ለቀውሱ መስፋት ካህኑን ተጠያቂ ያደረጉት ፓትርያርኩ፥“የሰላም መስቀል ይዘን ሕዝቡን የሰላም ኃይል ማድረግ እንዴት አቃተን?” ሲሉ ጠየቁ

 

 • ሚኒስትሩንም ጄኔራሉንም፣ ወጣቱንም ሽማግሌውንም፣ ምሁሩንም ተመራማሪውንም የካህኑ ልጅ አድርጎ እግዚአብሔር ሰጥቶአል፤
 • የምእመናን የቅርብ ጠባቂ፣ ከላይ ያሉት ባለሥልጣናት ሳይኾኑ በነፍስ አባትነት ደረጃ በቅርብ ያሉ ካህናት ናቸው፤ በሌላ ማመካኘት ተቀባይነት አይኖረውም፤
 • ሌላው በራሱ ስሕተት ሲጠየቅ፣ ካህኑ ግን ሕዝበ እግዚአብሔርን የመጠበቅ ሓላፊነት ስለተሰጠው፣ በሕዝቡ ስሕተት የመጠየቅ ግዴታም አለበት
 • ወንድማማቾች ሲነታረኩ፣ መስቀሉን ይዞ ከመካከል በመግባት ስመ እግዚአብሔርን ከጠራ የማይሰማ የለም፤ ችግሩ ከአሰሚው ነው፤

†††

 • የጋራ ሓላፊነታችንን አልተወጣንም፤ ከብፁዓን አባቶች ጀምሮ ሀብተ ክህነት ያለው ሁሉ ለሰላምና ለሕዝብ አንድነት መጠበቅ ማስተማርና መስበክ አለበት፤
 • ክህነታዊ ተልእኮውን በስኬት ለማከናወን፣ በተሟላ መንፈሳዊ ሰብእና መቆም ያስፈልጋል፤ በግዴለሽነትና በኢቀኖናዊነት ከተፈጸመ ተጠያቂነቱ ከባድ ነው
 • ያለሰላም ህልውና፣ ያለሕዝብ አንድነትና ያለሀገር ልማት ቀጣይነቷ አስተማማኝ የኾነች ቤተ ክርስቲያን ልትኖር እንደማትችል ካህናት ማስተዋል አለብን፤
 • ለምትወደንና ለምንወዳት ቤተ ክርስቲያን ህልውና መቀጠል ስንል በሰላሙ ጥበቃ፣ በሀገር አንድነት፣ በሕዝብ ለሕዝብ ትስስርና በልማቱ ሥራ ያለመታከት እናስተምር!!

†††

pat anba mathias 5th enth anniv

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

“አንትሙሰ ጽንዑ ከመ ዕብን መንፈሳዊ ወኩኑ ታቦተ መንፈሳዌ ለክህነት ቅድስት ወንጽሕት ከመ ታቅርቡ ወታዕርጉ መሥዋዕተ መንፈሳዌ ዘይሰጠወክሙ እግዚአብሔር በእደዊሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ =

እናንተስ እንደ መንፈሳዊ ዕብነ ማዕዘንት ኹኑ፤ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እጅ የሚቀበላችሁን መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡና ታሳርጉ ዘንድ ቅድስትና ንጽሕት ለኾነች ክህነት መንፈሳዊ ታቦት ኹኑ፡፡” (1ኛጴጥ.2፥5)

‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡

እግዚአብሔር የጎደለውና የሚጎድለው የሌለ ምሉእ ጸጋ ወጽድቅ አምላክ እንደኾነ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንማራለን፡፡ ይኹን እንጅ ደስ የሚያሰኘውና የማያሰኘው አካሔድና አቀራረብ እንዳለው ከጥንት ጀምሮ ገልጾአል፡፡ እግዚአብሔር ኹሉን የፈጠረና ያስገኘ፥ ኹሉን የሚያስተዳድርና የሚመግብ፥ ኹሉን የሚያስተባብርና የሚቆጣጠር፥ የፍጥረታት ኹሉ ባለቤት፥ የበላይ መሪና ገዥ በመኾኑ ይህን መለኰታዊ ኃይሉን ዐውቀን እንድንከተለው ይፈልጋል፡፡

አምልኮና ምስጋና፥ መታዘዝና ኅብረትም ከፍጡራኑ ይጠብቃል፡፡ አምላከ አማልክት እግዚአብሔር ከሰው የሚፈልገውን ኹሉ በቅዱስ መጽሐፍ በዝርዝር የገለጸ ሲኾን፤ ፈቃዱን የሚያስፈጽሙ አካላትንም በልዩ አጠራር እየሾመ ወደ ሥራ ሲያሠማራ፥ በሓላፊነትም ሲያስቀምጥ ኖሮአል፤ ለወደፊቱም እንደሚቀጥልበት በቃሉ አረጋግጦአል፡፡

ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ የኾነው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ፣ እግዚአብሔር ደስ ከሚሰኝባቸው ነገሮች አንዱን ጠቅሶ ሲያስተምር፦ “መንፈሳዊ መሥዋዕትን ማቅረብ” እንደኾነ ይነግረናል፡፡ መሥዋዕት ከተነሣ ዘንድ ካህን ማስፈልጉ የግድ ነውና፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት የሚያቀርቡ ካህናትም ቅዱሳን ይኾኑ ዘንድ በመንፈሳዊ ዕውቀትና ብቃት መገንባት ሐዋርያው አበክሮ ያስተምራል፡፡

የክህነት አገልግሎት ከእግዚአብሔር ጋራ በቀጥታ ግንኙነት ያለው በመኾኑ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ፣ ጥበቃና ክብካቤ ሊደረግለት እንደሚገባ ከዚህ መረዳቱ አይከብድም፡፡ ቅድስና፥ ንጽሕና፥ ሓላፊነት፥ ጥንቃቄና ፈሪሀ እግዚአብሔርን ገዢ ባደረገ መልኩ ክህነታዊ አገልግሎት ሲከናወን የሚሰጠው ዋጋ ታላቅ የመኾኑን ያህል፥ በግድየለሽነት ሃይማኖቱና ቀኖናው ከሚያዘው ውጭ ከተፈጸመ ተጠያቂነቱ ከባድ እንደኾነ በቅዱስ መጽሐፍ የተገለጸ እውነት ነው፡፡

ሌላው ሰው የሚጠየቀው ራሱ በፈጸመው ስሕተት ሊኾን ይችላል፤ ካህን ግን ሕዝበ እግዚአብሔርን የመጠበቅ ሓላፊነት የተሰጠው ስለኾነ በሕዝቡ ስሕተት የመጠየቅ ግዴታም አለበት፡፡ ከዚህ አኳያ በዚህ በዓለ ሢመተ ክህነት፣ ማስታወስና ማሰላሰል ያለብን እኛ ካህናት ልንሠራው ከሚጠበቅብን የሠራነው ምን ያህል ነው? የሚለውን ነው፡፡

ምናልባት አንዳንድ ሰዎች፣ የቤተ ክርስቲያን ሓላፊነት ከላይ በተቀመጡ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ብቻ እንዳለ ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን እንደዚህ ያለው አስተሳሰብ የጠሳሳተና ሌላውን ሳይኾን ራስን ለድክመት የሚዳርግ ኃጢአት ከሚኾን በቀር በእግዚአብሔርም ኾነ በሕግ ፊት ማምለጫ ሊኾን ከቶ አይችልም፡፡

ይልቁንም ጌታችን በቅዱስ ወንጌል በግልጽ እንዳስተማረን ባለአምስት መክሊትም፥ ባለኹለት መክሊትም፥ ባለአንድ መክሊትም እንደየአቅማቸው በተሰጣቸው ስጦታ መሠረት መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እውነቱን ለመናገር፥ በጎቹን በቅርብ የሚጠብቅ የበጎች ባለቤት ሳይኾን ቀኑን ሙሉ ሳይለያቸው የሚውል እረኛው ነው፡፡ የምእመናን የቅርብ ጠባቂም ከላይ ያሉት ባለሥልጣናት ሳይኾኑ በነፍስ አባትነት ደረጃ በቅርቡ ያሉ ካህናት ናቸው፡፡ ይህም ከኾነ በእጅ ያሉ ምእመናንን ነቅቶና ተግቶ መጠበቅ ሲቻል በሌላ እያመካኙ ስንፍናን ማስተናገድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

ከዚህ አኳያ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እያንዳንዱን ምእመን ከነቤተሰቡ የሚጠብቅ ካህን መድባ እያለ እነ ገብረ ሥላሴ፣ እነ ወለተ ሥላሴ በተኵላ ሲነጠቁ ካህኑ የት ሒዶ ነው? ሰላም፥ ፍቅርና መግባባት በወንድማማቾች መካከል እየተሸረሸረ የጎሪጥ መተያየቱ ሲሰፋ ካህኑ የት ሒዶ ነው? ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን ለሦስት ሺሕ ዓመታት እንደ ዝናመ ክረምት ያለማቋረጥ በፈሰሱባት ምድር አንድነቱና ማኅበራዊ ትስስሩ እንደ ብረት የጠነከረ ሕዝብ ያላት ሀገር ወዲህ ወዲያ የሚያወዛውዝ ነፋስ በየት ገባባት? የዚህ ክፍተት ተጠያቂስ ከካህን በቀር ማን ሊኾን ይችላል? የሚል ጥያቄ ወቅታዊ ኾኖ ይገኛል፡፡

ምክንያቱም እግዚአብሔር ባለሥልጣኑንም፥ ምሁሩንም፥ ተመራማሪውንም ኹሉ የሰጠ ለካህን በመኾኑ ነው፤ ሚኒስትሩንም ጄኔራሉንም የካህን ልጅ አድርጎ እግዚአብሔር ሰጥቶአል፤ ሽማግሌውንም ወጣቱንም፥ ወንዱንም ሴቱንም፥ ሀብታሙንም ድኻውንም፥ ገበሬውንም ነጋዴውንም ኹሉ ለካህን ሰጥቶአል፡፡ ሌላው ኹሉ ከካህን በኋላ ነው፡፡

ሕዝቡም ይህን በሚገባ ስለሚያውቅ አልቀበልም፤ አልሰማም ብሎ አያውቅም፡፡ ችግሩ ከሰሚው ሳይኾን ከአሰሚው እንደኾነ ማየቱ አይከብድም፡፡ ኹለት ወንድማማቾች ሲነታረኩ፣ ካህኑ እንደ አባቶቹ መስቀሉን ይዞ በመካከል በመግባት ስመ እግዚአብሔርን ከጠራ የማይሰማ እንደሌለ በርግጠኝነት እናውቃለን፡፡ ታድያ ይህን የሰላም መስቀል ይዘን ሕዝቡን የሰላም ኃይል ማድረግ እንዴት አቃተን?

28471256_1827435253943065_4663614715656667136_n

ኹለት ወንድማማቾች ሲነታረኩ፣ ካህኑ እንደ አባቶቹ መስቀሉን ይዞ በመካከል በመግባት ስመ እግዚአብሔርን ከጠራ የማይሰማ እንደሌለ በርግጠኝነት እናውቃለን፡፡ ታድያ ይህን የሰላም መስቀል ይዘን ሕዝቡን የሰላም ኃይል ማድረግ እንዴት አቃተን?ችግሩ ከሰሚው ሳይኾን ከአሰሚው እንደኾነ ማየቱ አይከብድም፡፡ (ፎቶ: Birhan Bihil)

ከዚህ አኳያ ሲመዘን፣ የጋራ ሓላፊነታችንን በመወጣት ረገድ ክፍተት እንዳለ እየታየ ነውና ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ሀብተ ክህነት ያለው ኹሉ፣ በዚህ ዘመን ከምንም በላይ ለሰላምና ለሕዝብ አንድነት መጠበቅ ያለዕረፍት ማስተማርና መስበክ አለበት፡፡ ይህን አምላካዊ ተልእኮ በስኬት ለማከናወንም፣ በተሟላ መንፈሳዊ ሰብእና መቆም ያስፈልጋል፡፡ “መሥዋዕትን ሳይኾን ምሕረትን እወዳለሁ” ብሎ ራሱ የመሰከረለትና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የይቅርታ መንፈሳዊ መሥዋዕት ማለት ይህ ነውና፡፡

የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የኾን ካህናት፣ በውል ማወቅና ማስተዋል ያለብን፣ ያለሰላም ህልውና፥ ያለሕዝብ አንድነትና ያለሀገር ልማት ቀጣይነቷ አስተማማኝ የኾነች ቤተ ክርስቲያን ልትኖር የማትችል መኾኑን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከሌለች ደግሞ፣ የምድሩም የሰማዩም ቤታችን ይናዳል፡፡ ይህ እንዳይኾን፣ ለምትወደንና ለምንወዳት ቤተ ክርስቲያን ህልውና መቀጠል ስንል በልማቱ ሥራ፥ በሰላሙ ጥበቃ፥ በሀገር አንድነት፥ በሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ያለመታከት ማስተማር፥ መምከር፥ ማሳመን ይጠበቅብናል፤ በማለት መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝባችንን ይባርክ፤ ይቀድስ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ አሜን፡፡

አባ ማትያስ ቀዳማዊ

ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ

ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም

ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

Advertisements

14 thoughts on “ለቀውሱ መስፋት ካህኑን ተጠያቂ ያደረጉት ፓትርያርኩ፥“የሰላም መስቀል ይዘን ሕዝቡን የሰላም ኃይል ማድረግ እንዴት አቃተን?” ሲሉ ጠየቁ

 1. Anonymous March 7, 2018 at 12:54 am Reply

  Where were you when young Ethiopians murdered, and jailed in thousands? Why didn’t you face the dictator Woyane and tell them enough is enough?

 2. Anonymous March 7, 2018 at 5:56 am Reply

  This is really Godly message to Orthodox Christians to see their fellow brothers as themselves,which is the order of the Heavenly God.But,I have seen the message of the orthodox leaders from North America which is some what destructive,call for genocide which has to be corrected,they have to either separate themselves as secular organization or they have to disseminate the Gospel of peace of Jesus Christ.

 3. birhanbihil March 7, 2018 at 9:40 am Reply

  ከፓትርያርኩ…እንደ ቀደምት አባቶቻችን ገድል እንሥራ! የሚል ድምጽ ለመስማት የሚጠብቅ የዋህ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጅ ያለ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም በማንኛውም ጊዜ በዓላማቸው ጽኑ ናቸውና፡፡
  …እኔ ከደሙ ንፁህ ነኝ እያሉ ካህናትን የሚወቅሱት፣ ከተጠያቂነት ለማምለጥ የሚያደርጉት ሩጫ፣ ሕዝቡን ማሳት፣ የዐላውያንን ፈቃድ መፈጸምና ማስተጋባት ይብቃ! ከዘመነኞቹ ቢያጎራብት እንጂ ከጽድቅ አያወዳጅምና።
  ገኖ የሚሰማ ልቆ ከጫጫታ…አድማጭ ከተገኘ ጩኸት ነው ዝምታ፡፡

 4. Anonymous March 7, 2018 at 7:05 pm Reply

  አባ ማትያስ አሳፋሪ መንኩሴ ናቸው ደግሞ አንታቸው ረዥም ሆነ ሳለ አዙረው ማየት የተሳናቸው በእሳቸው ምክንያት የመጣውን መዓት ወደ ካህናቱ ማዞራቸው አባማትያስ ፍርደገምድል ጉባ ሰብሳቢ የቤተክርስቲያንዋን ስርአት በስልጣናቸው በመጣስ ጠቅላይ ቤተክህነት የማያዘው አዲስ አበባ ሀገረስብከትን ለግላቸው በማድረግ ወርሃዊ ቀለብና ልዩ ሌዪ ወጪ እንዲሸፍንላቸው ያደረጉ ዜጎች እየተፈናቀሉ ባሉበት ወቅት ጤንነታቸውን ለመጠበቅ መፆም አፀለይ መስገድ ሲገባቸው በቤተክርስቲያንዋ ታሪክ ተደርጎ ቀርቶ ታስቦ የማያውቅ በብር 750,000 ሰባት መቶ አምሳ ሺህብር የስፖርት ዘመናዊ መሳርያ ያስገዙ በቅጥርና ዝውውር እነ አቶ ጎይቶም ከአንድ እልቅና ከሚቀበሉት ብር 400,000 አራት መቶ ሽህብር ጉቦ እኩል በእኩል የሚካፈሉ ሌባ መነኩሴ በአደባይ ሙስና ይጥፋ ይላሉ በተግባር ማታ ማታ ከእለት ተቀጣሪዎች የጉቦ ገንዘብ ተሳስበው የሚቀበሉ ናቸው ስለ እለት ምግባቸውና የወይን መጠጥ አብዝተው የሚጨነቁ የሚያስብ ህሊና የሌላቸው ሆዳቸው አምላካቸው ያደረጉ መልከ ቀና ልበ ፈዛዛ ናቸው እሳቸው ከዚህ ወንበር ቢወርዱ ሀገራችን ሰላም ትሆናለች እነጎይቶም ለራሳቸውና ለሳቸው ገንዘብ ፍለጋ ሲሉ በቁጥር 200 የሚሆኑ የወሎ እና 159 የሚበልጡ ጎንደሬዎች ያለጥፋታቸው ከስራ ተባርረው በረሀብ አለንጋ እየተገረፉ የስራ መደባቸው ተሽጦ ተበላ መንግስት ተው ቢል የማይሰሙ ሆዳም ደንቆሮናቸው ይውረዱ

 5. Anonymous March 7, 2018 at 7:33 pm Reply

  The statement is very good. As we know this message was perapered by Nbured Eliyas not by the patriarch. But talking is cheap and action is very expensive. as most of us know, priests, preachers, scholars of the church are doing their spiritual job. But some of the bishops and administrators of the church are extremely corrupters in clouding the Patriarch. So before saying anything to the priests and others, he has to clean up his his office from this dairy admonition. Believe it or not the Patriaridh is doesn’t know anything but he has been breathing by Nuredin.

 6. Anonymous March 7, 2018 at 9:26 pm Reply

  አባ ማአት አንተ ፖትርያሬክ ሣትሆን ካድሬነህ ያአንተ እግዚወታ ትርጉም የለውም

 7. Anonymous March 8, 2018 at 4:31 am Reply

  ወሬኛ እርሳቸው አይደሉም እንዴ የሰላሙ ጠንቅ እስቲ ለሰላሙ ሲሉ እርሳቸውም ስልጣናቸውን ይልቀቁ አያፍሩም ደግሞ ሌላውን ተጠያቂ የደርጋሉ እርሰቸው ግን መቼ ነው ቃላየውና ተግባራቸው አንድ የሚሆነው አሁንስ እንደው እርሳቸውን ማየትና መስማት ነው የቀፈፈኝ ጭገር ብቻ አስመሳይ ዘረኛ እርሳቸውን ብሎ ፓትርያርክ ይልቁኑ ከሲኖዶሱ እውቅና ውጭ 150ሺህ ብር ከሀገረ ስብከቱ በየወሩ በድብቅ ጎይቶም የሚያበረክትላቸውን ወንጀል ያቁሙ ፡፡

 8. anonymous March 8, 2018 at 7:10 am Reply

  ብፁዕ አባታችን ያስተላለፉልን መልዕክት ለእኛ ለምዕመናን ብቻ ሳይሆን ለአለሙ ሁሉ የሚበቃ አለሙም(we) በመርህ ደረጃ የሚያቀው ግን ተግባራዊነቱ ለሁሉም እራስ ምታት፣ ተቆራኝቶት አልላቀቅ ያለው በሽታ ሆኖበታል። ለዚህ ይመስለኛል እርስዎም ክቡር አባታችን የአጵሎስ ወይስ…. ወገን ነዎት ተብለው ለታላቁ ክብር ለጵጵስና በቁ የኢኃዲግን ሃሳብ ባንቀበለውም እግዚአብሔር ፍቃዱ ባይሆን አይደለም 5 አመት አንድም ቀን በክቡር መንበሩ ሊቀመጡ እንደማይችሉ ስለምናቅ ይደለዎ፥ ይሁን ብለን ተቀበልን፤ በዚህ ነገር ተዘባብተው ከሆነና አሁን እርስዎ በያዙት መንገድ እርኩስ መንፈስ የተጠናወታቸው ዘረኞች ጎይቶምን ፣ ብዙ ክፉ የመምሪያ ሃላፊዎችን እና የአድባራ አለቆችን ወዘተ ከአካባቢዎ ካላራቁ እግዚአብሔር ለቤቱ የሚቆረቆርበት ወቅት በመድረሱ ቀጣዩ ስድስተኛ አመቶትን በመንበሩ እንደማቆዩ ያውቁታል , ታውቆዋል። ስለዚህ አባቴ እባክዎ ትምህርትዎን ወደ ተግባር በመለወጥ የአጵሎስ የጳውሎስ ማለትዎን ትተው የክርስቶስ ወገን የሆኑትን ሁሉ በአንድነት አሰባስበው ለመንጋው አርአያና እረኛ ይሁኑ። እግዚአብሔር ሁላችንን ይባርክ በቸርነቱ ይጠብቀን ወላዲተ አምላክ በምልጃዋ ከሁላችን ጋር ትሁን።

 9. Anonymous March 9, 2018 at 12:00 am Reply

  ማትያስ ከድሮውሞ የደርግ ካድሬ ከዛሞ ጵጵስና ከደፋ በኌላ ወደአሜሬካ ኮብልልሎ ደርግን በመቃወም
  ወያኔን በመደገፍ ስንቅ አቀባይ ሆነ ደርግ ሲወድቅ ፖትርያሬክ ለመሆን ሲሞሸር ሟቹ አባ ጳውሎስ ቀደመው
  ሞታቸውን በማሟረት ከእስራኤል ሲጮህ የወያኔ ፖትርያሬክ ጳውሎስን የእስራኤል አምላክ ቀሰፈው
  የጳውሎስን ሞትየሰማው ማትያስ ጺሙን ቅባት ቀብቶ በረረ ወደኢትዯጵያ የወያኔ ፓትርያሬክ ለመሆን
  ህዝብ ሲሞት ክርስቲያን ሲገደል የዋልድባ መናኝ መነኮሣት ሲታሠሩ ሲሰደዱ
  የወያኔ ፓትሬክ መሣለቅ ጀመረ ካህናቱ ሲገደሉ መስቀል ይዛችሁ አድሰላም የላችሁ በማለት ተሣለቀ
  አባ ማትያስ ቄስ ወይስፓትርያሬክ የትኝው ይበልጣል በማህረግ
  ሙስሊሞች ሣይቀር የዋልድባ መነኮሣት ይፈቱ ሲሉ የውሸት ፓትርያሬክ ማትያስ ትንፍስ አላለም
  ለነገሩ ከወያኔ ትግሬ ምን ይጠበቃል ሂዱልን ያኑቁልቋላችሁን ብሉ አንላቀቅም ቆይብቻ
  በፀጉር አናምን አባ ማት አንተንብሎ ፖትሬያሬክ አፍራሽ

 10. Anonymous March 9, 2018 at 10:08 pm Reply

  ሰላም ለሁሉ ይሁን
  ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
  ወእጨጌ
  ማትያስ
  ምናለ ባይዋሹ ክርስቲያኑ ቀርቶ ስለውሸትወ ሙስሊሙ ያቀወታል እጨጌ ማትያስ
  ጉደኛ

 11. የጥፋትን ርኩሰት በተቀደስው ስፍራ ስታዩ ቀኑ እንደቀረበ አስተውሉ፡፡ https://astemhro.com/2018/03/10/debrezeit/

 12. ነጻነት ይቅደመው March 26, 2018 at 9:49 am Reply

  የቀውሱ ዋና ተዋናይ እና ሞተሩ እራስቸው ፓትርያርኩ ናቸው ማን ላይ ልአላክኩ ይፈልጋሉ። ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት አልያም ለማዳከም ፣ቀኖናዋን ለመበረዝ በወያኔ መንግሥት በነ ስብአት ነጋ በነ አቦይ ፀሐዬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ላይ የተጫኑ ድንጋይ ናቸው

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: