በልማት ስም ካቴድራሉን የንግድ መናኸሪያ ያደረጉት የሰዓሊተ ምሕረት: አለቃ፣ ጸሐፊና ሒሳብ ሹም እንዲነሡ ተጠየቀ

ሕገ ወጡን የሰበካ ጉባኤ ሽፋን በማድረግ፣ ሕግንና አሠራርን እየጣሱና ከጥቅመኛ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋራ እየተመሣጠሩ የደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ካቴድራልን በስመ ልማት ወደ ንግድ መናኸሪያነት ቀይረው ካህናቱን፣ የሰንበት ት/ቤቱን አባላትና ምእመናኑን የሚያሠቃዩት፥ አስተዳዳሪው መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነ ብርሃን(ግራ)፣ዋና ጸሐፊው ሊቀ አእላፍ ዕፁብ የማነ ብርሃን(ቀኝ ላይ)እና ሒሳብ ሹምነትን ከሕግ ክፍል ሓላፊነት የደራረቡት ሊቀ ትጉሃን ዘርኣ ቡሩክ ኣብርሃ(ቀኝ ታች)፤


 • ከሳሪስ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፥ በተቀራራቢ ጊዜ የተዛወሩ ልማደኛ የቡድን መዝባሪዎች ናቸው
 • የምዝበራው የጎማ ማኅተም ያደረጉት ሕገ ወጡ ሰበካ ጉባኤ፣ካህኑንና ምእመኑን አይወክልም
 • ፀረ-ቀኖና፣ ፀረ-ቃለ ዓዋዲ፣ ፀረ-ካህን፣ ፀረ-ሰንበት ት/ቤት፣ ፀረ-አካባቢና ፀረ-ቅርስ አማሳኞች!
 • “ከጂቲፒው ፈጥነን ካቴድራሉን ያሳደግን፥የአረንጓዴ ውበት ተሸላሚ ልማታዊ ነን፤”ቢሉም…
 • በቤተ ክርስቲያኗ ዙሪያ የተሠሩ ግንባታዎችና ሱቆች፥ዲዛይኑን ያላገናዝቡ ሕገ ወጦች ናቸው
 • በባለሀብቶች ተገንብተው ለረጅም ዓመት በብላሽ ተከራዩ፤ እይታዋን ሸፈኑ፤ገጽታዋን አበላሹ!
 • “ለቀጣይ ፕሮጀክት አቅም ሊፈጥሩ” ቀርቶ፣ለይዞታ በሚያሰጋ የኪራይ ውል መጠቀሚያ ኾኑ!

†††

sealite mihret cathedral

 • ዋና ጉልላቱን አፍርሰው ለመሥራት አስበዋልየዐውደ ምሕረቱ አሠራር ብልሽት ሽፋን ነው
 • የሦስት ብሎክ ፉካዎች ግንባታ“የመቃብር እጥረትን ያቃልላል፤50ሚ. ብር ያስገኛል፤”ይላሉ
 • ኾኖም ድኻ ምእመናን፣ የቀብር ቦታ አጥተው፣ በምልስ አፈርና በወንዝ ዳር እየተቀበሩ ነው!
 • ልማቱ፥ሳይንሳዊና ይዞታን የሚያረጋግጥ ነው እያሉ ቅርሱንና ሀገር በቀል ዐጸዱን ጨፈጨፉ
 • ካህናቱ ይደበደባሉ፤ ነባሮቹ ይዛውራሉ፤ ተተኪዎቹ ይሸማቀቃሉ፤ አበ ነፍስነትም ተከለከሉ
 • ሰንበት ት/ቤቱ፥ በጣልቃ ገብ ተበደለ፤ቢሮው ተዘረፈ፤በስሙ ስለሚሠራው ሕንጻ ጥያቄ አነሣ
 • ኑፋቄን እንዳይከታተል ተከለከለ፤ የተሐድሶ ኑፋቄ ተጠርጣሪን የጠቆሙ አባላቱ ተቀጥተዋል

†††

sealite mihret sunday school singers

 • የአለቃው የሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት፣ምእመናንን ከሱታፌና ከካቴድራሉ እያራቀ ነው
 • ምእመኑን፥የጉርድ ሾላ ድኻና የሲኤምሲ ባለሀብት በማለት እየለዩ ያንቋሽሻሉ፤ይሰድባሉ
 • የተሳላሚ ሹሞችን ስም እየጠሩ፣ማንም አይነካኝም እያሉ ካህኑንና ምእመኑን ያስፈራራሉ
 • ቅዱስ ሲኖዶስንና አባቶችን እየናቁ፣የፓትርያርኩም ባለውለታ ነኝ እያሉ ተስፋ ያስቆርጣሉ
 • ባለፈው ኃሙስ ወደ መንበረ ፓትርያርኩ የተመሙትንም ምእመናን በፖሊቲካ ወንጅለዋል

†††

†††

sealite mihret cathedral chantors

 • “በጎውን እንጅ ችግር መኖሩን አላውቅም ነበር፤” ያሉት ፓትርያርኩ አቤቱታውን ተቀበሉ
 • ሀገረ ስብከቱ እንዲያጣራ አዘዋል፤ ሪፖርቱ ለቋሚ ሲኖዶሱ ቀርቦ እንደሚወሰን ይጠበቃል
 • አቤቱታ አቅርባችኁብኛል በሚል ሰንበት ት/ቤቱ በአለቃው ታሸገ፤ሥራ አመራሩም ታገደ
 • የሀ/ስብከቱየሰንበት ት/ቤቶች አንድነትአፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥያደርግ ዘንድ ጠየቀ፤

†††

በካቴድራሉ አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነ ብርሃን ላይ የቀረቡ አነጋጋሪ ጥቆማዎች፡-
 • በተደጋጋሚ ለረጅም ወራት ወደ ሰሜን አሜሪካ እየተጓዙ የካቴድራሉን ሥራ ይበድላሉ፤
 • ከጋምቤላ ለትምህርት ያመጧቸውን 30 ደቀ መዛሙርት፣ አያስፈልጉም ብለው አባረሩ፤
 • ልጃቸውን፣ ቤተ መቅደስ ውስጥ አስገብተው፣ ጥምቀተ ክርስትና እንድትነሣ አደረጉ፤
 • በመዓስባን ሥርዐት ጋብቻ ለመፈጸም ለመጡት፣ሥርዐተ ተክሊል እንዲፈጸም አደረጉ፤
 • ቀድሰው ሳያቆርቡ ቤተ መቅደስ ገብተው ይቀመጣሉ፤ያልቀደሰ ካህን እንዲያቆርብ ያዛሉ፤
 • በቅዳሴው ፍጻሜ፣ ካህናቱ፥ ለቆረቡትና ላስቀደሱ ምእመናን ዕጣን እንዲያበሉ ያዛሉ፤
 • ያላገቡ ዲያቆናት፣ በ40 ቀን ውስጥ አጋር ፈልገው ትዳር እንዲይዙ መመሪያ ሰጥተዋል፤
 • በመመሪያው የተጨነቁና ፍላጎት የሌላቸው ዲያቆናት፣ ያለጊዜ እስከ መመንኮስ ደርሰዋል

†††

በካቴድራሉ ቅጽር፣ የ285ሺሕ ብር ጃኩዚ የተገጠመለትና በውድ ቁሳቁሶች የተሞላ እጅግ ዘመናዊና ቅንጡ መኖሪያ ቤት ለራሳቸውMelake Birhan Rufael Yemane Birhan2 አሠርተዋል፤ «ይህን ያደረግሁት ለራሴ ሳይኾን ቅዱስ ፓትርያርኩ ሲመጡ እንዲያርፉበት ነው፤» ይላሉ፤

በበዓላት ላይ ለመሳተፍና በክብር እንግድነት ተጋብዘው የሚመጡ የአንዳንድ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ስም በመጥቀስ፣ «እነ እገሌ የተባሉት ባለሥልጣናት ወዳጆቼ ናቸው፤ ማንም ምንም ሊያደርገኝ አይችልም፤» እያሉ አገልጋዩንና ምእመኑን ለማስፈራራት ይሞክራሉ፤

“ክፍተቶቹ የማይታረሙ ከኾነ ለቅዱስ ሲኖዶሱና ለቅዱስ ፓትርያርኩ እናሳውቃለን፤” ሲባሉ ደግሞ፣ «ሲኖዶስ ማለት እኛ ነን፤ እነዚህ የቆብ ተዝካራቸውን ያልጨረሱ ሽማግሌ ጳጳሳት እኔን አያዙኝም፡፡ ፓትርያርኩም ቢኾኑ ከኔ ፈቃድ አይወጡም፡፡ አሜሪካን ሀገር በነበሩበት ወቅት ብዙ ውለታ የዋሉላቸው የሚስቴ ቤተሰቦች ናቸው፡፡ አሁንም ቢኾን ለሕክምናና ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ አሜሪካን ሲሔዱ ወጪያቸውን ሸፍኜ፣ ማረፊያ አዘጋጅቼ፣ መኪና መድቤ የምከባከባቸው እኔ ነኝ፤ የሚስማማቸውን ምግብ እያዘጋጀኹ ወጪያቸውን የምሸፍነው እኔ ነኝ፤» በማለት ምእመናን ቅሬታ ይዘው ወደ ወደ ቅዱስ ሲኖዶሱ እና ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ እንዳይሔዱ ተስፋ ለማስቆረጥ በተደጋጋሚ ይሞክራሉ፡፡

ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ፣ ለሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ለሀገረ ስብከቱ ካላቸው ንቀት የተነሣ፣ ካቴድራሉ፣ የስፋቱን ያህል የስብከተ ወንጌልና የፀረ ተሐድሶ እንቅስቃሴ እንዲኖረው ቀናዕያን አገልጋዮችን አያሳትፉም፤ የግል ስምና ዝናቸውን ከሚጠብቁላቸው ጥቂቶች በቀር!

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የዲግሪ ምሩቅ ቢኾኑም፣ ወደ ኮሌጁ የገቡበት የማትሪክ ውጤት የተጭበረበረ እንደኾነበሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት በመረጋገጡ፣ አባ ፎርጅድ ወይም 3D/3F በሚሉ የተሣልቆ ስያሜዎች በስፋት ይታወቃሉ፡፡

ካህናቱን እያንበረከኩ፣ በየሰበቡ በጥፊ እየተማቱ፣ ደመወዛቸውን እየቆረጡ፣ ሲሻቸው እያገዱና ወደ ሌላ ደብር እያዛወሩ ከሚያሳዩት ጭካኔና ዓምባገነንነት የተነሣ፣ ዳግማዊ አጋግ እየተባሉም ይጠራሉ፤ ቀድሶ እንባውን በታቦቱ ላይ የማይረጭ፤ ጸሎተ ማርያም የማይደግምባቸው ካህን የለም፤ ይላሉ ታዛቢዎች፤ የማኅበረ ካህናቱን የሰብአዊ መብቶች ጥሰትና መመረር ሲገልጹ፡፡

የሐውልትና የመቃብር ተቆጣጣሪ ኾነው ሥራ ከጀመሩበት ከየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ጀምሮ በቁጥጥርና በጸሐፊነት በሠሩባቸው በብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ፣ በጽርሐ ኣርያም ሩፋኤል፣ በደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና በሳሪስ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አብያተ ክርስቲያናት ያላቸው ታሪክ፥የአለመግባባት፣ የብጥብጥና የምዝበራ በመኾኑ ከመሰሎቻቸው ዘርኣ ብሩክ ኣብርሃና ዕፁብ የማነ ብርሃን ጋራ ኹነኛ ውሳኔ ሊተላለፍባቸው ይገባል፡፡

Advertisements

25 thoughts on “በልማት ስም ካቴድራሉን የንግድ መናኸሪያ ያደረጉት የሰዓሊተ ምሕረት: አለቃ፣ ጸሐፊና ሒሳብ ሹም እንዲነሡ ተጠየቀ

 1. Debrezeit December 13, 2017 at 4:37 am Reply

  Yigermal

 2. Debrezeit December 13, 2017 at 4:49 am Reply

  ሰውየው እኮ ያደጉበትን ነው እያደረጉ ያሉት::

  አባታቸው አለቃ የማነብርሃን ስዮምና እናታቸው ወይዘሮ አበራሽም ተመሳሳይ ታሪክ ነበራቸው:: በቀድሞ ስማቸው አቡዬ ወይም ሩፋኤል በመባል የሚታወቁትና በደብረዘይት ከተማ ተወልደው ቅዱስ ሩፋኤል ደቁነው ለዚህ የበቁት እኚህ ሰው መሰረታቸው የሚገርም ነው:: አባታቸው አለቃ የማነብርሃን ስዪም የደብረዘይት ቅዱስ ሩፋኤል አለቃ ነበሩ:: ያኔ ታድያ ሚስታቸው ወይም የአቡዬ እናት ነበሩ የደብሩ አለቃ:: ካህናትን እያዘዙ እቤታቸው ከብት ያሳልቧቸው ነበር:: እበት ያስለቀልቁ ነበር:: አለቃ የሚእስሉት እሳቸው እንጂ ባላቸው አይመስሉም ነበር::

  አለቃ የማነም አምባገነንና በብዙ ነገር የሚታሙ ሰው ነበሩ:: ግቢያቸው አይለው ጫት ስር ምን ይሰሩ እንደነበር ብዙ የደብረዘይት ሰው ያውቃል:: በዚህ ምክንያት ከወንድማቸው አለቃ ያሬድ ጋር ተጣልተው አለቃ ያሬድ መናፍቅ እስከምሆን ደርሰዋል:: የደብረዘይት ሕዝብም ዲያቆን ረዳ ውቤ እና ፍቅሩ ሰብሕዎ በሚባሉ ዲያቆናት ስተባባሪነት ከፍተኛ አቤቱታ አቅርቦ አለቃ የማነ ከደብረዘይት ቅዱስ ሩፋኤል ተነስተዋል:: የሚያሳዝነው እኚሁ ሰው የወለዷቸው ልጆችም ተመሳሳይ መሆናቸው ነው::

  እንጨት ተራ ተብሎ በሚጠራው የሩፋኤል መግቢያ በኩል ብዙ መቃብር ቤቶች አሉ:: በዚያ በኩል ቁልቋል ስር ቁጭ ብለው ቤተ ክርስትያን ለመሳለም የሚመጡ ሴቶችን ያስቸግሩ ነበር – እነ አቡዬ:: መቃብር ቤትም ብዙ ለመስማት የሚቸግሩ ነገሮች ተፈጽመዋል:: አለቃው ሲባረሩ ግን ልጆቹም አብረው ከደብረ ዘይት ቅዱስ ሩፋኤል ተባረሩ:: አለቃ የመነ ልደታ ሲሄዱ ብጥብጥ _ የካ ሚካኤል ሲሄዱ ብጥብጥ በመፍጠር ብዙ ረብሻ ፈጥረዋል:: አሁዬም የተቀጠረው ያኔ ነው:: ከመቃብር ምናምንነት ተነስቶ ዛሬ አለቃ ሆነ:: ይደንቃል:: ቤተሰቡ ያሳዝናል:: ፓይለት የሆነው ትልቅ ወንድማቸውን ፈለግ ቢከተሉ ጥሩ ነበር:: እሱ በየዓመቱ ሩፋኤልን የሚዘክር ጨዋ ሰው ነው:: የደብረ ዘይት ሰው ይመስክር – አቡዬ ማን እንደሆነ!

  • Azeb December 16, 2017 at 2:27 am Reply

   I am just reading your comment and wondering if you believe in God at all. Respected church leaders has been blackmailed, disrespected since the inception of Mahebre Kudusan. Every Orthodox knows why you continue to disrupt our church. May God give you what you deserve. You can continue to be disrespectful to church leaders and try your very best to shame them but you are now known as the disrupters of our church and our beloved Ethiopia. If there is any institution to be blamed of stealing or corruption, it is you MAHEBRE KUDUSAN AKA MAHEBRE SEITAN. Stop it right now before we pursue legal actions.
   Cyber bullying is illegal.

   • Anonymous December 20, 2017 at 5:17 am

    If there is no problem, why then you worry. God is working and you will soon be exposed.

 3. Anonymous December 13, 2017 at 6:57 am Reply

  I don’t blame him personally. If the decayed and corrupted church administration allowed this to happen, why then we blame individuals who used the opportunities.

  Look at the church administration which is staffed by incompetent, corrupted and egoist leaders.

  It is really saddening and worrying what we hear and see in our church.

  All this is a result of weak church administration.

  Thank you Hara for letting us know about the current situation of our church.

 4. Anonymous December 13, 2017 at 7:05 am Reply

  Fetari yrdan enashenfalen

 5. Fekade Silase December 13, 2017 at 11:03 am Reply

  selam enidet nachu gin enanite edi tederege bilachu enesu kesilitanachew
  aliweredum yesealite mihiretu ye ayat abune gebire menifes kidusim edezaw
  naw gize yiwesdal leze degimo?

 6. Anonymous December 13, 2017 at 3:16 pm Reply

  ሃራ ተዋህዶ

  • Anonymous December 19, 2017 at 12:20 pm Reply

   Mekebabatus teresa enda……

  • Anonymous December 19, 2017 at 12:22 pm Reply

   Mekebabatus teresa ends……

 7. Anonymous December 13, 2017 at 5:40 pm Reply

  ሠላም ሀራዎች
  በጣም ይገርማል
  የ አለቃ የማነብርሃን ልጆች 2ቱም ዲያቁናት ነበሩ አጅግ በጣም ዱርዬዎች ጠጥተዉ ቤተ መቅደሥ የሚገቦ ብቻ በአባታቸዉ ሥልጣን የሚመኮ የደብረዘይት የቅዱሥ ሩፋኤል ዲያቆናት ነበሩ
  አቃቄ መድሃኒ አለም ሊያነግሡ ሂደዉ ጠጥተዉ እና ሠክረዉ እንደለመዱት ቤተመቅደሥ ገብተዉ ለመጋደም ሢሞክሩ የመድዬ ዲያቆናት እጅና እግራቸውን አንጠልጥለዉ በምእመናን ፌት ከቅድሥቱ ላይ ወረወሩአቸዉ
  ይሄ መቼም የማልረሣዉ ነው
  አቶ አባታቸዉ ደሞ የለየላቸው ድግምተኛ ነበሩ በንሥሃ ተመልሠው ከሆነ አላቅም አንድ እጃቸው ሠላላ ሥለሆነች የሠንበት ተማሪዎች በጣም እንፈራቸዉ ነበረ እንዲህ አይነት ሠዎች በብዛት ጠንቅ ወዋይ ሥለሆኑ
  እና አሁን ከዘመናት በዋላ የአባትና ልጆቹን በቅድሥት ቤተክርሥቲያን ላይ እንዲህ አይነት ክፎ ሥራ ሢሠሩ ምን ይገርማል ?ሥማቸው የመላእክት ግብራቸው ግብረ ዲያብሎሥ አፍኒን እና ፌንሀሥን አሣድገው መከራ አሥቀመጡብን አሁንም እግዜአብሄር ቤቱን ያጽዳ እነሡ ቤተሠቦች ቤተ እግዜአብሄርን እንደ መንግሥታዊ ድርጅት እንጂ እንደ ቤተ እግዜአብሄር እየኑሩበት አላደጉም ለዛ ማክበሩን ከየት ያምጡት

 8. Anonymous December 13, 2017 at 5:43 pm Reply

  ye debru astedader betam balege nachew meskerem 21. 2010 nigs lay papasachin balubet nber ke kidasew ina tabotu ke geba buhala wede dejeselam marefia gebten nber kezan abatachin migibun ke bareku buhala migib le meblat self yalutin ke hagere america yemetut yetekeberu ye papasu wedaj ayto ayinun afito yikesegnal bemil aschokuay nw ahunu yiwutulin bemalet tilik qilet yesera mehonun ine mulu dataw alegn izaw neberkugn..ye duriye sidib iyetesadebe lelochin siyaweta nber…indiw fetari kale yan balege astedader biyanesalin destaye nw.

 9. Anonymous December 14, 2017 at 5:47 am Reply

  “Gud saysemu meskerem ayteba”

  It is really surprising and worrying. Oh God have mercy upon us.

  I am sure there are many other even worrying stories and deeds of this man.

  My question is what is the Holy Synod waiting for to happen?

  If allowed, I am sure, this evil man will declare that the church is his own.

  It needs urgent attention. Many church children in other parishes have already shown the way how to save and protect the church from the evil deeds of such immoral, corrupted, ungodly and selfish church workers.

  I am wondering why the Patriarch and members of the Holy Synod prefer to keep silent.

  What will be the long lasting effect on the trust and relationship of church fathers and followers?

 10. Anonymous December 14, 2017 at 8:46 am Reply

  “ካህናትን እያዘዙ እቤታቸው ከብት ያሳልቧቸው ነበር:: እበት ያስለቀልቁ ነበር::”

  He does the same thing what his mother has been doing.

  He is insulting the priests and deacons and even slapping on their faces. He has no the slightest respect even for the elderly priests.

  What unparalleled rudeness he has!!

  He is a shame for our church.

  • Anonymous December 14, 2017 at 4:17 pm Reply

   My sisters and brothers Followers of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church don’t you know? This evil man is not the only one who have beeen destroying church. I personally know this man and He is not a priest and even he doesn’t believe in God. Just he is a businessman. I can say the problem is not his but the patriarch Abune Mathiyas. Because of the patriarch luck of faith and knowledge, today the entire church is at high risk.

   You will see tomorrow, the patriarch will never give any attention on this matter; because the relationship between Rufael and Abune Matthiyas is very deep and they have hidden secret. Just like Nbured and the patriarch.

   Dear my brothers and sisters followers of the mother church . Lets stand together in order to protect the church. Lets us clean the dirty administration of the church and out church needs to be cleaned from the hand of the evil leaders .

   We have to say to them, enough is enough.

   • Anonymous December 18, 2017 at 2:52 pm

    “He is not a priest and even he doesn’t believe in God”.

    Oh my God, that is too much!!

  • Anonymous December 14, 2017 at 10:00 pm Reply

   ምነው ምነው በምን ደግሞ ተጣላችሁ ወዳጅ አልነበራችሁም እንዴ ፡ አይ ማህበረ እኩያን። አሁን ደግሞ ስድብና አድማ ጀመራችሁ፡ ማህበረ ቅዱሳን የሚባል አጋንንት ካልጠፋ እዚህ አገራችን ላይም ገና ብዙ ፈተና ያመጣሉ። የፈለጋችሁትን ብታወሩና ብታሳድሙ አለቃው ታሪካዊ ሥራ ሠርተዋል አልምተዋል። ሞት ለማህበረ ቅዱሳን ።

   • Anonymous December 15, 2017 at 5:26 pm

    Ha ha ha …

    Meslohal!!

 11. Anonymous December 14, 2017 at 6:16 pm Reply

  ምንአደረገ ሩፋኤል ምንስ አቅም አለው እንናውቀዋለን ፀሀፍ በነበረበት የመጨረሻ ቦቅባቃ ፈሪ ሰው እንደ ሩፋኤል የለም ሰማይ የሰቀሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አባ ማትያስ ናቸው የልብልብ የሰጡት ከሱ እግር መበርከካቸው የሰላም አይመስለኝም ምክንያቱ በጠንቋዩ አባቱ ሳይሆን ይቀራል ብላችሁ ነው የምመስለኝ ታዲያ ቅ ስላሴ ፣ገነተ ጽጌ ቅ ጊዮርጊስ ፣ ምስካዬ ህዙናን፣ ቦሌ መድሃኔ ዓለም የመሳሰሉት ማስቀደስ ስችሉ ፓትርያርኩቹ ከእሱ ስር አይወጡም

  ዘር እየለየ ያዘውራል የመሰለውን የሾማል የጠላውን ከመቀየር አልፎ ደመወዝ ይቀጣል አሁን ቅድስት ድንግል ማርያም ሳትፈርድበት ይቀራል ብላችሁ ነው

  አባ ማትያስ ጉቦ አስለምዶአቸዋል ይባላል እሱም የተለያየ የአፕልና የአትክልት እያቀረበ ይባላል፡፡ ባካችሁ አባቶች ንስሀ ግቡ፤ ተው ስለእውነት ተናገሩ፤ አባ ማትያስ ፍርድ የማይሰጡ ከሆነ ክርስትያኖች ሆ ብሎ ከመንበርዎ እንደሚያነሰዎ አልጣራጠርም፤ ጎይትኦም የተባለው መናፍቅ ቅጥረኛ እንደፈለገ አባቶች ያግዳል፤ ለመሆኑ እርስዎ በወንበሩ አሉ፣ ግን እንደሌሉ ነው፤ ምክንያቱ ከመተኛትና ከመብላት የታገደ ሰው ይመለስ ብለው ያዘዙት ሰው አለ?

  እርስዎ እኮ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ይሳለቁ ነበር፤ ግን ???ያሳዝናል!!! መንበሩ ሰው የለውም! እኮ አሳዛኝ ግዜ የደረሰ ይመሰለኛል፡፡ በዘመንዎ ጠባሳ ታርክ ጥለው እንደሚያልፉ አልጠራጠርም፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የእርስዎን ውድቀት ያፋጥነው፤ የዘወትር ልመናየ ነው፤ ቤተ ክርስቲያንዋ ሳትጠፋ። አሜን አሜን አሜን፣፣፣፣

  • Anonymous December 15, 2017 at 5:25 pm Reply

   I fully agree that the so called patriarch has a deep corrupted relationship with this man.

   It is not surprising to see nowadays that some church workers claim that they are priests and merigetas but actually they are not. Some are soldiers, some come to the church because they found the church the best place to steal and corrupt.

   I do have hope in the patriarch.

   God is working in His own time.

   God will cleanse these evils, eaters and drinkers from the mother church.

   Pray that God gives strength to the true fathers and church workers.

   Oh God please have mercy upon us and protect our country, people and church.

   God bless Ethiopia and its people.

 12. Anonymous December 15, 2017 at 12:17 pm Reply

  Ha ha ha …

  Meslohal!!

  • Anonymous December 17, 2017 at 8:45 am Reply

   መጀመሪያ ደረጃ ምንም የቤተክርስቲያን እውቀት የሌለው መሀይም አለቃ ተብሎ ሲሾም ነው ትልቁ ጥፋት። እኔ የማውቀውን ልመስክር ከዚህ ቀደም ሳሪስ አቦ እያለ ይኸው አምባገነን ሌባ ቤተክርስቲያን እንዳይደርስ ተብሎ ተባሮ በማግስቱ ወይዘሮዋ ለአቡነ ጳውሎስ ነግራ እግዱ አሻረች። ከዚያ በኋላ ቤተክህነቱን ተቆጣጠረው። አሁንም ጥንቃቄ ያስፈልጋል
   ቸር ይግጠመን

   • Anonymous December 19, 2017 at 5:17 am

    For the benefit of the church and of themselves, the patriarch and the church administration have to take careful action. Otherwise, the people in the parish church will take action as is the case in other parish churches.

    The only and lasting solution resides in the people / parish church followers.

    We are in a different time now. The church fathers and administrators can’t behave in an old fashioned way. They need to know that present-day church followers are more educated and know about church orders.

    Thanks to the Digital Age, we have everything digitized and we all know what is right and what is not.

    It is better to listen to and be responsive to the demands of the church followers.

    Otherwise, whom are they serving? Is it not the people of God / church followers?

    It seems that they are serving themselves and forget about the people.

 13. mem aiel December 19, 2017 at 11:02 am Reply

  መስቀል ትተው የጦር መሣሪያ የሚታጠቁ፣ ቤተ ክርስቲያን ትተው ሱቅ የሚገነቡ፣ ገዳማትን መርዳት ትተው የከተማ ቦታ የሚቸበችቡ፣ ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት ትተው ሙስናን የሚያስፋፉ፣ በጎችን ማሠማራት ትተው ዘመዶቻቸውን በየሥራ መስኩ የሚያሠማሩ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን አደኽይተው እነርሱ በብልጽግና የሚንፈላሰሱ ምንደኞች በቤተ ክህነቱ መሠማራታቸውን ቢያውቁ እነዚያ አበው ምን ይሉ?

 14. wondemagegn January 1, 2018 at 12:22 pm Reply

  መስቀል ትተው የጦር መሣሪያ የሚታጠቁ፣ ቤተ ክርስቲያን ትተው ሱቅ የሚገነቡ፣ ገዳማትን መርዳት ትተው የከተማ ቦታ የሚቸበችቡ፣ ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት ትተው ሙስናን የሚያስፋፉ፣ በጎችን ማሠማራት ትተው ዘመዶቻቸውን በየሥራ መስኩ የሚያሠማሩ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን አደኽይተው እነርሱ በብልጽግና የሚንፈላሰሱ ምንደኞች በቤተ ክህነቱ መሠማራታቸውን ቢያውቁ እነዚያ አበው ምን ይሉ?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: