አጭበርባሪው የተሐድሶ መናፍቅ ናትናኤል ታዬ: በፖሊስ እየታደነ ነው፤ ለደብረ ብርሃን ፖሊስና የማኅበረ ቅዱሳን ማዕከል ይጠቁሙ!

  • በገንዘብ ዋስትና ከወጣ በኋላ አድራሻውን ሰውሯል
  • ፍርድ ቤቱ፣ ለጥር 1 ቀን ታስሮ እንዲቀርብ አዝዟል
  • ለምን ታሰረ ባይ ፕሮቴስታንቶች አቤት ብለው ነበር
  • በኹለት የወንጀል አድራጎቶች ክሥ ተመሥርቶበታል

*               *               *

pastor-natnael-taye-arrested
በቅሠጣ ተግባር በቁጥጥር ሥር ውሎ ክሥ የተመሠረተበት “መነኵሴ ነበርኩ” ባዩ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቅ፣ ናትናኤል ታዬ፣ በዋስትና ከወጣ በኋላ በተከታታይ የችሎት ቀጠሮዎች ባለመገኘቱ፣ ከአለበት በፖሊስ ታድኖና ተይዞ ለጥር 1 ቀን እንዲቀርብ ፍ/ቤት አዘዘ፡፡

የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያንን ተልእኮ ለማስፈጸም በተቀበለው ስምሪት፣ ባለፈው ኅዳር አጋማሽ በደብረ ብርሃን ከተማ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤት ውስጥ በቅሠጣ ተግባር ላይ ሳለ እጅ ከፍንጅ የተያዘው የተሐድሶ መናፍቁ፣ ዐቃቤ ሕግ በመሠረተበት ክሥ ምስክሮችን ለመስማት፦ ለታኅሣሥ 11 እና ለታኅሣሥ 18 ቀን ኹለት ቀጠሮዎች ቢሰጡም ባለመቅረቡ ነው ፍ/ቤቱ ትእዛዙን የሰጠው፡፡

በከተማው አስተዳደር ፖሊስ ጣቢያ የተጣራው የምርመራ መዝገብ የደረሰው ዐቃቤ ሕግ፣ በቀረቡለት ማስረጃዎች መሠረት፦ የሌላውን ሃይማኖት የመስደብና የማዋረድ ንግግር እንዲኹም ድርጅት/ግቢ መድፈር በሚሉ ኹለት የወንጀል አድራጎቶች፣ በአጭበርባሪው ‘መጋቢ’ ናትናኤል ታዬ ላይ ክሥ መመሥረቱ ታውቋል፡፡

እንደ ክሡ አቀራረብ እንዲያስረዱ፣ ዐቃቤ ሕግ የቆጠራቸው ሦስት የዓይን ምስክሮች፣ የከተማው አስተዳደር ፍ/ቤት በሰጠው ተከታታይ ቀጠሮ ቢቀርቡም ተከሣሹ አለመቅረቡ ተጠቅሷል፤ በጥር 18ቱ ኹለተኛ ቀጠሮ ችሎቱ የጠየቃቸው ፕሮቴስታንቱ ጠበቃ፣ “አድራሻውን አላውቀውም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ተከሣሹ፣ በማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ብርሃን ማዕከል በሚያስተዳድረው የአቡነ ጎርጎርዮስ ዐጸደ ሕፃናት ውስጥ ኅዳር 17 ቀን ሲቀሥጥ፣ የግእዝ ትምህርት በመከታተል ላይ በነበሩ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች አማካይነት በፖሊስ ተይዞ እስከ ኅዳር 21 ቀን በቁጥጥር ሥር ቆይቷል፤ ጉዳዩን በውጭ እንዲከታተል ተፈቅዶለት የወጣውም፣ በአራት ሺሕ ብር የገንዘብ ዋስትና እንደኾነ ተገልጿል፡፡

ዋስትናው በተፈቀደበት ቀን በችሎቱ ሳለ፣ ለምን ይታሰራል በሚል ወደ አዛዡ ቀርበው አቤት ያሉት የኑፋቄ ተባባሪዎቹ እንደነበሩ ታዛቢዎች ተናግረዋል፤ ይኹንና፣ አዎንታዊ ምላሽ ሳያገኙ አፍረው ተመልሰዋል፤ ይላሉ ታዛቢዎቹ፡፡ ቀሣጢው፣ በዋስትና ከወጣ በኋላ ወደ አዲስ አበባ መመለሱ ቢታወቅም አድራሻውን ሰውሯል፤ ፖሊስም የፍ/ቤቱን ትእዛዝ ለማስፈጸም ማደኛ አውጥቶ እየተከታተለው ይገኛል፡፡

“ዐማኑኤል ኅብረት” የተሰኘው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጅ አንጃ አባል የኾነውና “Christ International Worship” በሚል የራሱን “የሚኒስትሪ ፈቃድ” አውጥቶ እንደሚንቀሳቀስ የሚናገረው ተከሣሹ፣ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሳይኾን እንደኾነና ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሳይላክ እንደተላከ በማስመሰል ሲቀሥጥ እጅ ከፍንጅ በተያዘበት ወቅት፣ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይና ሥራውም ፓስተር እንደኾነ የሚያረጋግጥ መታወቂያ ተገኝቶበታል፡፡

የአብነት ተማሪዎችን ለመርዳት በሚል ከአገር ውጭ ጭምር እንደሚንቀሳቀስና የተለያዩ ልምዶችን መቅሰሙን ለግቢ ጉባኤያቱ ተማሪዎች የተናገረ ሲኾን፤ ከእነርሱም፣ “ቴዎሎጅያንንና ጳጳሳትን የማፍራት ውጥን” ይዞ እንደሚሠራ ማስታወቁ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

“መነኵሴ/አባ/ ነበርኩ” ባዩ አጭበርባሪው ናትናኤል ታዬ፣ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ፍጻሜ ምን እንደኾነ በግልጽ የሚያሳይ ግሁድ ምስክር ነው፡፡

ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማንነትና ማዕከላዊ አንድነት ስጋት የኾነውን ሰርጎ ገብ የኑፋቁውን ሤራ ለማስወገድ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ በተወሰነው መሠረት፣ በነቃ የመከላከልና በጠንካራ የመቋቋም ተጋድሎ ላይ የሚገኙ አገልጋዮችና ሠራተኞች ኹሉ፤ ይኼን የሕግ ተፈላጊ(wanted) ቀሣጢ አድኖ ለፍትሕ ለማቅረብ በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡

natnael-taye
ጥቆማቸውንም፣ ለደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አልያም ለማኅበረ ቅዱሳን የዋናው ማዕከል እና የደብረ ብርሃን ማዕከል ጽ/ቤቶች ማድረስ እንደሚችሉ ተገልጧል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: