የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዐቢይ ኮሚቴ: ለሶማሌ ሀ/ስብከት ተጎጅዎች የመጀመሪያ አስቸኳይ ርዳታ ነገ ያደርሳል፤ ምእመናኑን ያጽናናል፤ ጉዳቱን ያጠናል

38917952_671152836582945_5135487740082651136_n

 • ዐቢይ ኮሚቴው፣ በሦስት ንኡሳን ኮሚቴዎች ተዋቅሯል፤
 • የዘላቂ ድጋፍ የገንዘብ ርዳታ የሚሰበሰብበት አካውንት በንግድ ባንክ ከፍቷል
 • አህጉረ ስብከት፣ ግለሰቦች፣ መንግሥታዊ የኾኑና ያልኾኑ አካላት እንዲተባበሩ ጠየቀ፤

†††

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000254922898

አራት ኪሎ ቅርንጫፍ

†††

በኢትዮጵያ ሶማሌ ሀገረ ስብከት፣ በጅግጅጋና የአካባቢው ዞኖች፣ በተፈጸመው አሠቃቂ ግድያና የንብረት ውድመት ጉዳት ለደረሰባቸው ካህናት፣ ምእመናንና አብያተ ክርስቲያን፣ ድጋፍ የሚያደርግና ርዳታ የሚያሰባብስብ ዐቢይ ኮሚቴ፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ደረጃ የተቋቋመ ሲኾን፣ የመጀመሪያውን አስቸኳይ ርዳታ፣ ነገ ቅዳሜ ረፋድ እንደሚያደርስ ተገለጸ፡፡

በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ የሚመራውና አምስት አባላት ያሉት የዐቢይ ኮሚቴው አካል፣ ነገ ቅዳሜ፣ ነሐሴ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጅግጅጋ በመብረር፣ የተሰባሰቡ ደረቅ ምግቦችንና የታሸገ ውኃ በረኀብና ጽም ቀናትን ላስቆጠሩ ካህናትና ምእመናን እንደሚያደርስ ታውቋል፡፡

Jijiga atari committee

የምድቡ ዋና ተልእኮ፣ በጅግጅጋና የአካባቢው ዞኖች በተፈጸመው ግድያና የንብረት ውድመት የደረሰውን ጉዳት መጠን አጣርቶና ለይቶ ሪፖርት ማቅረብ ሲኾን፤ ሕዝበ ክርስቲያኑንም የማጽናናት ሓላፊነት እንደተሰጠው በምደባ ደብዳቤው ተገልጿል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የዐቢይ ኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ዛሬ ከቀትር በኋላ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋራ የሰጡት መግለጫ እንደሚያስረዳው፥ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ ከማኅበረ ቅዱሳን፣ ከደጆችሽ አይዘጉ፣ ከማኅበረ ጽዮን የተውጣጡ አባላትን የያዘው ዐቢይ ኮሚቴ፣ በሦስት ንኡሳን ክፍሎች የተዋቀረ ነው፡፡

Jijiga Abune Mathewos

ጊዜያዊ የምግብና አልባሳት ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ፣ ከበጎ አድራጊ ግለሰቦችና አካላት ርዳታውን በማሰባሰብ ለተጎዱት ወገኖች የማድረስ አደራ ተጥሎበታል፡፡ 13 አባላት ያሉት ሲኾን፣ የጠቅላይ ጽ/ቤቱ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ዋና ሓላፊ አፈ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌትነት በሰብሳቢነትና የጠቅላይ ጽ/ቤቱ የዕቅድና ልማት መምሪያ ምክትል ሓላፊ መጋቤ ሥርዐት ደስታ ጌታሁን በጸሐፊነት ያስተባብሩታል፡፡

Jijiga sub committee

በየብስ መንገዱ እስኪከፈት ድረስ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በቀን 300 ኪሎ ግራም የሚመዝን ደረቅ ምግቦችንና አልባሳትን ለማመላለስ ቃል እንደገባና በጎ አድራጊዎች፥ በ20፣ በ20 ኪሎ ለክተው በካርቶን በማሸግ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ለሚገኘው የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ እንዲያስረክቡ፣የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በመግለጫው አስታውቀዋል።

የተጎዱትን ምእመናን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋምና የተቃጠሉትን አብያተ ክርስቲያን ዳግም ለማሠራት፣ የገንዘብና የማቴሪያል ርዳታ የማሰባሰቡ ሓላፊነት፣ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሰብሳቢነትና በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት ቀሲስ ክብሩ ገብረ ጻድቅ ጸሐፊነት ለሚመራው ዐቢይ ኮሚቴው የተሰጠ ሲኾን፣ በጠቅላላው 12 አባላት እንዳሉት የምደባ ደብዳቤው ያመለክታል፡፡

Jijiga Abiy committee

የገንዘብ ርዳታው የሚሰበሰብበት አካውንት፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደተከፈተ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ ለርዳታ ማስተባበር ሥራው መሳካት፥ አህጉረ ስብከት፣ በጎ አድራጊ ግለሰቦች፣ መንግሥታዊ የኾኑና መንግሥታዊ ያልኾኑ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉ፣ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000254922898

አራት ኪሎ ቅርንጫፍ

ሦስተኛው የዐቢይ ኮሚቴው አካልየአርክቴክትና የምሕንድስና ባለሞያዎችን የያዘ ቡድን ሲኾን፤ የዲዛይንና የጥገና ተግባራትን የማስተባበር ሓላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ በጎ ፈቃደኛ ባለሞያዎች ከንኡስ ኮሚቴው ጋራ ከወዲሁ በመገናኘት፣ መንገዱ ሲከፈትና ጸጥታው ሲረጋጋ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚችሉ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Advertisements

One thought on “የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዐቢይ ኮሚቴ: ለሶማሌ ሀ/ስብከት ተጎጅዎች የመጀመሪያ አስቸኳይ ርዳታ ነገ ያደርሳል፤ ምእመናኑን ያጽናናል፤ ጉዳቱን ያጠናል

 1. Amanuel August 11, 2018 at 5:04 am Reply

  እጅግ በጣም ጥሩ ቅንብር ነው ለሁኔታው እና ለቦታው የሚመጥኑ የቤተክርስቲያን ልጆችን ማቀፉ ይበል የሚያሰኝ ነው ።

  እናምናለን! ማሕበረ ቅዱሳን ፣ ደጆችሽ ፣ እና ማሕበረ ጽዮን ተቀናጅተው ተዓምር ይሰራሉ፤ እንቅፋት እንኳ ቢኖር እንዴት አልፈው ግባቸውን እንደሚያሳኩ ተፈትነው ያለፉበት እና በወርቅ ቀለም ያስጻፉት ጉልሕ ታሪካቸው ምሥክር ነው ።

  መናኙም አባት የሃ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማቲዮስ ልጆቻቸውን አቀናጅተው አባታዊ አመራር እየሰጡ ጅምሩን ከግብ እንደሚያደርሱ አንጠረጥርም ፤ /ዳሩ ዝቋላን የወጣ የወረደ አባት ይህ አይሳነውም / ።
  የየካ ሚካኤሉም አስተዳዳሪ መልዓከ ብርሃናት ቀሲስ ክብሩ ገ/ጻዲቅም የዋዛ ሰው አይደሉም፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ በደብሩ ያመጡት ለውጥ የሚያስደምም እና የሚያስመሰግናቸው ነው ፍጻሜአቸውን ያሳምርልን ።

  ባጭሩ ለዚህ ዓብይ ጉዳይ ወሳኝ ወሳኝ የሆኑ የቤተክርስቲያኗ ልጆች በግልም በማሕበርም መካተታቸው ይበል የሚያሰኝ ነው ከእኛ የሚጠበቀው በፍጹም ዕምነት ያለስስት በመለገስ ሰማዕታቱ በደም ያገኙትን በረከት እኛ ደግሞ በተፈቀደልን እና ቤተ ክርስቲያን በምታሳስበን መሠረት ለተራቡት እና ለታረዙት ፈጥኖ ለመድረስ ደረቅ ምግቦችን እንደ ቆሎ ፣ ዳቦ ፣ በሶ ፣ ግሪሲኒ እና የመሳሰሉ ምግቦችን እና የታሸጉ ውሃዎችን በግልም በማሕበርም በመሆን ማቅረብ፣ (በተለይ የጽዋ ማሕበራት ታሪክ መስራት ይጠበቅባችኋል) በገንዝብ ልገሳው፣ማቴሪያል በማቅረብ ፣ በሙያ፣ በሀሳብ ፣ እና በጸሎትም በመረባረብ ጂጂጋ እና አካባቢዋ ላይ አጋንንት የፈጸሙትን ግፍ እና ቁስል የሚያክም ሥራ መሥራት ለነገ የማይባል ነውና ለዚህ በመትጋት የተዘጋጀልንን በረከት ለመቀበል እንፍጠን!!!

  እግዚአብሔር አምላካችን አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ያስታግስልን ፤
  የአዛኝት ማርያም ምልጃ አይለየን!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: