የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ አስከሬን ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ

  • ማምሻውን ቦሌ አየር ማረፊያ ደርሷል፤

ከኹለት ወራት በፊት በሎንዶን ከተማ ያረፉት፣ የብሪታንያ እና አየርላንድ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ አስከሬን፣ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

ብፁዕነታቸው ካረፉበት መጋቢት 20 ቀን ጀምሮ አስከሬናቸው በዚያው በሎንዶን ዐርፎ የቆየ ሲኾን፣ በሀገረ ስብከቱ እና በቅርብ ቤተ ሰዎቻቸው አማካይነት፣ ልክ በኹለት ወራቸው ዛሬ ኀሙስ፣ ግንቦት 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ መደረጉ ታውቋል፡፡

ዕረፍታቸውን ተከትሎ ቋሚ ሲኖዶስ አካሒዶት በነበረው ስብሰባ፣ በዓለም አቀፉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በተጣሉት እግዳት ሳቢያ፣ ለሥርዐተ ቀብሩ ኹኔታዎች እስኪመቻቹ ድረስ፣ ለብፁዕነታቸው ጸሎተ ፍትሐት እንዲደረግ እና ስማቸው በጸሎት እየተጠራ እንዲቆዩ፣ አስከሬናቸውን ለማቆየት አስፈላጊው ወጪ ኹሉ ሀገረ ስብከቱ በሚያቀርበው መሠረት በጠቅላይ ጽ/ቤቱ እንዲሸፈን ውሳኔ ማሳለፉ ተጠቅሷል፡፡

ቀጣይ የሽኝት እና የቀብር ሥነ ሥርዐትን በተመለከተ፣ መንበረ ፓትርያርኩ እየተነጋገረበት እንደኾነ ተገልጿል፡፡ ጸሎተ ፍትሐቱ፥ ብፁዕነታቸው ምንኵስናም ቅስናም በተቀበሉበት፣ በቀዳሽነት፣ በመጋቢነት እና በመምህርነት ባገለገሉበት በደብረ ጽጌ ገዳም፤ ሥርዐተ ቀብራቸውም በምናኔ በኖሩበት በደብረ ሊባኖስ ገዳም እንዲኾን ቀደም ሲል ተጠቁሞ እንደነበር በመረጃው ተመልክቷል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: