ምልአተ ጉባኤው: ለሲኖዶሳዊ ልዩነቱ የመጨረሻ እልባት ለመስጠት ዝግጁነቱን አረጋገጠ፤ አስተዳደራዊ ማሻሻያ በጥናት እንዲፈጸም አዘዘ፤ ነገ ጠዋት መግለጫ ይሰጣል

holy-synod-ginbot2010-2nd-day

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ለዛሬ ማክሰኞ፣ ሐምሌ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. የጠራውን አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ፣ በሲኖዶሳዊው የዕርቀ ሰላም ሒደትና በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ላይ በትኩረት ከተወያየ በኋላ ውሳኔና መመሪያ በመስጠት ማምሻውን አጠናቋል፡፡

ሲኖዶሳዊውን የዕርቀ ሰላም ሒደት በተመለከተ፡-

 • ልኡካን አባቶች፣ እንዳስፈላጊነቱ የሚወስኑበትን ሙሉ ሥልጣን ሰጠ፤
 • በሠየማቸው 3 ልኡካን አባቶች የመጨረሻ እልባት እንዲያገኝ ወስኗል
 • ለቋሚ ሲኖዶሱ፣ የአካሔድና የሥርዐት 5 ነጥቦች፣ ይኹንታ ሰጥቷል፤
 • የሀገር ወስጥና የውጭ ሲኖዶስ መባሉ“ታሪካዊና አሳዛኝ ግድፈት ነው፤
 • ሽማግሌዎች፣ሒደቱን የሚያስጨርስ ነገር ሊቀርብ እንደሚገባ መከሩ፤

†††

 • “ከቅ/ሲኖዶስ ዕውቅናና ውክልና ውጭ የሚሰጡ መግለጫዎች አግባብነት የላቸውም፤”
 • “ዕርቀ ሰላሙ ሲደከምበት የኖረ እንጅ አኹን የተፈጠረ እንዳልኾነ መታወቅ አለበት፤”
 • “ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ በ4 የተለያዩ ጊዜያት ልኡካን መድቦ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፤”
 • “በ2ቱም በኩል የተላለፈው ውግዘትና ሌሎች ዝርዝሮች ከዕርቀ ሰላሙ በኋላ ይታያሉ፤”

†††

የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ወቅታዊ ችግሮችን በተመለከተ፣ 6 አባላት ያሉት የብፁዓን አባቶች ኮሚቴ ያቀረበውን መነሻ ተመልክቶ፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በዋናነት ተይዞ የሌሎች አህጉረ ስብከትም ዐበይት ክፍተቶች በጥናት ተደግፎ መፍትሔ እንዲሰጣቸው አዝዟል

 • ትልቁ ችግር፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን የማስፈጸም አቅም ማጣት ነው፤
 • አፋጣኝ እርምት ባለመሰጠቱ፣ ምእመናን እና ወጣቶች ቢሮዎችን አሽገዋል
 • ሕዝባዊ መማክርት ለሲኖዶስ ለሚሉ ክፍሎችም መንገድ ሊከፍት ችሏል፤
 • በባለሥልጣናት ንግግሮችና በተቋማት ሪፖርቶች ለክሥና ወቀሳ አጋልጦናል
 • ለሰብአዊ መብት መከበር ግንባር ቀደም ከመኾን ይልቅ በጥሰት ተጠቅሰናል፤

†††

 • በመንግሥት ከተለዩ 18 ጥሰቶች 2ቱ ለቤተ ክርስቲያናችን ብቻ ተገልጸዋል
 • የአ/አበባ ሀ/ስብከትና የአጥቢያ ሓላፊዎች የተደራጀ ዝርፊያ ዐይነተኛው ነው
 • ሀገረ ስብከቱን፣ ለ4 ሊቃነ ጳጳሳት የመክፈል የከሸፈ ሐሳብ ውድቅ ተደርጓል፤
 • የአ/አ እና የሌሎችም አህጉረ ስብከት ክፍተት የሚታይበት ልዩ ጥናት ያሻል፤
 • የተጠናው የመዋቅር ለውጥም፣ሙስናነና ጎጠኝነትን የምናጠፋበት ነው፤ይታይ
 • ከሃይማኖት ሕጸጽ እና ከሌብነት ነጻ የኾኑ የታገዱ ሠራተኞች እየታዩ ይመለሱ፤

†††

በተያያዘ ዜና ነገ በሚያወጣው መግለጫ፡-

 • ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ሰላምና ትብብር መመለሳቸውን ቅ/ሲኖዶሱ አንሥቷል፤
 • ቀጣይነቱ የሠመረ እንዲኾን ግንኙነቱን በመደገፍ የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጿል፤
 • የጠ/ሚኒስትሩ፣የመደመር እሳቤበመግለጫ ረቂቁ ቢነሣም በማከራከሩ ቀርቷል፤
Advertisements

2 thoughts on “ምልአተ ጉባኤው: ለሲኖዶሳዊ ልዩነቱ የመጨረሻ እልባት ለመስጠት ዝግጁነቱን አረጋገጠ፤ አስተዳደራዊ ማሻሻያ በጥናት እንዲፈጸም አዘዘ፤ ነገ ጠዋት መግለጫ ይሰጣል

 1. Amanuel July 11, 2018 at 6:38 am Reply

  ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን እንደማያውቅ መፃህፍት ተባብረው ይመሰክራሉ ፤
  የህግ ሁሉ ፍጻሜውም ፍቅር መሆኑንም እናውቃለን ወንድምህን ውደድ የተባለው ቃል ምንኛ ገዢ ነው

  በተለይም ለመንጋው አርዓያ ሊሆኑ ከሚገባቸው እረኞች ካህናት እና ሊቃነ ጳጳሳት ይህ ጉዳይ ከምንም በላይ ሊያሳስባቸው በተገባ!!
  ጥረት እና ትግል በራሱ ግብ አይሆንም ግቡ ውጤቱ ነው፤ አዎን ለእርቀ ሰላሙ 4 እና ከዚያ በላይ ዓመት ተለፍቶና ተደክሞም ይሆናል ያ ግን ስኬት አይደለም ስኬቱ እርቀ ሰላሙን ፈፅሞ ሁለትነትን አጥፍቶ አንድ መሆን ነው፤ እንጂ ለእርቁ 4 ወይንም 8 ዓመት ደከምን ማለቱ ሜዳሊያም አያሰጥ አክሊልም አያስደፋም !!

  አማላጂቱን ቤተ ክርስቲያን ለክብሯ በማይመጥን ሥርዓት ወዲህ ወዲያ መናጡ ባልተገባም ነበር፤ እናንተ አባቶች የፍቅር ልብ ሳይኖራችሁ እንዴት ክቡሩ መስዋዕት ፊት ልትቀርቡ እንደደፈራችሁ እናንተ ታውቃላችሁ በፍቅር ያልሆነስ ፀሎት እና ምልጃ ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ ግዳጅ ይፈጽም ይሆን? እንጃ!!

  እውነት እንነጋገር ከተባለ ለዚህች ሀገር መመሰቃቀል ሙሉ ሀላፊነቱን መውሰድ ይገባችሁ ነበር ። ምክንያቱም ለተሾማችሁበት ታላቅ ሀላፊነት በተገባ አልተገኛችሁምና ፤ ባጭሩ መንጋውን ለተኩላ ሰጥታችሁ አስበልታችሁታል ሀገሪቱንም አጥፊ እና ቀጣፊ ሊያጠፋት ሲረባረብባት አንገታችሁን ቀብራችሁ አላየንም አልሰማንም ማለትን መረጣችሁ ቢያንስ አቡነ ጴጥሮስ የተሰውሉትን ዓላማ መዘንጋት ተገቢ አልነበረም።

  የሆነው ሆኖ በአንድም በሌላም በኩል መንገድ ያለው እግዚአብሔር ሀገርን እና ሕዝቧን ከመበታተን ይታደግ ዘንድ ይህን የእነ ዶ/ር አብይን፣አቶ ለማን፣ አቶ ገዱን እና አቶ ደመቀን ወዘተ….አስነስቷል።

  ስለዚህ አሁን ለጥፋታችን ምክንያት የለንምና በቶሎ ድድር ልባችንን አቅልጠን ስለ ቤተክርስቲያን ክብር ፍቅርን እናስቀድምና አንድነትን እናምጣ ቤቷ ሰፊ ሀብቷም ብዙ የአገልግሎቷም ዘርፍ የትየለሌ ነውና ስስትን እና ጥላቻን አስወግደን ፍቅርን እናምጣ አባቶች ከእናንተ አሁንም ሀገር እና ቤተ ክርስቲያን ብዙ ይጠብቃሉና የሚባክን ጊዜ ባይኖራችሁ ይመረጣል!!!!!!!
  እግዚአብሔ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ይባርክ አሜን! !!

  • wondemagegn wosoro July 18, 2018 at 1:01 pm Reply

   ለጥፋታችን ምክንያት የለንምና በቶሎ ድድር ልባችንን አቅልጠን ስለ ቤተክርስቲያን ክብር ፍቅርን እናስቀድምና አንድነትን እናምጣ ቤቷ ሰፊ ሀብቷም ብዙ የአገልግሎቷም ዘርፍ የትየለሌ ነውና ስስትን እና ጥላቻን አስወግደን ፍቅርን እናምጣ አባቶች ከእናንተ አሁንም ሀገር እና ቤተ ክርስቲያን ብዙ ይጠብቃሉና የሚባክን ጊዜ ባይኖራችሁ ይመረጣል!!!!!!!
   እግዚአብሔ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ይባርክ አሜን!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: