ጠቅላይ ቤተ ክህነት: ለተጎዱት የሶማሌ ሀ/ስብከት ምእመናንና አብያተ ክርስቲያን፣ የርዳታና መልሶ ማቋቋም አስተባባሪ ኮሚቴ ሠየመ

 • ነገ ዓርብ በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሥራ ይጀምራል፤
 • በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ይመራል፤
 • የገንዘብ አሰባሰቡ በማእከል በሚከፈት ሒሳብ ሊኾን ይገባል፤
 • ጥቃትን አስቀድሞ ማስቀረት፣ በጉዳትም ፈጥኖ መድረስ፤

†††

በኢትዮ ሶማሌ ሀገረ ስብከት፣ ባለፈው ሳምንት በተፈጸመው የጭካኔና የዐመፅ ድርጊት ለተጐዱት ካህናትና ምእመናን እንዲሁም ለተቃጠሉት አብያተ ክርስቲያናት፣ የርዳታና መልሶ ማቋቋም አስተባባሪ ኮሚቴ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተሠየመ፡፡

አስተባባሪ ኮሚቴውን፣ የኢትዮ ሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በሰብሳቢነት ይመሩታል፡፡ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ፣ ከማኅበረ ቅዱሳንና ከምእመናን የተውጣጡ 12 አባላትን በዐቢይ ኮሚቴነት የያዘ ሲኾን፣ ከ5 እስከ 7 ንኡሳን ኮሚቴዎች እንደሚኖሩት ተጠቅሷል፡፡

his-grace-abune-mathewos-visited-1024x576

የአስተባባሪ ኮሚቴውን መቋቋም ለማሳወቅና የርዳታ ማሰባሰቡን ሒደት ለማስጀመር፣ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ፣ ነገ ዓርብ፣ ነሐሴ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡

በጅግጅጋና ጥፋቱ በተፈጸመባቸው የደጋሃቡር፣ ቀብሪደኃርና ዋርዴር ከተሞች፣ ቤት ንብረታቸውን አጥተው በቤተ ክርስቲያን፣ በካምፖችና በሌሎችም መሸሸጊያዎች ለተጠለሉ ካህናትና ምእመናን ፈጥነው መድረስ ያለባቸውን የምግብ፣ የአልባሳትና የቤት ዕቃዎችን ማሰባሰቡ ቅድሚያ ተሰጥቶታል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በየቀኑ የተወሰነ መጠን ለማጓጓዝ በመፍቀዱ፣ በተለይ ደረቅ ምግቦችን፣ ከነገ ጀምሮ፣ በ20 ኪሎ ለክቶና በካርቶን አሽጎ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ወስዶ ለተቋቋመው አስተባባሪ ኮሚቴው ማስረከብ እንደሚቻል ተገልጿል፡፡

በሕዝቡና በአብያተ ክርስቲያናቱ ላይ የደረሱ ጉዳቶችን ማጥናትና የሚያስፈልገውን ድጋፍ መለየት ሌላው የአስተባባሪ ኮሚቴው ሥራ ሲኾን፣ የተቃጠሉት አብያተ ክርስቲያናት ዳግመኛ የሚሠሩበት፣ ምእመናኑም መልሰው የሚቋቋሙበትን የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ የሚያሰባስብ ይኾናል፡፡

ለጊዜያዊው አስቸኳይ ርዳታ፣ ከግለሰብ እስከ ድርጅት፣ ከሀገር አቀፍ እስከ ዓለም አቀፍ ተቋማት እየተረባረቡ እንዳሉት ኹሉ፤ ጊዜና ገንዘብ ለሚጠይቀው በዘላቂነት የማቋቋም ተግባርም፣ የሞያና የሀብት ባለቤቶች ዝግጁነታቸውን እንዲያስታውቁ ጥሪ ተላልፏል፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን፣ የጭካኔና የዐመፅ ድርጊት ስትል ባወገዘችው ያለፈው ሳምንት ቅዳሜና እሑድ የነውጠኞች ጥቃት፣ 7 አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉና ሲዘረፉ፣ ከ15 ያላነሱ ካህናትና ምእመናን በአሠቃቂ ኹኔታ መገደላቸው ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል፣ የኢትዮ ሶማሌ ሀገረ ስብከትን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች በቤተ ክርስቲያን ላይ በተደጋጋሚ እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችን አስቀድሞ ለመከላከል፣ ጉዳት ሲያጋጥምም ፈጥኖ ለመድረስ የሚያስችል መደጋገፍን ማዳበር፣ ወቅቱ የሚጠይቀው የህልውና ጉዳይ መኾኑን ያሳሰቡ ሰባክያነ ወንጌልና ምሁራን፣ ነቅቶ የመከላከልና ጠንክሮ የመመከት ክርስቲያናዊ አስተሳሰብን ከማዝለቅ አንሥቶ በተቋምና አሠራር ደረጃም የሚዘረጋበት ኹኔታ እንዲፈጠር እያሳሰቡ ይገኛሉ፡፡

Advertisements

One thought on “ጠቅላይ ቤተ ክህነት: ለተጎዱት የሶማሌ ሀ/ስብከት ምእመናንና አብያተ ክርስቲያን፣ የርዳታና መልሶ ማቋቋም አስተባባሪ ኮሚቴ ሠየመ

 1. Amanuel August 10, 2018 at 5:34 pm Reply

  አዎን አፋጣኝ መፍትሄ ያስፈልጋል ድረሱልን እያሉ የጣር ጩኸት ለሚጮሁ ወገኖቻችን ለመድረስ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ።

  በተመሳሳይ ሁኔታ በጂማ በሻሻ እና አካባቢው በአክራሪ አህዛብ በተፈጸመ አሰቃቂ ግድያ እና የሞቱትን ከአብያተ ክርስቲያናቱ ጋር በማቃጠልና የተረፉትንም በግድ የማስለም ሙከራ በተደረገበት በዚያ ወቅት የቤተ ክርስቲያኗ የቁርጥ ቀን እና የስስት ልጆች ማሕበረ ቅዱሳን ፣ ደጆችሽ አይዘጉ ፣ እና ሌሎች በማህበርም በግልም በመሆን በአካባቢው የፈጸሙት ድንቅ እና የተወደደ ተግባር መቼም መች የሚዘነጋ አይሆንም ።

  አሁንም ቤተ ክህነት ከዚህ በላይ ትኩረት የሚሻ ወቅታዊ ጉዳይ የለምና ከካዝናዋም ጭምር ገንዘብ በመመደብና አርአያም በመሆን እንዲሁም ቅን እና በዚህ ጉዳይ ልምድ ያላቸውን እና እምነት የሚጣልባቸውን እንደ ማህበረ ቅዱሳን እና ደጆችሽ አይዘጉ እና መሰል ማህበራትን በማሳተፍ እና የቤተ ክርስቲያን እስትንፋስ የሆኑ እንደ ሐራ ፣ ማህበረ ቅዱሳን፣ እና ኢ ኦ ተ ቲቪን በመጠቀም እና በተገቢው ለምዕመናን እና ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ እንዲደርስ ያለመታከት በመስራት በጂጂጋ እና አካባቢ ላሉ ወገኖቻችን ከመድረስም በላይ የጥፋት መልዕክተኞቹን አንገት የሚያስደፋ ስራ በመስራት በጅማና አካባቢው የተሰራውን ታሪክ በመድገም እና ተከታታይ መንፈሳዊ ጉዞዎችንም በማዘጋጀት አለንላችሁ ልትላቸው ይገባል ።

  እግዚአብሔር አምላካችን አፅራረ ቤተ ክርስቲያንን ያስታግስልን!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: