ፓትርያርኩ: የማኅበረ ቅዱሳን ዓመታዊ ሪፖርት በአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ እንዳይቀርብ ትእዛዝ ሰጡ

 • ተወካዮቹም፣ በአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ እንዳይሳተፉ ከለከሉ
 • ማኅበሩ፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ እንደተጠየቀው፣ ሪፖርቱን በሐምሌ ልኮ ነበር
 • ላለፉት 25 ዓመታት፣ በአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊነት እየተካፈለ ቆይቷል
 • የቴሌቭዥን ፕሮግራሙ እንዲታገድ ከመንግሥት ደብዳቤ አምጥቻለሁ፤” (ብፁዕ አባ ማርቆስ)
 • “ጥቂት አባቶችን እየለዩ መምከራቸው ለሲኖዶሳዊ አንድነቱ አደጋ ነው፤” (ብፁዓን አባቶች)

†††

his-holiness-abba-mathias

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አባ ማትያስ፤ በ2007 ዓ.ም. በተካሔደው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 33ኛው ዓመታዊ ስብሰባ መክፈቻ ‘ቃለ ምዕዳናቸው’፥ ቤተ ክርስቲያን በአንድ ማኅበር ቅኝ እንደተገዛች በመግለጽ ቅስቀሳ ያደረጉበት የእልከኝነት ገጽታቸው ይህን ይመስል ነበር፤ ጥቅምት 6 ቀን በሚጀምረው የዘንድሮው 36ኛ ዓመታዊ ስብሰባም፣ የማኅበሩ ሪፖርት እንዳይቀርብና ተወካዮቹም እንዳይሳተፉ በመከልከል መሰል ቅስቀሳ ለማሰማት እየመከሩ ይገኛሉ፡፡ አጠቃላይ ጉባኤውን የማዘጋጀት ሓላፊነት ያለበት ጠቅላይ ጽ/ቤቱ እና ተጠሪ የኾነለት ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ ለዚህ ዓይነቱ ዓምባገነናዊና ሕገ ወጥ አካሔድ የሚኖራቸው አያያዝና ምላሽ ምን ይኾን???

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤትና መላው አህጉረ ስብከት፣ የየዓመቱን የሥራ ፍሬያቸውን በሚያቀርቡበት፣ ተሞክሮዎችን በሚለዋወጡበትና በዕቅዶች ላይ በሚወያዩበት የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 36ኛ ዓመታዊ ስብሰባ ላይየማኅበረ ቅዱሳን ሪፖርት ቀርቦ እንዳይሰማ፣ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ማትያስ ትእዛዝ ሰጡ፡፡

ፓትርያርኩ ትእዛዙን የሰጡት፣ ዛሬ፣ ዓርብ፣ መስከረም 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ፣ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ በጻፉት ደብዳቤ ሲኾን፤ የማኅበሩ ተወካዮችም በአጠቃላይ ጉባኤው ላይ እንዳይሳተፉ በትእዛዛቸው መከልከላቸው ተገልጿል፡፡

በመጪው ጥቅምት 6 እስከ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ የሚካሔደውን 36ኛ ዓመታዊ ስብሰባ፣ ፓትርያርኩ በርእሰ መንበርነት፣ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በምክትል ሰብሳቢነት የሚመሩትና፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና የድርጅት ሓላፊዎች፣ የ50 አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፣ የካህናት፣ የምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ልኡካን፤ በድምሩ ከ600 ያላነሱ ጉባኤተኞች የሚካፈሉበት፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ስብሰባ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንም፣ ላለፉት 25 ዓመታት በአመራርና በአስፈጻሚ አካሉ እየተወከለ ሲሳተፍበት ቆይቷል፡፡

እንደ አህጉረ ስብከቱ ኹሉ ማኅበረ ቅዱሳንም፣ ለአጠቃላይ ጉባኤው የሚቀርበውን የበጀት ዘመኑን የክንውን ሪፖርት እንዲልክ፣ ባለፈው ዓመት ሰኔ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ እንደተጠየቀና የተሳትፎ ጥሪ ደብዳቤም እንደ ደረሰው ተገልጿል፡፡ ጥሪውን በመቀበል፣ ሪፖርቱን ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ በሐምሌ ወር መላኩንና እንደተለመደው፣ በጉባኤው አዘጋጅ አካል፣ ከአህጉረ ስብከቱ ሪፖርት ጋራ በአንድነት ተጠናቅሮ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ እንዲቀርብ ዝግጅቱ ተጠናቆ እንደ ነበር ተመልክቷል፡፡

ይኹንና ማኅበሩ፣ “ድርጅትም መምሪያም አይደለም፤” ያሉት ፓትርያርኩ፣ ዓመታዊ የአገልግሎት ክንውኑ፣ የብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት አካል ኾኖ እንዳይቀርብ፤ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያም፣ ለዓመታዊ ስብሰባው በሚያሳትመው የዐዋጅ ነጋሪ” መጽሔት እንዳያካትተው መከልከላቸው ተጠቁሟል፡፡

ፓትርያርኩ፣ በትላንትናው ዕለት የጠቅላይ ጽ/ቤቱን ሓላፊዎች በመጥራት፣ ትእዛዙን በቃል ሰጥተው የነበረ ቢኾንም፣ በዛሬው ዕለት በጽሑፍም ማሳወቃቸው ነው የተጠቀሰው፡፡

ከትእዛዙ ጋራ በተያያዘ፣ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የብዙኃን መገናኛ አገልግሎት ድርጅቱ የቦርድ ሰብሰቢ ብፁዕ አባ ማርቆስን እንዲሁም፣ በቅርቡ የተሾሙ አራት ኤጲስ ቆጶሳትን በመጥራት አስቀድመው መምከራቸው ታውቋል፡፡

የማኅበሩ የአሌፍ ቴሌቭዥን ጣቢያ ፕሮግራም እንዲታገድ ለቋሚ ሲኖዶስ አቅርበውት የነበረው አጀንዳ ተቀባይነት በማጣቱ በራሳቸው እገዳ ቢያስተላልፉም፣ ሳምንታዊ ሥርጭቱ ሳይቋረጥ ቀጥሏሎ፤ በአንጻሩ ጠንካራ ዓለም አቀፍ ተቃውሞና ውግዘት እየወረደባቸው ይገኛል፡፡ በዚህም ያልተገሠጹት ፓትርያርኩ፣ ዛሬም ቋሚ ሲኖዶሱን መሰብሰብና ማማከር ሳያስፈልጋቸው እገዳንና ክልከላን በላይ በላዩ ከማዘዝ አልታቀቡም፡፡

በዛሬው ዕለት መካሔድ የነበረበትን፣ የቋሚ ሲኖዶሱን ሳምንታዊ ስብሰባም በማስታጎል ነው፣ ከእነ ብፁዕ አባ ማርቆስ ጋራ የመከሩበትን ሌላ የእገዳ ትእዛዝ በማኅበሩ ላይ ያስተላለፉት፡፡ ከቋሚ ሲኖዶሱ አባላት ውጭ የኾኑና የተወሰኑ አባቶችን በመያዝ በተመሳሳይ ሕገ ወጥ አካሔድ መምከራቸውን ከቀጠሉም፣ ለአጠቃላይ ሲኖዶሳዊ አንድነቱ አደጋ እንደሚጋረጥ፣ ብፁዓን አባቶች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ – በምክሩ የተሳተፉትን አራት ብፁዓን አባቶች በስም በመጥቀስ፡፡

በምክሩ ወቅት፣ “በአንድ ቤት ኹለት ጣቢያ አይኖርም፤” ያሉት ብፁዕ አባ ማርቆስ፣ የማኅበሩን ፕሮግራም ለማሳገድ፣ ከመንግሥት ደብዳቤ ይዘው እንደመጡ ተናግረዋል፤ ተብሏል፡፡

በሢመተ ፕትርክናቸው ቃል የገቡለትን፣ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ለማጥፋት በሰጡት መመሪያ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በጥናት የተደገፈ እንቅስቃሴ ከተጀመረ በኋላ፤ በአማሳኞች ምክር የተደናገሩትና የተጠለፉት ብፁዕ ወቅዱስ አባ ማትያስ፥ የለውጥ ሒደቱን ያመከኑትና ቤተ ክርስቲያን በቅኝ ግዛት እንደተያዘች በመጥቀስ ፀረ ማኅበረ ቅዱሳን ቅስቀሳ ያካሔዱትበ2007 ዓ.ም. በተደረገው የአጠቃላይ ጉባኤው 33ኛው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ዛሬም በሰጡት ትእዛዝ፣ የማኅበሩ ተወካዮች ወደ አጠቃላይ ጉባኤው እንዳይገቡና ምንም ዓይነት ቀረፃና ዶክመንቴሽን እንዳይኖር በመከልከል፣ መሰል ፀረ ማኅበረ ቅዱሳን ዲስኩር ለማሰማት እየተሟሟቁ እንዳሉ ተጠቁሟል፡፡

በዚህም፣ ብፁዕ አባ ማርቆስን ጨምሮ በምክሩ ከተሳተፉት አራት ዐዲስ ተሿሚዎች መካከል፣ የአዊ ዞን ጳጳስ ብፁዕ አባ ቶማስ፣ አለንልዎት፤ ደማችን ይፈሳል፤ ባዮች ኾነው እንደተገኙ ተነግሯል፡፡

የተቀሩት ሦስት የምክሩ ተሳታፊዎች፡- የጋምቤላና ደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ጳጰስ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል፣ የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ እና የሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ የሚይዙት አቋምም ውሎ አድሮ የሚታይ ይኾናል፡፡

በቃለ ዐዋዲው የሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያት አጠቃላይ መዋቅር መሠረት፣ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ቀጥሎ የሚገኝና ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ የኾነ ከፍተኛ አካል ነው፡፡የተልእኮውን ያኽል አልሠራበትም እንጂ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ እንደተደነገገው፤ የቤተ ክህነታችን ጠቅላላ የሥራ ሒደት የሚገመገምበት፣ በመንፈሳዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ኹሉ ውሳኔ የሚተላለፍበት ከፍተኛ መድረክም ነው፡፡

eotc top down org str

በዓመት አንድ ጊዜ በጥቅምት ወር የሚሰበሰብ ሲኾን፤ የየዓመቱን የሥራ ፍሬና የወደፊት ዕቅድ የሚያስረዳ ሪፖርት በማዳመጥ የውሳኔ ሐሳብ ያቀርባል፤ የጋራ መግለጫ ያወጣል፤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ሲጸድቅም፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ አማካይነት ለአህጉረ ስብከት እየተላለፈ፣ የበጀት ዘመኑ የሥራ መመሪያ ኾኖ ያገለግላል፡፡

በዓመታዊ ስብሰባው የሚቀርበው ሪፖርት፥ ስብከተ ወንጌልን፣ ሰበካ ጉባኤን፣ የአብነት ት/ቤትን፣ የሰንበት ት/ቤትን፣ የፐርሰንት አሰባሰብንና የራስ አገዝ ልማትን በማስፋፋትና በማጠናከር አህጉረ ስብከት ያደረጉትን እንቅስቃሴ፣ የተመዘገበውን ውጤትና ያጋጠመውን ችግር ያካተተ ነው፡፡

ከአህጉረ ስብከቱ ጋራ በየደረጃው ተናብቦና ተቀናጅቶ የሚያገለግለው ማኅበረ ቅዱሳንም፤ በስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብር፣ በቅዱሳት መካናትና በአብነት ት/ቤቶች የድጋፍ ፕሮጀክቶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት የትምህርተ ወንጌል አገልግሎት…ወዘተ. ያከናወናቸው ተግባራት ከገቢና ወጪ መግለጫው ጋራ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት ተካቶ እንደሚቀርብ ይታወቃል፤ ጉባኤተኛውም፣ የጋለ ድጋፉን እየሰጠውና እያበረታታው ቆይቷል፡፡

Advertisements

20 thoughts on “ፓትርያርኩ: የማኅበረ ቅዱሳን ዓመታዊ ሪፖርት በአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ እንዳይቀርብ ትእዛዝ ሰጡ

 1. Amanuel September 30, 2017 at 9:21 am Reply

  አሁን አሁን በእውነት እያሳዘኑኝ መጡ ምክንያቱም በክፉ የጠበኝነት እና የጥላቻ መንፈስ የግርግሪት ታስረዋልና ። ከዚህ ማሰሪያ ይፈታቸው ዘንድ እውነተኛ አባቶች ያስፈልጓቸው ነበር እንዳለመታደል ሁኖ እርሳው ደጋጎቹን አባቶች እና ስነ ምግባር ያላቸውን ልጆቻቸውን ባይኔ አልይ አሉ። ይሄ ትልቁ የተጣባቸው ክፉ ደዌ ነው። ‘ የተጠጓቸው ሌሎቹ ደግሞ የጠሏቸውንና በጥቅማቸው የመጡባቸው የሚመስላቸውን በርሳቸው እጅ ለመምታት ከንቱ ወሬ የሚያሾከሹኩላቸው ናቸው። በነጋ በጠባ ተንኮልና ነገር ይዘው እየመጡ እዚህች ላይ ይፈርሙ እያሉ ከሚጠመዟቸው ክፉ መካሪዎቻቸው የተነሳ ደግ ነገር ክውስጣቸው እየተእየተሰደደ የፀበኝነት የምቀኝነት የተንኮል የነገረሰሪነት የጎጠኝነት ታንከር ሆነዋል ። – ታድያ እኒህን ሰው ለዚህ ለሞት ከተሰጠ ሕይወታቸው ማን ይታደጋቸው? አንዳንዴ ያናድዱኝና እሰይ ይበላቸው ባልጠፋ መልካም ሰው ከነኚህ ነገረ ሰሪዎች ለምን ተጠጉ? ይኸው ክሰሱ ሲሏቸው ሲከስሱ አግዱ ሲሏቸው ሲያግዱ ያሉበትን ታላቅ ቦታ ዘንግተው የነገረ ሰሪዎች ተላላኪ ሆነው አረፉት ብዬ እበሳጫለሁ። — አንዳንዴ ደግሞ ያሳዝኑኝና እነኚህ የከበቧቸው ክፉ ሰዎች ሰውየውን ሊያሳብዷቸው እንደሚችሉ ሳስብ ይጨንቀኛል። የሚጨንቀኝ በዚህ አካሄድ ከቀጠሉና የማይቀረውም እብደት ከመጣ ለሰሚውም ይከብዳልና በዓለምም በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ኢትዮጵያዊዉና ብቸኛውና በክፉ ወዳጆቻቸው ሰዎች ምክር ያበዱ የቤ/ክ መሪ ተብለው በታሪክ ሲወሱ መኖራቸውን ሳስብ ይጨንቀኛል ።
  አሁን ቆም ብለው ነገሮችን ማሰብ ይጠቅባቸው ይመስለኛል። ነገረ ሰሪዎችን ከራሳቸው ማራቅና በጎውን ሊመክሯቸው፣ ሊፀልዩላቸው ፣ትምክህታቸውን በእግዚአብሔር ላይ እንዲያደርጉ የሚያሳስቧቸው፣እለት እለት ነገረ እግዚአብሔርን እንዲያስቡ የሚያበረቷቸው፣ መልካም የሚያደርጉ ልጆቻቸውን ከማሳደድ ተቆጥበው እንዲያፈቅሯቸው በስራቸውም እንዲደግፏቸው የሚያነቋቋቸው፣ ጠላትን እንኳ እንድንወድ እንጂ ልጆቻችንን እንድንጠላ የታዘዝንበት የወንጌ ቃል የለንም እያሉ
  የሚገስጿቸው ፣ “አለንልዎ ደማችን ይፈሳል” የሚለው ልወደድ ባይና የውሸት አርበኛ ጉራ እንደማይጠቅምና እንዲህ ዓይነት ጉረኛ ሰው የመከራ ጊዜ ወዳጅ ሊሆን እንደማይችልና ለጊዜአዊ ጥቅም ሲል የሚያገሳ መሆኑን የሚያስታውስ ፣ – በአጠቃላይ በፀሎት ጥሙድ ሆነው በክፉ መካሪዎች ምክንያት ያጡትን ፍቅረ ሰብ እና ሞገሰ እግዚአብሔር ያገኙ ዘንድ ቀሪዋን ጥቂት እድሜአቸውን እግዚኦ መሃረነ ወተሰሃለነ እያሉ ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ስራ ሰርተው እንዲያልፉ የሚመክሯቸው ደጋግ አባቶችን ደጅ መጥናት ይጠበቅባቸዋል። “”””” እንጂ በ77 ዓመት እድሜ እንደ 18 ዓመት ጎሩምሳ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት የጤና አይመስለኝም ያ ከላይ ያልኩትና የፈራሁትም(እብደት) ምልክቱ ይመስለኛል እና ያስቡበት። በቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት የሰው እድሜ በ4 ክፍል ይመደባል። የነፋስ (የልጅነት):የእሳት(የወጣትነት) :የውሃና (የጉልምስና) የመሬት(የእርግና) ተብሎ። በመሬት እድሜ ላይ እሳት ከመሆን ያድነን !!!!!

 2. Anonymous September 30, 2017 at 12:13 pm Reply

  ስያስጠላ

 3. Sabawi mengesha September 30, 2017 at 1:08 pm Reply

  Aba matiyas is not fit to lead this great church. He has mental problems. Really he had mental health problem. Alzheimer disease, dementia and lot more.

  How can the church listen to a mad man? Just mad. That is it

 4. Anonymous September 30, 2017 at 4:06 pm Reply

  he is not mentally sick ,he is restless and mad because of the current anti tehadisso movement and the winning sprite of Mahiberkidusan> I think he isn’t from orthodox church ,he should go like Begashaw and Asged ,sorry to say this

 5. Anonymous September 30, 2017 at 8:57 pm Reply

  ፓትርያርኩ፥ የማኅበረ ቅዱሳን ዓመታዊ ሪፖርት በአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ እንዳይቀርብ ትእዛዝ ሰጡ
  ቅዱስ አባታችን በቅድሚያ ቅዱስነትዎ ቡራኬ ይድረሰን
  እድሚዎን ያርዝምልን
  ቅዱስ አባታችን መናፍቃንን እቃወማለሁ እያለ ከመናፍቃን በላይ ያሬዎስ ስራ የሚሰረው ቅዱሣን ባይማህበር
  የወሰዱት እርምጃ ታሬክ ይዘክ ረወታል ነጋዴ ማህበር፣።

 6. Anonymous September 30, 2017 at 9:10 pm Reply

  በዚህም፣ ብፁዕ አባ ማርቆስን ጨምሮ በምክሩ ከተሳተፉት አራት ዐዲስ ተሿሚዎች መካከል፣ የአዊ ዞን ጳጳስ ብፁዕ አባ ቶማስ፣ “አለንልዎት፤ ደማችን ይፈሳል፤” ባዮች ኾነው እንደተገኙ ተነግሯል፡፡

  የተቀሩት ሦስት የምክሩ ተሳታፊዎች፡፡ የጋምቤላና ደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ጳጰስ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል፣ የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ እና የሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ የሚይዙት አቋምም ውሎ አድሮ የሚታይ ይኾናል፡፡
  ስማቸውን አታንሱ ማቅአውያን ድሮማ የዘራችሁትን ነው የምታጭዱ
  ከዚህ በላይ ስማቸውን ያነሣችሁት ብፁአን ጳጳሣት ላገልግሎት እደይሰየሙ ፈተና ሁናችሁባቸው እደነበር ታውቁታላችሁ
  ስለዚህ ይደግፉናል ብላችሁ ታስባላችሁ እድትፈርሱ ይጥራሉእጂ ይገባችሁአል የዘራችሁትን አጬዱ
  የርቅ የሰላም ጠላቶ ች ናችሁና።

 7. Anonymous October 1, 2017 at 5:30 am Reply

  ማኅበረ ቅዱሳን ማለት ከእያንዳንዱ አባላት ያለው ሀሳብ ማለት ነው ። ስለዚህ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ማኅበረ ቅዱሳንን አፍርሱት የሚሉት እንዴት ነው። እኛ የማኅበረ ቅዱሳን አባል ካልሆንን የማኅበረ ሰይጣን አባል ሁኑ እያሉ እንደሆነ የሚመክራቸው አባት ጠፋ እንዴ!!! እግዚአብሔር አምላካችን የትለንትናውን ዘመን ማለትም ከእግዚአብሔር ጋር ያልነበረነውን ዘመን በህይወት ዘመናችን አትቁጠረው። ለወደፊት ከእግዚአብሔር ጋር አብዝተን የምንገናኝበት ዘመን፣ እንዲሁም ለብፁዕ አቡነ ማትያስ ንፁሕ ልቡና ያድላቸው ዘንድ የእርሱ የአምላካችን የአባታዊ መልካም ፈቃድ ይሁን። አምላካችን ሆይ የቀደመውን በደላችንን አታስብብን አሜን!!!

 8. Toto October 1, 2017 at 4:40 pm Reply

  He is a cadre and non believer hurting on the chair to district the church

 9. Anonymous October 1, 2017 at 7:33 pm Reply

 10. Anonymous October 1, 2017 at 7:35 pm Reply

 11. Anonymous October 2, 2017 at 8:29 am Reply

  አባ ማትያስ አሜሪካዊ ነው። ተልዕኮ ሊኖረው ይችላል።ከመንግስትም አይግባባም። የሰውየው ነገር በቀላል መታየት የለበትም።ንቡረእድ ኤልያስ ከሰዉየው ጋር ያለው ሚስጢር ያልታወቀ እስከ አብሮ መተኛት የዘለቀ ግንኙነት ለወደፊት ግልጽ የሚሆን ሆኖ ሰዉየው ይሸታል ሙጃ ነው የሚሉ አባባሎች ምልክት አላቸው። ሰውየው እንደራሴ ይደረግለት!!!

 12. kefyalew Endale October 2, 2017 at 9:19 am Reply

  Mahibere Kidusanene maferes ayichalim Mikiniyatum fetary be Erasu gize yasenesawum fim esat new. tehdeson ena menfikin eyakatele yale FIm ESAT

 13. Anonymous October 2, 2017 at 10:26 am Reply

  We pray that God protects our church. What we hear and see everyday is not a surprise. It is the sign of the coming of the dooms day. We should be aware and be prepared that even the church leaders are failing to keep the word of God and serve God with peaceful mind, clean heart and devotion.

  We see and hear that the church administration is full of thieves, money lovers and all kinds of useless, incompetent and selfish people who have no belief at all. They cover themselves in robes but they are wolves inside. They never care for the church, for the people and for the gospel of God.

  The stand of Aba Matiyas (I don’t even want to call him father; I don’t want to have such an devilish father) is not good.

  The church followers inside and outside should careful think and be prepared to prevent such destruction of the church. It needs an urgent call of action; otherwise the church will soon be disintegrated.

  The intention of this evil-spirited man and his followers is to deny and destroy the work of the true sons and daughters of the church “Mahbere Kidusan).

  I am really surprised to see the decay of the church administration.

  Where are we going to? Will there be any followers of the church in the future? Can we really trust priests, deacons and fathers?

  Does the church has quality assurance for the ordinance of church servants?

  I am really sorry for the Synods. What are they waiting for? What are they doing there?

  Please let’s all pray to God that He corrects all the wrong-doings in the church administration.

  I plea to all church followers abroad and in the country to watch out what is going in within each single parish church. Watch out the deeds of everyone in the church.

  God saves our church. Amen.

 14. Anonymous October 2, 2017 at 1:17 pm Reply

  አሁንስ እኚህ ፓትርያርክ ጀገኑ ይህን በላዔ ሰብእ ማሕበር ማጥፋቱ መልካም ነው፡፡

 15. Anonymous October 2, 2017 at 2:38 pm Reply

  አቤቱ ይቅር በለን

 16. Anonymous October 2, 2017 at 9:03 pm Reply

  አንድ ጥያቄ አለኝ፣ ማህበረ ቅዱሳን የሚጮኸው የራሱ ጥቅምሲነካበት ብቻ ነው? ምነው ሕዝብ በጥይት ሲቆላ፡ በስደት ሲታረድና በረሐብ ሲያልቅ ፍርድ ተዛብቷል፣ ቤተክርስቲያን ከተገፋው ጋር መቆም አለባት፣ ዝም ማለት የለባትም ብሎ ለምን ድምጹን አላሰማም? አይበርዳችሁ፣ አይሞቃችሁ!! የራሳችሁ ጥቅም ሲነካ ብቻ ዘራፍ ትላላችሁ።

  እናንተ የምትንጫጩት ማህበረ ቅዱሳን ሲነካ ብቻ ነው።
  እውነት የሚናገረውን ፖለቲከኛ ብለው ትፈርጃላችሁ። እውነት መናገር ፖለቲካ አይደለም። ሆዳችሁን ትታችሁ ለእውነት ቁሙ። ዝም አትበሉ!!

  እውነት እውነት ናት። እናንተ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ማሕበሩን የምታስቀደሙ፣ ከእናንተ ጋር ያልሆነን ልዩ ስም እየሰጣችሁ የምታስጠሉ፣ ሀገር ሲጠፋ እያያችሁ እንዳላየ፡ መንግሥትየራሱን ካድሬዎች አስገብቶ ቤተ ክርስቲያን የህዝብ እንባ አባሽ ከተገፋ ጋር መቆም ሲገባት ልማታዊ ክርስትናን ስትሰብክ ዝም ብሎ “እኛ ጋር እስካልመጣ ምንአሻን ክርስትናና ፓለቲካ አብሮ አይሄድም” በማለት በተዘዋዋሪ መንገድ የሃሰትተባባሪ አድር ባዮች ሆናችሁ ኖራችሁ? አሁንቲቪ ጣቢያ ታገደብን ብሎ ታላቅ የዶግማና ቀኖና ጥሰትእንዳለ አድርግ ነገሮችን አንሸዋርሮ ማቅረብ ብዙ አያሳምንም።

  ይልቁስ መጽሐፉ እንደሚለን ክፉትን ጭካኔን በወገናችሁላይ እየደረሰ ያለውን መከራ ጥሉ። ቤተ ክርስቲያናችሁን ከማሕበራችሁ በማስቀደም (በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ) የሚደረገውን ግፍ ፣ ፍቅረ ነዋይ መውደድ፣ ዘረኝነትን ማስፋፋት ተቃወሙ። ሌላ ጊዜ ዝም በማለት የእናንተ ጥቅም ሲነካ ብቻ መጮህ አቁሙ። በጥንቃቄ ነው የምንጓዘው የሚል የአድርባይነት አካሄድ አቁሙ። ፈሪ ሁለቴ ይሞታል የሚባለው እንዳይደርስባችሁ ይሁን።

  “ከአህጉረ ስብከቱ ጋራ በየደረጃው ተናብቦና ተቀናጅቶ የሚያገለግለው ማኅበረ ቅዱሳንም፤ በስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብር፣ በቅዱሳት መካናትና በአብነት ት/ቤቶች የድጋፍ ፕሮጀክቶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት የትምህርተ ወንጌል አገልግሎት…ወዘተ. ያከናወናቸው ተግባራት ከገቢና ወጪ መግለጫው ጋራ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት ተካቶ እንደሚቀርብ ይታወቃል፤ ጉባኤተኛውም፣ የጋለ ድጋፉን እየሰጠውና እያበረታታው ቆይቷል፡”

  ለመሆኑ የሰንበት ት/ቤት ማደራጃ ሥር ከሆኑ ለምን ለብቻቸው የአመራር አካሎቻችሁን ለስብሰባ የምትልኩት? እናንተ ለብቻቸሁ የ ልማት ስብከተ ወንጌል ሪፖርት ለምን እንድታቀቡ ተደረጋችሁ? ፧ በሰንበት ት./ቤት ማደራጃ ሥር ከሆናችሁ ይህ ሁሉ አስፈላጊ አይደለም። ነገር ግን ማሕበረ ቅዱሳን የራሱ መንግሥት፣ የራሱ ሲኖዶስ የራሱን ወንጌል የሚያስፋፋ ድርጅት ነው። የቤተ ክርስቲያኗን መዋቅር የሚያከብረው ለእራሱ እስከተመቸው ድረስ ነው።
  አሁን ቴሌቪዥን ጣቢያ አታስተላልፉ ተብለው ትአዛዝ ከተሰጣቸሁ? ለምን ት ዕዛዝ አታከብሩም፧ ወይንስ ለእናንተ ሲሆን የተለየ ህግ አለ?

 17. Anonymous October 3, 2017 at 7:18 am Reply

  beneger hulu egziabher ayzengan

 18. Anonymous October 4, 2017 at 10:55 am Reply

  ማህበረ ቅዱሳን ሕንጸጻውና ሪፖርቱ ነው አንዴ! ማህበረ ቅዱሳን እኮ የአገልግሎት ማኅበርና አገልግሎቱ ነው፡፡ የቤተክርስቲያን አገልግሎት በሰዎች በጎ ፍቃድ ብቻ የሚመጣ አይደለም፡፡ አንድ ላይ መሥራት ለአገልግሎት ውጤታማነትና ስኬት ከዚያም ሲያልፈፍ ጥፋት ሲኖር ደግሞ ተጠያቂውን ለመለየት ይጠቅማል፡፡
  ብፁዕነታቸው እና ወሬ አቀባዮች ያልተረዱት ነገር ያለ ይመስለኛል፡፡ ለቤተክርስቲያን የሚያስቡ ና ያለምንም ሥጋዊ ጥቅም ጊዜውን፣ ገንዘቡን እና ዕውቀቱን በነፃ ለቤተክርሰቲያን አገልግሎት የሚሰጥ ትልውልድ ቤተክርስቲያ እንዲኖራት የማድረግ ዓላማ ያላቸው ከሆነ የሰንበት ትምህርት ቤት እና የማኅበረ-ቅዱሳን አገልግሎት በቅንጅትና በተመጋጋቢነት ሊከናወን የሚችልበትን አካሄድ መዘርጋት መቻል ነው፡፡
  ትውልዱ በቅድመ ዪኒቨርሲቲ እና ኮሌጅ ጊዜው የሰንበት ትምህርት ቤት አገልግሎት፣ ከዚያ ሲያልፍ ደግሞ የማኅበሩ አገልግሎት ሁኔታ ሁለት ወሳኝ የአገልግሎት ቦታዎች ናቸው፡፡ ከዚህ በአግባቡ ማለፍ ሲችል ትውልዱ በሰበካ ጉባኤና በሌሎች የቤተክረስቲያ የአገልግሎት ሁኔታዎች ውስጥ በዕውቀት ላይ ተመርኩዞ ሊጠቅምና ሊጠቀም የሚችለው፡፡
  እርሳቸው የሚያዩት አባሉ በራሱ ፍቀድ የሚያዋጠው ወርሐዊ አስተዋፅኦ እና ለገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች እርዳታ የሚመጣው ገቢ ለአጥቢያ ሊገባ ይችላል ከዚያም ፈሰስ እናገኛለን የሚል ግምት ይመስለኛል፡፡ ይሄ ግምት አሁን ምዕመኑ ያለበትን የግንዛቤ ደረጃ ካለማወቅ የሚመጣ ነው፡፡ አሁን ባለበት ስር የሰደደ የሙስና ሁኔታ ካልተሻሻለ ቀጣዩ ትውልድ ከሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዘለለ ምንም ዓይነት ገንዘብ በቤተክርስቲያን በኩል ለሚፈልገው አገልግሎት ይውልልኛ በማለት መስጠት የማይፈልግበት ጊዜ ይመጣል የሚል ሥጋት አለኝ፡፡
  በኔ እምነት አገልግሎቱ ቢስተካከልና ተደራሽነቱ ቢያድግ የማኅበረ ቅዱሳን መኖር አለመኖር ጥያቄ ሊሆን አይችልም የሚል ነው፡፡
  በአጠቃላይ አባታችን በቅድሚያ መሥራት ያለባቸውን ሥራ ቢሠሩ መልካም ነው፡፡ እግዚአብሔር የማሰቢያ ጊዜ ይስጣቸው፡፡

  • Anonymous October 8, 2017 at 11:37 am Reply

   ይህ የምርጥ ሌቦች ስብስብ ማህበር ማህበረ ሰይጣን እንጂ ማህበረ ቅዱሳን ያሚይስብል ምን ምልክት አለው ሀራ የተባለ ድህረ ገፅ አዘጋጅቶ ቤተክርስቲያን እና ለፍላጎቱ ተገዥ ያልሆኑትን መሪዎችና ንፁሃን ሰራተኞች በፖለቲካ ቅዠት ተውጦ በብሄር ጥላቻ ተነሳስቶ እራሱ ሳይገባው የዘረፋትን ቤተክርስቲያን እንደዘረፋ አድርጎ ሲሰድብ ቆይተዋል ከዚህ በኋላ መገበርያ መብላቱን ያቆማል ስዕለት መሰብሰቡን ያቆማል አባላቱን ባለ ሀብት ባለመኪና ባለ ድርጅት ያደረገ የሌቦች ስብስብ ማህበራ በሃራ ፀሀፊነት እዴሜውን ማርዘም በቃው ጤናና እድሜ ለብፁእ ወቅዱስ ፓትርያርክ አማትያስ እገሌ ወልደዎል እገሌ አጭበርብረዋል እያል ስም ማጥፋቱ እንደ እቃ ተቆጥረዋል የማህበረ ቅንቅናም ረዥም ምላስ ራ ተዋህዶ ቻው ያጠፋ በማስረጃ ሲገኝ ቤተክርስቲያንዋ በህግዋ ትቀጣለች እንጂ የነሱ ቀረርቶ ሞተ

   • Anonymous October 16, 2017 at 6:50 pm

    ማንን እንደቀጣች???

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: