የከተማ አስተዳደሩ የጃንሜዳን ባሕረ ጥምቀት ይዞታ ለቤተ ክርስቲያን ለማረጋገጥ ትኩረት እንዲሰጥ ቅዱስ ፓትርያርኩ ጠየቁ

  • ጃንሜዳን ለበዓለ ጥምቀት ዝግጁ የማድረግ ሥራ በይፋ ተጀምሯል

ጃንሜዳን ለበዓለ ጥምቀት ዝግጁ የማድረግ ሥራ፣ ዛሬ ኀሙስ፣ ታኅሣሥ 8 ቀን 2013 ዓ.ም. ማለዳ 12:00 ሰዓት ላይ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ክብርት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ሓላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ በክንውኑ ላይ ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት፣ የከተማ አስተዳደሩ የጥምቀት በዓል ከመድረሱ በፊት ጃንሜዳን አጽድቶ ለማስረከብ በገባው ቃል መሠረት የገበያ መዋያውን በማንሣት እና በማጽዳት፣ ለበዓሉ ዝግጁ በማድረጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። የይዞታ ባለቤትነቱን በማረጋገጥ ረገድም፣ የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት እንዲሰጥበት ጠይቀዋል።

ክብርት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፣ የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የከተማዋን ሕዝብ ከቫይረሱ ሥርጭት ለመታደግ ሲባል፣ የአትክልት ገበያው ወደ ጃንሜዳ መዘዋወሩ እና እስከ ዛሬ ድረስ አገልግሎት እየሰጠ መቆየቱን ጠቅሰው፣ የከተማ አስተዳደሩ ከጥምቀት በዓል አንድ ወር በፊት የአትክልት ገበያውን ከጃንሜዳ ሙሉ በሙሉ በማንሣት ቦታውን ለበዓሉ ዝግጁ የማድረግ ሥራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ምክትል ከንቲባዋ አያይዘውም፣ በቀሪዎቹ ቀናት መሬቱን የመደልደል እና አረንጓዴ የማድረግ ሥራ፣ በከተማ አስተዳደሩ በኩል ተጠናከሮ እንደሚቀጥል አመልክተው፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተደራጁ ወጣቶችም የከተማ አስተዳዳሩ ከሚያከናውነው ሥራ ጎን በመቆም የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ እምነታቸው ገልጸዋል። በቀጣይም፣ በጃንሜዳ ባለቤትነት በሚነሡ ጉዳዮች ዙሪያ፣ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋራ በመመካከር እና በመወያየት እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

አትክልት ተራ፣ በአኹኑ ሰዓት ከጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት ሙሉ በሙሉ መነሣቱ ተረጋግጧል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: