የሰንደቅ ዋና አዘጋጅ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከቀረበበት የወንጀል ክሥ በነፃ ተሰናበተ

 • በፍትሐ ብሔሩ ክሥ፣ በተከሣሽ መከላከያነት የተቆጠሩት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በጽሑፍ የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል


journalist-firew-and-the-patriarch-aba-mathias

ሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከቀረበበት የስም ማጥፋት ወንጀል ክሥ በነፃ ተሰናበተ፡፡

ዋና አዘጋጁ አቶ ፍሬው አበበ፣ ከክሡ በነፃ የተሰናበተው፣ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው፣ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቂርቆስ ምድብ ኹለተኛ ወንጀል ችሎት፣ ዛሬ፣ ረቡዕ ጥር 17 ቀን ረፋድ በሰጠው ውሳኔ ነው፡፡

ፍ/ቤቱ በውሳኔው፣ ተከሣሹ የቀረበበትን የስም ማጥፋት ክሥ፦ በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች በበቂ ኹኔታ በመከላከሉ ጥፋተኛ እንዳልኾነ በመጥቀስ በነፃ እንዳሰናበተው ገልጿል፡- “ውሳኔው ሰፊና ረዥም ነው፤ ከመዝገብ ቤት መውሰድ ትችላላችኹ፤ በአጭሩ ግን፥ ተከሣሽ ለቀረበበት ክሥ፣ በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች ራሱን በበቂ ኹኔታ ተከላክሏል፤ ፍ/ቤቱም ይህን ተቀብሎ ጥፋተኛ አይደለም፣ ብሏል፤ ስለዚኽ በነፃ አሰናብቶታል፤ መዝገቡን ዘግተናል፡፡”

ጠቅላይ ቤተ ክህነት ክሡን የመሠረተው፣ ዋና አዘጋጁ፣ “ፓትርያርኩ: ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድህነት ስጋት” በሚል ርእስ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተጻፈውንና በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ ከሙስና፣ ብልሹ አሠራርና ከመናፍቃን ውስጣዊ ሤራ ጋራ በተያያዘ የሚታየውን ኹኔታ የሚተች ሒሳዊ አስተያየት በጋዜጣው በማተሙ እንደነበር ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡


የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ መኾኑን የሚናገረዉ ጋዜጠኛ ፍሬዉ አበበ፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት በዓለማዊ ፍርድ ቤት መከሠሡ የፈጠረበትን ስሜትም ገልጿል፡፡

«የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነኝ፤ በቤተ ክርስቲያን ትልልቅ አባቶች ጭምር የሚታወቅ ክሥ ዉስጥ ገብቼ በዚኽ ደረጃ መከሠሤ ለሞራሌ ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለብኝ ጉዳይ ነው፤ ምክንያቱም ይኼ በቀላሉ በይቅርታ መቀረፍ የሚችል ጉዳይ ነበር። አባቶች እንደመኾናቸዉ መጠን ሊሥጹኝም ይችሉ ነበር። በዓለማዊ ፍርድ ቤት ሙግት መግጠማቸው፤ እነርሱ ወደ ፍርድ ቤት የሚሔዱ ከኾነ እኔ ወደ ቤተ ክርስቲያን የምሔድበት ምን መሠረት አለኝ? የሚል የሞራል ጥያቄ ኹሉ አስከትሎብኛል፡፡» /ዋና አዘጋጁ ስለ ክሡ ሒደትና ስለ ውሳኔው፣ ለዶቼ ቬለ ራዲዮ ከተናገረው/


በተያያዘ ዜና፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ የ100 ሺሕ ብር የኅሊና ጉዳት ካሳ በመጠየቅ አሻሽሎ በመሠረተው የፍትሐ ብሔር ክሥ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ከተከሣሽ አራት የመከላከያ ምስክሮች መቆጠራቸው ግራ ቀኙን ሲያከራክር ቆይቷል፡፡

ይኹንና ችሎቱ፣ ከሕግ የእኩልነት መርሕና የተከሣሽ መብት እንዲኹም፤ ለፍትሕ ሊሰጥ ከሚገባው ከበሬታ አኳያቅዱስነታቸው ካሉበት ኾነው በጽሑፍ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ በመበየኑ፣ ተከሣሽ በጽሑፍ ያዘጋጃቸውን ጥያቄዎች ችሎቱ ከተመለከተ በኋላ፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ ለተከሣሽ በጽሑፍ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፤ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Advertisements

2 thoughts on “የሰንደቅ ዋና አዘጋጅ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከቀረበበት የወንጀል ክሥ በነፃ ተሰናበተ

 1. Lusif January 25, 2017 at 6:54 pm Reply

  I have a religion. I am not a religious person. I do not like to involve to much in the church rituals and organization. I have a 78 yrs Mom. I accompany her to a near by church, pray , comeback and do what I get to do for a living.
  I believe, the church has to withstand the test of time, so that it could come out strong and pure. One of the spiritual treasure of the church is patience, tolerance, forbearance and forgiveness. Judgement and triumph come from God himself.
  Now a days, the church has become a business center. Those who want the larger share of the business always quarll among themselves. Those who are pushed off from the larger share will get resentful. So, critisism, complain, gossip and what have you, would be common place like the secular political entities.
  I believe, the church’s focus need to be to clean out those greedy, irresponsible, worldly religious merchants of its house. Not those individuals who exposed the truth, with verifiable documents. That is what Jesus did. From my limited knowledge.
  I guess it is fair to compensate those who suffered undeservingly.
  The government, the church, the business, the industry and service centers… Kebeles, Gulit markte places, house hold , and else where is grievances and accusations. What is wrong with us?. Family against family, neighbours against neighbours,, community against community, society against society, citizens against government, political parties against political parties…. all theses phenomenon are really indications of the coming of the end of time. Is TPLF / EPRDF IS THE MESSANGER of destruction? The religious, social, political, economic and environmental look not good.
  In such bad time, where is the roll of religious institutions and leadership. Or believers are left with out a shepherd, to do what ever they can, with whatever they find.
  It looks like. We all be judged. Sooner or later each of us will collect what he/she deserves. This is inevitable and it is here, a few meters away. Let us be serious.

 2. ዳሞት January 26, 2017 at 3:29 am Reply

  1000000( አንድ መቶ ሺ) ብር የሕሊና ካሳ ያስፈልጋቸዋል ብሎ መጠየቅ ያሳፍራል። ለመሆኑ በገንዘብ ነው ህሊና የሚካሰዉን? ይህን የገንዘብ ካሳ መጠየቅ ራሱ በእግዚአብሔር ቤት ለምን እንደቁሙ የሚናገር ነው። በቤተ ክርስቲያን ላይ በመጽሐፍ ታትሞእምነቷ ያልሆነው እምነቷ ተብሎ ሲታወጅ፣ አሥተምሮዋ ያልሆነው የክህደት ትምህርት በአውደምህረቷ ሲታወጅ ምንም አላሉም፤ አላደረጉም። ብዙ የሚነገር ቢኖርም በዚሁ ላብቃ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: