ቅዱስ ሲኖዶስ: መንግሥት እና ተቃዋሚዎች የሀገር ችግሮችን በጋራ ውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ

 • መላው ካህናትና አገልጋዮች፣ ሕዝበ ክርስቲያኑ ለአገሩ ሰላምና አንድነት ተባብሮ እንዲቆም በየጉባኤያቱ እንዲያስተምሩ መመሪያ አስተላለፈ
 •  ከ201 ሚሊዮን ብር በላይ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የ2009 ዓ.ም. የበጀት ዕቅድ በሙሉ ድምፅ አጸደቀ
eotc-holy-synod-fathers-2009tik

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አባላት

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከጥቅምት 12 ጀምሮ ላለፉት አምስት ቀናት ሲያካሒድ የቆየውን ስብሰባ በማጠናቀቅ፣ ዛሬ፣ ጥቅምት 16 ከቀትር በኋላ ባለ12 ነጥቦች መግለጫ በማውጣት አጠናቀቀ፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ቋንቋዎች ተናጋሪ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለአያሌ ዘመናት የኖሩባትና አኹንም የሚኖሩባት በአርኣያነት ልትጠቀስ የሚገባት ብቸኛ አገር መኾኗን ያስገነዘበው ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ በአኹኑ ጊዜ ግን፣

 • የሰዎች ሕይወት እየጠፋ መኾኑን፣
 • የአገር ሀብትና ንብረት እየወደመ መታየቱን፣
 • ከነበሩበትና ከኖሩበት ቦታ የሕዝቦች ፍልሰት ማስከተሉን፣
 • በዚኽም ሳቢያ በሰላማዊው ኅብረተሰብ ዘንድ ከፍተኛ ስጋት እየሰፈነ መምጣቱን አብራርቷል፡፡

በመኾኑም ጥያቄዎች፣ ኢትዮጵያዊነትን በተላበሰ፣ በሰከነና በተረጋጋ ኹኔታ ለሚመለከተው አካል እንዲቀርቡ፤ መንግሥትም፣ ለሚያስተዳድራቸው ዜጎች እንደ ቤት ሓላፊና እንደ መሪ መጠን፣ ጥያቄዎቹን በአግባቡ በመፈተሽና በማጥናት ለአገርና ለወገን የሚጠቅም ምላሽ እንዲሰጥባቸው፣ ለሕዝቡ የገባውንም ቃል በተግባር አውሎ በሥራ እንዲተረጉም ምልዓተ ጉባኤው በመግለጫው አሳስቧል፡፡

የሀገር ጉዳይ የጋራና የውስጥ ጉዳይ በመኾኑ፣ የሀገሪቱ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ከመንግሥት ጋራ በሰላማዊ መንገድ ተቀራርበው የክብ ጠረጴዛ የጋራ ውይይት በማካሔድ ችግሮችን እንዲፈቱም ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

እየታየ ባለው የሰላም መታጣት፣ የውጭ ጣልቃ ገቦች እጅ እንዳለበት በርካታ አመላካች ኹኔታዎች መታየታቸውን የጠቀሰው ምልዓተ ጉባኤው፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ፣ ድርጊቱን እንደምትቃወምና የውጭ ዜጎች ከአጥፊ ተልእኳቸው እንዲገቱ አሳስቧል፡፡

ቤተ ክርስቲያን ዕለት በዕለት ከምታከናውነው መንፈሳዊ አገልግሎት ባልተናነሰ፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት፤ መላው ካህናትና አገልጋዮች፣ በዕለተ ሰንበት፣ በማታ ጉባኤ፣ በወርኃዊና ዓመታዊ በዓላት ኹሉ ሕዝበ ክርስቲያኑ በሥነ ምግባር ታንፆ በፈሪሃ እግዚአብሔር ለአገሩ ሰላምና ለሕዝቡ አንድነት ተባብሮ እንዲቆም የሚያስችል ትምህርት እንዲሰጡ ቅዱስ ሲኖዶሱ መመሪያ አስተላልፏል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው፣ የ35ኛውን የመንበረ ፓትርያርክ ሰበካ መንፈሳዊ አጠቃላይ ጉባኤ የጋራ መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ አንዳንድ ማሻሻያዎችን በማድረግ የ2009 ዓ.ም. በጀት ዓመት የሥራ መመሪያ እንዲኾን አጽድቋል፡፡

ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ የበጀትና ሒሳብ መመሪያ ለ2009 ዓ.ም. ተዘጋጅቶ የቀረበውን የብር 201 ሚሊዮን 490 ሺሕ 338 ብር ከ01 ሳንቲም የበጀት ረቂቅም መርምሮ ማጽደቁ ታውቋል፡፡ ይህም በ2008 ዓ.ም.ተመድቦ ከነበረው የ159 ሚሊዮን 316 ሺሕ 269 ብር ከ22 ሳንቲም አጠቃላይ በጀትና ከተመዘገበው የገቢ ዕድገት አኳያ የ26 በመቶ ብልጫ እንደታየበት ተገልጧል፡፡ 

የአጠቃላይ በጀቱን 23 በመቶ ከሚሸፍነውና ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ ደመወዝ፣ ዕቃ ግዥና የሥራ ማስኬጃ ከተያዘው 46 ሚሊዮን ብር ያኽል መደበኛ ወጪ ቀጥሎ፣ በቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች አዲስ ለሚሠሩ ሦስት ሕንፃዎች ቅድመ ክፍያ፤ ለአህጉረ ስብከት ድጎማ እና የካህናት ማሠልጠኛ ከፍተኛ በጀት እንደተመደበ በዝርዝሩ ተመልክቷል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው በተጨማሪም፣ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት በቋሚ ሲኖዶስ ተለዋጭ አባልነት የሚያገለግሉ ስምንት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ምርጫ አካሒዷል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሰብሳቢነት በሚመሩትና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በቋሚ አባልነት በሚገኙበት ቋሚ ሲኖዶስ፤ ተለዋጭ አባላቱ ለሦስት፣ ለሦስት ወራት የሥራ ጊዜ ያገለግላሉ፡፡

በዚኽም መሠረት፡- ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ እና ብፁዕ አቡነ ኤልያስ እስከ ጥር ላሉት ሦስት ወራት፤ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እና ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ እስከ ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ ላሉት ተከታዮቹ ሦስት ወራት የቋሚ ሲኖዶሱ አባላት በመኾን የምልዓተ ጉባኤውን ውሳኔዎች ያስፈጽማሉ፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን መግለጫ ሙሉ ቃል ይመልከቱ

holy-synod-megtik2009holy-synod-megtik2009b

Advertisements

One thought on “ቅዱስ ሲኖዶስ: መንግሥት እና ተቃዋሚዎች የሀገር ችግሮችን በጋራ ውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ

 1. Anonymous October 28, 2016 at 6:40 pm Reply

  እናተ ጥቁርለባሾች እግዜብሔር ይፈረደባችሁ የሲኖዶስ ስብሰባ ሰይሆን የዎያኔቅማላም ድስኩርነዉ
  ጳጳስነን ህዝቦ እደጳጳስ ያየናል ትሉይሆናል የኢትዮጵያህዝብ ከናተይልቅ በአንድጅ የሜገለዉን ወያኔይሻለዋል
  ስንታመት ቀለብናችሁ ከወያኔ ያልተሻለ ዉሳኔአችሁ ታዘብናችሁ አፈርንባችሁ ጥቁር ለባሽሁሉ ሲነጋ
  እንተያይአለን ደርግም ሀይለስላሲም ሁሉም አልፈዋል ወያኔም ይንኮታኮታል አስርጊዜም በታኮወ ቢደገፍመዉደቁ አይቀሬነዉ
  ሆዳምሁሉ ጳጳስተብየ ድንቄም ጳጳስ ኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: