በ2008 ዓ.ም. ከ50 ሺሕ በላይ አማንያን ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተጨመሩ

 • 18 ሺሕ 578ቱ፣ ከማኅበረ ቅዱሳን መርሐ ግብር ጋር በመቀናጀት የተጠመቁ ናቸው
 • ጥሙቃኑን ለማጠናከርና በቅድመ ጥምቀት ለሚማሩቱ፣ ኹለንተናዊ ድጋፍ ተጠይቋል
 • ያሉንን ምእመናን፣ ካህናትና አብያተ ክርስቲያን ቁጥር መዝግቦ የማወቅ ሒደቱ ቀጥሏል

*               *              *

timkete-kirstina

የሐዲሳን አማንያን ጥምቀተ ክርስትና ሲካሔድ(ፎቶ: የማኅበረ ቅዱሳን ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ገጽ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፥ የካህናት፣ የምእመናን፣ የገዳማት፣ የአድባራትና የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ብዛትና ያሉበትን ኹኔታ ለማወቅ ምዝገባ እያካሔደች ነው፡፡ “በጎቼንና ጠቦቶቼን ጠብቅ፤ ግልገሎቼን አሰማራ”/ዮሐ.21፥ 15-18/ የሚለውን የጌታችንን ቃል ልንፈጽም የምንችለው ስናውቃቸው ነው፡፡

መጠናቸውንና ያሉበትን ኹኔታ መዝግቦና አጥንቶ ማወቅ፣ መንፈሳዊ አገልግሎታችንን ዐቅደንና በሕዝብ ላይ መሥርተን እንድንሠራ ያደርገናል፤ የት ቦታ ምን ዓይነት አገልግሎት፣ የትኛው የልማት ወይም የማኅበራዊ ተቋም መሠራት እንዳለበት የሚወሰነው መዝግቦ በማወቅ እንደኾነ፣ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ያስረዳሉ፡፡

አህጉረ ስብከት፣ ይህን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ለማስፈጸም፡- ከፍተኛ በጀት በመመደብና የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶችን፣ ምእመናንንና ካህናትን በማስተባበር ጥረት እያደረጉ እንደኾነ በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ጉባኤ 35ኛው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ከቀረቡ ሪፖርቶች ለመረዳት ተችሏል፡፡

አህጉረ ስብከት ምዝገባውን ለማካሔድ፣ በወረዳዎች የተለያዩ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ሥልጠናዎችን ሰጥተዋል፤ ግንዛቤ አስጨብጠዋል፡፡ የምዝገባ ቅጾችን አባዝተው በማሠራጨት ቆጠራውን አከናውነው ውጤቱን ከሪፖርት ጋር ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ያሳወቁ ሲኾን፣ ኹነቱ ከምንም በላይ የህልውና ጉዳይ መኾኑን አስምረውበታል፡፡ በአቅም ማነስ ሥራቸውን በተባለው ጊዜ ያላጠናቀቁ አህጉረ ስብከትም ይገኙበታል፡፡

በሰሜን ወሎ፣ ከሚሴ፣ ድሬዳዋ፣ ደቡብ ኦሞ እና ወላይታ ኮንታ አህጉረ ስብከት፥ ምዝገባው በበጀት ዘመኑ ተከናውኖ ውጤቱ የታወቀ ሲኾን፤ በአሶሳ፣ ሐዲያና ስልጤ አህጉረ ስብከት በከፊል ተጠናቋል፡፡ እንደ ዋግ ኽምራ፣ መተከል እና ሰሜን ሸዋ ባሉት አህጉረ ስብከት ደግሞ፣ ለምዝገባው ፈጻሚዎች ሥልጠናዎችን በመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡


ያሉንን ካህናትና ምእመናን ከነቤተሰቦቻቸው፣ አብያተ ክርስቲያናቱን ከነሀብቶቻቸው ቅድሚያ ሰጥቶ ለማወቅና ለመመዝገብ የተፈጸመውን አገልግሎት ያኽል፤ በክሕደትና በኑፋቄ ማዕበል ተመተው የጠፉትን በመመለስ ቤተ ክርስቲያንን ለማስፋት አህጉረ ስብከቱ የፈጸሙት ሐዋርያዊ ተልእኮም፣ ለእናት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ውጤት እንዳስገኘ የሪፖርቶቹ አኃዛዊ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በተጠናቀቀው የአገልግሎት ዘመን ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት፣ 50 ሺሕ737 ሐዲሳን አማንያን ለጥምቀተ ክርስትና በቅተው ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደተጨመሩ፣ ከ23 አህጉረ ስብከት የቀረቡ ሪፖርቶች አረጋግጠዋል፡፡ እንደ መተከልና ደቡብ አሞ ባሉት አህጉረ ስብከት፣ ለጥሙቃኑ፥ አብያተ ክርስቲያናት ተተክለዋል፤ የቋንቋው ተናጋሪ መምህራን ሠልጥነዋል፤ አገልጋይ ካህናት ተመድበዋል፡፡

በ2008 ዓ.ም. የአገልግሎት ዓመት በየአህጉረ ስብከቱ የተመዘገቡ ሐዲሳን አማንያን ብዛት

 1. ሰሜን ወሎ፡- 409
 2. አሶሳ፡- 217/የክልሉን ም/ል ፕሬዝዳንት አቶ አብዱል ሙሐመድ ኢብራሂምን ጨምሮ/
 3. መተከል፡- 13 ሺሕ 019
 4. ከሚሴ፡- 130
 5. ሲዳማ፡- 1ሺሕ 817
 6. ምሥራቅ ወለጋ፡- 341
 7. ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፡- 1ሺሕ 631
 8. ሰሜን ምዕ/ሸዋ – ሰላሌ፡- 71
 9. ጋምቤላ፡- 87
 10. ምዕራብ ወለጋ፡- 887
 11. ምዕራብ ሸዋ፡- 5ሺሕ 500
 12. ካፋ፡- 4ሺሕ 550
 13. ማይጨው፡- 81
 14. ሸካ ቤንች ማጂ፡- 957
 15. ሐዲያና ስልጤ፡- 1ሺሕ 224
 16. ደቡብ ኦሞ፡- 6ሺሕ 075
 17. ምዕራብ ሐረርጌ፡- 114
 18. አዊ ብሔረሰብ ዞን፡- 52
 19. ባሕር ዳር፡- 25
 20. ጋሞጎፋ፡- 12ሺሕ 099
 21. ምዕራብ ጎጃም፡- 90
 22. ወላይታ ኮንታ፡- 1ሺሕ 305
 23. ደቡብ ጎንደር፡- 55

ወደ ሌሎች የኮበለሉቱን በቁጥር ገልጸው በዘገባቸው ያካተቱት እንደ ሐዋሳ፣ ሐዲያና ስልጤ ያሉት አህጉረ ስብከት፤ የምእመናን ወደ ባዕድ እምነት መግባት የሚያስቆጭ በመኾኑ፣ አስፈላጊው የመመለስና የማዳን ጥረት ይደረግ ዘንድ ኹለንተናዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡

10686871_1545240562394077_8055472982779963736_n
በቀጣይ ለመጠመቅና የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አባል ለመኾን የቅድመ ጥምቀት ትምህርት በመከታተል ላይ ያሉ በርካታ ወገኖች መኖራቸውን፣ በአሶሳ እና በመተከል አህጉረ ስብከት ሪፖርቶች ተጠቁሟል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን፣ በስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብሩ አማካይነት፣ ለመምህራኑ የበጀት ድጎማ በማድረግ ላይ እንዳለ ተገልጧል፡፡

10953180_1545240005727466_8634995926444202303_n
በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁና በአህጉረ ስብከቱ ሪፖርቶች እንደቀረበው፣ ማኅበረ ቅዱሳን በበጀት ዓመቱ በቅንጅት ባስፈጸማቸው የመርሐ ግብሩ ዕቅዶች፡- በደቡብ ኦሞ 5ሺሕ024፣ በመተከል 12ሺሕ 927፣ በጋሞጎፋ 627 አማንያን በአጠቃላይ 18 ሺሕ578 ጥሙቃን ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተቀላቅለዋል፡፡ ይህም ባለፉት አምስት ዓመታት በማኅበሩ መርሐ ግብር የተጠመቁትን ሐዲሳን አማንያን ድምር 69 ሺሕ እንዳደረሰው የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሪፖርት አስታውቋል፡፡

በ2008 ዓ.ም. በቤንሻንጉል ጉምዝ እና በጋሞጎፋ አህጉረ ስብከት የተካሔዱ የሐዲሳን አማንያን የጥምቀተ ክርስትና ምስሎችን ይመልከቱ

ቅድመ ክርስትና ትምህርት፤

dsc01334

ጥምቀተ ክርስትና፤

dsc01396

ማዕተበ ክርስትና

_dsc4430

ድኅረ ጥምቀት – ቊርባን፤

dsc01405

????????????????????????????????????

የመመኪያችን ዘውድ የደኅንነታችን መጀመሪያ፤

_dsc2472

 

Advertisements

8 thoughts on “በ2008 ዓ.ም. ከ50 ሺሕ በላይ አማንያን ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተጨመሩ

 1. Egualetsyone October 21, 2016 at 7:13 am Reply

  Egzeabher Yesebah!

 2. Anonymous October 21, 2016 at 7:49 am Reply

  የተጠመቁትንም ሆነ የተመለሱትን ማጽናት እጅግ ወሳኝና መሠረታዊ ሥራ ነው፡፡ ነፍሳትን የሚሰበስቡ እንዲህ ያሉ አባቶች፣ ሰበካ ጉባዔያት፣ አህጉረ ስብከቶች፣ ማኅበራት እንዳሉ ሁሉ በጣም የሚበዙት ግን ዝም ብሎ በዘልማድ የመጣውን ሥራ ያውም ያለ ዓላማ የሚሰሩ በመሆናቸው የገቡትን ነፍሳት ያህል ወይንም የበለጠ ከአማናዊው በረቱ ይወጣል፡፡ ተቋማቱና አባቶቹ ደግሞም ግድ የላቸውም፡፡ ስለዚህ የምዕመናን ቆጠራው ለሀገራዊ መረጃነት ብቻ ሳይሆን ለአጥቢያ ነፍሳት መከታተያነትም እንዲውል መሥራት ያስፈልጋል፡፡ በአዲስም ሆነ በመመለስ የሥላሴ ልጅነት ያገኙትን ያጽናቸው፡፡ ዝም ብዬ ሳስበው ለቤተ ክርስቲያን ትንሳኤ ቀዳሚ ተሰላፊ እነዚህ ይመስሉኛል፡፡ እኔም ወቃሽ ብቻም እንዳልሆን እኔስ ምን እየሰራው ነው ብዬ ራሴን ደጋግሜ እጠይቃለሁ፤ ጉድለቴንም አያለሁና ልታረም ይገባኛል፡፡ ወቃሽ ብቻም እንዳልሆን እኔስ ምን እየሰራው ነው ብዬ ራሴን ደጋግሜ እጠይቃለሁ፤ ጉድለቴንም አያለሁና ልታረም ይገባኛል፡፡

 3. Anonymous October 21, 2016 at 10:34 am Reply

  egziabher yerdachehu

 4. Anonymous October 22, 2016 at 1:11 pm Reply

  Egziabher yimesgen !

 5. Anonymous October 24, 2016 at 12:30 pm Reply

  God bless u !!!10q

 6. […] በስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብሩ ብቻ፣ በየዓመቱ እልፍ ሐዲሳን ጥሙቃንን እያስመዘግበ ቢኾንም፣ ለምእመኑ ቁጥር መቀነስም ተጠያቂ […]

 7. […] በስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብሩ ብቻ፣ በየዓመቱ እልፍ ሐዲሳን ጥሙቃንን እያስመዘግበ ቢኾንም፣ ለምእመኑ ቁጥር መቀነስም ተጠያቂ […]

 8. […] ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብሩ ብቻ፣ በየዓመቱ እልፍ ሐዲሳን ጥሙቃንን እያስመዘግበ ቢኾንም፣ ለምእመኑ ቁጥር መቀነስም ተጠያቂ […]

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: