ቅዱስ ሲኖዶስ: ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዘጎሬን በሰማዕትነት ሠየመ

abune-mikael-the-martyr

ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዘጎሬ

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከመጀመሪያዎቹ አምስት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት አንዱ ለነበሩትና በፋሽስታዊው የኢጣልያ መንግሥት፣ በግፍ ሰማዕትነት ለተገደሉት፣ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዘጎሬ የሰማዕትነት ሥያሜ ሰጠ፡፡

ብፁዕነታቸው፣ በ1928ቱ የፋሽስት ኢጣልያ የአምስት ዓመት የወረራ ዘመን፣ ለተዋሕዶ ሃይማኖታቸው እንዲኹም ለሀራቸው ልዕልና እና ነፃነት ከፍተኛ ተጋድሎ መፈጸማቸውን ቅዱስ ሲኖዶሱ በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

ከኢትዮጵያውያን ሐርበኞች ጎን በመኾን ጠንክረው እንዲዋጉ ሲያስተምሩ በነበረበት ወቅት፣ በ1929 ዓ.ም. በፋሽስታዊው መንግሥት በጎሬ ከተማ በግፍ ሰማዕትነት እንደተገደሉ ምልዓተ ጉባኤው ገልጾ፣ ሰማዕት ተብለው እንዲጠሩ መወሰኑን፣ ዛሬ፣ ረቡዕ ጥቅምት 16 ቀን ከቀትር በኋላ ባወጣው ሲኖዶሳዊ መግለጫው አስታውቋል፡፡

the-memorial-statue-of-abune-michael-the-martyr
ብፁዕ አቡነ ሚካኤል፣ መንበረ ጵጵስናቸው በነበረበትና በሰማዕትነት ባለፉበት በኢሉ አባ ቦራ ሀገረ ስብከት ጎሬ ከተማ የቆመላቸው ሐውልተ ስምዕ፣ ባለፈው ዓመት መጋቢት አጋማሽ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የተመረቀ ሲኾን፤ የቤተ መዘክር ግንባታ ዕብነ መሠረት መቀመጡም ይታወሳል፡፡

Advertisements

One thought on “ቅዱስ ሲኖዶስ: ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዘጎሬን በሰማዕትነት ሠየመ

  1. Anonymous October 26, 2016 at 11:26 pm Reply

    በጣም ደሥ የሚል ጉባኤ አንኳን የጵጵስና ሹመት ቀረ ያላቹ ትበቃላቹ ሌላ በላተኛ አያስፈልገንም

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: