ቤተ ሳይዳ – የአገልጋዮች መረዳጃ ዕድር: አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሒዳል

  • የመተዳደርያ ደንቡን ያሻሽላል
  • የአባላት ቤተሰብን ይመዘግባል
  • የአባልነት ደብተር ይሰጣል

%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8c%8b%e1%8b%ae%e1%89%bd-%e1%88%98%e1%88%a8%e1%8b%b3%e1%8c%83-%e1%8b%95%e1%8b%b5%e1%88%ad
ባለፈው ኅዳር አጋማሽ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ሠራተኞች የተመሠረተው፣ ቤተ ሳይዳ የመረዳጃ ዕድር፣ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን፣ በመጪው ጥር ወር መጀመሪያ ላይ እንደሚያካሒድ አስታወቀ፡፡

የመረዳጃ ዕድሩ፣ ኃሙስ ጥር 4 ቀን 2009 ዓ.ም.፣ ከቀኑ 8:30 ጀምሮ የሚያካሒደው ጠቅላላ ጉባኤ፦ በመሥራች ጉባኤው ወቅት በተስማማበትና በመተዳደርያ ደንቡ አንቀጽ 24 ንኡስ ቁጥር 2፣ ስለ አስቸኳይ ስብሰባ የተደነገገውን መሠረት በማድረግ የተጠራ መኾኑ ተገልጿል፡፡

አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤው በዕለቱ፣ የመተዳደርያ ደንብ ረቂቁ በመሥራች ጉባኤው በቀረቡ ሐሳቦች መሠረት መሻሻሉንና መቃናቱን አረጋግጦ እንደሚያጸድቅ በመርሐ ግብሩ ተጠቅሷል፤ በተያያዘም፣ በቤተሰብ መዝገብ ቅጽ የአባላት ቤተ ሰዎችን እንደሚመዘገብና የአባልነት ደብተር እንደሚሰጥም ተመልክቷል፡፡

ጠቅላላ ጉባኤው እስከሚካሔድበት ጥር 4 ቀን ድረስ የሚገቡ አገልጋዮችና ሠራተኞች፣ በመሥራች አባልነት የሚመዘገቡ ሲኾን፤ በመተዳደርያ ደንቡ አንቀጽ 6 እንደሰፈረው፣ ብር 300 መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከጠቅላላ ጉባኤው በኋላ የአዲስ አባላት የመግቢያ ክፍያ ብር 500 እንዲኾን በደንቡ ተወስኗል፡፡ እያንዳንዱ አባልም በየወሩ ብር 50 በመደበነኛነት መክፈል ይኖርበታል፡፡

የመሥራች አባላት ምዝገባ በስፋት እየተካሔደ ሲኾን፣ ከኢትዮጵያ ውጭ ካሉትም የመረዳጃውን ዓላማ በመደገፍ በአባልነት የመመዝገብ ፍላጎቱ እንዳለ ተጠቁሟል፡፡ በተለያየ ምክንያት በአካል ቀርበው ለመመዝገብና ክፍያ ለመፈጸም የማይችሉ አገልጋዮችና ሠራተኞች፥ የዕድሩን የባንክ ሒሳብ ቁጥር መጠቀምና የሚመለከታቸውን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ማነጋገር እንደሚችሉ ተገልጧል፡፡


ቤተ ሳይዳ የአገልጋዮች መረዳጃ ዕድር
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የሒሳብ ቁጥር፡- 1000191216176

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

መምህር ዮናስ ነጌሶ – የመረዳጃ ዕድሩ ሒሳብ ሹም – 091-3659650
መጋቤ ሥርዓት ደስታ ጌታሁን – የመረዳጃ ዕድሩ ዋና ሰብሳቢ – 091-1413150

መምህር በላይ ወርቁ – የመረዳጃ ዕድሩ ም/ል ዋና ሰብሳቢ – 091-1061164
መምህር ዓቢይ መኰንን – የመረዳጃ ዕድሩ ጸሐፊ – 091-1439593


በአገልጋዮችና በሠራተኞች መካከል፦ ቤተሰባዊነትንና ወዳጅነትን ማጠናከርን፤ በማንኛውም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እክሎች መደጋገፍን እንዲኹም በጋራ ተደራጅቶ በመሥራት ራስን፣ ቤተ ክርስቲያንና ሀገርን መጥቀምን ዐበይት ዓላማዎቹ በማድረግ በበጎ ፈቃድ የተመሠረተ ነው – ቤተ ሳይዳ የመረዳጃ ዕድር፡፡

ቤተ ሳይዳ፦ በትርጉሙ፣ የምሕረት ቤት ማለት ሲኾን፣ ከመቃብር በላይ በሐዘንም በደስታም መረዳዳትንና መደጋገፍን ዋናው ዓላማው አድርጎ መቋቋሙን ያመለክታል፤ ተብሏል፡፡

የመቋቋሙ አነሣሾችና መሥራቾችም፡- በዐዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ በአህጉረ ስብከት፣ በገዳማትና በአድባራት፤ በመንፈሳውያን ኮሌጆች፣ በሰንበት ት/ቤቶችና በማኅበራት በመደበኛነት የሚሠሩና በትሩፋት የሚያገለግሉ ወንድሞችና እኅቶች እንደኾኑ ቀደም ሲል መዘገቡ ይታወሳል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: