጠር ካህን የወር ደሞዝ የሚሆን፡፡ ይህ ክፍያ የተጀመረው በነዚሁ ቡድኖች እንደሆነም ልናውቅ ቀገባል፡፡ ዘፋኝዋ ዘመረች ህጻንዋ ዘመረች አይነ ስውሩ ዘመረ የመሳሰሉትን በማለት እራሳቸውን አደራጁ ህዝቡን በዘበዙ፡፡ ሚሊየነርም ሆኑ ስለዚህ እረፉና እንደ ምእመን ተቀመጡ ሊባሉ ይገባቸዋል፡፡

  15. Anonymous October 5, 2013 at 7:05 pm Reply

    በበጎ ፈቃደኝነት ተጣምሮ የቅድሰት ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ደኅንነት ተከብሮ እንዲኖር የሚተጋው የሰባክያን ኅብረት በግልና በጥምረት የሚደርስበትን ፈተና ታግሶ ትግሉን መቀጠሉ ይበል ያስብለዋልግን ተጀመረ እንጅ አላበቃምና ጥብቅናውን ይቀጥል እላለሁበተረፈ ሐራ ያቀረብሽው አሳብ የጋራችን አሳብ ነውና እንዲህ አይነቱን ሊቃውንታዊና ሃይማኖታዊ ዘገባሽን አጠናክረሽ ቀጥይ

  16. Anonymous October 5, 2013 at 7:51 pm Reply

    ይህቺ እሩጫ ለምን እንደሆነ ባይገባኝም አካሄዱ ግን በደንብ ሊጤን ይገባዋል፡፡ ጳጳሳቱን በግል ማናገር ምን ይዞ ይመጣል ብንል በሲኖዶስ ስብሰባ ወቅት ሲነጋገሩበት ሁሉም የለዘበ ሃሳብ ይዘው እንዲገቡ ለማድረግ ነው፡፡ ከአቡነ ገብርኤል መልስ እንኩዋን ብንመለከት እኔ በግሌ ይቅር ብያለሁ ማለታቸው ቀድመው ምንም አደረጉ ምን ነገሮች እንዲለዝቡ እድል የሰጠ ነው፡፡ ጠንከር ያለ ክርክርና ቁርጥ አቁዋም እንዳወሰድም እንቅፋት ነው፡፡ አቡነ ገብርኤልን ያክል የፈተኑት ባይኖርም ሁሉም ደርሶዋቸዋል ማለት ግን ይቻላል፡፡ በቤተክርስቲያንዋ ቀደም ሲል ይቅርታ ጠይቀው የነበሩ ሁዋላ ግን በዛው ስራ ላይ ገኝተው የተሰናበቱት ጥቂት ሃይማኖተ አበው ማህበር የነበሩ አይነት እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡ ጳጳሳቱ በሊቃውንት ጉባኤ ያስመረመሩትን ስብከቶቻቸውን መዝሙሮቻቸውን በመመርመር ውሳኔ በመጀመሪያ መስጠት የግድ ነው፡፡ ግድፈት የበዛው ከሆነ ነገሩን የሰራው ሰው እንደገና እርምት እንዲሰጥ ማድረግ ነው፡፡ ከአውደምህረት እንዲርቁ ማድረግ ምክንያቱም ከዚህ በሁዋላ ለማገልገል ሞራሉም የላቸውም፡፡ ባገኙት ሃብት ኢንቨስት አድርገው ቢቀመጡ ጥሩ ነው፡፡ አስታራቂዋም ነገሮችን በበጎ ማየት ይኖርባታል፡፡ ነገ ለሚመጣው ማንኛውም ችግር ተጠያቂነት እንዳለበት ማወቅ አለበት፡፡

    • hiruy October 7, 2013 at 9:11 am Reply

      እናንተ እነሱን ከሲኖዶስ ውሳኔ በፊት ተሀድሶ/መናፍቅ የማለት መብት/ድፍረት ከየት አገኛችሁ?????
      ይቅርታ ጠየቁ ያላችሁበት ዘገባ ይቅርታቸውን ስለሁከቱ እንጅ ስለሃይማኖት ህጸጽ እንዳቀረቡ አያሳይም.በሌላ አነጋገር የሃይማኖት ችግር አለብን ብለው አላመኑም.
      አቀራረቡ ሊበሉአት ያሰቡዋትን ጅግራ….ይመስላል
      የሸመገለቻቸዉን ዘማሪስ ያን ያህል ክፉ እንደሰራች መወንጀል ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ጌታን ከዲያብሎስ ለማስታረቅ ያረገችዉን ተጋድሎ እየሰማ ካደገ ምዕመን የሚጠበቅ ነዉን??

  17. Matiwos Aschalew Bisetegn October 6, 2013 at 5:24 pm Reply

    እርቁ ከተፈለገ መልካም ግን ጀረባው ምን አዝሎዋል? እውነት በደለናል ብለው አምነው ሊመለሱ ወይስ የቀረውን ምህመን በኑፋቄያቸው ለምመረዝ ? በደንብ ይተና እላለው

  18. Anonymous October 7, 2013 at 1:43 am Reply

    Silematawuquachew sewoch sitzelabidu mesbmat yatakital. Andachihum kenzih sebakian yegziabiher qaal tekaflachihu atawkum. Sile tifat yemitaweru hulu andachihum tenageru bitibalu yemitlut yelachihum. Christos be yikirtaw yigobgnachihu. lela min yibalaal.?

  19. yeshet October 7, 2013 at 7:06 am Reply

    ፐፕለላነን በቢ የመሚለሉተት ፈለሊጠጥ አእነንደሀሆነ መማነን የያጠጣወዋለል በቢለሎወው የይሀሆነን!!!!;

  20. Anonymous October 7, 2013 at 7:22 am Reply

    ማንም በበጎ አይምሮ ከሆነ የማንንም መጥፋት አይፈልግም፡፡ በግል ይቅርታ መጠየቅ ምን የሚሉት እንደሆነ አልገባኝም፡፡ አቡነ ገብርኤል የመለሱት መልስ እራሱ ትክክል አይደለም፡፡ እኔ በግሌ ይቅር ብያችሁዋለሁ እኔን የሰደባችሁ አይምሰላችሁ ቤተክርስቲንን እንጂ በማለት ነበር ግን በምን መልኩና ዙሪያ ተነጋግረው ነው ያለ ቀኖና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይቅር ብያችሁዋለው የተባለው፡፡ ማለት የነበረባቸው ይቅርታ መጠየቁ ጥሩ ሆኖ ሳለ ጉዳዩ በቅዱስ ሲኖዶስ የተያዘ ስለሆነ አሁን እኔ ምንም ልል አልችልም ብለው መዝጋት ነበረባቸው፡፡ የግል ቂም ይመስል ይቅር ብያለሁ ለምን፡፡ ያጠፉትን ጥፋት በመጀመሪያ በዝርዝር እራሳቸው እንዲያቀርቡ ማድረግ ሌሎችም ካሉ ማሳወቅና መተማመን ላይ መድረስ ወደፊት ስላለው ነገር ማስተማመኛ እንዲሰጡ ማድረግ እንደውም በቤተክርስቲያንዋ እስካሁን ባገኙት ብር ወደ ኢንቨስትመንት ቢገቡ ይመረጣል ምክንያቱም ድሮም አገልጋይ አልነበሩምና፡፡ ከዚህ በፊትም ተመልሰናል ብለው ብዙውን ይዘው የሄዱ ሃይማኖተ አበው የተባሉ ግን በምንፍቅና የጠፉ የተወሰኑ ነበሩ፡፡ እንደ እነሱ እንዳይሆኑ ቡድናቸውን ከቤተክርስቲያን አገልግሎት እንዳይሳተፍ ማድረግ፡፡ በምእመንነታቸው እንዲቀጥሉ ማድረግ ይህንንም ለማድረግ በኢቢኤስ ጣቢያቸው ለመጨረሻ ጊዜ እስከ ዛሬ ያስተማሩዋቸውን በካሴትም ይሁን በተቪው እንዲሁም በመጽሄት ትምህርቶች በሙሉ ዝማሬያቸውን በሙሉ በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶ በሚሰጥ እርማት መልእክቱን ያስተላለፈው ሰው ይህ ስህተት ነበር እያሉ እንዲናገሩ ትምህርቶቹንም ማንም እንዳይጠቀማቸው በማድረግ በተለያየ በሎግ ላይም እንዲወጡ በማድረግ ስለሰጡትም ማረሚያ በተለያየ መገናኛ ብዙሃን እራሳቸው እንዲናገሩ ማድረግ የተናገሩትን እርማት ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ማድረግ በየአጥቢያው እንዲነገር መረጃም እንዲቀመጥ ማድረግ የመሳሰሉትን ማድረግ ከሲኖዶስ እንጠብቃለን፡፡ አስታራቂም የተባለችው አሜሪካዊ ሆና እንደ ቀድሞው የተዋህዶ ነገር በቅርብ መጥታ እንዳየሁዋት በአለባበስዋ በዝማሬዋ ሁሉ አይታይባትም ልጅዋም ብትሆን በማህበራዊ ሁሮ የስነ ምግባር ችግር አለባት እኔ እንደውም ከነሱ ጎራ ሳትቀላቀል አትቀርም፡፡ ዝማሬዋ ሁሉ ወደነሱ ሄድዋል፡፡

  21. ገ/ሚካኤል October 7, 2013 at 7:37 am Reply

    andebetachihun teqotateru christianoch kehonachihu Yekrstina nigigire ena astesaseb yinurachihu.
    Erq yemitela Diablos bicha new.
    Kesash Diablos bicha new.
    Yesidib af Yetesetew le Diablos bicha new
    Feraj Egziabher bicha new.
    May The Almighty save our beloved EOTC from ignorants and enemies.

  22. Dilagegne October 7, 2013 at 1:38 pm Reply

    ምን ዓይነት ስራ ነው በሃይማኖታችን እየተሰራ ያለው፣ለማመኑ የሚከብድ ነገር ነው።አሉን ብለን ከምንታማመንባቸው መንፈሳዊ ወንድሞቻችን እንደዚህ ዓይነት የሰይጣን ስራ እየሰሩ ሲገኙ በጣም ያሳዝናል።ኢግዚኣብሄር ይቅር ይበላቸው።ጊዘው ብጣም ከፍተዋል የሚታመን ሰው በአሁን ግዜ እየጠፋ በመሆኑ እግዚአብሄር ይጠብቐን። ለተሳሳቱ ወንድሞቻችን ደግሞ ኢግዚኣብሄር ወደ ድሮ የነበሩበትን ጥንካሬ እንዲመልሳቸውም እንዲሁም ጥሩ ማለትም ንፋቄ የሌለበት ኣካሄድ እንዲሁም ይቅርታቸው የእውነት እንዲሆን እንፀልይላቸው።የእመቤታችን የድንግል ማርያም ልጅ መድሃኔ አለም ሃይማኖታችን ይጠብቅልን በሃይማኖታችን ፀንተን እንድንኖር ብርታቱ ይስጠን።

  23. Habtewold shumiye October 7, 2013 at 3:39 pm Reply

    This is very vague.Can you explain your evidences.Where is the truth ?As far as my knowlege i heard some litrature and spritual songs from those guys.I can realise that they witness about the lord christ jesus.They have strong belief in christ.They are called to witness for the name above all names that is christ Jesus.Theerfor please donot argue eachother as christ died for every body of us.EOTC has strong knowlegde about Jesus but it is considerd as secrete.The very important thing the EOTC followers need to hear is that jesus’s voice it is not about individual differences.We will be saved only because Jesus christ died for us not for the argument that you and those guys so think of for your eternal life.
    May God bless all christians in Ethiopia.peace

  24. Anonymous October 8, 2013 at 7:24 am Reply

    ታሪክ የማይረሳቸው እጅጋየሁ በየነ ወይም ዮዲትጉዲት ቡድን እነበጋሻው፣ ትዝታው፣ ያሬድ አደመ ለመሆኑ በቤተክርስቲያን ላይ ያደረሱት በደል እንዲህ በቀሳሱ የሚረሳ ነው። አሁንም ቢሆን የበግ ለምድ ለብሰው በየጋዜጣው ብቅ እያሉ ነው እንጠንቀቅ

  25. danie October 8, 2013 at 8:01 am Reply

    ይቅርታ ማለታቸው ደስ የሚያሰኝ ሆኖ ሳለ ሂደቱ ግን የሲኖዶሱ ውሳኔ ከታወቀ ቦሃላ መሆን አለበት ፡፡ ይህ ክህደት ግለሰቦችን ማስቀየም ብቻ ሳይሆን የሀይማኖት ክህደት ስለሆነ እርቁ ቢፈቀድ እንክዋ የስርዐተ ቤተክርሰቲን ደንብ በተከተለ መልኩ ብቻ ሆኖ በቀኖና ቤተክርሰቲን እና ያጠፉትን ጥፋት አምነው የከፋፈሉትን ሕዝብ በይፋ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው ፡፡ ቢሆንም ግን እነዚህ ጡት ነካሾች / መናፍቃን የተመለሱት ጥቅማቸው ስለጎደለ /ለሌላ ነገር ሊሆን ስለሚችል የቤተክርቲያን አባቶች በየዋህነት ብቻ ሳይሆን በማስተዋል ጉዳዩን ሊያዩት ይገባል ፡፡ የተዘናጋ እረኛ በጎቹን ለተኩላ ያጋልጣልና እባካችሁን በሀላፊነት ያላችሁ አባቶች ለመንጋው ተጠንቀቁ ፡፡
    ነገር ግን ከእንግዲህ በየትኛውም መድረክ ልናያቸው አንፈልግም ፡፡
    በሀገር እና በሀይማኖት ቀልድ የለም !!!

  26. Anonymous October 8, 2013 at 11:50 am Reply

    እኔ በበኩሌ አልተመቸኝም ምንም አላምናቸውም ደግሞም እነሱ የመለመሉአቸው ተሃድሶያውያን እስካሁንም አሉ በየመብሎጉ እየሞገቱም ነው፡፡ ለብልጠት እንጂ በእውነት ለመመለስ አይመስለኝም የሚፈልጉት ጥቅምፀ በአካፋ ማፈስ ስለቀረባቸው የተፈጠረች ዘዴ ናት መቸም ክርስትና ፈተና ነው አባቶችም ሰው ይቅርታ ሲጠይቅ እምቢ ማለት በደል ስለሚመስላዠው ይህን ሁኔታ በመጠቀም በተገኘው ቀዳዳ ገብቶ ለማወክ ስለሆነ እኔ ከነሱ ይቅርታ ቢቀርብንና ላልተወሰነ ጊዜ ቤተክርስቲያን የራሷን ጥናት ብታካሂድባቸው የተሻለ ነው በፍጹም መድረክ ላይ ከዚህ በኋላ ልናያቸው አይገባም፣ ጥቅም የሚያገኙበትን ቀዳዳ ሁሉ ማጥፋት ግድ ይላል ቤተክርስቲያናችንና ምዕመኗ አጠገበቻቸው ፈነደቁ አለነሱ አዋቂ የሌለባት አስመሰሉ አዋረዱአት ከዚህ በላይ ምን ይድረስብን አሳልፈው ሰጡን እንዲህ ያሉ ልጆች ሊኖሩን አያስፈልግም ቢቀሩብንስ ምነው በሰላም ብንኖር ደግሞ ሌላ ታሪክ ተፈጥሮ እንዳናዝን ቀፈውኛል እባካችሁ ይቅሩብን ተኩላ ምን ሂዜም ተኩላ ነው፡፡

  27. Anonymous October 10, 2013 at 12:55 pm Reply

    all of you are stupid!!

  28. Mamush October 14, 2013 at 1:46 pm Reply

    Insulation is the sign of PROTESTANTISM.

  29. anoys October 17, 2013 at 7:51 am Reply

    ይህቺ እሩጫ ለምን እንደሆነ ባይገባኝም አካሄዱ ግን በደንብ ሊጤን ይገባዋል፡፡ ጳጳሳቱን በግል ማናገር ምን ይዞ ይመጣል ብንል በሲኖዶስ ስብሰባ ወቅት ሲነጋገሩበት ሁሉም የለዘበ ሃሳብ ይዘው እንዲገቡ ለማድረግ ነው፡፡ ከአቡነ ገብርኤል መልስ እንኩዋን ብንመለከት እኔ በግሌ ይቅር ብያለሁ ማለታቸው ቀድመው ምንም አደረጉ ምን ነገሮች እንዲለዝቡ እድል የሰጠ ነው፡፡ ጠንከር ያለ ክርክርና ቁርጥ አቁዋም እንዳወሰድም እንቅፋት ነው፡፡ አቡነ ገብርኤልን ያክል የፈተኑት ባይኖርም ሁሉም ደርሶዋቸዋል ማለት ግን ይቻላል፡፡ በቤተክርስቲያንዋ ቀደም ሲል ይቅርታ ጠይቀው የነበሩ ሁዋላ ግን በዛው ስራ ላይ ገኝተው የተሰናበቱት ጥቂት ሃይማኖተ አበው ማህበር የነበሩ አይነት እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡ ጳጳሳቱ በሊቃውንት ጉባኤ ያስመረመሩትን ስብከቶቻቸውን መዝሙሮቻቸውን በመመርመር ውሳኔ በመጀመሪያ መስጠት የግድ ነው፡፡ ግድፈት የበዛው ከሆነ ነገሩን የሰራው ሰው እንደገና እርምት እንዲሰጥ ማድረግ ነው፡፡ ከአውደምህረት እንዲርቁ ማድረግ ምክንያቱም ከዚህ በሁዋላ ለማገልገል ሞራሉም የላቸውም፡፡ ባገኙት ሃብት ኢንቨስት አድርገው ቢቀመጡ ጥሩ ነው፡፡ አስታራቂዋም ነገሮችን በበጎ ማየት ይኖርባታል፡፡ ነገ ለሚመጣው ማንኛውም ችግር ተጠያቂነት እንዳለበት ማወቅ አለበት፡፡

  30. Gonder October 17, 2013 at 7:54 am Reply

    ይቅርታ ማለታቸው ደስ የሚያሰኝ ሆኖ ሳለ ሂደቱ ግን የሲኖዶሱ ውሳኔ ከታወቀ ቦሃላ መሆን አለበት ፡፡ ይህ ክህደት ግለሰቦችን ማስቀየም ብቻ ሳይሆን የሀይማኖት ክህደት ስለሆነ እርቁ ቢፈቀድ እንክዋ የስርዐተ ቤተክርሰቲን ደንብ በተከተለ መልኩ ብቻ ሆኖ በቀኖና ቤተክርሰቲን እና ያጠፉትን ጥፋት አምነው የከፋፈሉትን ሕዝብ በይፋ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው ፡፡ ቢሆንም ግን እነዚህ ጡት ነካሾች / መናፍቃን የተመለሱት ጥቅማቸው ስለጎደለ /ለሌላ ነገር ሊሆን ስለሚችል የቤተክርቲያን አባቶች በየዋህነት ብቻ ሳይሆን በማስተዋል ጉዳዩን ሊያዩት ይገባል ፡፡ የተዘናጋ እረኛ በጎቹን ለተኩላ ያጋልጣልና እባካችሁን በሀላፊነት ያላችሁ አባቶች ለመንጋው ተጠንቀቁ ፡፡
    ነገር ግን ከእንግዲህ በየትኛውም መድረክ ልናያቸው አንፈልግም ፡፡
    በሀገር እና በሀይማኖት ቀልድ የለም !!!

  31. Anonymous October 24, 2013 at 1:15 pm Reply

    ykr yemil hu ykrta ysetewal ykr yemayl gn?

  32. Anonymous October 29, 2013 at 9:30 am Reply

    Sew fetin yayale E/re gene lebene yimermeral. manene new yemyatalute ybetekersitiyan rase yhone getachin Easuse Krostos yiferedebachew.

  33. fikru negadh May 30, 2016 at 9:22 pm Reply

    አመቱን ሙሉ የሲኖዶስ ስራ ምንንድነው?ቤ.ክያንን ከኑፋቄ ህዝቡን ከውዝግብ ካለዳኑ ምንድነው ስራቸው? አለበለዚይ የፌደሬሽን ወይ የተወካዮች ምክርቤት ገብተው ቢቀመጡ ይሻላል።በየገጠሩ ስንት ታሪካዊ አድባራትና ገዳማት ሲፈርሱ……አዝናለሁ እሄን በማለቴ

Leave a comment