የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ: የጸሎት እና ትምህርት ቀጥታ ስርጭቱን የጋራ ስምምነት በመጣስ በቀረበው ፕሮግራም ውሳኔ አሳለፈ

  • ቤተ እምነቱ እና የቴሌቪዥን ጣቢያው ይቅርታ ይጠይቃሉ

97431643_3219965728129779_6151194982431588352_o

ጉዳዩን አስመልክቶ፣ የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳስታወቁት፥ የኹሉም አብያተ እምነቶች እና የሚዲያ ግብረ ኃይሎች በተገኙበት፣ ከትላንት በስቲያ በጽ/ቤቱ በተደረገ አስቸኳይ ስብሰባ፣ የጋራ ስምምነቱን በመጣስ ስለ ሌላው ቤተ እምነት አስተምህሮ አጓጉል ነቀፌታ ያስተላለፈው ቤተ እምነት እና አስፈላጊውን እርምት በወቅቱ ያልወሰደው ዋልታ ቴቪ ይቅርታ እንዲጠይቁ ተወስኗል፡፡ በቀጣይም፣ መሰል ጠብ ጫሪ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ለመከላከል በሚያስችሉ አሠራሮችም ከስምምነት ላይ መደረሱን ጠቅላይ ጸሐፊው አስታውቀዋል፡፡

በመኾኑም፣ ግንቦት 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት፣ በዋልታ ቴሌቪዥን በተላለፈው የረመዳን ወር የጸሎት (ዱዓ) ሥነ ሥርዓት ላይ፣ ኢትዮጵያዊ የአብሮነት ዕሴትንና የጋራ ስምምነቱን በመፃረር፣ የክርስትናን አስተምህሮ በማጥላላት በተላለፈው መልእክት፣ ቤተ እምነቱ እና የቴሌቪዥን ጣቢያው ይቅርታ እንዲጠይቁ ተወስኗል፡፡

፨፨፨ ለግንዛቤ ይረዳን ዘንድ፨፨፨

91699638_3109251249201228_9004327222995058688_n

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ በመላው ዓለም የተከሠተው የኮቪድ-19 ተላላፊ በሽታ ወደ አገራችን መግባቱ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ፣ ኹሉም አብያተ እምነቶች በቴሌቪዥን የአየር ሰዓት ድልድል ተደርጎላቸው፣ ምእመኖቻቸው የአምልኮ ተግባሮቻቸውን በየቤታቸው እንዲፈጽሙ በማሰብ በብዙኀን መገናኛ እንዲተላለፍ እያደረገ ይገኛል።

ይኹን እንጂ፣ ከትላንት በስቲያ በዋልታ ቴሌቪዥን በተላለፈው ፕሮግራም ላይ፣ ቀደም ሲል፣ ከኹሉም አብያተ እምነቶች እና ሚዲያዋች ጋራ ስምምነት ከተደረሰበት የጋራ መግባቢያ ሰነድ ውጪ ማለትም፣ በሚተላለፈው የትምህርት ክፍለ ጊዜ፣ አንድ የሃይማኖት ተቋም የአስተምህሮ ጉዳዮችን ሲያነሣ የሌሎችን ሃይማኖትንና እምነትን መንቀፍ መተቸት እና አክብሮት አለማሳየት አይገባም፤” የሚለውን አንቀጽ የሚጣረስ እና ከሃይማኖት ተቋማቱ የጋራ ዕሴት ያፈነገጠ ፕሮግራም በቀጥታ ስርጭት ተላልፏል፡፡

ይህንም ተከትሎ ዛሬ፣ ከኹሉም አብያተ እምነቶች እና የሚዲያ ግብረ ኃይል ጋራ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ ስሕተቶቹን ነቅሰን በማውጣት ከዚህ በታች በተጠቀሱት ነጥቦች ላይ የጋራ መግባባት ተደርሷል።

97210332_1154347598247698_2970587857963450368_o

  1. ስሕተት የፈጸመው ቤተ እምነት፣ ከተቋሙ የበላይ ሓላፊዎች ጋራ በመነጋገር፣ ከዚህ በኃላ ስሕተቶች እንዳይፈጸሙ እና ለተፈጸመውም ስሕተት ይቅርታ እንዲጠይቅ፤
  2. ከዚህ በኃላ የሚተላለፉ ዝግጅቶች፣ ቀድመው የተዘጋጁ እና የተገመገሙ ፕሮግራሞች ብቻ ሊኾኑ እንደሚገባ ውሳኔ ላይ ተደርሷል፤
  3. ዋልታ ቴሌቪዥንም በመግባቢያ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው አቅጣጫ ውጪ መልእክት ሲተላለፍ፣ አስፈላጊውን እርምት በወቅቱ ባለመውሰዱ ይቅርታ እንዲጠይቅ በጋራ ወስነናል

በተጨማሪም ሰሞኑን፣ በአዲስ አበባ እና በአንዳንድ የክልል ከተሞች፣ ”ንሰሐ ግቡ”በሚል ሰበብ፣ በታክሲ ተራ፣ በሌላ ቤተ እምነት በር አካባቢ፣ በየአውራ መንገዱ ላይ የእጅ ማይክሮፎን በመጠቀም አላስፈላጊ ግጭቶች እንዲነሡ ለማድረግ በሚሰሩ አካላት ላይ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስድ ለሚመለከተው አካላት ደብዳቤ እንደሚጻፍ ተነጋግረናል ።

ከዚህ ውጪ፣ በሶሻል ሚዲያ ከዚህ ጉዳይ ጋራ በተያያዘ አላስፈላጊ ግጭት የሚያሥነሱ እና ኢትዮጵያዊ የአብሮነት ዕሴቶቻችንን የሚሸረሽሩ ሐሳቦችን ከመሰንዘር ይልቅ፣ የሚያግባቡንን የጋራ ገንቢ ሐሳቦችን እያጎለበትን እንድንሔድ በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት እና በራሴ ስም የአክብሮት መልእክቴን አቀርባለኹ።

ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: