በሰ/አሜሪካ ሦስት ገዳማትን ለማቋቋም ታስቧል፤ በውጭ አህጉረ ስብከት አደረጃጀት ደንብ ረቂቅ ተጨማሪ ጥናት ይደረጋል

eotc-patriarchate-head-office

በሰሜን አሜሪካ ዩናይትድ ስቴትስ፣ በተመረጡ ሦስት ቦታዎች ገዳማትን ለማቋቋም፣ የአህጉረ ስብከቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በጋራ፣ ትላንት ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ምክረ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡

ዋሽንግተን፣ ሜሪላንድ እና ካንሳስ፣ ሦስቱን ገዳማት ለማቋቋም የተመረጡ ቦታዎች ሲኾኑ፣ የሚጠይቁት ወጪም በምክረ ሐሳቡ ተካቶ ቀርቧል፡፡

በአጀንዳው ተ.ቁ.(10) ጉዳዩን ይዞ የተወያየበት ምልአተ ጉባኤው፣ ከዘላቂ የመተዳደርያ ኹኔታ፣ ከቦታ አቀማመጥ ምቹነት፣ ከቦታዎቹ ግዢ እና ጠቅላላ ወጪ አንጻር፣ ያለቀለትና የተሟላ ኾኖ ለቀጣዩ ምልአተ ጉባኤ እንዲቀርብ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ የሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከትን በተገቢው መንገድ ለማደራጀት ያስችላል ያሉትን የሕግ እና የመተዳደርያ ደንብ ረቂቅ ለምልአተ ጉባኤው አቅርበዋል፡፡

ረቂቁ የሰሜን አሜሪካን ብቻ ሳይኾን፣ የኹሉንም የውጭ ክፍላተ ዓለም(የአውሮጳን፣ የካናዳን፣ የአውስትራልያን…) ሊያካትት እንደሚገባ አስተያየት የሰጠው ምልአተ ጉባኤው፣ በሥራ ላይ ካለው ሕገ ቤተ ክርስቲያንና ቃለ ዐዋዲ ጋራ ተገናዝቦ እንዲዘጋጅ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

የውጭ አህጉረ ስብከት አደረጃጀት እና የውጭ አብያተ ክርስቲያን መመሪያ መነሻ ረቂቁን ካቀረቡት ብፁዓን አባቶች ጋራ አብረው የሚሠሩ ተጨማሪ ብፁዓን አባቶችን ከየክፍላተ ዓለሙ ሠይሟል፡፡ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የውጭ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ሓላፊ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ፣ ከሰሜን አሜሪካ የሰሜን ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ እና የምሥራቅ አውስትራልያ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የተመደቡ ሲኾን፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመምሪያ ዋና ሓላፊዎችና የሕግ ባለሞያዎች እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡

ለአራተኛ ጊዜ በተሻሻለው የቤተ ክርስቲያናችን መተዳደርያ ደንብ(ቃለ ዐዋዲ) አንቀጽ 65 መሠረት፣ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ አህጉረ ስብከት፣ የቃለ ዐዋዲውን ይዘት ሳይለቅ፣ ከየአገራቱ ሕግ ጋራ የተጣጣመ ደንብ በየቋንቋው በማዘጋጀት ሊሠሩበት እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡

One thought on “በሰ/አሜሪካ ሦስት ገዳማትን ለማቋቋም ታስቧል፤ በውጭ አህጉረ ስብከት አደረጃጀት ደንብ ረቂቅ ተጨማሪ ጥናት ይደረጋል

  1. Debela November 8, 2019 at 4:34 pm Reply

    We kindly advise you to earn fake Masters degrees from Must University and Corllins university like Abune Philipos, your Dean, who was a stooge for Abune Timothewos while working as a fake teacher .

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: