ኹለቱ የዋልድባ መነኰሳት ስለ እስር ቆይታቸው

 • ተፈታን የምንለው፥በሀገርና በቤተ ክርስቲያን የተተበተበው ማነቆ ሲበጠስና ሲፈታ ነው
 • …የአገር ሰላምና አንድነት፣የመናገርና የመጻፍ መብት ሲረጋገጥ፤መልካም አስተዳደር ሲሰፍን
 • ቆብህን፣ የሃይማኖት ልብስህን አውልቅ” እያሉ መሬት ለመሬት እየጎተቱ ሥቃይ ደርሶብኛል
 • አይዟችሁ ብለው ለደገፉንና ለጠየቁን ኹሉ፣በዋልድባ ገዳም ስም በእጅጉ እናመሰግናለን

†††

VOAAmharic

በዛሬው ዕለት ከእስር የተፈቱት ኹለቱ የዋልድባ መነኰሳት፣ አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማርያም እና አባ ገብረ ሥላሴ ወልደ ሃይማኖት፥ “ተፈታን የምንለው፣ አገራችንና ቤተ ክርስቲያናችን ከታሰሩበት ማነቆ መፈታት ሲችሉ ነው፤ ብለዋል፡፡ አያይዘውም በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ ያሉ ብዙ ሰዎች ሲፈቱና የአገሪቱ ሰላም ሲረጋገጥ፣ ከእስር በመፈታታቸው እንደሚደሰቱ ነው የገለጹት፡፡ ጽዮን ግርማ አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡

አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማርያም፡-

እንኳን ከእስር ተፈቱ፡፡ ዛሬ ነው ከእስር የወጡት፤ ስንት ሰዓት ላይ ነው?Aba Gebrayesus

እንኳን የአበው አምላክ ከእናንተ ጋራ አገናኘን፤ ዛሬ 5 ሰዓት አካባቢ ነው የወጣነው፤

የታሰራችሁበት ጊዜና የእስር ኹኔታችሁ ምን ይመስል ነበር? በፍ/ቤት የነበረው ኹኔታ በዘገባ ሲወጣ ነበር፤ በእናንተ አንደበት እንዴት ትገልጹታላችሁ?

እኛ የታሰርነው ታኅሣሥ 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ነው፡፡ የፍ/ቤት፣ የማዕከላዊ እና የቂሊንጦ ችግር፤ በእኔ አንደበት ብቻ ተገልጾ የሚዘለቅ አይደለም፡ ወደፊት ብዙ የምንነጋገርበት ይኾናል፡፡ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይኹን፤ በእውነት የአባቶቻችን አምላክ ከብዙ ፈተናዎች አውጥቶ ለመነጋገር አብቅቶናል፤ ደካሞች ብንኾንም፣ በሕዝባችን ትግልና ጥረት፣ በአባቶቻችን አምላክ ኃይል የመጣብንን ፈተና አስወግዶ አሁን ከወገናችንንና ከሕዝባችን ጋራ እንድንቀላቀል አድርጎናል፡፡

ከነበረው ጊዜ ከባዱና ተገላገልነው የምትሉት የትኛው ነበር?

አሁን ተገላግለናል ማለት አይደለም፡፡ ከእስር ተፈታን የምንለው ሀገራችን፣ ቤተ ክርስቲያናችን ከታሰሩበት ማነቆ፣ የተተበተበው ማነቆ ሲበጠስና ሲፈታ ነው፤ ከእስር ተፈታን ብለን የምንናገረው፡፡ አሁን ግን ታግተን ነበር፤ ተለቀን ወደ ማኅበረሰቡ፣ ብዙኃኑ ወደታሰረበት እስር ቤት ተገናኘን፣ አብረን በአንድ ላይ ተቀላቀልን ማለት እንጅ ከእስር ተፈታን ማለት አይደለም፡፡

ምክንያቱም፣ በብዙ ነገር ታስረን ነው እየተንቀሳቀስን ያለነው፡፡ እዚያ ውስጥ አካላችን ነው የታሰረው፤ መንፈሳችን አይታሰርም፡፡ ብዙ ወገኖቻችን ታስረዋል፤ አሁንም እንደነ አሸናፊ አካሉ ያለ ያለምንም ፍርድ ለአምስት ዓመት ከሦስት ወር በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ያስቆጠሩ ወንድሞቻችን እንደታሰሩ ነው፡፡ እነኚህ እስካልተፈቱ ድረስ፣ ከእስር ተፈታን ብለን ደፍረን ልንናገር አንችልም፡፡ በእገታ ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችን ሲፈቱና የአገራችን ሰላምና አንድነት ሲረጋገጥ፤ የመናገርና የመጻፍ መብት ሲጠበቅ፤ መልካም አስተዳደር ሲሰፍን፣… ያኔ ነው ከእስር ተፈታን ብለን የምንናገረው፡፡

ኹለተኛ፥ በማዕከላዊም ኾነ በቂሊንጦ የእኛን መታሰር፣ መቸገር፣ መንገላታት በተለያዩ ሚዲያዎች ሲተላለፍ በመስማት ለተባበሩን፣ ከቦታው ድረስ መጥተው ለጠየቁን ክርስቲያንና ሙስሊም የሌላም እምነት ተከታዮች፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ላሉ ኹሉ በዋልድባ ገዳም ስም እጅግ አድርገን እናመሰግናለን፡፡ በእነርሱ አይዟችሁ ባይነት፣ ሞራልና ድጋፍ ሰጭነት፣ ከታገትንበት ወጥተን ከወገኖቻችን ጋራ እንድንቀላቀል አድርገውናል፡፡

አባ ገብረ ሥላሴ ወልደ ሃይማኖት፡-

Aba Gebrasilassieየእስር ቆይታችሁን እንዴት ይገልጹታል? ዛሬ ከእስር በመውጣትዎ ያልዎት ስሜት ምንድን ነው?

ከእገታ ነው የወጣነው እንጅ ከእስር ተፈታን ማለት አይቻልም፤ ምክንያቱም፣ ብዙ ወንድሞቻችን በሥቃይና በመከራ ውስጥ ነው ያሉት፡፡ እኛም ብዙ መከራና ሥቃይ አይተናል፡፡

ኹለታችሁም የምንኵስና ልብሳችሁን እንድታወልቁ ስትገደዱ፣ በማረሚያ ቤት ውስጥ መሬት ለመሬት ተጎትተዋል፤ የሚል ቀርቦ በዘገባችን አካተን ነበር፤ ጠበቃችሁም በወቅቱ ገልጸውልን ነበር፡፡ እርሱን ኹኔታ በእርስዎ አንደበት ደግሞ ቢገልጹልን?

ጠበቃችን ልክ ናቸው፤ እውነት ነው፡፡ ኅዳር 14 ቀን ሰው ወደሌለበት ጨለማ ቤት ይዘውኝ ሒደው፣ ቀጠሮ የሌለኝን ቀጠሮ አለህ ብለው አታለው አውጥተው አራት የጎማ ብትር የያዙ ባሉበት አንዱ መሬት ለመሬት እየጎተተ፣ ሌሎቹ ደግሞ በኋላ በኋላ እየተከተሉ፣ ከጠዋቱ 2 እስከ 4 ሰዓት ድረስ፣ “ቆብህን፣ የሃይማኖት ልብስህን አውልቅ” እያሉ እየተሳደቡ፤ የተወለድኩበትን አገርና ማንነቴን እየሰደቡ ብዙ መከራና ሥቃይ አድርሰውብኛል፡፡ እኔን ቢሰድቡኝ ጥሩ ነበር፡፡እኔም ብቻ ሳልኾን፣ እንደ ወንድምም እንደ አባትም የማያቸው አባ ገብረ ኢየሱስም ብዙ ሥቃይ አይተዋል፡፡

አባ ገብረ ሥላሴ፣ ኹለታችሁም ለሰጣችሁ ማብራሪያ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ሰፋ ባለ ማብራሪያ እመለሳለሁ፡፡

Advertisements

3 thoughts on “ኹለቱ የዋልድባ መነኰሳት ስለ እስር ቆይታቸው

 1. Anonymous April 16, 2018 at 1:46 pm Reply

  “አሁን ተገላግለናል ማለት አይደለም፡፡ ከእስር ተፈታን የምንለው ሀገራችን፣ ቤተ ክርስቲያናችን ከታሰሩበት ማነቆ፣ የተተበተበው ማነቆ ሲበጠስና ሲፈታ ነው፤ ከእስር ተፈታን ብለን የምንናገረው፡፡ አሁን ግን ታግተን ነበር፤ ተለቀን ወደ ማኅበረሰቡ፣ ብዙኃኑ ወደታሰረበት እስር ቤት ተገናኘን፣ አብረን በአንድ ላይ ተቀላቀልን ማለት እንጅ ከእስር ተፈታን ማለት አይደለም፡፡
  ምክንያቱም፣ በብዙ ነገር ታስረን ነው እየተንቀሳቀስን ያለነው፡፡ እዚያ ውስጥ አካላችን ነው የታሰረው፤ መንፈሳችን አይታሰርም፡፡ ብዙ ወገኖቻችን ታስረዋል፤ አሁንም እንደነ አሸናፊ አካሉ ያለ ያለምንም ፍርድ ለአምስት ዓመት ከሦስት ወር በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ያስቆጠሩ ወንድሞቻችን እንደታሰሩ ነው፡፡ እነኚህ እስካልተፈቱ ድረስ፣ ከእስር ተፈታን ብለን ደፍረን ልንናገር አንችልም፡፡ በእገታ ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችን ሲፈቱና የአገራችን ሰላምና አንድነት ሲረጋገጥ፤ የመናገርና የመጻፍ መብት ሲጠበቅ፤ መልካም አስተዳደር ሲሰፍን፣… ያኔ ነው ከእስር ተፈታን ብለን የምንናገረው፡፡”

  this is the truth…This is what the Church should say. But Aba Mathias talks about ” Lemat”

 2. Hailu April 16, 2018 at 5:19 pm Reply

  The true fathers of the Ethiopian Orthodox tewahedo church. Leave it the patriarch and Sinodos.

 3. Anonymous April 24, 2018 at 8:06 am Reply

  “But Aba Mathias talks about ” Lemat”

  Lemat? What?

  What is Lemat? Is it nepotism? Is it corruption? Is it ungodliness? Is it racism? Is it going against church orders? Is it punishing the true church fathers in different forms?

  “Lemat” is the cover (False Flag).

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: