ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት: ምክትል ሥራ አስኪያጅ ይሾማል

 • የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ሓላፊ ርእሰ ደብር መሓሪ ኃይሉ ተመረጡ
 • የሥልጣነ ክህነትና ሞያዊ አግባብነት መመዘኛዎቹ ተሟልተው አልታዩም፤”/አስተያየት ሰጭዎች/

†††

ተሿሚው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅርእሰ ደብር መሐሪ ኃይሉ

ቋሚ ሲኖዶስ፣ ዛሬ፣ ረቡዕ መስከረም 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ባካሔደው ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው፣ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ የመረጠ ሲኾን፤ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሚፈረም ደብዳቤ እንደሚሾም ተገልጿል፡፡

የምክትል ሥራ አስኪያጁ ምርጫና ሹመት፣ ባለፈው ዓመት ሐምሌ 9 ቀን፣ ለደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስነት በተሾሙት የቀድሞው ምክትል ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ(ፊት ዶ/ር አባ ኃይለ ማርያም መለሰ) ቦታ ለመተካት የተደረገ ነው፡፡

ተሿሚው ምክትል ሥራ አስኪያጅ፥ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 41 ንኡስ አንቀጽ 3 መሠረት፣ የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ለቋሚ ሲኖዶሱ ካቀረቧቸው ሦስት ዕጩዎች መካከል የተመረጡ እንደኾኑ ተጠቅሷል፡፡

በዕጩነት የተጠቆሙት ሦስቱ ተወዳዳሪዎች፥ የአልባሳት ማደራጃና ምርት ሥርጭት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበብ ምናሴ ወልደ ሐና፤ የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ሓላፊ ርእሰ ደብር መሐሪ ኃይሉ እና የውጭ ግንኙነት መምሪያ ጸሐፊ መጋቤ ሀብታት ቃለ ወንጌል ታደሰ ሲኾኑ፤ ርእሰ ደብር መሐሪ ኃይሉ መመረጣቸው ታውቋል፡፡

በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጠቋሚነት፣ በቋሚ ሲኖዶሱ ለምክትል ሥራ አስኪያጅነት የተመረጡት ርእሰ ደብር መሐሪ ኃይሉ፣ በቅዱስ ፓትርያርኩ በሚፈረም ደብዳቤ የሚሾሙ ይኾናሉ፡፡

በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ የሴሚናሪ ምሩቅና የሐዲሳት ትርጓሜ መምህሩ ርእሰ ደብር መሓሪ፣ ቀደም ሲል፥ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በስብከተ ወንጌል ክፍል ሓላፊነት፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የመንፈሳዊ ፍርድ ቤት ሰብሳቢነት፣ በትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅነት የሠሩ ሲኾን፣ በአኹኑ ወቅት ደግሞ የትምህርትና ማሠልጠኛ መመሪያ ዋና ሓላፊ ኾነው እየሠሩ ነበር፡፡

እንደ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሦስት ዓመት የሥራ ዘመን አላቸው፡፡ ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ተጠሪ በመኾን፣ በማይኖሩበት ወቅት ተወክለው ከመሥራት ባሻገር፣ ከብፁዕነታቸው፣ ተለይተው በመመሪያ የሚሰጧቸውን ተግባራት ያከናውናሉ፡፡

ይህም ኾኖ፣ በምርጫው ላይ አስተያየት እየሰጡ ያሉ ወገኖች፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ በመመዘኛነት ያስቀመጣቸው ድንጋጌዎች በተሟላ መልኩ አልታዩም፤ ሲሉ ተችተዋል፡፡ ተሿሚው ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣ ሥልጣነ ክህነት እንደሌላቸው በቀዳሚነት የሚያነሡት ተቺዎቹ፣ ከአስተዳደር ብቃትና ችሎታ አንጻርምበዘመናዊ ትምህርት ያላቸው ዝግጅትና ሞያ መፈተሽ እንደነበረበት አስረድተዋል፡፡


ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 44 ንኡስ አንቀጽ 4፡- ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ፡- ሥልጣነ ክህነት ያላቸው ኾነው፣ በነገረ እግዚአብሔር ወይም በአንድ የጉባኤ ትምህርት የተመረቁ፣ በቂ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ያላቸውና በአስተዳደር ችሎታቸው ብቁ የኾኑ ሰዎችን በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ዕጩ በማድረግ በቋሚ ሲኖዶስ ያስመርጣል፡፡


ጠቅላይ ጽ/ቤቱ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን የሥራ አስፈጻሚነትና የአስተዳደር ተግባር በማእከልነት የሚያከናወን ከፍተኛ አካል እንደመኾኑ፣ በምክትል ሥራ አስኪያጅነት የሚቀመጠው ሓላፊ፦ ከቤተ ክርስቲያን ትምህርት በተጨማሪ፥ በሥራ አመራር፣ በገንዘብና ንብረት አስተዳደር እንዲሁም በውስጥና በውጭ አካላት ግንኙነቶች፣ ሞያዊ ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል በቂ ልምድና የተግባቦት ክህሎት ቢኖረው እንደሚመረጥ ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ አኳያም፣ “የሌሎቹ ዕጩዎች የትምህርት ዝግጅትና የሥራ ልምድ በአንፃራዊነት ተመራጭ ስለሚያደርጋቸው ቢጤን የተሻለ ነው፤” ብለዋል፡፡

በአስተያየት ሰጭዎቹ እንደተገለጸው፥ በተወዳዳሪነት የቀረቡት የአቋቋምና የቅኔ ባለሞያው መጋቤ ጥበብ ምናሴ ወልደ ሐና፣ በሥራ አመራር የኹለተኛ ዲግሪ ምሩቅ ሲኾኑ፤ በሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ በስታቲስቲክስ ክፍል ሓላፊነት፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰው ኃይል አስተዳደር ሓላፊነት፣ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ ዲንና በሊቃውንት ጉባኤ አባልነት ሠርተዋል፡፡ መጋቤ ሀብታት ቃለ ወንጌል ታደሰም፣ በጉጂ ሊበን ቦረና ሀገረ ስብከት በሥራ አስኪያጅነት፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ በጀትና ሒሳብ መምሪያ ምክትል ሓላፊነትና በሕንፃዎችና ቤቶች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መሥራታቸው ተመልክቷል፡፡

Advertisements

2 thoughts on “ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት: ምክትል ሥራ አስኪያጅ ይሾማል

 1. Anonymous October 5, 2017 at 9:12 am Reply

  እነኚህ ሰዎች ምን መሆናቸው ነው ሁሉንም እነሱው ጠቅለው ያዙት እኮ ቁልፍ ቦታዎችን ሁሉ እነርሱው ብቻ ተቆጣጥረው የፈለጋቸውን ያለ ከልካይ ያተራምሳሉ

  • Anonymous October 7, 2017 at 12:38 pm Reply

   Good news!
   Our beloved father Aba Serekebirhan
   Woldesamuel haw appointed as a head of the Education and Training Department . He was working in that place before he had taken the office of his holiness. Father Serekebirhan has been fighting against the church corrupters and the evil act of Mk. Last year, when he took the office of his holiness, he had made a strategic plan for his holiness. but he was removed from that office by the evil advice of Nbured Elias ,Aba Kaletsidk and Muse Because they do know the strategy is going to completely blocked them their business (which is corruption)
   Howeve, Father Serekebirhan has been working in the department of Likawunt Gubae( as a member of the scholars) for the last eleven months.
   we heard that father Aba Serekebirhan woldesamuel is going to release two new books very soon.
   We expect from these books something new.
   Dear father please keep going strongly against the corrupters. As you said it in your speech in 2007 in the assembly meeting, the big problem of the church is not only MK but the leadership of the church must be changed

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: