ከሰማይ ወረደ በተባለው መስቀል ጉዳይ ቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ይሰጣል

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ 13 ቁጥር 715፤ ቅዳሜ፣ መስከረም ፲፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም)

ዓለማየሁ አንበሴ

his grace abune estifanosበአቃቂ ቃሊቲ ገላን ጉራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ከሰማይ ወረደ ስለተባለው መስቀል፣ ቅዱስ ሲኖዶስ መርምሮ ውሳኔ* እንደሚያስተላልፍ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳትና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አስታወቁ፤ ሕዝቡ የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ በትዕግሥት እንዲጠባበቅ ብፁዕነታቸው አሳስበዋል፡፡

‹‹መስቀል ከሰማይ ወርዷል፣ አልወረደም፤ ትክክለኛ ነው፣ አይደለም፤›› የሚለውን ለመመለስ ቅዱስ ሲኖዶሱ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ ሊያስተላልፍበት ይገባል ያሉት ብፁዕነታቸው፣ ይህን ለማድረግም ጉዳዩን ለቋሚ ሲኖዶስ አባላት ማሳወቃቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹መስቀሉ እንደተባለው ከሰማይ የወረደ አለመኾኑ ከተረጋገጠም የደብሩ ሓላፊዎች ይጠየቁበታል፤›› ብለዋል ብፁዕነታቸው፡፡

መስቀል ከሰማይ ወርዷል በተባለ በአራተኛው ቀን ነሐሴ ፳፯ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ወደ ስፍራው በማቅናት ተገቢውን የጸሎት ሥርዐት ከደብሩ ካህናት ጋራ ካደረሱ በኋላ መስቀሉን ከወደቀበት መሬት አንሥተው ወደ ቤተ መቅደሱ እንዲገባ ማድረጋቸውን የገለጹት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ መስቀሉ ከሰማይ እንደወረደ በዐይናችን አይተናል ካሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች እንደማንኛውም ሰው መስማታቸውን ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡

መስቀሉን ከወደቀበት መሬት ያነሡት ብፁዕነታቸው፣ ‹‹መስቀሉ ያቃጥላል፤ ብርሃናማ ነጸብራቅ አለው›› የሚባለውን አለማስተዋላቸውን ጠቁመዋል፡፡ ‹‹መስቀል የሚያቃጥል ሳይኾን የድኅነት ኃይል ነው ያለው፤ የሚያቃጥል ቢኾን ከመሬት ላይ ማንሣት ባልተቻለ ነበር፤›› ብለዋል፡፡

ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል ለማየት ወደ ስፍራው የሚያቀኑ ምእመናን ለምን እንዳይመለከቱት ተከለከለ የሚል ጥያቄ ያነሣንላቸው ብፁዕነታቸው፣ ‹‹ጉዳዩ በቅ/ሲኖዶስ ተጣርቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ሕዝበ ክርስቲያኑ ኹኔታውን በጥሞና እንዲያጤነው በማሰብ ነው፤›› ብለዋል፡፡

– – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – – –

*  ከእግዚአብሔር የኾኑ ተኣምራትና መንክራት ሃይማኖታዊ እውነትን የማረጋገጥና እምነትን የማጽናት አስተዋፅኦ አላቸው፡፡ እንዲህም ስለኾነ÷ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ ከቤተ ክርስቲያን ትውፊትና ታሪክ አንጻር የተኣምራትንና መንክራትን ተቀባይነት በጳጳሳት ጉባኤ(Papal Committee) መርምሮ በሲኖዶሳዊ ውሳኔ አማናዊነታቸውን መቀነን/ማጽደቅ፣ የምእመናን መማጠኛ ማድረግ (Veneration/Canonization) የጥንታውያን አብያተ ክርስቲያን ነባር አሠራር እንደኾነ ይታወቃል፡፡

3 thoughts on “ከሰማይ ወረደ በተባለው መስቀል ጉዳይ ቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ይሰጣል

  1. Birhan Asfaw September 28, 2013 at 7:22 pm Reply

    Amlak hoy libona siten

  2. daniel September 28, 2013 at 8:41 pm Reply

    This is the right direction. This makes me to proud on my truthful spiritual fathers ( members of the Kidus Senod ). I was struggling about the so called ” …”. Even I surprised when many people shy to ask critical questions. Our church holy Bible advice us not to believe all spirits.

    As Yihuda, there are some false priest, preachers… They work day and night in cooperation of church enemies (devil…) to get money & fame. My heart is telling me about the priest who claimed he saw it first time: 1) he is a false witness or a human person throw it from airplane.

    Jesus Christ our Lord, King, Savior, God will protect our church from internal and external enemies.

  3. […]  https://haratewahido.wordpress.com/ posted by Gheremew Araghaw […]

Leave a comment