“ወልደ አብ” በተባለ የኑፋቄ መጽሐፍ ጉዳይ: ለብፁዕ አባ ማርቆስ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ፤“ሊያስወግዝዎና ከአባልነት ሊያሰርዝዎ ይችላል”/ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

  • ወልደ አብ” የክሕደት መጽሐፍ እንዲታገድና ምላሽ እንዲሰጥበት፣ አሳታሚዎቹም በሕግ እንዲጠየቁ የሀገረ ስብከቱ ካህናትና ምእመናን ቀደም ሲል ያቀረቡትን አቤቱታ በዚህ ፒዲኤፍ ፋይል ይመልከቱ፡፡

†††

  • በምሥራቅ ጎጃም ሀ/ስብከት ገዳማት፣ በድብቅና በስፋት እየተሠራጨ ነው
  • የሊቃውንት ጉባኤ ክሕደቱን መርምሮ እንዲያቀርብ በቋሚ ሲኖዶሱ ታዟል
  • ሊቀ ጳጳሱ፥በማውገዝ ፈንታ በዝምታ መደገፋቸው፣ ምእመናንን አስቆጥቷል
  • በንቀትና ትችት በፈጸሙት የቀኖናና የሕግ ጥሰትም፣አቤቱታው ተጠናክሯል

†††

  • በደላቸውን የሚያጣራ ልኡክ ቢመደብም፣ በፓትርያርኩ እንዲዘገይ ተደርጓል
  • ፓትርያርኩ ይኹንታ በሰጡት፣ፀረ ማኅበረ ቅዱሳን አድማቸው ቀጥለውበታል
  • ማኅበሩ፣ ከፍተኛ ድጋፍ የሰጠበትን ኹለገብ ሕንፃ፣በፓትርያርኩ ያስመርቃሉi
  • ለ5 ጊዜ አቤቱታ ቢያቀርብም፣ያልተደመጠው ምእመን፣እንዲያናግሩት ይሻል!

†††

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ“ወልደ አብ” መጽሐፍን ክሕደት ገልጸው ምእመናን እንይቀበሉት ቃለ ውግዘት ያስተላለፉበት ደብዳቤ

በሰሜን አሜሪካ የኒው ዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ፣ ወልደ አብ እና ምሥጢረ ሃይማኖትበሚል ርእስ በምሥራቅ ጎጃም በሚገኝ አንድ ገዳም አሳታሚነት የተሠራጨውን የክሕደት መጽሐፍ፣ የሀገረ ስብከታቸው ምእመናን እንዳይቀበሉት ያወገዙ ሲኾን፤ ኅትመቱንና ሥርጭቱን በዝምታ ተመልክተዋል፤ ያሏቸውን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስን ደግሞ፣ ስለ ቸልታቸው በመገሠጽ በጥብቅ አሳሰቧቸው፡፡

“መምህር ገብረ መድኅን እንዳለው” በተባለ ግለሰብ ተዘጋጅቶ፣ በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት፣ ጎንቻ ሲሶ እነሴ/ጒንደ ወይን/ ወረዳ በምትገኘው፣ የምስካበ ቅዱሳን ቆጋ ኪዳነ ምሕረት ዐጸደ ኤዎስጣቴዎስ አንድነት ገዳም አሳታሚነት የታተመው መጽሐፉ፤ ወደ ሰሜን አሜሪካ ደርሶ ምእመናንን እያወከና እያጠራጠረ እንደሚገኝ፣ ቅሬታዎች እንደ ደረሷቸው ብፁዕነታቸው ገልጸዋል፡፡

መጽሐፉ፣ “ክርስቶስ በቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ፤” ብሎ ምሥጢረ ተዋሕዶን በመንቀፍና መጻሕፍትን በመቆነጻጸል ያሰፈረው ክሕደት፣ በንጉሥ ሱስንዮስ ዘመን፥ ካቶሊኮች፣ ጸጎችና ቅባቶች ያሠራጩት እንደነበር ጠቅሰው፤ ክሕደቱን የተቃወሙት የተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመናን፣ እንደ በግ መታረዳቸውን እንደ ሽንኩርት መቀርደዳቸውን ዘክረዋል፡፡

የመጽሐፉ ኅትመትና ሥርጭት፣ አያሌ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ሰማዕት በመኾን የተቋቋሙትንና አባቶቻችን ሊቃውንት ጉባኤ ሠርተው የረቱትን ክሕደት መልሶ ለማምጣት የተደረገ ሙከራ በመኾኑ፣ እንዳወገዙት አስታውቀዋል፤ በሰሜን አሜሪካ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንም፣ መጽሐፉን እንዳይቀበሉት በውግዘታቸው በጥብቅ አሳስበዋል፡፡

ይኸው የክሕደት መጽሐፍ፣ በሰሜን አሜሪካ ብቻ ሳይኾን፣ በታተመበትና በድብቅ እየተሠራጨ በሚገኝበት በምሥራቅ ጎጃም፣ “በየቀበሌውና በየገበሬ ማኅበሩ ምእመናንን እያወከና እያበጣበጠ ይገኛል፤” ያሉት ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ፤ ድርጊቱን የሚገታ አንዳችም ርምጃ ባለመውሰድ በቸልታ እየተመለከቱ ባሉት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አባ ማርቆስ ማዘናቸውንም በይፋ ገልጸዋል፡፡

 የመጽሐፉን ኅትመትና ሥርጭት በዝምታ በመመልከት የክሕደቱን መስፋፋት እየደገፉ ላሉት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አባ ማርቆስ የጻፉላቸው ተግሣጽና ማሳሰቢያ፤

ትላንት፣ መስከረም 24 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ በቁጥር 158/2010፣ ለብፁዕ አቡነ ማርቆስ በአድራሻ በጻፉላቸው ደብዳቤ፣ “ወልድ ተፈጠረ” የሚል ፍጹም ውጉዝ አርዮሳዊ ትምህርት ይዞ በሀገረ ስብከታቸው በታተመውና እየተሠራጨ በሚገኘው የክሕደት መጽሐፍ፣ ክርስቶስ አምላክ እንዳልኾነ የሚያመላክት ትምህርት እየተሰጠ መገኘቱ በእጅጉ እያሳዘናቸውና እያስተከዛቸው እንዳለ ገልጸውላቸዋል – “ሰላም በክርስቶስ ስልዎ፣ እጅግ እያዘንሁ እና እየተከዝሁ ነው፡፡ ምክንያቱም፣ በሀገረ ስብከትዎ፣ ክርስቶስ አምላክ እንዳልኾነ የሚያመላክት ትምህርት እየተሰጠ ነው፤” ብለዋል፣ ብፁዕነታቸው፡፡

ከመጽሐፉ ገጽ 126፣ “ከእግዝእትነ ማርያም በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከተከፈለ ደመ ድንግልና ጋር ተዋሕዶ ተፈጠረ፤” የሚለውን ለማስረጃነት የጠቀሱት ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ፣ ወልድ ተፈጠረ” የሚለውን ትምህርት ሰምቶ ዝም ማለት ዲያብሎሳዊነት ነው፤” ሲሉ የክሕደቱን አሠቃቂነት በመግለጽ ሊቀ ጳጳሱን ብፁዕ አባ ማርቆስን ገሥጸዋቸዋል፡፡

የሊቀ ጳጳሱ ዝምታም፣ የኑፋቄው “ወራሾች ነን” ባዮች፣ ለመጽሐፉ ክሕደት ድጋፋቸውን በዐደባባይ እንዲገልጹ እያበረታታቸው እንደኾነ አመልክተዋል፡፡ የሉማሜ ወረዳ ነዋሪ የኾነና አንተነህ ምትኩ የሚባል ግለሰብ፣ በመጽሐፉ ላይ ያስተላለፉትን ውግዘት ተቃውሞ፣ “በፍጹም የቅባት መጽሐፍ፣ ከአባቶች እንደወረስነው ወደፊትም ያስተምራል፤ ይቀጥላል፤” በማለት በፐብሊክ ሚዲያ መናገሩን ብፁዕነታቸው ጠቁመው፣ “የቅባቱ መጽሐፍ ያስተምራል፤ ይቀጥላል፤” የሚለው “ወልድ ተፈጠረ” የሚለውን እንደኾነ አስረድተዋል፡፡

ይህ ፍጹም አርዮሳዊ ክሕደት፣ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርቱዕ ነገረ መለኰታዊ አስተምህሮ፣ ከጥንቱም መሠረት ይዞ ትርጓሜውና ምሥጢሩ ሲተነተንና ሲራቀቅ በኖረበት በጎጃም ምድር፣ ሲሰበክና ሲታወጅ በዝምታ መመልከቱ በከፍተኛ ደረጃ ሳያስጠይቃቸውና ጥብቅ ርምጃ ሳያስወሰድባቸው እንደማይቀር አስጠንቅቀዋቸዋል!! – ብፁዕ ወንድማችን አቡነ ማርቆስ፥ ይህ “ወልድ ተፈጠረ” የሚል አርዮሳዊ ክሕደትን የያዘ መጽሐፍ አስተምህሮ፣ በታላቁ ሲኖዶሳዊ መንበር ጎጃም ሀገረ ስብከት ሲሰበክና ሲታወጅ ዝም ብለው በመመልከትዎ፣ ሊያስወግዝዎና ከቅዱስ ሲኖዶስ አባልነትዎ ሊያሰርዝዎ እንደሚችል ላሳስብዎ እወዳለሁ፡፡” ብለዋል – ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ፡

ብፁዕነታቸው፣ ይህንኑ የማሳሰቢያ ጦማራቸውን፡- ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤትና ለመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት በግልባጭ አስታውቀዋል፡፡

በተመደበበት ሀገረ ስብከት ለሚገኙ ገዳማት፣ አድባራትና የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ካህናትና ምእመናን፣ መንፈሳዊ አባትና መሪ እንዲኾን የተሾመ የአንድ ሊቀ ጳጳስ መቅድማዊ ተግባሩና ሓላፊነቱ፣ ኖላዊነት ነው፡፡ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች፥ ሃይማኖታቸውን፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናቸውንና ኦርቶዶክሳዊ ትውፊታቸውን አጽንተው እንዲኖሩ ብርቱ ጥበቃ ማድረግ ነው! የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊነትና ታሪካዊነት፣ የሀገር ፍቅርና አንድነት በሰላም ተጠብቆ እንዲኖር መድከም ነው!!

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ፣ “ወልደ አብ” የክሕደት መጽሐፍን ከማውገዛቸውና ብፁዕ አባ ማርቆስንም ከማሳሰባቸው ቀደም ሲል፣ የምሥራቅ ጎጃም ምእመናን፣ ሥርጭቱ እንዲታገድና መጽሐፉን ለማሳተም ከምስካበ ቅዱሳን ቆጋ ኪዳነ ምሕረት ዐጸደ ኤዎስጣቴዎስ አንድነት ገዳም ወጭ የተደረገው ገንዘብ ተመርምሮ፣ ገንዘቡን ወጭ ያደረጉ አካላት ለሕግ እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ ሲማፀኑ ቆይተዋል፡፡ ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አባ ማርቆስም፣ ስለ ጉዳዩ ቢነገራቸውም፣ በማውገዝ ፈንታ በዝምታ ድጋፍ እየሰጡ በመኾኑ፣ ከሀገረ ስብከቱ እንዲነሡላቸውም ካለፈው ዓመት ጀምሮ በመጠየቅ ላይ እንደሚገኙ ይታወሳል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ቋሚ ሲኖዶስ፣ ሐምሌ 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ባሳለፈው ውሳኔ፣ መምህር ገብረ መድኅን እንዳለው በተባለ ግለሰብ ጸሐፊነትና በምስካበ ቅዱሳን ቆጋ ኪዳነ ምሕረት ዐጸደ ኤዎስጣቴዎስ አንድነት ገዳም አሳታሚነት የወጣው“ወልድ አብ እና ምሥጢረ ሃይማኖት” የተሰኘው የክሕደት መጽሐፍ፣ በሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮ እንዲቀርብለት ማዘዙ ታውቋል፡፡

የብፁዕ አባ ማርቆስ ሃይማኖታዊ ችግር ግን፣ በዚሁ የክሕደት መጽሐፍ ኅትመትና ሥርጭት ብቻ ያልተወሰነ፣ ከዚያም በፊት የቆየና ዘርፈ ብዙ መኾኑን፣ ምእመናኑ፣ ካለፈው ዓመት ግንቦት 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በየጊዜው ወደ መንበረ ፓትርያርኩ እየተመላለሱ ያቀረቧቸው አቤቱታዎች ያሳያሉ፡፡ ቀኖናዊ መነሻ ያላቸውና የብፁዕ አባ ማርቆስን ስሑት አቋም የሚያጋልጡ እንደኾኑ ከዝርዝሩ ለመረዳት ይቻላል፡፡ እንደ አቀራረባቸው ለማስቀመጥ ያህል፡-

  1. ከአራት ዓመት አንድ ጊዜ በዘመነ ዮሐንስ፣ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ታኅሣሥ 28 ቀን መከበር እንደሌለበት ሲያስረዱ፣ “እንደዚህማ ከኾነ ጥምቀትም በ10፣ ግዝረቱም በ5 መኾን ይኖርበት ነበር፤” በማለት የቅዱስ ሲኖዶስን ቀኖና መጋፋታቸው፤
  2. ሰኔ ጎልጎታ የሚጸልየውን ምእመን፣ “ይህ ልብ ወለድ ነው፤ ከእግዚአብሔርም አያገናኝም፤” በማለት በጸሎቱ እንዳይጽናና ማድረጋቸውና ያልጸኑ ምእመናን በክብረ ቅዱሳን ጥርጣሬ እንዲገባቸው መኾኑ፤
  3. የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሥርዓት መጻሕፍት በኾነው በፍትሐ ነገሥት መሠረት፣ የጌታችን የጾም ወራት በሚታሰብበት፣ በጾመ ኢየሱስ(ዐቢይ ጾም)፥ በአርምሞ፣ በጾምና ጸሎት፣ በንሥሓና ቅዱስ ቁርባን በመቀበል፣ በሱባዔ፣ የጌታን ሕማማተ መስቀል እያሰቡ ማዘን፣ ማልቀስ የሚገባ በመኾኑ ከበሮ የማይመታ፣ የማይጨበጨብ ቢኾንም፤ ብፁዕነታቸው፥ ይህን ሥርዓት በመተው፣ ምእመናን፣ “አለመድንም፤ ከበሮ አንመታም፤ አናጨበጭብም” እያሉ፣ “እኔ ሊቀ ጳጳሱ ተቀምጩ፣ እኔ ፊታችሁ እያለሁ” በማለት በደብረ ማርቆስ ከተማ በሚገኘው ጽርሐ ጽዮን አብማ ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተደረጉ ጉባኤያት፣ ምእመኑ ሳይፈልግ በማስገደድ በወርኃ ጾም ከበሮ አስመትተዋል፤ አስጨብጭበዋል፤
  4. የሰንበት ት/ቤቶች በአጽዋማት ጊዜ፣ ምእመኑን በማሰባሰብ፣ የጸሎተ ኪዳኑንና የቅዳሴውን ሰዓት በማይነካ መልኩ ሰዓቱን በማመቻቸት ከተጀመረ ከ25 ዓመታት በላይ የኾነውንና በአባቶች ጸሎተ ማዕጠንት እየተደረገ ይካሔድ የነበረውን የጋራ ጸሎትና ስግደት፣ “አያስፈልግም፤ ይልቁንም በምትኩ ትምህርት እናስተምራችሁ፤ ያለበለዚያ ጸሎትና ስግደት አያስፈልግም፤” በማለት የተሰበሰበው ምእመን በየአጥቢያው እንዲበታተን አድርገዋል፤
  5. ብፁዕነታቸው፣ ነገረ ቅዱሳንን በተመለከተ ግራ የሚያጋባ አቋም ያላቸው ሲኾን፤ የሀገረ ስብከቱን ሰባክያነ ወንጌልን በመንበረ ጵጵስናው ሰብስበው፣ ክርስቶስን ስበኩ እንጅ አቡሀይ እሙሀይ አትበሉ፤” በማለት ስለ ቅዱሳን ያላቸውን አመለካከት ተናግረዋል፤
  6. የአብማ ጽርሐ ጽዮን ማርያም ቤተ ልሔም ሲመረቅ፣ ከባረኩ በኋላ፣ “ቤተ ልሔሙን እንደ ማብሰያ፣ ቤተ ክርስቲያኑን እንደ አዳራሽ ቁጠሩት፤” በማለት የንቀት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ራሳቸውን፥ ከኹሉም የተለየ፣ የማይገኙ፣ የማይተኩ፣ እርሳቸው ያሉትን የማይቀበል ያልዳነና ያልገባው እንደኾነ በመግለጽ በካህናቱና ምእመናኑ ላይ ትችት፣ ንቀት፣ ስድብና እርግማን የሚያወርዱት የብፁዕ አባ ማርቆስ በደል፣ በብልሹ አስተዳደር፣ በጎጠኝነትና በገንዘብ ምዝበራ እንደሚገለጽም አቤቱታው አመልክቷል፡፡

አስተዳደራዊ ችግሮች፡-

  1. ብፁዕ አባ ማርቆስ ወደ ሀገረ ስብከቱ ከመጡ ጀምሮ ብዙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከቱ ቢኖሩም፣ ፊደል ይቁጠርም አይቁጠርም ከላይ እስከ ታች(ከሀገረ ስብከቱ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን) ያስያዙት በቅርብ ዘመዶቻቸው ነው፤ በአብያተ ክርስቲያናቱም ፍትሕ ርትዕ ጎድሏል፤ ጠፍቷል፤
  2. በቃለ ዐዋዲው መሠረት የተቋቋሙትን የሰንበት ት/ቤቶች፣ በ2005 ዓ.ም.፣ “ወንበዴዎች፣ ሌቦች፣ አሸባሪዎች” ብለው በሕዝብ ፊት ተሳድበው ለሰዳቢ ከመስጠታቸው በተጨማሪ፣ በ2009 ዓ.ም. ደግሞ የሰንበት ት/ቤቶችን ማሸግ፤ ውስጥ ለውስጥ የሰንበት ት/ቤቶችን ማዳከም፤ ብሎም በመምሪያ ደረጃ በተሐድሶ ኑፋቄ የሚጠረጠር ሰው እንዲመራው ማድረግ፤
  3. ቃለ ዐዋዲውን ያልተከተሉ፣ ተቋማዊ መዋቅሩን የጣሱ ዝውውሮችና ሹም ሽሮች በማካሔድ ካህናት ተረጋግተው እንዳይሠሩ ማድረጋቸው፤ ለአብነት ያህል በመጡበት አምስት ዓመት ውስጥ፦ በአብማ ማርያም አራት፣ በዋሻው ቅዱስ ሚካኤል አምስት፣ በደብረ ፀሐይ ቅዱስ ማርቆስ አራት፣ በኪዳነ ምሕረት አምስት እና በእንድማጣ ደብረ ኢየሱስ ስድስት አስተዳዳሪዎችን በማፈራረቅ ተረጋግተው እንዳይሠሩ አድርገዋቸዋል፡፡
  4. በቃለ ዐዋዲው መሠረት እየሠሩ፣ የቤተ ክርስቲያንን ሀብት በአግባቡ የሚቆጣጠሩ የመንፈሳዊ ሰበካ ጉባኤ አባላትን ሕዝብ ባላወቀው መንገድ መሻርና አብያተ ክርስቲያኑን ለምዝበራ ማጋለጥ፤ ምሳሌ፡- የደብረ ሕያዋን ዋሻው ቅዱስ ሚካኤል በአንድ ወር ውስጥ አራት የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላትን ሽረዋል፤
  5. “የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ናችሁ፤” በሚል፣ ምእመናን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባልነት እንዳይመረጡና በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ እንዳይገቡ ማድረግ፤ ከተመረጡም ወዲያውኑ እንዲሻሩ ማድረግ፤ ምሳሌ፡- ሉማሜና የባሕረ ጥምቀቱ ኮሚቴ፤
  6. ወደ ምሥራቅ ጎጃም ከመምጣታቸውም በፊትም ኾነ ከመጡም በኋላ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ ተስማምተው አለመሥራታቸው ቢታወቅም፣ አኹን ግን ከምንጊዜውም በላይ፣ “ማኅበሩ የሸዋ ነው፤ ዳግም ጥምቀት ያጠምቃል፤ ለራሳቸው ስለት ይቀበላሉ” እያሉ ስም ከማጥፋታቸው በተጨማሪ፣ የግለሰቦችን ስም እየጠሩ፣ “ስለት የሚቀርብላቸው ታቦት ናቸው፤” በማለት በ30/08/2009 ዓ.ም. የቅዱሰው ማርቆስን በዓል ለማክበር ለመጣው ሕዝብ በዐውደ ምሕረት በመናገር አሳዝነዋል፤ ሕዝቡም ይህን ሲሰማ ጥሏቸው ወጥቷል፡፡
  7. በዚሁ የቅዱስ ማርቆስ የንግሥ ክብረ በዓል፣ የዩኒቨርሲቲ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች በግቢ ጉባኤ መንፈሳዊ ትምህርት እንዳይማሩ፣ የመንግሥት አካላት እንዲያስቆሙላቸው በመናገራቸው፣ ምሥጢሩን የሚያውቀውን ሕዝበ ክርስቲያን አንገት አስደፍተዋል፡፡

የፋይናንስ እና የቁጥጥር ችግሮች፡-

  1. የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴን ማዋቀርና ማፍረስ፤ ከብፁዕ አባ ማርቆስ ልዩ መገለጫ አንዱ፣ ኮሚቴ ማዋቀር ሲኾን፤ አንድን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በራሳቸው መልካም ፈቃድ ካቋቋሙና ያሰቡትን የገንዘብ ማሰባሰብ ‘ፕሮጀክት’ ካስፈጸሙ በኋላ፣ ምን ያህል ገንዘብ እንደተሰበሰበና ወደፊት ምን ምን ዓይነት ሥራዎች እንደሚሠሩ ምሥጢሩን የሚያውቀውን የኮሚቴ አባል ያባርሩና እንደገና በአዲስ ያቋቁማሉ፤ ለምሳሌ፡የሀገረ ስብከቱ የሕንፃ ግንባታ ኮሚቴና የባሕረ ጥምቀቱ ኮሚቴ፤
  2. ቤተ ክርስቲያንን ለመባረክና በጉባኤ ለጥቂት ሰዓታት ለመገኘት፣ ከፍተኛ ክፍያ መጠየቅና ዘመድ አዝማዶቻቸውን እያስከተሉ በመሔድ ለኹሉም አበል እንዲከፈላቸው ማድረጋቸው፤

በአጠቃላይ፣ ብፁዕ አባ ማርቆስ ወደ ምሥራቅ ጎጃም ከመጡበት ኅዳር 2004 ዓ.ም. ጀምሮ በካህናት፣ በዲያቆናትና በሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱ ምእመናን ዘንድ ያልተለመዱ፣ በርካታ እንግዳ ኹኔታዎች ተከሥተዋል፤ ምእመናንንም ግራ እያጋቡ፣ ለመናፍቃን ሰርጎ ገብነትም በር የከፈቱና የሚከፍቱ ናቸው፡፡ በሀገረ ስብከቱ ያደረሱት ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ በደል ከላይ ለማሳያ ያህል የተዘረዘሩት ብቻ አይደሉም፤ “የቤተ ክርስቲያንንና የአባቶችን ክብር የሚያስደፍሩ በመኾናቸው አላካተትናቸውም፤” ብለዋል ምእመናኑ በአቤቱታቸው፡፡

እነኚህን ዘርፈ ብዙ ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ ችግሮች ለመፍታት ከብፁዕነታቸውና ከመንግሥት አካላት ጋራ ተደጋጋሚ ውይይት ለማድረግ ምእመናኑ ቢሞክሩም፣ ብፁዕ አባ ማርቆስ በሚያሳዩት፣ “አባታዊ ያልኾኑ ንግግሮችና ድርጊቶች” ምክንያት ውጤታማ ሊኾኑ እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡ ይብሱኑ፣ የቤተ ክርስቲያንን እሴት የሚያንኳስሱ አሠራሮች ከዕለት ዕለት እየበዙ በመምጣታቸው፣ መዋቅሩን በጠበቀ መልኩ ጉዳዩን ለቅዱስ ሲኖዶስ፣ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ ለማቅረብ እንደተገደዱ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም መሠረት፣ ወደ ቦታው አምርተው፣ ችግሩን ጥንቃቄ በተሞላበት ኹኔታ አንድ በአንድ አጣርተው ውጤቱን በሪፖርት እንዲያቀርቡ፣ ሦስት የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ልኡካን ተሰይመው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ ባለፈው ነሐሴ 23 ቀን 2009 ዓ.ም.፣ በቁጥር 798/1064/2009፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፊርማ ወጪ የተደረገ ደብዳቤ ለአጣሪ ልኡካኑ በየስማቸው ቢደርሳቸውም፣ ስምሪታቸው በፓትርያርኩ እንዲዘገይ ተደርጓል፤ ተብሏል፡፡

ለስምሪቱ መዘግየት የተለያዩ ሰበቦች ቢጠቀሱም፣ ኹነኛው ምክንያት ግን ከሰሞኑ ግልጽ ኾኖ እንደታየ የጉዳዩ ታዛቢዎች ይስማማሉ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን፣ በዓመቱ መባቻ በአሌፍ ቴሌቭዥን ጣቢያ የ7 ሰዓት ሳምንታዊ ፕሮግራም መጀመሩን ተከትሎ ፓትርያርኩ የጫሩት ውዝግብ፣ ለብፁዕ አባ ማርቆስ፣ በሀገረ ስብከታቸው ከተነሣባቸው ሕዝባዊ ተቃውሞና ውጥረት የመሸሸጊያ ዕድል የፈጠረላቸው መስሏል፡፡ የማኅበሩን የአየር ሰዓት ለማሳገድ፣ “ከመንግሥት አጻፍኩት” ያሉትን ደብዳቤ ይዘው ከመንቀሳቀስ ባሻገር፣ በፓትርያርኩ ይኹንታ የተሰጠውንና ጥቂት አበሮቻቸው የሚሳተፉበትን አድማ በመምራትና ከዕለት ዕለት በማጠናከር ማኅበሩን እንደሚያጠፉ በግልጽ እየዛቱ ይገኛሉ፡፡

“ከጊዜው የፈጠነ ነው፤” የተባለ የኹለገብ ሕንፃ ምረቃ መርሐ ግብርም አዘጋጅተዋል፡፡ በነገው ዕለት ወደ ደብረ ማርቆስ የሚያመሩት ፓትርያርኩ፣ የፊታችን ቅዳሜ ኹለገብ ሕንፃውን እንዲመረቁ መርሐ ግብር ተይዞላቸዋል፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ማርቆስ ማእከልም፣ በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ እንዲገኝ ጥሪ ደርሶታል፡፡ ትልቁ ምፀትም፣“ስእለት ይበላል” እያሉ በየዐውደ ምሕረቱ ስሙን ያጠፉት ማኅበረ ቅዱሳን፣ በዋናው ማእከሉና በማእከሉ ግቢ ጉባኤያት በኩል ለሕንፃው ግንባታ ከፍተኛ የገንዘብና ልዩ ልዩ ድጋፎችን ያደረገ መኾኑ ነው፡፡

ሊቀ ጳጳሱ፣ የተነሡባቸውን ዘርፈ ብዙ ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ ችግሮችን ለማድበስበስ የሚሞክሩበት አጋጣሚ እንደሚኾን ከወዲሁ ቢታወቅም፣ ለአምስት ጊዜ ያህል በራሳቸው ከፍተኛ ወጪ ወደ መንበረ ፓትርያርኩ እየተመላለሱ አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ የቆዩት የሀገረ ስብከቱ ምእመናንም፣ ከፓትርያርኩ ጋራ በግልጽ መድረክ ለመወያየት በእጅጉ እንደሚሹ ነው የተጠቆመው፡፡

በብፁዕ አባ ማርቆስ፣ እንደ ሕዝብ የተሰደበበትን ትችት፣ ንቀትና እርግማን ችሎ፣ በቤተ ክርስቲያን ልጅነቱ መዋቅሩን ጠብቆ በትዕግሥትና በሰላማዊነት ሲያቀርብ ለከረመው አቤቱታ፣ አባታዊ ፍቅር የተመላበትና የኖላዊ ኄር ሓላፊነት የሚታይበት ኹነኛ አያያዝና ምላሽ ይጠብቃል፡፡  

16 thoughts on ““ወልደ አብ” በተባለ የኑፋቄ መጽሐፍ ጉዳይ: ለብፁዕ አባ ማርቆስ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ፤“ሊያስወግዝዎና ከአባልነት ሊያሰርዝዎ ይችላል”/ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

  1. ቴዎድሮስ ግደይ October 5, 2017 at 12:53 pm Reply

    አባቶቻችን በምግባርም በፀሎትም እየደከሙ ነው ፣እኔ የምኖረው በእንግሊዝ ማንቸስተር ሲሆን በአጥቢያችን የሥላሴ የቤተክርስቲያናችን ችግር እየተባባሰ የመጣው በብፁአን አባቶች ነው፣ገንዘብ ወዳድ እንጂ ለእውነት የሚጋፈጡ አይደሉም ባጠቃላይ የተወሰኑ ካልሆኑ በስተቀር ሁሉም ያው ናቸው ግን እማዝነው እነሱን የምንወቅስ ትውልድ መሆናችን ነው።መስቀል ለመሳለም ብርቅየ የነበሩ አባቶች ዛሬ እኔም ማንም በረከሰ አንደበት ያነሳቸዋል የዚህ ተጠያቂዎቹ እነሱ ናቸው
    ወስበሃት ለእግዚአብሄር

  2. Amanuel October 5, 2017 at 1:46 pm Reply

    እኔ እምለው? ሰውየው (አባ ማርቆስ)የሲኦል ዜጋውና የሁሉቱ ወንድማማቾች / የፀጋና የቅባት /አባት የአልፎንዙ ሜንዴዝ ተክል ናቸው እንዴ ? ያ ከሆነ ሰውየውን ኦርቶዶክሳውያን አባቶች እንዴት ይሁንታን ሰጥተው እስከዚህ አደረሷቸው? ‘ ‘ ሰውየው ቀደም ብሎም በዚህ ማንነት መታማታቸው ግልፅ ቢሆንም እስከዚህ አይን ያወጣ ክህደት ውስጥ ይዘፈቃሉ ተብሎ አይጠረጠርም ነበር ። ‘ ‘ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን የንስሃ ቤት እንደመሆኗ ያን የሞት ኮተት አራግፈው ከሸክማቸው አርፈዋል ተብሎ ይገመት ነበርና!! ‘ ‘ ለካንስ ልብስ አይሸፍነው ነገር የለምና በልብስ ተሸፍነው ነበር ።ግና የሚሰሩትን ክህደት በቀሚስና ቆቡ ሸፍኖ መዝለቅ አይቻልምና በአደባባይ ተገለጠ።ድሮውንስ ማንነት መች ተቀብሮ ይቀራል ያውም የእውነት ዓምድ በሆነችው በእግዚአብሔር ቤት በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ !! ‘ ‘ የሚገርመው ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ ……ይሉት ሀገርኛ ብሂል ነበር፤ አሁን አሁን ማቀሰስ ብቻም ሳይሆን ያጰጰስም ይዟል ። ዘለዓለማዊውን ክብር በጊዜአዊ ደስታ፣ ገነትን በሲኦል ፣ ሕይወትን በሞት፣ ክብርን በውርደት፣እምነትንበክሕደት፣ እረኝነትን በምንደኝነት መለወጥ ምንኛ መዝቀጥ ነው !! ‘ ‘ ለአባታችሁ(አልፎንሱ) ያልጠቀመ ክህደት ምን ይጠቅመን ብላችሁ?? ይጠቅመናል ካላችሁስ ከአባቶቻችን ጋር መመሳሰሉን ለምን ሻታችሁ? በበጎችስ መሀል እንደ ተኩላ መገኘታችሁ ምነው? አያችሁ በምታምኑበት ታፍራላችሁ። እርግጥም የፀጋና ቅባት እምነት ተከታይ ተሆኖ ያልታፈረ በምን ይታፈር ??? ‘ ‘ እውነተኛ እረኛ ግን የበጎቹ ነገር ይገድደዋል ። ከተኩላ ጥቃት ይጠብቃቸዋል እንጂ በበረታቸው ውስጥ ተኩላ አያራባም ። ምንደኛው ግን ከሌባው (ሰይጣን) በመተባበር እንዲጠብቅ አደራ የተሰጡትን በጎቹን ያለምህረትና ርህራሄ አርዶ ይበላል(ቅድስት ሃይማኖታቸውን ያስክዳል)። እርሱ ግን በጎቹን እንዲጠብቅለት የቀጠረው የበጎቹ ባለቤት ሲመጣ ግን መልስ ይሰጥበታል ። እስከዚያው ግን አመፀኛውም ያምፅ ርኩሱም ይርከስ ….እንደተባለው ነው። አቤቱ ጌታችን ሆይ የሆነብንን አስብ መጥተህም እርዳን !!!!

  3. Anonymous October 5, 2017 at 8:53 pm Reply

    የሌባ አይነ ደረቅ አቡነ ዘካርያስ
    የሀገረ ስብከቱን ካዝና ሙጥጥ አድርገው ከተለያዮ ሲቶች ለወለዶአቸው ዲቃላወች ካወረሱ በሗላ ተዘረፍኩኝ
    ተጭበረበርኩኝ በለው የማያስመስል ውሸት አቅርበው ልመና ወደ አሚሬካ የዋህ ሕዝብ እደፈረደበት ከፈለ
    ጳጳሱ ኪሣቸው ሲሞላ ወደአገርቤት በረሩ አሁንም ያገገመው የምስራቅ ጎጃም ደብረማርቆስ
    ተመልሰው ሊሔዱበትነው ለዘረፋ የሌባ አይነደረቅ አባዘካርያስ

  4. Anonymous October 6, 2017 at 10:18 am Reply

    It is getting even worse. A call for all followers of the church – it is absolutely foolish and nonsense to give your money to the church. Only serve and help deacons and priests in your own local church with care. I am convinced that we have no church fathers at this time and the church administration is decaying.

    With our money, they are making us to suffer.

    Wake up and take action. We respect them as long as they remain true fathers. Otherwise, they are enemies of God and the Cross.

    A call to action for all church followers. Do not attend events where this evil man is present; disregard and denounce him by leaving him stand alone.

    He and his colleges will be judged by God and will be thrown to hell.

    I am also happy at the same time. It seems that God is to free the church.

    All the bad, false fathers are exposed and we will soon see the church flourish with true brothers and fathers.

    God saves our church and gives the wisdom and strength to our true fathers.

  5. Anonymous October 6, 2017 at 2:05 pm Reply

    አቡነ ቅባት(ማርቆስ) በጣም የማይጠቅሙ ሰው ናቸው ስራቸው የሚሰራን በማሳደድ ስራቸው አድርገው በሀገረ ስብከታቸው የሚሰራውን የት ያዩታል በጣም ተዋረዱአንድ የሀገረ ስብከት ጳጳስ የስወግዞታል መባሉ ውርደት ነው ለነገሩ አርሳቸውና ፓትሪያሪኩ የያዙት ትግል ከማህበረ ቅዱሳን ጋር እንጂ ቀኖናና ዶገማ ጣጣ አይሰጣቸውም ህገ ቤተክርስቲያን ይከበር የሚልን ሰው ማሸማቀቅ ነው የሚፈልጉት በጣም ነው የሚያሳዝነው እግዚአብሔር ግን ፍረዱን ለእነዚህ ሰዎች ፍርዱን የስጥ እኛስ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን ብንኛር የሚሰማን የለም ብንታወቅ ከቤተክርስቲያን አገልግሎት ለማገድና ደመወዝ ለማገድ ጃቸውን ያሾላሉ በእያለበት ካህናቱ ሁሉ ውስጣችን እያረረ ዝም ዝም አልን የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን

    • Anonymous October 7, 2017 at 2:30 am Reply

      የምግባርና የሀይማኖት ህፀፅ ይለያያል…ክርስቲያን በምግባር ቢወድቅ በንስሃ ይመለሳል …ፃዲቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል ሰባት ጊዜ ይነሳል እንዲል መፃህፉ….የሀይማኖት ህፀፅ ግን እንደ አሪዮስ ተመክሮ ካልተመለሰ ያስወግዛል

    • Anonymous October 8, 2017 at 10:42 am Reply

      What are you trying to say my friend? I think you are not part of the church. Your call is completely wrong. Church members and followers must stand together in order to protect the mother church but not by stopping donating money to church. Yes. We know some bishops are not doing well and they are engaging with earthly things but our church has many and many archbishop who are dedicated themselves to God and to the church
      So, before pointing our one finger to another our three fingers are pointing at our heart. May God protect our mother church from the hand of her enemies

  6. Anonymous October 6, 2017 at 3:21 pm Reply

    he is another Begashew why other synodos members are keeping silent

  7. Anonymous October 8, 2017 at 5:32 pm Reply

    The guy has been a patriarch since 16 years back and the people were complaining since then. All top position holders in the church including the pop are all cadres, thieves, liars and cheaters. Their job is stealing all the church resources, serving the regime,dis-intergrating the followers,fucking women in all corners. They don’t have the moral and capacity the church at all. Let God save the church not them.

    • Anonymous October 10, 2017 at 8:33 pm Reply

      Good news!
      Our beloved father Aba Serekebirhan
      Woldesamuel haw appointed as a head of the Education and Training Department . He was working in that place before he had taken the office of his holiness. Father Serekebirhan has been fighting against the church corrupters and the evil act of Mk. Last year, when he took the office of his holiness, he had made a strategic plan for his holiness. but he was removed from that office by the evil advice of Nbured Elias ,Aba Kaletsidk and Muse Because they do know the strategy is going to completely blocked them their business (which is corruption)
      Howeve, Father Serekebirhan has been working in the department of Likawunt Gubae( as a member of the scholars) for the last eleven months.
      we heard that father Aba Serekebirhan woldesamuel is going to release two new books very soon.
      We expect from these books something new.
      Dear father please keep going strongly against the corrupters. As you said it in your speech in 2007 in the assembly meeting, the big problem of the church is not only MK but the leadership of the church must be changed

  8. Shimelis October 10, 2017 at 10:59 pm Reply

    …ተጠንቀቁ። ማቴ 24፤4
    ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና፤
    የኢየሱስ ክርሰቶስ ትምህረቱ ይኸውና።
    እኔ ክርሰቶስ ነኝ እየሱስ እያሉ፤
    ብዙዎች አሳቾች በስሜ ይመጣሉ።
    እነሆ አሰቀድሜ ነገርኩዋችሁ ንቁ፤
    ከሀሳዊ መሲህ ተኩላ ተጠንቀቁ፤
    ይህ ሊሆን ግድ ነው ብሎአል ተጠበቁ።ማቴ 24።
    የሆነውም ሳይሆን፤የመጣው ሳየመጣ፤
    ነግሮ አስጠንቅቆናል ከእምነቱ እንዳንወጣ።
    ሰይጣን ሲነቃበት ዽልመቱን ሰውሮ፤
    የብርሃን መልአክ መስሎ ይመጣል ዞሮ።
    የእርሱም ተከታዮች ሐዋርያት መስለው፤
    እኛ የማናውቀውን ሌላ ኢየሱስ ሰብከው። 2ቆሮ 11፤ 4-15።
    እንደ ከዚህ ቀደም ሃይማኖት ሳይነቅፉ፤
    የበግ ለምድ ለብሰው በጎች የሚጠልፉ፤
    በማያውቁት ግዕዝ የሚኮላተፉ።
    የአባቶችን ትምህር ትውፊት ተጠግቶ፤
    በቤተክርስትያን ነጠላን አጣፍቶ።
    መሰቀሉን አጥልቆ ተክህኖ ቆብ ደፍቶ፤
    ካባውን ደረቦ ቤተመቅደስ ገብቶ፤
    ይሸጣል ያተርፋል…ገበያ ዘርግቶ፤
    ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትያን ነኝ ብሎ፤
    የቅድሰት ማርያም፤የቅዱሳን መላእክት… አክባሪ ወዳጅ መስሎ።
    መቋሚያ ዽናዽል…ከበሮውን ይዞ፤
    ሲመታ ሲያዘምም… ያየውን መርዞ።
    ወረቡ ፤ሽብሻቦው… ጭብጫቦ መዝሙሩ፤
    የዽዋው ማህበር፤ ቤት ለቤት መዞሩ፤
    መሸፋፈኝ ነው…የድብቅ ሚስጥሩ፤
    የዝሙት መዳራት የሀጢት ስሩ። 2ቆሮ 12፤21።
    የላሰቲክ አበባ የተፈጥሮን መስሎ፤
    ቤትህን ያፈረሳል ዓይንህን አታሎ።
    ከእነርሱ ወግኖ… ደጋፊ ያልሆነ ሰው፤
    ተጠልቶ ይፈረጃል…. ሰም እየተሰጠው።
    እውነተኛው አማኝ ዽኑ እየተገፋ፤
    ገለል ይደረጋል አንገት እንዲደፋ።
    በተቀላቀል ስልት… የጨበጣ ውጊያ፤
    ስንቱ ተማረከ ሆኖት መዘናጊያ።
    በተዋህዶ ካባ በርኖሱን ደረቦ፤
    ቀጣፊ አመንዝራ እምነት አሰድቦ።
    በጠቆረ ልቡ ተንኮልን አሳቢ፤
    ነጭ ለብሶ አደግድጎ በድፍረት ቆራቢ።
    ቅስፈት የማይፈራ ምሽጉን ቆፋሪ፤
    የሃማኖት አይጥ ውስጥ ውስጡን ቦረቧሪ፤
    አዽራረ ክርስቶስ ነው ነገረ ሠሪ።
    የዚህ ሁሉ አሰራር ዋና መሀንዲሱ፤
    ጥንተ ጠላታችን ሰይጣን ነው እርኩሱ።
    የሃይማኖት ምስጦች ከመጡ ጀምሮ፤
    ውስጥ ውስጡን ነቅዘናል ግንዱ ተቦርቡሮ።
    አክራሪ መናፈቅ ልዝብ ተሀድሶ፤ 1ጢሞ 3፤6።
    አመንዝራ ግብዝ እራሱን ቀድሶ።
    ዲያቆን ቄስ መነኩሴ… ጳጳስም ተሆኗል፤
    እንደ ድፎ ዳቦ ከላይ ታች ነደናል።
    በስልጣን ጥቅማ ጥቅም ዘረኝነት ዝተው፤
    ተዋህዶን ለማጥፋት ይዋጉናል ዘምተው።
    የክርስቶስ ወንጌል ቃሉ እንዳይሰበክ፤
    እውነት ያግዳሉ እንዳትወጣ መድረክ።
    አይሆንላቸውም ግን ይሄን እወቁ፤
    እንደ እባብ ልባሞች ሁኑ ተጠንቀቁ። ማቴ 10፤16።
    የእግዚአብሔርን ዕቃ ጋሻ ጦሩን አንሱ፤
    የመንፈስን ሰይፍ ጥሩር ቃል ልበሱ።
    ከክፋት ሠራዊት ለመጋደል ታጥቀን፤
    በጌታ ሀይል ችሎት ብርቱዎች እንሁን።
    የዲየቢሎስ ሽንገላ እንቃወመው ዘንድ፤
    የእውነትን ትጥቅ ይዘን ይሉንታ እናሰወግድ። ኤፌ 6፤10-20።
    እንደ ባህታዊ ትንቢትን ተናግሮ፤
    በየአድባራቱ አንገት አቀርቅሮ፤
    ገዳማዊ መሳይ ተኩላና ቀበሮ።
    ማርያም አማላጄ ቅዱሳን…እያለ፤
    በስም የሚነግድ ጉድአጉድም አለ፤
    በተግባሩ በታኝ እየከፋፈለ።
    በቅዳሴ ሰዓት አሀዱ አብ…ሲባል፤
    እጆቹን ዘርግቶ…ተሰጥኦ ሲቀበል፤
    ለዐሎት ሲነሳ ሰግዶ እግዚኦታ ሲል፤
    እውነተኛ አማኙን ምዕመን ይሳጣል፤
    ጥራዝ ነጥቆ ጠቅሶ በቃሉ ይሸቅጣል፤
    ወጣኒ ካገኘም አሰናክሎ ያስወጣል።
    እሱ ራሱ አሰመሳይ ተቃዋሚ ሆኖ፤
    ሰዎች ይኰንናል በስም ተሸፋፍኖ።
    እየሱስ የሚል ስም ቀድማ ያወጣችለት፤
    የአማኑኤል እናት ቅድስት ማርያም ናት። ሉቃ 1፤31።
    እርስዋን አቃላችሁ በስሙ አትነግዱ፤
    የማታምኑባትን አትችሉም ልትወዱ፤
    እስስት፤ መናፍቃን ከእኛ ተወገዱ ።
    በስንዴ እርሻ መሀል እንክርዳድ የዘራው፤
    ይገሰዽ ዲያቢሎስ እስኪደርስ አዝመራው።
    እስከዚያው ያስመስል፤ ያልሆነውን ሆኖ፡
    ለአሳዊ መሲሀን ለታመኑት ታምኖ፤
    የአንተ እምነት ለራስህ ይሁንልህና፤
    አትፈታተነው የእኔን ህልውና።
    በሠራዊት ብዛት አድማህ አትመካ፤ 1ቆሮ 1፤30።
    ድል የስላሴ ነው እምነቴን አትንካ፡፤
    ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ሃይመኖቴ ብቻ፤ ኤፌ 4፤5።
    መጠሪያ ክብሬ ናት ወደር የለሽ አቻ፤
    ደባል አትፈልግም እንጥልጥል ጉትቻ ፤
    ደም ተከፍሎባታል እስከ ዓለም ዳርቻ። ማር 6፤16። የሐዋ 12፤2።
    የወንጌሉ ሚስጢር ያልገባው ሥጋዊ፤
    አውደ ምህረት ቆሞ ይሰብካል ምድራዊ።
    ማስተዋሉን ጋርዶ ቀን ያጨለመበት፤
    ያ እርኩስ መንፈስ ነው የተጠመቀበት።
    እውነተኛው ዳኛ ኢየሱስ ሲመጣ፤
    ፍርድ ይሰጥበታል መዝገቡ እየወጣ። ማቴ 25፤31።
    የበግ ለምድ ለባሽ…አክራሪ መናፍቅ፤
    የቀና ሃይማኖትክን እንዳይበክል ጠብቅ። ዕብ 4፤14
    በመጨረሻው ቀን እጅግ የሚያስጨንቅ፤
    የራስ ወዳድ ዘመን እንዲመጣ እወቅ፤
    ትዕቢት ከነፋቸው ተንኮለኞች እራቅ። 2ጢሞ 3፤1-6።
    ሁሉም ለበጎ ነው…በፈተና እንኑር፤
    ወንጌል ተመርኩዘን ህያው ቃል እንመስክር።
    እኛ በፊልጶስ እጅ የተጠመቅን፤
    ብሉይን ከሀዲስ አጣምረን ያወቅን፤
    ማተብ የማንበጥስ በኢየሱስ የአመንን፤
    ቀዳማይ ክርስትያን ኢትዮጵያውያን ነን፤ የሐዋ.ሥ 8፤26-38
    የተዋህዶ ልጆች ኢትዮጵያውያን ነን።
    በእንተ ማርያም ብለን የምንማዸነው፤
    የቅድሰት ድንግል ልጅ ኢየሱስ አንድነው።
    በቤተክርስትያን አንገቱን የደፋ፤
    ከሳሻችን ሰይጣን ተገስዾ ይጥፋ።
    በሃይማኖት ንቁ ጎልምሱ ጠንክሩ፤ 1ቆሮ 16፤13።
    የሰይጣንን ውግያ ገድላችሁ ቅበሩ።
    መለከት ተነፍቶ ተነግሮአል አዋጁ፤
    መጠንቀቅ ዛሬ ነው ዘመን እየዋጁ።
    ሃይማኖተ አበው ስንክሳሩን ብታውቅ፤
    አትስትም ነበር በአጉል መመዻደቅ።
    በአመንኩበት እውነት ቃል ስለምመካ፤
    የአንተ ለአንተ ይሁን የኔንም አትንካ።
    ኢየሱስ ሲመጣ ጥያቄ እንድትመልስ፤
    የበቃሁ ቅዱስ ነኝ ብለህ አትኮፈስ፤
    ወንጌል እወቅና እራስህን አድስ፤
    ጥራዝ እየነጠክ ዘለህ ቀንድ አትንከስ።
    ወሰብሀት ለእግዚአብሔር።

  9. አመተ ማርያም October 11, 2017 at 12:25 pm Reply

    በእግዚአብሔር ሀይል – ይሳካልናል
    እንሮጣለን አይደክመን እናስባለን ይፈፅምልናል፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
    “ማህበሩ የደም ስራችን ነው”

  10. Anonymous October 11, 2017 at 6:12 pm Reply

    ማህበሩ የደም ስራችን ነው
    እንዘምራለን የወያኔ ፓትሪያሬክ ማትያስ
    የሰፈረበት አሚሬካ በካባቸው አፍሰው ያመጡት ሰይጣን እስከ ሚለቃቸው
    እንዘምራለን በቅዱሣን ስም ውጣ የማትያስ ሰይጣን እረ በቅዱሣን ስም ማህበረ ቅዱሣን የደምስሬ ነው

    • anonymous October 13, 2017 at 1:36 pm Reply

      ከቤተ ክርስቲያ ልጅ እና ከማህበሩ አባል ይህ አንደበት አይጠበቅምና ስለ አዛኝቷ ትንሽ ትህትና እንላበስ ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን።

  11. esu yawkal October 15, 2017 at 9:50 am Reply

    min yilutal?? eotc tv endih azig bemadreg hizbe mimenun le kalawadi tv eyegeberut nw……hi bay atwal esachew

  12. degu October 29, 2017 at 12:47 pm Reply

    atikededu

Leave a reply to Anonymous Cancel reply