የጌዴኦ ዞን ሀገረ ስብከት ራሱን ችሎ እንዲቋቋም ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ

  • በጊዜያዊነት በብፁዕ አቡነ ገብርኤል ይመራል

***

his-grace-abune-gabrielበሲዳማ፣ ጌዴኦ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሥር የነበረ ሲኾን፣ እንደ ሀገረ ስብከት ራሱን ችሎ እንዲቋቋም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ወስኗል፡፡

ምልአተ ጉባኤው፣ በትላንቱ የቀትር በኋላ ውሎው ውሳኔውን ያሳለፈው፣ የዞኑን ምእመናን ጥያቄ መነሻ በማድረግ ነው፡፡ ከመንበረ ጵጵስናው እና የሐዋሳ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ያለው ርቀት፣ የመናፍቃንና የፀራውያን ተጽዕኖ በጥያቄው ተነሥቷል፡፡

ራሱን ችሎ እንደ ሀገረ ስብከት መቋቋሙ፣ እኒህን ችግሮች በመቅረፍ እና ተጽዕኖውን በመቋቋም፣ አስተዳደሩንና መንፈሳዊ አገልግሎቱን በቅርበት ለማከናወን ምቹ ኹኔታ እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡

በውሳኔው መሠረት፣ አዲሱ ሀገረ ስብከት፣ በሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በጊዜአዊነት እየተመራ፣ የራሱ ሥራ አስኪያጅ እና ሠራተኞች እንዲመደቡለት ተወስኗል፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያን ድንጋጌ መሠረት፣ ሀገረ ስብከት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ተለይቶ የተከለለና በሊቀ ጳጳስ፣ ጳጳስ ወይም ኤጲስ ቆጶስ የሚመራ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ እና አስተዳደራዊ ክልል ሲኾን፣ በአዲስ መልክ የሚቋቋመው የጌዴኦ ዞን ሀገረ ስብከት፣ ከ53ቱ የሀገር ውስጥ አህጉረ ስብከት 54ኛ ኾኖ[Edit] ይጨመራል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ባለፈው ዓመት የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤው፥ የምዕራብ አርሲ-ሻሸመኔ፣ የምዕራብ ጎንደር እና የማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች አህጉረ ስብከትን[Edit] በአዲስ መልክ እንዲቋቋሙና እንዲደራጁ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: