የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥንን/ኢኦተቤ-ቴቪ/EOTC TV/ ፕሮግራሞችን ይከታተሉ

 • ስብከተ ወንጌል – ትምህርተ ሃይማኖት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ – ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
 • ነገረ ቅዱሳን – ቅኔና ዜማ – የግእዝ ትምህርት – ከአበው አንደበት – እንወቃቸው…
 • ዐውደ ተዋስኦ – አገልግሎትና አገልጋዩ – የቤተሰብ ጊዜ – ለወራዙት – ለሕፃናት…
 • የቤተ ክርስቲያን እጆች – ታሪክና ቅርስ…

*                    *                    *

eotc-tv
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት አደረሳችኹ፤ አደረሰን፡፡

ካለፈው ዓመት ሰኔ አንሥቶ በሙከራ ሥርጭት የቆየው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን/ኢኦተቤ-ቴቪ/EOTC TV/፤ ወደ መደበኛ ሥርጭት መሸጋገሩ፣ ትላንት፣ ታኅሣሥ ፳፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም.፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በተከናወነ የማስጀመርያ መርሐ ግብር ተገልጿል፡፡

መደበኛ ሥርጭቱ ከ27 ያላነሱ የፕሮግራም ዓይነቶችን ያካተተ ነው፡፡ የእያንዳንዱ ፕሮግራም፦ ዓላማ፣ ይዘት፣ አቀራረብ፣ የቆይታ ጊዜ፣ ታላሚ ተመልካች(target audience) እና ፈጻሚ አካል በዝርዝር ተለይቷል፡፡ ይህንንም ለሥራ ዝግጁ በማድረግ በኩል ሓላፊነቱ፥ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የብዙኃን መገናኛ አገልግሎት ድርጅቱ የቦርድ አባላትና የሚዲያ ባለሞያዎች የተዋቀሩበት የዓይነትና የይዘት አሰናጅ ኮሚቴ ድርሻ ነበር፡፡

በመደበኛ ሥርጭቱ ጅማሬ የአየር ሽፋን የሚሰጣቸው ፕሮግራሞች፦ ስብከተ ወንጌል፣ ትምህርተ ሃይማኖት ዘኦርቶዶክስ፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ የግእዝ ትምህርት፣ ቅኔና ዜማ፣ ከአበው አንደበት(ዝክረ አበው)፣ ለሕፃናት፣ ለወራዙት የመሳሰሉት ሲኾኑ፤ የሚተላለፉበት ዕለትና ሰዓት ከሚወስዱት ጊዜ ጋር ተወስኖላቸዋል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ፥ ቅዳሜ እና እሑድ ለስምንት ሰዓታት ያኽል እንደሚቀርቡና ከዚያ በኋላ ከሰኞ እስከ ዓርብ ባሉት የሳምንቱ ዕለታት በወጣላቸው መርሐ ግብር የሚዞሩ(በድጋሚ የሚቀርቡ) ይኾናሉ፡፡ የዜና ሽፋንን ጨምሮ ሌሎቹ ፕሮግራሞችም የጣቢያውን የሰው ኃይል፣ የሎጅስቲክና የበጀት አቅም በማገናዘብ በሒደት እንደሚካተቱና በአጠቃላይ በ40 ሚሊዮን ብር የበጀት አቅም መታቀዳቸው ተመልክቷል፡፡


 • ስብከተ ወንጌል
 • ትምህርተ ሃይማኖት ዘኦርቶዶክስ
 • ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
 • ነገረ ቅዱሳን/ዝክረ ቅዱሳን
 • ቅኔ እና ዜማ(ማሰማት)
 • የግእዝ ትምህርት
 • ከአበው አንደበት/ዝክረ አበው፡- ያለፉና በሕይወት ያሉ አባቶች ታሪክና ሥራዎች
 • እንወቃቸው/ዘጋቢ ፊልም፡- ቅዱሳ መካናት፣ ቅዱሳት መጻሕፍት
 • ታሪክ እና ቅርስ፡- የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶች
 • ዐውደ ተዋስኦ/talk show/
 • አገልግሎት እና አገልጋዩ/በክህነት፣ በሰንበት ት/ቤት እና በማኅበራት/
 • የቤተሰብ ጊዜ/ትዳርን ጨምሮ ክርስትና በማኅበራዊ ኑሮ/
 • ለወራዙት/ወጣትነትና ክርስትና፤ የሰንበት ት/ቤቶች የጥያቄና መልስ ውድድር/
 • ለሕፃናት/በዬኔታ፣ በካርቱንና በተለያዩ ጥንቅሮች/
 • የቤተ ክርስቲያን እጆች፡- የማኅበራዊ ልማትና የራስ አገዝ እንቅስቃሴዎች
 • በውጭ ግንኙነት/የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ማንነትና እንቅስቃሴ
 • ዜና ቤተ ክርስቲያን…

ሥራ አስኪያጁንና የፕሮግራም ዳይሬክተሩን ጨምሮ በ21 ባለሞያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች መደበኛ ሥርጭቱን የጀመረው የኢኦተቤ-ቴቪ(EOTC TV)፤ ሐዋርያዊ ተልእኮን ለማጠናከርና ለማስፋፋት በሚያደርገው ጥረት፣ በበጎ ፈቃድና በቀናነት የሚያግዙትን ሞያተኛና ባለሀብት አርቶዶክሳውያንን ድጋፍ ይሻል፡፡ “ዳር ቆሞ ከመተቸት ቀርቦ ማገዝ” የሚሉት የድርጅቱ ባልደረቦች፣ ድጋፉ:-“ተሽከርካሪን ከሹፌር ጋር፤ ቪዲዮ ካሜራን ከካሜራው ሞያተኛ ጋር ከማዋስ ይጀመራል፤” ይላሉ፣ ጣቢያው ያለበትን እጥረት በመጠቆም፡፡

ለሥራው ስፋት የሚመጥኑ በቂ ክፍሎች ያሉትን ቋሚ ቢሮ ለማግኘት ከአባቶችና ከሚመለከታቸው የጠቅላይ ጽ/ቤቱ አካላት ጋር እየሠራ ይገኛል፡፡ ወደፊት አህጉረ ስብከት፣ የየራሳቸውን የኮሚዩኒኬሽን/የሚዲያ ክፍል በማቋቋምና በጀት በመመደብ ግብአት የሚኾኑ መረጃዎችን እንዲልኩ ይታሰባል፤ በመዋቅሩም:- የሰንበት ት/ቤቶች፣ ዕውቅና ያላቸው የአገልግሎት ማኅበራትና ከአስተምህሯችን ጋር የማይጋጭ ተልእኮ ያላቸው አካላት የአየር ሰዓት እየተከራዩ በአጋርነት የሚስተናገዱበት አሠራር እንደሚዘረጋ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን/EOTC TV/ ፕሮግራሞችን ይከታተሉ!!!
Advertisements

2 thoughts on “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥንን/ኢኦተቤ-ቴቪ/EOTC TV/ ፕሮግራሞችን ይከታተሉ

 1. ሩፊኖስ January 7, 2017 at 2:00 pm Reply

  እግዚአብሔር ሆይ የቤ/ክ እውነተኛ ድምጿ እንዲሆን እና ፍሬ እንዲአፈራ ቅዱስ ፈቃድህ ይሁን፡፡

 2. betelhem January 9, 2017 at 6:45 am Reply

  የእያንዳነዱ መርሐግብር የሚጀምርበት ሰአት ቢገለጽ ለመከታትል ምቹ ይሆናለ የምታውቁት ነግር ካለ ወይም ብትጠይቁልን

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: