ከሲኖዶሳዊው ዕርቀ ሰላም ውይይት በፊት የተላለፈው ውግዘት እንዲነሣ የሰሜን አሜሪካ ማኅበረ ካህናት ጠየቀ፤ “ልኡካኑ ሳይመጡ እንዲፈታ እንጠይቃለን”

Maheberat on synodal reconciliation

 • በይቅርታ እና ምሕረት የኢትዮጵያ ትንሣኤ እየታየ ያለበት ወቅት ነው
 • የ20 ዓመት የኢትዮ-ኤርትራ ጠላትነት ሲፈታ ሲኖዶሱም አንድ ይኹን፤
 • ሲኖዶሳዊ ዕርቀ ሰላም ለታላቋ ቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ሊተገበር ይገባል፤
 • ባይሳካ፣የቤተ ክርስቲያን ችግር የበለጠ ይወሳሰባል፤ አገልግሎቷ ይጎዳል
 • የሊቃውንትና የካህናት ጸጋ፣የምእመናን ሞያና ገንዘብ ብክነቱ ይቀጥላል፤
 • በአንድ እምነት ኹለት አስተዳደር ሳቢያ ካህናት እየተጎዳን አንቀጥልም፤
 • የአገር ውስጥና የውጭ አመራር ብለን ሳንከፋፍል ለማገልገል እንገደዳለን፤

†††

North America Mah Kah2010

የፊታችን ሐምሌ 12 እስከ 20 ቀን 2010 ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ እንዲካሔድ ቀጠሮ የተያዘለት፣ ሲኖዶሳዊው የዕርቀ ሰላም ንግግር ከመጀመሩ በፊት፣ በውጪው አስተዳደር ላይ የተላለፈው ውግዘት እንዲነሣ፣ የሰሜን አሜሪካ ማኅበረ ካህናት ጠየቀ፡፡

በማኅበረ ካህናቱ 246 አባላት ፊርማ ተደግፎ፣በሰብሳቢው መልአከ ሰላም አባ ሰይፈ ገብርኤል ኦብሰን ተፈርሞ ለኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተላከው መግለጫ፣ የተመደቡ ልኡካን አባቶችና አስታራቂ ሽማግሌዎች ወደ ሰሜን አሜሪካ ከመጓዛቸው በፊት፣ ከኢትዮጵያ ውጭ ባለው አስተዳደር ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተላለፈው ውግዘት እንዲነሣ  የተጠየቀ ሲኾን፣ ይህም ለዕርቀ ሰላሙ ስኬት የራሱ አስተዋፅኦ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ትንሣኤዋን እያየች የምትገኝበት የአኹኑ የይቅርታና የምሕረት ወቅት፣ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ አንድነቷን የምታስመልስበት ወሳኝ ዕድል ከእግዚአብሔር እንደተሰጣት የገለጸው የሰሜን አሜሪካ ማኅበረ ካህናት፣ በሰበብ አስባቡ ዕርቁ ባይሳካ፣ ችግሯ የበለጠ የሚወሳስብበትንና አገልግሎቷ የሚጎዳበትን ስጋቱን ጠቁሟል – “በውጭ ያለው አስተዳደር ሀገር ቤት ገብቶ ጽ/ቤት ከፍቶ ሥራ ለመሥራት የሚከለክለው ምንም ዐይነት የፖሊቲካ ተጽዕኖ እንደማይኖር በመንግሥት የተረጋገጠ ስለኾነ፣ ይህን ጥፋት ለማስቀረት ወቅቱ አኹን መኾኑን ለአባቶቻችን ልናሳስብ እንወዳለን፤” ብሏል፡፡

መንግሥትና የፖሊቲካ ባላንጦች በይቅርታ እየተቀራረቡ ያሉበት፣ ለ20 ዓመታት በጠላትነት ይፈላለጉ የነበሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ የጦርነት ኹኔታዎችን በይፋ አቁመው ዕርቅ የፈጸሙበት ይህ ወቅት፣“ስታለቅሱበትና ስትናፍቁት የነበረው የኢትዮጵያ ትንሣኤ እየታየ ያለበት ነው፤” ያለው ማኅበረ ካህናቱ፣ ለታላቋ ቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ሲባል የይቅርታ መምህራን ከኾኑት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሚጠበቀው፣ የተላለፈውን ውግዘት ከዕርቀ ሰላም ንግግሩ በፊት አስቀድሞ ማንሣት እንደኾነ አስገንዝቧል፡፡

አስተዳደራዊ አንድነቷ ለኹለት ተከፍሎ በቆየባቸው ያለፉት ኻያ ዓመታት፣ ለአገር ግንባታና ለትውልድ ጥቅም ልታውለው የምትችለው የሊቃውንት ዕውቀት፣ የካህናት ጸጋ፣ የምእመናን የሞያና የገንዘብ የተባበረ አቅም ለብክነት መዳረጉን አስረድቷል፤ ይህም፣ የታሪካዊቷን ቤተ ክርስቲያን አስተዋፅኦ እንዳደበዘዘውና ተቀባይነቷንም እንደቀነሰው በቁጭት አስፍሯል፡፡

ቤተ ክርስቲያን ቀደም ሲል አስተዳደራዊ አንድነቷን ለመመለስና ለማጠናከር ያገኘቻቸውን ዕድሎች እንዳልተጠቀመችባቸው ያወሳው ማኅበረ ካህናቱ፣ “የአሁኑን ዕድል እንድትጠቀምበት አባቶቻችንን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን፤” ሲል ተማፅኗል፡፡ ኾኖም፣ ዕርቀ ሰላሙ ሳይሳካ ቀርቶ “በአንዲት እምነት ኹለት አስተዳደር” የሚቀጥል ከኾነ፣ ከማንም በላይ ተጎጅዎቹ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ካህናት በመኾናቸው፣“ቤተ ክርስቲያናችንን ለመታደግ የአገር ውስጥና የውጩ አስተዳደር ብለን ሳንከፋፍል ያለምንም ልዩነት ለማገልገል የወሰንን መኾናችንን በታላቅ ትሕትና ለማስታወቅ እንወዳለን፤” በማለት አሳስቧል፡፡

Advertisements

One thought on “ከሲኖዶሳዊው ዕርቀ ሰላም ውይይት በፊት የተላለፈው ውግዘት እንዲነሣ የሰሜን አሜሪካ ማኅበረ ካህናት ጠየቀ፤ “ልኡካኑ ሳይመጡ እንዲፈታ እንጠይቃለን”

 1. Anonymous July 10, 2018 at 7:00 pm Reply

  We all pray to GOD that the dispute will be resolved and our Church will start the reconciliation and healing process.

  But the statement “ኾኖም፣ ዕርቀ ሰላሙ ሳይሳካ ቀርቶ “በአንዲት እምነት ኹለት አስተዳደር” የሚቀጥል ከኾነ፣ ከማንም በላይ ተጎጅዎቹ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ካህናት በመኾናቸው፣“ቤተ ክርስቲያናችንን ለመታደግ የአገር ውስጥና የውጩ አስተዳደር ብለን ሳንከፋፍል ያለምንም ልዩነት ለማገልገል የወሰንን መኾናችንን በታላቅ ትሕትና ለማስታወቅ እንወዳለን” is flat out wrong.

  The clergy in both administration have the obligation to abide by the decision of their respective Synods. If they start cherry picking rules to ignore/respect, then it is the beginning of another chaos within the Church.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: