የፀረ ኮቪድ-19 የተስፋ ልዑክ ዐቢይ ግብረ ኃይል የመጀመሪያ መግለጫውን ሰጠ፤በቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ አተገባበር ክፍተት ባሳዩ አድባራት ላይ የእርምት ርምጃ እየወሰደ ነው!

ከነገ ጀምሮ፥ ለነዳያንና ለተቸገሩ ወገኖች ደረቅ ምግቦችንና የጽዳት መጠበቂያ ቁሶችን በየአጥቢያው ይሰበስባል፤ ለምእመናን የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል፡፡

~~~et-600x387

 • ካህናት፣ መምህራንና ሐኪሞች የተካተቱበት፥ እስከ አጥቢያ ድረስ የተዘረጋ ግብረ ኃይል ነው፤
 • ወጥ መዋቅር አዘጋጅቶ፥ለኹሉም አህጉረ ስብከት፣ወረዳ አብያተ ክህነትና አጥቢያዎች ልኳል፤
 • ከቀኖና ጋራ የተያያዙ ጉዳዮችንና የማስተማሪያ ሰነዶችን አዘጋጅቶ ለቋሚ ሲኖዶስ አቅርቧል፤
 • ትምህርትና ማብራሪያዎችን፣ በመደበኛና ማኅበራዊ ሚዲያዎች እንደሚሰጥ አስታውቋል፤
 • ዛሬ ከቀትር በኋላ፣ ለአዲስ አበባ አድባራት አስተዳዳሪዎች እና ሰባክያን ሥልጠና ይሰጣል፤
 • በቅ/ሲኖዶስ መመሪያ አተገባበር አድባራቱ ባሳዩት ክፍተት የእርምት ርምጃ እየወሰደ ነው!

***

#የፀረ ኮቪድ_19_የተስፋ_ልዑክ

በኢትዮጵያ ርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
በፀረ ኮቪድ-19 የተስፋ ልዑክ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ

____________

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡

በአገራችን በኢትዮጵያ በገጠር እና በከተማ እንዲሁም በመላው ዓለም ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች እና መላው ኅብረተሰብ በሙሉ

እንደሚታወቀው ኹሉ ቋሚ ሲኖዶስ፣ መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ፣ የወረርሽኙን አሳሳቢነት በመመልከት፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ በየደረጃው የተስፋ ልዑክ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም በወሰነው መሠረት፣ ካህናት አባቶች፣ መምህራነ ወንጌል እና የሕክምና ባለሞያዎች ያሉበት የተስፋ ልዑክ ዐቢይ ግብረ ኃይል ተቋቁሟል፡፡

Bete Kihinet Anti COVID 19

ግብረ ኃይሉ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ ይኸውም፡-

1. ግብረ ኃይሉ በሥሩ፣ አራት ንዑሳን ኮሚቴዎችን አዋቅሯል። ለንዑሳን ኮሚቴዎቹ ተግባር እና ሓላፊነት አዘጋጅቶ ሰጥቷል፤ በግብረ ኃይሉ የተዋቀሩት ንዑሳን ክፍሎችም የሚከተሉት ናቸው።

፩. የትምህርት፣ ሚዲያ እና ሕዝብ ግንኙነት ንዑስ ግብረ ኃይል፣

፪. የድጋፍ አሰባሳቢ እና ፋይናንስ ንዑስ ግብረ ኃይል፣

፫. የቴክኒክ፣ አደጋ ዝግጁነት እና ትንበያ ንዑስ ግብረ ኃይል፣

፬. የአጥቢያ የፀረ ኮቪድ 19 ተስፋ ልዑክ ግብረ ኃይል ክትትል ንዑስ ግብረ ኃይል ናቸው፡፡

2. ንዑሳን ኮሚቴዎቹ፣ በተሰጣቸው ሓላፊነት መተግበር ያለባቸውን ጉዳዮች ዐቅደው ወደ ሥራ ገብተዋል።

3. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተስፋ ልዑክ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም ተደርጓል፤ በየደረጃውም ተመሳሳይ ሥራዎች እንዲሠሩ እና ሥራዎች በአግባቡ እንዲቀናጁ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ እስከ አጥቢያ ድረስ ሊያስተሳስር የሚችል፣ ወጥነት ያለው የሥራ መዋቅር እና ሓላፊነት ተዘጋጅቶ ለኹሉም አህጉረ ስብከት፣ ወረዳ ቤተ ክህነት እና አጥቢያዎች ተልኳል።

4. በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ቡድን አቋቁሞ፣ ወደ ቅጽሩ የሚገቡ ሠራተኞችንም ኾነ ባለጉዳዮችን እየመረመረ ይገኛል።

5. ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጋራ የተያያዙ ጉዳዮችንና የማስተማሪያ ሰነዶችን አዘጋጅቶ ለማጸደቅ ለቋሚ ሲኖዶስ አቅርቧል።

6. ከጤናው ጋራ የተያያዙ የማስተማሪያ ፓወር ፖይንት እና ተለጣፊ ወረቀቶች ተዘጋጅተዋል።

7. ዛሬ ቅዳሜ፣ መጋቢት 19 ቀን በስምንት ሰዓት፣ በአዲስ አበባ ላሉ ለሁሉም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች እና የስብከተ ወንጌል ሓላፊዎች:-

 • በበሽታው መተላለፊያ መንገዶች
 • መከላከያ መንገዶቹ
 • ቤተ ክርስቲያን ያላትን ጉልሕ ሚና
 • እነርሱም የበኩላቸውን የሚወጡበትን መንገድ ለማሳየት ሥልጠና ይሰጣል።

8. በብዙኀን መገናኛ ስለ በሽታው ትምህርት እየሰጠ ይገኛል፣ ይህንም አጠናክሮ ይቀጥላል።

9. በአንዳንድ አድባራት ላይ የሚታዩ ክፍተቶች ላይ የእርምት ርምጃ እንዲወሰድ ከሚመለከተው አካል ጋራ ሠርቷል፤ ወደ ፊትም ይቀጥላል።

10. ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰናቸውን ውሳኔዎች ያለመሸራረፍ እንዲተገበሩ ያግዛል፤ ያስተገብራል።

11. ግብረ ኃይሉ ባስቀመጠው ዕቅድ መሠረት ጉዳዮችን እያከናወነ አስፈላጊ በሚኾንበት ጊዜ በብዙኀን መገናኛ እና ማኅበራዊ ሚድያዎችን (በቴሌግራም፣ ዩቲዩብ እና ፌስቡክ) ላይ አስፈላጊ ማብራሪያ ይሰጣል። ከግብረ ኃይሉ የሚወጡ የተለያዩ ጉዳዮችንና ትምህርቶችን ከዚያ ማግኘት ይቻላል።

12. ኹሉም ምእመን፣ ለተቸገሩ ወገኖቹ መድረስ እንዳለበት በቅዱስ ሲኖዶስ ተወስኗል።

13. ስለኾነም፣ ለነዳያንና ለተቸገሩ ወገኖቻችን የሚኾን ደረቅ ምግቦች፣ የጽዳት መጠበቂያ ቁሶችን ከነገ ጠዋት ጀምሮ በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ ተመድበው ለሚሰበስቡ የቤተ ክርስቲያን አካላት እንድትወስዱ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በዚሁ አጋጣሚ፣ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ እና የጤና ሚኒስቴር እንደወሰኑት፡-

 • አካላዊ ርቀታችንን በመጠበቅ፣
 • እጃችንን ደጋግመን በመታጠብ፣
 • አስፈላጊ ከኾኑ ጉዳዮች ውጭ ከቤት ውስጥ ባለመውጣት እና
 • ሰዎች በብዛት በሚሰበሰቡበት ቦታ ባለመሔድ

ራሳችንንና ወገናችንን ከዚህ ክፉ ወረርሽኝ እንድንጠብቅ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

_____________________

እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጅ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይኾን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፡፡” (ኤፌ.5÷15)

የእግዚአብሔር ቸርነት አይለየን፤ አሜን፡፡

One thought on “የፀረ ኮቪድ-19 የተስፋ ልዑክ ዐቢይ ግብረ ኃይል የመጀመሪያ መግለጫውን ሰጠ፤በቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ አተገባበር ክፍተት ባሳዩ አድባራት ላይ የእርምት ርምጃ እየወሰደ ነው!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: