የቦሌ ክ/ከተማ:የሰዓሊተ ምሕረት ምእመናንንና ሀ/ስብከቱን ያወያያል፤የፀረ አማሳኞች ተጋድሎው ተጠናክሮ ውሏል!

sealite mihret row and aa dio2

 • በተባረረው አስተዳዳሪ፣ የፓትርያርኩ እና የሥራ አስኪያጁ በልዩነት መጠባበቅ ኹኔታውን እያከፋው ነው፤
 • ምእመናኑን፣ “ዱርዬዎች” የሚሉት ፓትርያርኩ፣የተባረረው አስተዳዳሪ እንዲመለስ ማዘዛቸው ተጠቁሟል፤
 • ሥራ አስኪያጁ፣ የክፍለ ከተማውን የፖሊስ ኃይል ድጋፍ በደብዳቤ እንዲጠይቅ በማዘዝ ምእመኑን በቆመጥ አስደበደቡ፤
 • በጽናት የተቋቋመው ምእመኑ፣ በጸሎተ ምሕላ እና በዝማሬ ጥበቃውን አጠናክሮ ውሏል፤የተባረረውን አስተዳዳሪ መመለሱ ይቅርና፣“ዛሬ ጠዋት በካቴድራሉ ውስጥና አካባቢ ታይቷል፤”መባሉ፤የምእመኑን ቁጣ አብሶታል፤ንቃቱንና ተቃውሞውን አጠናክሮታል፤
 • በጠዋቱ የምእመናኑ የጥበቃ መርሐ ግብር ቅይይር አጋጣሚ፣ ወደ ካቴድራሉ ከገባው የክፍለ ከተማው ፖሊስ ጋራ፣ደወል ቤቱን ቀድሞ ለመቆጣጠርና በነቂስ የወጣው ምእመን እንዳይገባ ለመግታት፣ፍጥጫና ትንቅንቅ ነበር፤ተኩስም ተሰምቷል፤
 • ምእመኑ፥“ቤተ ክርስቲያናችን እናታችን ናት፤ ከእርሷ የሚበልጥብን የለም፤” ብሎ በአቋሙ በመጽናት ካቴድራሉን በመቆጣጠሩና በማስከበሩ ቀጥሏል፤
†††
 • የክፍለ ከተማውን ፖሊስ ለማገዝ የተጠራ አድማ በታኝ ፖሊስ፣ እስከ ጊዜ ቅዳሴ በካቴድራሉ ዙሪያ ከበባ ቆይቷል፤
 • ካህናቱ እና የሀ/ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ከምእመናኑ አልተለዩም፤ ጸሎቱ እና ቅዳሴውም አልታጎለም፤
 • የምእመናኑ ተወካዮች፣ “ከሀገረ ስብከቱ ጋራ አነጋግሩን፤ መፍትሔ አሰጡን፤” ሲሉ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደርን ጠየቁ፤
 • ጥያቄውን መነሻ በማድረግ፣ የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ፣ ምእመኑን ወርዶ በማወያየት ችግሩን እንዲፈታ የፍትሕ እና ጸጥታ ቢሮ አሳሰበ፤
 • ሥራ አስኪያጁ፣ “በቂ የፖሊስ ኃይል ካልተመደበልኝ እኔስ ምን ዋስትና አለኝ፤” ብሎ ቢያንገራግርም፣የሀ/ስብከቱን ልኡካን ይዞ ምእመናኑን ለማነጋገር ተስማማ፤
 • ነገ ጧት፥የክፍለ ከተማው ሥራ አስፈጻሚ፣ የሀገረ ስብከቱን ልኡካንና ምእመናኑን በካቴድራሉ ያወያያል፤
 • ምእመናኑ፣ ከነገው የቋሚ ሲኖዶስ ሳምንታዊ ስብሰባም ትኩረትና ማጽናኛ እንጠብቃለን፤ ቢሉም ፓትርያርኩ “ተዉኝ፤ጣልቃ አትግቡብኝ፤ሥራ አስኪያጁ በሚያቀርብልኝ ሪፖርት ውሳኔ እሰጣለሁ፤”ብለዋል ላነጋገሯቸው ብፁዓን አባቶች፡፡
†††

6 thoughts on “የቦሌ ክ/ከተማ:የሰዓሊተ ምሕረት ምእመናንንና ሀ/ስብከቱን ያወያያል፤የፀረ አማሳኞች ተጋድሎው ተጠናክሮ ውሏል!

 1. anonymous January 5, 2018 at 7:42 am Reply

  እግዚአብሔር አምላክ ስለ ቤተ እግዚአብሔር ፍቅር እስካሁን ለከፈላችሁት መስዋዕትነት ዋጋውን እርሱ በስውር ይከፍላችኃል። በቦታው ያልተገኘነው ሁላችንም ምዕመናን ከዛሬ ጀምሮ ለቤተ ክርስቲያን ልዕልና ሰንል ሰአሊተ ምህረት እመቤታችን ቤተ ክርስቲያን እንገኛለን። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።

 2. Amanuel January 5, 2018 at 5:06 pm Reply

  ፓትርያርክ አባ ማትያስ እና በቤተሰባዊነት የሾሙት ስራ አስኪያጅ ጎይቶም ያይኑ የሚዋረዱበት ቀን ሩቅ አይሆንም፤ ሰዎቹምኮ (የሰዓሊተ ምህረት አመራሮቹ) ይህንኑ የእነርሱን እርዳታ ስለሚያውቁ ነው እንዲህ ቤተ ክርስቲያኗን የግል ሱቃቸው በማስመሰል ራሳቸው አርክቴክት ራሳቸው ቀያሽ ራሳቸው ተቆጣጣሪ ራሳቸውራሳቸው አከራይ በመሆን ያሻቸውን ሲሰሩ ሃይ ባይ ያልነበራቸውና ሁኔታው ቅጥ ሲያጣ ቦታዋን ለመታደግ ምዕመናን በቀናዒነት መነሳሳታቸው ያስቆጣቸው!

  ያሻቸውን ሲሰሩና ብዙ ነገር ሲያበለሻሹ አይዞህ ባይ ሳይኖራቸው አልነበረም፤ ለዚህ ለክፉ ቀናቸው አይዟችሁ የሚሏቸውና የሚጮሁላቸው ፍርፋሪ የሚጥሉላቸውም ውሾች አሏቸው ። ለዚህ ነው ከዚህ ከተባረርኩ ሌላጋ መድቡኝ ሲል የመዳቢነት ስልጣን ደረጃ ለደረሱ ቃንጃዎቹ አስተዳዳሪው ዓይኑን በጨው ታጥቦ የጠየቀው። ይህ ቀበኛ ሌላም ቦታ ጥፋቱን ሊደግም ማለት ነውኮ!

  +++ አይ እናት ቤተ ክርስቲያን ማንም በቅጡ ያልተወለደ ሽል ሁሉ የተወደደች እና መልካም በሚሏት በመቅደስሽ እንዲህ ይቀልድ???+++

  ዳሩ ምን ያርጉ አንዴ ተተክለው ደሟን ሲመጠምጡ የሚያስቆማቸው ባለመኖሩ የግል ርስታቸው እንደሆነች እስከማመን ደረሱ፤ በቅርቡ በኢ ኦ ተ ቤ ክ በምግባረ ሰናይ ሆስፒታል የዘመድ አዝማድ አሰራሩ መስመር በማለፉ ቤተ ክህነቱ ቁጥጥር ማድረግ ሲጀምር “ቤተ ክህነት ምን አገባው?” እስከማለት ደርሰው እንደነበር ሃራ አስነብባን እኛም ተገርመን ነበር ። ሰዓሊተ ምህረት እየሆነ ያለውም እንዲያ ይመስላል፤

  ቤተ ክርስቲያኗን አባ ማትያስ እና ዘመዳቸው ጎይቶም ያይኑ ፣ አስተዳዳሪው እና፣ የቅርብ አገልጋዮቹ በአክሲዮን የያዟት ይመስላል ለዚህ ነዋ የነቀዘው ብልሹ አሰራር ይስተካከል ያሉ ምዕመናን ምን አገባችሁ ተብለው በፓሊስ የሚደበደቡት። ምክንያቱም እነርሱ አድራጊ ፈጣሪ ናቸውና ።
  ታድያ ይሄ እስከመቼ ይቀጥል ይሆን? እነርሱ እንዲሁ እንደፋነኑና ያሻቸውን እንዳደረጉ ይኖሩ ይሆን በፍፁም በፍፁም ሁሉን ለማየት የምንበቃበት ቀን ይስጠን እንጂ ውርደታቸውንማ በብዙ እናያለን፤ ******ሁሉም የዘራውን ያንኑ የሚያጭድበት ቀን ይመጣል። አዎን የዘራማ በርግጥም ያጭዳል እሾህ የዘራ ያው እሾሁን ወይንም የዘራ ያው ወይኑን!

  እንደ ፈርኦን ልባቸውን ያደነደኑ አማሳኞችን ባህሩ አስጥሟቸው እንድናይ ያብቃን እንጂ ምን እንላለን? ለነኚህና ለወዳጃቸው ሰይጣን ምህረት አንለምንምና አዎ አምላካችን ያንኑ ፍርዳቸውን ያሳየን አሜን ወአሜን ለይኩን ለይኩን!!!

 3. Anonymous January 10, 2018 at 6:33 am Reply

  What is happening in the church administration from time to time is really sad and worrying. I don’t think there will be a solution to this deep-rooted problem.

  The church will soon be like churches abroad. I don’t think the church will be able to maintain followers who will bear this level of corruption and ungodliness.

  Through time. the church will lose followers significantly.

  Church followers will not trust and respect so-called “church fathers”.

  It is really saddening to see how the “patriarch” is behaving.

  Thieves and their corruption network is really affecting the unity and health of the church.

  Money is worshiped this days. Money is power.

  I don’t see any solution from the church administration and the Holy Synod.

  God will work in his own time. With the Will of God, the only solution I see is in the unity and power of the priests, Sunday school members and counsel of parish churches.

  The counsel of parish churches should be very strong working in close collaboration with church followers.

  We have to dry up the breeding space for corruption by having a strong local level church administration though a close collaboration of counsel of parish churches and followers.

 4. Anonymous January 10, 2018 at 6:34 am Reply

  It is time for the EOTC to be reformed administratively.

 5. Anonymous January 10, 2018 at 6:36 am Reply

  ዱርዬዎች” የሚሉት ፓትርያርኩ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: