ጠቅላይ ቤተ ክህነት በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ያቀረበውን ክሥ አሻሻለ

  • የክሥ ሒደቱ፣ በሚዲያ እንዳይዘገብ ቢጠየቅም ተቀባይነት አላገኘም

(አዲስ አድማስ፤ ዓለማየሁ አንበሴ፤ ቅዳሜ፣ ኅዳር 17 ቀን 2009 ዓ.ም.)

journalist-firew-and-the-patriarch-aba-mathias
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት፣ በሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ፍሬው አበበ ላይ ያቀረበውን የስም ማጥፋት ክሥ አሻሽሎ ያቀረበ ሲኾን፤ የፍርድ ሒደቱን ጋዜጠኞች እንዳይዘግቡ የቀረበውን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም፡፡

ክሡ የተሻሻለው፥ ፍርድ ቤቱ ኅዳር 5 ቀን 2009 ዓ.ም. በዋለው ችሎት፣ ቀደም ሲል የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ፍሬው አበበ ላይ፣ መጋቢት 21 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ “ፓትርያርኩ ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድህነት ስጋት” በሚል ርእስ፣ በዲ/ን ዳንኤል ክብረት ተጽፎ በእይታዎቹ መጦመርያ ላይ ከወጣ በኋላ በጋዜጣው የታተመው መጣጥፍ፥ “የፓትርያርክ አቡነ ማትያስን ስም ያጠፋ ነው” በሚል ያቀረበውን ክሥ በተመለከተ ተከሣሹ፣ “የፓትርያርኩ ጉዳይ በቀጥታ ጠቅላይ ቤተ ክህነትን የሚመለከት አይደለም፤” የሚል የክሥ መቃወሚያ ማቅረቡን ተከትሎ፣ ፍርድ ቤቱ ክሡ ተሻሽሎ እንዲቀርብ በሰጠው ትእዛዝ ነው፡፡

ጠቅላይ ጽ/ቤቱ እንደ ትእዛዙ አሻሽሎ አቅርቧል፡፡ ተከሣሽ ጋዜጠኛ ፍሬው አበበም፣ የተሻሻለውን ክሥ አስመልክቶ ምላሽ ለመስጠት በጠየቀው መሠረት፣ ፍ/ቤቱ ለታኅሣሥ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በዕለቱ ተከሣሽ ሰንደቅ ጋዜጣን ጨምሮ ሌሎች ብዙኃን መገናኛዎች ክሡን እየዘገቡ ያቀረቡበት ኹኔታ በየጊዜው እየተደጋገመ ቤተ ክህነትን መጉዳቱን በመጥቀስ፣ ፕሬሶች በሒደት ላይ ያለውን ክሥ ጉዳይ እንዳይዘግቡ እንዲደረግ፣ በከሣሽ በኩል አቤቱታ ቀርቧል፡፡

ተከሣሽ በበኩሉ፣ ፕሬሶች ጉዳዩን እየተከታተሉ መዘገባቸው ሕጋዊ ሒደት መኾኑን አስረድቷል፤ ፍ/ቤቱም፣ ሚዲያዎችን እንዳትዘግቡ ማለት እንደማይቻል፤ ሚዲያዎችም ቢኾኑ፣ በዘገባ ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ትእዛዝ በመስጠት፣ ቀጣዩን ሒደት ለመከታተል ለታኅሣሥ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Advertisements

One thought on “ጠቅላይ ቤተ ክህነት በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ያቀረበውን ክሥ አሻሻለ

  1. Anonymous December 5, 2016 at 7:13 am Reply

    የተባሉን ነገር ቢያስተካክሉ አይሻላቸውም፡፡ ከሳቸው ሰው ምን ይማራል ፍርድ ቤት መሄድን ወይንስ እርቅን፡፡ ምን አለበት በቤተክርስቲያን ቴሌቭዥን ባናያቸው የያዙት መስቀልኮ አስተማሪ ነው ቢያውቁት ፡፡ ክሱን ሰርዙ ይሻሎታል፡፡ አቡነ ጳውሎስኮ ሰዎች እስር ቤት ለማስገባት ወይም ለማስቀጣት ፍርድ ቤት አልቆሙም ይልቁን እየተባሉ ዝም አሉ እንጂ አድናቂያቸው ነኝ፡፡ የታሰረውን ያስፈቱ ነበር፡፡ ደርጎች እንዲፈቱ ያደረጉ አባት ናቸው፡፡ ምክንያቱም አሳስሮ ስለታሰሩ ሰዎች እንማልዳለን ብሎ ነገር የለምና፡፡ ሰው ሲበደል በረከትን ያገኛል ከሶ ሳይሆን ዝም ብሎ፡፡ ምነው መናፍቃን ቤተክርስቲያኒቱን ሲሳደቡ ዝም ማለታችሁ የሰው ይበልጣል የእግዚአብሔር፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: