ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ዐረፉ

  • የቀብር ሥነ ሥርዐታቸው ነገ ጠዋት በ3፡00 በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል

የቀድሞው የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት፣ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፣ ዛሬ ጠዋት ዐርፈዋል፡፡

ከሓላፊነታቸው ተገልለው በመንበረ ፓትርያርኩ በሚገኘው ማረፊያቸው ለረጅም ጊዜ በሥጋ ሕመም የቆዩት ብፁዕነታቸው፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ኅዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም.  ጠዋት በሞተ ሥጋ ተለይተውናል፡፡

ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፣ በአምስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ እድ፣ ሐምሌ 5 ቀን 1991 ዓ.ም. ኤጲስ ቆጶስነት ከተሾሙት 16 ብፁዓን አባቶች አንዱ ነበሩ፡፡

በፊት ስማቸው አባ አምኃ ሥላሴ አሳየኸኝ ይባሉ የነበሩ ሲኾን፣ ብፁዕ አባ ኤጲፋንዮስ ተብለው ለከፋ ሸካ ሀገረ ስብከት ተመድበው ነበር ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን የጀመሩት፡፡

የብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ የቀብር ሥነ ሥርዐት፣ ነገ ኀሙስ፣ ኅዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ3፡00፣ ሊቀ ሥልጣናት ኾነው በአስተዳዳሪነት በመሩት በመንበረ  ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሓላፊዎች እና የድርጅቶቹ ሓላፊዎች፣ የአዲስ አበባ አድባራት እና ገዳማት ሓላፊዎች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት እንደሚፈጸም፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: