መንግሥት: ለቤተ ክርስቲያን አንድነት መጠበቅ ድጋፉን ገለጸ፤ በባለሥልጣናቱ ለተፈጸሙት ግፎች ይቅርታ እንደማይጠይቅና ካሳም እንደማይከፍል አስታወቀ

pm with eotc synod members

  • ቅዱስ ሲኖዶስ በጠራውና ትላንት በተጀመረው አስቸኳይ ስብሰባ የተገኙት ከ25 የማያንሱ የምልአተ ጉባኤ አባላት፣ ዛሬ ዓርብ፣ ጳጉሜን 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ ባደረጉት ውይይት፣ የመንግሥታቸው ባለሥልጣናት በቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸሙትን ግፍ እና በደል በዋና ጸሐፊው ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ አማካይነት በንባብ አሰምተዋል(ሙሉ ይዘቱን ይመልከቱ)፤
  • የቀረበው ጽሑፍ፣ ክሥ መኾኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “እኔ ካህናትንና ምእመናን አልገደልኹም፤ ቤተ ክርስቲያንን አላቃጠልኹም፤ አዝናለኹ፤ ሳላጠፋ፣ ሳልበድል እንዴት ይቅርታ ጠይቅ፤ ወርቅ ላበደረ ጠጠር እባላለኹ፤ ይቅርታ አልጠይቅም፤ ካሳም አልከፍልም፤” በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል፤ ጥያቄው የመተጋገዝ ከኾነ እንደሚቀበሉትና እንደሚረዱም ተናግረዋል፤
  • በውይይቱ ላይ የቤተ ክርስቲያንን ሐሳብ እንዲገልጹ በምልአተ ጉባኤው የተመረጡት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ እና ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል፣ አቤቱታው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በግል እንደማይመለከትና በሥራቸው ማለትም በመንግሥታቸው መዋቅር ውስጥ ያሉ ባለሥልጣናትን እንደኾነ ገልጸው ዶ/ር ዐቢይ ቅሬታቸውን እንዲያነሡ ጠይቀዋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ለሀገር እና ለቤተ ክርስቲያን የተከናወኑ በጎ ተግባራትንም በመዘርዘር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፤
  • የቀድሞዎቹን ርእሳነ መንግሥታት በመጥቀስ፣ “እስከ አሁን እንዲህ የጻፍችኹባቸው የሉም፤ ካሉ አያይዛችኹ አቅርቡ፤” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩም፣ የእርሳቸውም ኾነ የመንግሥታቸው ፍላጎት የተጠናከረች፣ ለሀገር ግንባታ የሚቻላትን ኹሉ የምታደርግና አንድነቷ የተጠበቀ ቤተ ክርስቲያንን ማየት መኾኑን ገልጸዋል፤ የቀረቡት ችግሮች በለውጥ ውስጥ ካጋጠሙት ተግዳሮቶች መካከል መኾናቸውን አንሥተዋል፤ “ዕንቅፋት የሚፈጥሩትን አካላት መታገል ያለብን በጋራ ነው፤” ብለዋል።
  • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን በበኩላቸው፣ “ኦርቶዶክስ አንድነቷን ይዛ ትቀጥላለች፤ በምንም መልኩ አትከፈልም፤ አንድነቷን መፈታተን ለእኔ ድፍረት ነው፤ በዚህ ላይ መንግሥት ጠንካራ አቋም አለው፤” ብለዋል፤
  • “የኦሮሚያ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት አደራጅ ኮሚቴ” በማለት የሚንቀሳቀሱትን በተመለከተ መንግሥት እንደማያውቃቸውና ቤተ ክርስቲያን በውስጥ አሠራሯ እንድትመረምረውና እንድታርመው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል – “ቀሲስ በላይ፣ ፕሮቴስታንት ወይም ሙስሊም መኾን ይችላል፤ የጅማ ማርያምን ግን መውሰድ አይችልም፤” ብለዋል ዶ/ር ዐቢይ፡፡
  • ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ትላንት ኀሙስ፣ ነሐሴ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. የጀመረውን አስቸኳይ ስብሰባ፣ ዛሬ ከቀትር በኋላ የሚቀጥል ሲኾን፣ ጥሪ የተደረገላቸው እነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንንና የኮሚቴ አባሎቻቸው በምልአተ ጉባኤው ፊት ቀርበው እንደሚጠየቁ ታውቋል፤ ቅዱስ ሲኖዶስ በነገው ዕለት መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡EOTC Holy Synod to PM1EOTC Holy Synod to PM2EOTC Holy Synod to PM3EOTC Holy Synod to PM4EOTC Holy Synod to PM5

One thought on “መንግሥት: ለቤተ ክርስቲያን አንድነት መጠበቅ ድጋፉን ገለጸ፤ በባለሥልጣናቱ ለተፈጸሙት ግፎች ይቅርታ እንደማይጠይቅና ካሳም እንደማይከፍል አስታወቀ

  1. Anonymous September 23, 2019 at 7:04 am Reply

    Ye Ethiopia mengst Betekrstiyann Ykrta alteykm maletu betam yasaznal! Egziabher lehulum lbona ysten Amen

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: