“ዕርቀ ሰላሙ በዘመናችን በመፈጸሙ ለደስታዬ ወሰን የለውም”- ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ

 • ከዕርቀ ሰላሙ ሐሳብ አመንጪዎች፣ ቀዳሚው ናቸው፤
 • ይህን ከአሁን ቀደም እኔም ራሴ ብዙ ጊዜ አሳስቤ ነበር፤
 • “ቀኑ ሲደርስ፣ እግዚአብሔር ሲፈቅድ በመፈጸሙ……
 • ቤተ ክርስቲያን ተደስታለች፤የኢትዮጵያ ሕዝብም ተደስቷል፤”

†††

ባለፈው ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ በዋሽንግተን ዲሲ ለተበሠረው የአባቶች ዕርቀ ሰላምና ለተመለሰው ፍጹም የቤተ ክርስቲያን አንድነት፣ በተለያየ ዙር የተቋቋሙ የኮሚቴ አባላት፣ ማኅበረ ካህናትና ማኅበረ ምእመናን፣ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በመከታተል ጥረት ማድረጋቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በመግለጫው ጠቅሷል፡፡ ያለሦስተኛ ወገን አነጋጋሪነት ተገቢውን ውይይት አካሒደው ለውጤት ያደረሱት ልኡካን አባቶችም፣ ለአምስተኛ ጊዜ ወደ ሰሜን አሜሪካ የተላኩ መኾኑን አስፍሯል፡፡

በሒደቱና በውጤቱ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩት ሲመሰገኑ ወጣንያኑም መዘንጋት አይገባቸውምና፣ 6ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ከዕርቀ ሰላሙ ሐሳብ አመንጪዎች በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት ናቸው፡፡

በዘመናችን የተፈጠረው የመለያየት ችግር፣ የቤተ ክርስቲያንና የትውልድ ጠንቅ ሳይኾን በዘመናችን እንዲፈታ፣ ከአሁን ቀደም ብዙ አሳስቤ ነበር፤ ሲሉ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው፣ ላለፉት 26 እና 27 ዓመታት ተለያይታ የነበረችው ቤተ ክርስቲያን ቀኑ ሲደርስና እግዚአብሔር ሲፈቅድ አንድ በመኾኗ ለደስታዬ ወሰን የለውም፤” በማለት የተሰማቸውን ገልጸዋል፡፡

በጋራ ስምምነቱ የተደረሰባቸውን የዕርቀ ሰላምና አንድነት ነጥቦች፣ ቅዱስ ሲኖዶስ መቀበሉን ያስታወቀበትን የትላንቱን አስቸኳይ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ በርእሰ መንበርነት የመሩበትን ኹኔታ፣“በጣም ጥሩ” በማለት ነው ብፁዓን አባቶች የገለጹት፡፡

ከምልዓተ ጉባኤው መጠናቀቅ በኋላም ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በተናጠል ያነጋገራቸው ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ የሚከተለውን ብለዋል፡፡

‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን

ዕርቀ ሰላሙ በዘመናችን በመፈጸሙ እጅግ የሚያስደስት ነው፡፡ ለብዙ ዓመታት ሲሞከር ቆይቶ፣ ላለፉት 26/27 ዓመታት ተለያይታ የነበረችው ቤተ ክርስቲያን በዘመናችን አንድ በመኾኗ ለደስታዬ ወሰን የለውም፡፡

ይህን ከአሁን ቀደም እኔም ራሴ ብዙ ጊዜ አሳስቤ ነበር፤ ነገር ግን ጊዜው ስላልደረሰ ሊሳካ አልቻለም፡፡ በዘመናችን የተነሣውን መለያየት በዘመናችን ካልፈታነው ለወደፊት ሕዝቡ እንደ ባህል፣ እንደ ሃይማኖት ይይዘዋልና እኛ ሳለን ካልተወገደ ለቤተ ክርስቲያን ጠንቅ ኹኖ ነው የሚቀጥለውና ይህን ጉዳይ እናስወግደው ያልኩበት ብዙ ጊዜ ነበር፡፡

ሁሉም የሚኾነው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፣ ቀኑ ሲደርስ፣ እግዚአብሔር ሲፈቅድ በመፈጸሙ ደግሞ በጣም ደስ ብሎኛል፤ ቤተ ክርስቲያንም ተደስታለች፤ የኢትዮጵያ ሕዝብም ተደስቶአል፤ እኔም ደግሞ በእውነቱ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡


 

Advertisements

2 thoughts on ““ዕርቀ ሰላሙ በዘመናችን በመፈጸሙ ለደስታዬ ወሰን የለውም”- ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ

 1. […] በዘመናችን የተፈጠረው የመለያየት ችግር፣ የቤተ ክርስቲያንና የትውልድ ጠንቅ ሳይኾን በዘመናችን እንዲፈታ፣ ከአሁን ቀደም ብዙ አሳስቤ ነበር፤ ሲሉ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው፣ “ላለፉት 26 እና 27 ዓመታት ተለያይታ የነበረችው ቤተ ክርስቲያን ቀኑ ሲደርስና እግዚአብሔር ሲፈቅድ አንድ በመኾኗ ለደስታዬ ወሰን የለውም፤” በማለት የተሰማቸውን ገልጸዋል፡፡Read more>> […]

 2. Amanuel August 2, 2018 at 9:20 am Reply

  ከአስራ ሰባት ዓመታት በላይ ተቆራርጠው የቆዩት ሀገራት ኢትዮጵያና ኤርትራ መሪዎች ለእርቅ እና አንድነቱ ሲገናኙ የፕሮቶኮል ጉዳይ እስኪረሳ ድረስ በፍቅር እየተጓተቱ እኛም በፍቅር እየተመለከትናቸው ዐይናችን ዕንባ ሲያዝል እና ልባችን በሃሴት ስትዘል ነበር ።

  ሃያ ሰባት ዓመታት ተለያይታ የቆየች ሲኖዶሳችን ወደ አንድ ስትመጣ አባቶች ምን ዓይነት ፍቅር እና ትህትና አሳይተው ያስደምሙናል ስል ዓይኔን ከረጢት ለእንባ አስፍቼ በጉጉት ብጠብቅ ከጥቂት የቃላት አሸንክታብ ውጭ ፍቅር ፍቅር የሚሸች ነገር አጥቼ አዘንኩ፤
  ቅዱሳን ፓትርያርኮች አባቶች ሆይ እናንተ በፍቅር እየተሳሳማችሁ ትህትና ስትለዋወጡ ለማየት መድፍ መተኮስ አለበት? ወይንስ የተለየ ድግስ ያስፈልግ ይሆን?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: