ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ሕንድን ይጎበኛሉ

his-holiness-abune-mathias-the-first-and-his-holiness-abune-baselios-mar-thoma-paulose-the-second

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት(በግራ)፤ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ማር ቶማ ጳውሎስ ዳግማዊ ካቶሊኮስ ዘመንበረ ቶማስ ሐዋርያዊ መጥሮጶሊጣን ዘማላንካራ(በቀኝ)

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ በሕንድ የአምስት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ፡፡

ዛሬ ኅዳር 9 ቀን ማምሻውን ወደዚያው እንደሚያመሩ የተጠቀሰ ሲኾን፤ እስከ ኅዳር 14 ቀን በሚዘልቀው ቆይታቸው፣ ከሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ርእሰ መንበር ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማር ቶማ ጳውሎስ ዳግማዊና ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ተጠቅሷል፡፡

ከቅዱስነታቸው ጋር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የወሊሶ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና የመቐለ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ አብረዋቸው እንደሚጓዙ ታውቋል፡፡

ቅዱስነታቸው አቡነ ባስልዮስ ማር ቶማ ጳውሎስ ዳግማዊ፥ እ.አ.አ ከኖቨምበር 2010 ጀምሮ በሕንድ ኦርቶዶክስ  ቤተ ክርስቲያን መንበረ ቶማስ የተሠየሙ 91ኛው የምሥራቅ ካቶሊኮስና የማላንካራ መጥሮጶሊጣን ናቸው፡፡

በሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በ52 ዓ.ም. የተመሠረተችው፣ የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፤ በምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርት የመለኰትንና የትስብእትን ተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ብለው በማመን ከጸኑና የኬልቄዶንን ጉባኤ ከማይቀበሉ አምስቱ አኃት አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ናት፡፡

አምስቱ አኃት አብያተ ክርስቲያናት፡- የግብጽ እስክንድርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ የሶርያ/አንጾኪያ/ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ የአርመን ኦርቶዶክስ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኾኑ፤ የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአስተምህሮና ትውፊት በተለይም ከ17ኛው መ/ክ/ዘ (1665 ዓ.ም.) አንሥቶ ከሶርያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር የተሳሰረ ግንኙነት አላት፡፡

በታወቀው ኦፊሴሊያዊ ስያሜዋ፣ የማላንካራ ኦርቶዶክስ ሶርያ ቤተ ክርስቲያን ወይም የኦርቶዶክስ ሶርያዊ ምሥራቅ ቤተ ክርስቲያን ተብላ የምትጠራውም ከዚኹ ጋር በተያያዘ ነው፤ በሶርያው አባት ሥር መቀጠልን በመቃወም በአስተዳደር የተለዩም አሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከምትገለገልባቸው ስድስት የሥርዓተ ቅዳሴና የሥራ ቋንቋዎችም ሲሪያክ አንዱ ነው፡፡ ኬሬላ ወይም ማላንካራ በደቡብ ሕንድ የምትገኝና በሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ሰማዕትነት የክርስትና መሠረት የተጣለባት የመንበሩ መቀመጫ ስትኾን፤ ካቶሊኮስ የሚለው የርእሰ መንበሩ ሥያሜ የፓትርያርክ አቻ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

የማላንካራ ሶርያዊ ማኅበር(The Malankara Syrian Association)፤ የጳጳሳት፣ የካህናትና የምእመናን የሰበካ ተወካዮች የሚገኙበት ላዕላይ ምክር ቤት ሲኾን፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ዐበይት ጉዳዮች ላይ ለመወሰን የሚሰበሰብ ነው፡፡ እንደ እኛው ቤተ ክህነት የአስተዳደር ሥራውን የሚመራውን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ(Managing Committee) ይሠይማል፤ ከኮሚቴው አባላት የምእመናኑ ቁጥር ከካህናቱ በዕጥፍ የሚበልጥ መኾኑ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለምእመናን ተሳትፎ የሰጠችውን ቦታ ያሳያል፡፡

church_of_india_-_all_bishops

የቤተ ክርስቲያኒቱ አበው ጳጳሳት

ይህም ኾኖ እምነትን፣ ሥርዓትንና ዲስፕሊናዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከፍተኛው የሥልጣን አካል፣ ኤጲስ ቆጶሳት በሙሉ የሚገኙበት ሲኖዶሳዊ ጉባኤ(The Episcopal Synod) ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ርእሰ መንበር የኾኑት የምሥራቅ ካቶሊኮስና የማላንካራ መጥሮጶሊጣን የሚመረጡት በማላንካራ ሶርያዊ ማኅበር ሲኾን፤ በመንበሩ የሚሠየሙት ግን በዚኹ ሲኖዶሳዊ ጉባኤ ነው፡፡

በፖርቱጋል ካቶሊክ ሚስዮናውያንና በእንግሊዝ የአንግሊካን ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያን ቀሣጢነትና መሠሪነት የፈተና ንብርብር የደረሰባት የሕንድ ቤተ ክርስቲያን፣ በገጠማት የመከፋፈል አደጋ ልጆችዋን አጥታለች፡፡ ይኹንና ፈተናውን በከፍተኛ ተጋድሎ በመቋቋም፤ ኦርቶዶክሳዊ ማንነቷን፣ ሐዋርያዊ ትውፊቷንና የመንበሯን ነፃነት አስጠብቃለች፤ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመሩ 25 አህጉረ ስብከትንም አቋቁማለች፡፡

በተለይም፣ ከ20ኛው መ/ክ/ዘ በኋላ ከሕንድ ክፍለ አህጉር አልፋ በዓለም ዙሪያ(በምሥራቅና ደቡብ ምሥራቅ ኤዥያ፣ በአፍሪቃ፣ በአሜሪካና ኦሺንያ) ሐዋርያዊ ተልእኮዋን በመወጣት ላይ ትገኛለች፡፡ በአኹኑ ጊዜም ከ2.5 ሚሊዮን በላይ አገልጋዮችና ምእመናን አሏት፡፡

የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የዓለም አብያተ ክርስቲያናት አባል ናት፡፡ ከሌሎች ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ጋር በነገረ ክርስቶስ ልዩነቶች በሚደረጉ ንግግሮች በኤኩሜኒዝም መንፈስ በንቃት ትሳተፋለች፡፡ ለዚኽም፣ እንደ ማር ጳውሎስ ጎርጎርዮስ እና ቀሲስ ቪ.ሲ ሳሙኤል ያሉት ዕውቅ የሥነ መለኰት ሊቃውንቷ ያላቸው አስተዋፅኦ ይጠቀሳል፡፡

ቀሲስ ቪ.ሲ ሳሙኤል፣ በቤተ ክርስቲያናችን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ካገለገሉ ምሁራን በስፋት የሚታወቁ ሲኾኑ፤ ከመምህርነት ተጠርተው ለማዕርገ ጵጵስና የበቁም አሉ፡፡ የአኹኑ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጉብኝት፤ በዚኽና በሌሎችም የኹለቱ አብያተ ክርስቲያናት እኅትትማችነት ዙሪያ የቆየውን ግንኙነትና ትብብር በማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡

በሕንድ ኒውዴልሂ፣ ከጥር 19 እስከ 23 ቀን 1999 ዓ.ም. ተካሒዶ በነበረውና የዓለም እምነቶች መሪዎች በተሳተፉበት የሰላም ጉባኤ፣ የቀድሞው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ተካፍለው፤ ግጭትን በማስወገድ በፍቅርና ተባብሮ በመኖር አስፈላጊነት መልእክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል፡፡

 

Advertisements

One thought on “ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ሕንድን ይጎበኛሉ

  1. Anonymous November 18, 2016 at 10:06 pm Reply

    ወጋወጉ እንደሐየወች አሉ አለቃብረሀና ይባላል እኔማለት የፈለኩት የፖትርያሬክ ማትያስ የህንድጉብኝትና አብረዋቸዉ
    የሚጓዙትከቅዱስነታቸው ጋር የመቐለ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ እና የአውሮጳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ አብረዋቸው እንደሚጓዙ ታውቋል፡፡ይገርማል አይሰሙ አያስተረጉሙ አባ ሙሴ አውሮፖማንእደሚመራቸዉ ጀሮአቸዉን ቢቆርጡት ከትግሬኞ በስተቀር ምንምአይሰሙ የመቀሌዉም እንደዚሁነዉ
    መቸም የመጣብንም ማት መቀበልነዉ ሀገራችን እና ትልቛን ቤተክርስቲያን አታዋርዳት በፈጠራቸሁ ከምትሄዱበት
    እዛችሁትየምትመጡትን እናያለን ጉደኞች

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: