ሊቄ አሰፋ ሥዩም የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊነት ተመደቡ፤ አባ ሠረቀ “የሚያሳዩት የችኩልነትና የአለመረጋጋት መንፈስ በሥራው ላይ ችግር ፈጥሯል” /ልዩ ጽ/ቤቱ/

 • ልዩ ጽ/ቤቱን በአግባቡ የማዋቀርና በሰው ኃይል የማደራጀቱ ሥራ ይጠበቃል
liqee-assefa-seyoum

ሊቄ አሰፋ ሥዩም፤ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ

ባለፈው ሳምንት ሰኞ፣ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ የጸሐፊነት ሥራ በተነሡት ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ምትክ፣ ሊቄ አሰፋ ሥዩም ተመደቡ፡፡

ሊቄ አሰፋ ሥዩም፣ በተለያዩ ዘመነ ፕትርክናዎች፣ በምክትል ጸሐፊነት ደረጃ የልዩ ጽ/ቤቱን የጽሕፈት ሥራዎች በዋናነት ሲያከናውኑ የቆዩ ነባር ሠራተኛ መኾናቸው ተጠቅሷል፡፡

የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ኾነው ይሠሩ ዘንድ የተመደቡትም፣ ያላቸውን የረጅም ጊዜ ልምድ መሠረት በማድረግ እንደኾነ፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ ከቀትር በኋላ፣ በፓትርያርኩ ተፈርሞ በወጣው የምደባ ደብዳቤ ተገልጧል፡፡

ካለፈው ዓመት ሐምሌ 12 ቀን ጀምሮ በቦታው የቆዩት ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን፣ ከሥራው ጠባይ ጋር የማይጣጣም መንፈስ በማሳየታቸውና ሓላፊነታቸውንም በአግባቡ ባለመወጣታቸው ነው ከልዩ ጸሐፊነታቸው የተነሡት፡፡

ጥቅምት 21 ቀን፣ በቁጥር ል/ጽ/56/420/2009 በፓትርያርኩ ተፈርሞ የወጣው የልዩ ጽ/ቤቱ ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፡- አባ ሠረቀ ብርሃን በተመደቡ ሦስት ወራት ባልሞሉ ጊዜያት ውስጥ በሚታይባቸው የችኩልነትና አለመረጋጋት ባሕርይ የተነሣ፣ በአደራ የተጣለባቸውን የሥራ ሓላፊነት በአግባቡ አለመወጣታቸውን፤ የበላይ ሓላፊዎችን ትእዛዝ አለማክበራቸውንና አለመቀበላቸውን፤ በጠቅላላ የሚያሳዩት መንፈስ ከሥራው ጠባይዕ ጋር አብሮ የማይሔድና የማይጣጣም ኾኖ በመገኘቱ በሥራው ላይ ችግር ተፈጥሮአል፡፡

በመኾኑም፣ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ አባ ሠረቀ፣ ከሥራቸው እንደተነሡና ደመወዛቸውን እንደያዙ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉ መታዘዛቸውን አስታውቋል፡፡

የሊቄ አሰፋ ሥዩም ምደባ፣ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዘመነ ፕትርክና፣ በልዩ ጽ/ቤቱ የሠሩትን ልዩ ጸሐፊዎች ቁጥር ሦስት ያደርሰዋል፡፡ ነባሩ የልዩ ጽ/ቤቱ ባልደረባ፣ ከአባ ሠረቀ ብርሃን ቁልፍና ንብረት በመረከብ ልዩ ጸሐፊነቱን በሙሉ ሓላፊነት እንዲጀምሩ ቢደረግም፣ ያለፈው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በወሰነው መሠረት፤ ልዩ ጽ/ቤቱን በአግባቡ የማዋቀርና አገልግሎቱ በሚያስፈልገው የባለሞያ ኃይል የማደራጀቱ ሥራ የሚቀር ነው፡፡

aba-serekebirhan-woldesamuel-sacked

Advertisements

2 thoughts on “ሊቄ አሰፋ ሥዩም የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊነት ተመደቡ፤ አባ ሠረቀ “የሚያሳዩት የችኩልነትና የአለመረጋጋት መንፈስ በሥራው ላይ ችግር ፈጥሯል” /ልዩ ጽ/ቤቱ/

 1. Anonymous November 6, 2016 at 9:18 pm Reply

  ይህ ግልብልብ የዉሸት መነኩሴ ሰረቀ ብርህን እና አባኪዳነማርያም ይዉጡ
  ሁለቱም የዉሸት መነኮ ሳት ናቸዉ ስለዚህ የቅዱሡን አባት ስራእንቅፋት መሆንየለባቸዉም
  ፖትርያርኩ ትግሬ ከፈለጉ መቀሌይግቡና ያምጡ ሞልቷል እንዃን ሊያገባ አልመለኮሠም ይባላል
  መተዳደሬያ ነዉ ያረጉት አባ ሰረቀ ምንቁስ በል

 2. Anonymous November 7, 2016 at 9:56 pm Reply

  ለሊቀብረሀናትና ቆሞስ አባገብረህይዎት ዘሙኔክ መላከገነት አባ ብረሀነመስቀል መንግስቱ ዘበርሌን ጵጵስና መታጨታቸዉ
  ይታዎቃል እዉነት ለመናገር ከሆነ የደልዎ ይገባቸዋል ሁሉንችለው ሁሉዉን ታግሰዉ አባታዊ እርሩህነታቸዉ
  በባድአገር ሀይማኖትን ለአለማስነቀፍ ሲሉ ብዙ ዉ መሷይትነት ከፍለዋል የሚታይ የሚደሰስ ስራሰርተዋል
  ህዝብክርስቲያኑችን ሰይከፋፍሉ በማገልገል ለይ ይገኝአሉ በአንፃሩ አባ ዘድንግል ኑርበገን ፈረንሰይ ፓሬስ ለጵጵስና ታጭተዋል
  መነኩሴዉ በዘመናዊ ትምህርት እየገፉይገኝአሉ ይሁንጂ በመንፈሣዊ ህይዎታቸዉ
  እንዺሁም በፍቅረቢፅ የለላቸዉ ከመሆኑም በለይ ፖሬስ ፈረሰይ ከጀማይካዊዎችጋር አሽሽ እደሚያጨሱና በየጊዜዉ
  በፀራራፀሐይ እደሚሰክሩ ህዝቡንከሶስት እደከፈሉ የሚታዎቅሲሆን ምንምአይነት ለቅዳሴም ሆነ ለወንጌል ትጉ
  አይደሉም ለአባ ሙሴ የስም ጳጳስተብየ ለቀለብ የሚሰጣቸዉን የተማሬ ቀለብ በየወሩ ለሙሴ ተቆራጭ በማድረግ
  ጀሯቸዉን አቁመዉ ለአቡነሙሴ ምናዲስ ነገርአለ እያሉ በመደወል ጳጳሱ በማሣቀቅ ለይ ይ ገኝአሉ ስለዚህ
  አባ ዘድንግል ኑዉርበገን ጵጵስና አይገባቸዉም መልካቸዉ ድምፃቸዉም ደሳይሉም ሴሰኞ ዝሙተኞ ጭምርነዉ
  ይህ ላንቁሶ ደንቆሮ ጳጳስ ተብየ ሙሴ ሰይማር በዘር የተሸከመዉ ቆብ በትክክል ቢሆን የሱአልነበረም ስለዚህ
  የመይገባቸዉን ጵጵስና አቮማችሁ አለሁ ማለታቸዉን ቢያቆሙይቫላል ምከሮአቸዉ ስለሐይማኖትብላችሁ
  ክብር ለሚገበዉ ክብርስጡ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: