ከፍተኛ የብአዴን አመራሮች አቡነ አብርሃምን አነጋገሩ፤ “ሃይማኖታዊ ግዴታዬን ነው የተወጣኹት”/ብፁዕነታቸው/

 • በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ፣ መንግሥት ምን ማድረግ እንደሚገባው፣አባታዊ ምክር ሰጥተዋል
 • መናገር ያለብኝን ነው የተናገርኩት፤ ሃይማኖታዊ ግዴታዬን ነው የተወጣኹት፤” ብለዋል

  *               *               *

 • ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ሰው አላት ያሰኘና እውነትን መሠረት ያደረገ ወቅታዊ መልእክት ነው
 • ኹሉም ብፁዓን አባቶች፣ እንዲኽ፣ የኅሊናቸውን እውነት የሚናገሩበት ቀን ሩቅ አይኾንም!!

/አስተያየት የሰጡ ምእመናን/

Aba Abre

ብፁዕ አቡነ አብርሃም፤ የባሕር ዳር፣ የምዕ/ጎጃም፣ የአዊና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

(አዲስ አድማስ፤ መታሰቢያ ካሳዬ፤ ቅዳሜ፣ መስከረም ፳፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም.)

በባሕር ዳር ከተማ መስቀል ዐደባባይ በተካሔደው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኙትና የሰሞኑ አገራዊ የመወያያ አጀንዳ የኾኑት፣ የባሕር ዳር፣ የምዕ/ጎጃም፣ የአዊ እና የመተከል ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን፣ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ከትላንት በስቲያ አነጋገሯቸው፡፡

ከውስጥ ዐዋቂ ምንጮች ባገኘነው መረጃ መሠረት፤ የብአዴን ከፍተኛ አመራር ከኾኑት የመንግሥት ባለሥልጣናት መካከል፡- የፌዴራል እና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃንና በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ህላዌ ዮሴፍ ናቸው፣ ሊቀ ጳጳሱን ያነጋገሯቸው፡፡ የመነጋገርያ አጀንዳቸውም፣ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይና መደረግ በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እንደኾነ ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡

በባለሥልጣናቱ እና በብፁዕ አቡነ አብርሃም መካከል ስለተካሔደው ውይይት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ባንችልም፣ ባለሥልጣናቱ፣ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ መንግሥት ምን ማድረግ እንደሚገባው አባታዊ ምክራቸውን እንዲሰጡ ብፁዕነታቸውን መጠየቃቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በባሕር ዳር ከተማ መስቀል ዐደባባይ በተከናወነው የደመራ በዓል ላይ፣ ብፁዕነታቸው በሰጡት ትምህርትና ቃለ ምዕዳን፣ “እንደ ፖሊቲካ አይደለም የምናገረው፤ እንደ ሃይማኖት ግን መናገር ያለብኝ ነገር አለ ብዬ አምናለኹ፣ መንግሥትንም በተመለከተ፡፡ በፖሊቲካ ከመነዘረው የእርሱ ጉዳይ ነው የሚኾነው፤ ምንጊዜም ችግር የመሪው እንጂ የተመሪው ሕዝብ አይደለም፤ የሕዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት፤ ወታደሩ ከዚኽ በኋላ የሰላምን ምላጭ እንጂ የመሣርያን ምላጭ መሳብ የለበትም፤ በመሣርያ ሰላም አይገኝም፤ አይተነዋል፤ እያየነውም ነው፤ ሊኾንም አይችልም፡፡ ጉልበታችን ሊያስመካን አይገባም፡፡ ሊያስመካን የሚችል ቢኖር መስቀሉ ብቻ ሊኾን ግድ ነው፤” ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በዐደባባዩ የመስቀልን በዓል ለማክበር የተሰበሰበው ምእመን፣ በሊቀ ጳጳሱ ንግግር በመደሰት ስሜቱን በእልልታ እና በጭብጨባ የገለጸላቸው ሲኾን፤ ብፁዕነታቸውም፣ “…ግዴለም፣ ግዴለም አጨብጭቡልኝ እያልኩ አይደለም፤ ዝም ብላችኹ ስሙ፤”  በማለት ጭብጨባም ይኹን ሙገሳ እንደማያስፈልጋቸው ተናግረዋል፡፡ የደመራው ክብረ በዓል ሲጠናቀቅም፣ “በዐደባባዩ የተሰበሰበው ምእመን በሰላም ወደ ቤቱ መግባቱን ሳላረጋግጥ ከዚኽ አልሔድም፤” በማለት ሕዝቡን ወደየቤቱ በማስቀደም ነው ዐደባባዩን የለቀቁት፡፡

የብፁዕ አቡነ አብርሃም ንግግር በማኅበራዊ ሚዲያው የመነጋገርያ አጀንዳ ኾኖ ሰንብቷል፡፡ ሊቀ ጳጳሱ በክብረ በዓሉ ላይ ያስተላለፉት መልእክት፣ የብዙዎችን ስሜት በእጅጉ የነካና ለበርካታ የሃይማኖት አባቶች ትምህርት አርኣያ ሊኾን እንደሚችል፣ አስተያየት ሰጪዎች ጠቁመውናል፡፡ መልእክታቸው፣ ምእመኑ በቤተ ክርስቲያንዋ ላይ የነበረውን ተስፋ የመቁረጥ ስሜት፣ በአስገራሚ ኹኔታ የቀየረና ኹሉንም የእምነት ተከታዮች አንድ ያደረገ መኾኑን የገለጹልን የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪ የኾኑት አቶ ማስረሻ ተስፋሁን፣ “ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ሰው አላት ያሰኘና፣ እውነትን መሠረት ያደረገ መልእክት ነው፤” ብለዋል፡፡

“አቡነ አብርሃም፣ እንደ ሃይማኖት አባትነታቸው ማድረግ የሚገባቸውን ነገር ነው ያደረጉት፤ መገረም ካለብን የምንገረመው፣ እንደ ብፁዕነታቸው ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን ሳይጠብቁ የሃይማኖት አባቶች ነን፣ በሚሉት ነው፤” ያሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ፣ኹሉም የሃይማኖት አባቶች ለኅሊናቸውና ለሃይማኖታቸው አድረው እንዲኽ በዐደባባይ እውነትን የሚመሰክሩበት ቀን ሩቅ እንደማይኾን ተስፋ አደርጋለኹ፤” ብለዋል፡፡

HIs Grace Abune Abreham
ከሰሞኑ የአቡነ አብርሃም ንግግር ጋር በተያያዘ፣ በባሕር ዳር ከተማ ዙሪያ ግምገማ መካሔዱንም ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው ብፁዕ አቡነ አብርሃም በሰጡት ምላሽ፣ “በወቅቱ የተናገርኩት መናገር ያለብኝን ነው፡፡ ሃይማኖታዊ ግዴታዬን ነው የተወጣኹት፡፡ ከዚኽ በዘለለ ለጋዜጠኞችም ይኹን ለሌላ አካል መግለጫ መስጠት አልፈልግም፤” ብለዋል፡፡

Advertisements

11 thoughts on “ከፍተኛ የብአዴን አመራሮች አቡነ አብርሃምን አነጋገሩ፤ “ሃይማኖታዊ ግዴታዬን ነው የተወጣኹት”/ብፁዕነታቸው/

 1. D/N Egualetsyone October 3, 2016 at 12:40 am Reply

  Bitsue abatachinin kutir a’nd bilenal, degmo kettayu man yehon? Endih new abat hakkun tenagro bimotis! Semaetinet aydel!? Endersachew yalewun yabzalin. “Kineu Lenente teabi tsega… medhanit lenefis wesiga”Yane yehagerachin selam yetebekal.
  Egzeabher yagelgilot zemenachewun yarzimilin!Amen!

 2. Anonymous October 3, 2016 at 3:40 am Reply

  E/r ye agelglotwon zemen yabzaln ytebkwot

 3. Anonymous October 3, 2016 at 5:18 pm Reply

  People, don’t don’t don’t rush to celebrate! There is no way in the world the officials talk to him with a good intent to address the issues. The problems (raised by millions) are very clear if they want to tackle it from the get go. The first attempt they will try to do is to go down to earth to show him how good they are and eventually to pursued him to stay on their side. They will talk and do everything in private with him until he decides these are good people and really from the people to the people, then they will use him as a tool to calm down the mass, and finally say him good bye and turn their face. So, my people please measure events by their outcome rather than the actions and words of a technocrat politicians.

 4. Anonymous October 4, 2016 at 4:09 am Reply

  በከፍተኛ አመራሮች ከተጠየቁት ጥያቄ መካከል “የህዝቡ ጥያቄ ይመለስ” ሲሉ የትኛው ጥያቄ ነው የሚል ነበረ!………

 5. Tarekegn tilahun Zeleke October 4, 2016 at 6:43 am Reply

  ትክክለኛ አባት እ/ግ ረጅም እድሜ ያድልልን

 6. Abebe October 4, 2016 at 10:52 am Reply

  Hulum sew yetesetewn halafinet teshekimo kemenor besimum kemeterat mebtun bicha sayhon gidetawun biweta enkwan Hagern Alemn mekeyer Yichal.. Egziabher Melkam Abatochn Ayasatan …. Asmesayochn gn Anfeligim mechem bihon

 7. አግደው አክርሶ October 7, 2016 at 4:54 am Reply

  ደስ የሚል አባታዊ ምላሽ የሰማዩ አምላክ ተጋድሎኣቸውን ይዝግብላቸው።

 8. Anonymous October 7, 2016 at 8:46 pm Reply

  betetu kedus abba abreham patreark kedamawe zepetros
  abo yebarkehot

 9. Anonymous October 8, 2016 at 9:16 pm Reply

  አቡነ አብርሐም ቀዳማዊ ፖትርያሬክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘአቡነጴጥሮስ ቀዳሜሰማይት
  ብፁዕ አባታችን በቃልዎት የተናገሩት የሰማይአምላክ አናገሮዎት ምንእንናገራለ ን ብላችሁ
  አታስቡ የሰማይአምላክ ያናግራችሁአል አምላካችን
  ፄመረጂሙን አይፍሩት ፀጉሩን እያልመዘመዘ ይተኞ እስከመከር ድረስ ሸሞንዯ ማትያስ ፎርጂድ ዘወያኔ

 10. Anonymous October 15, 2016 at 1:17 pm Reply

  http://www.eotcnewyork.org/blog/megabihaddis

  ጉዳዩ፦ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁን ይመለከታል

  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የካህናት አገልግሎትን እና በሀገረ ስብከት ጣልቃ ገብነትን አስመልክቶ በወሰነው ውሳኔ መሠረት ማንኛውም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ሥር ያለ አገልጋይ ካህን፣ ሰባኬ ወንጌል፣ ጳጳስም ይሁን ቆሞስ በቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር ሥር ባልሆነ በየትኛውም ቦታ መሄድ እንደማይችል፤ በአስተዳደር ሥር ወደሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ከመሄዱ በፊትም የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ፈቃድ ማግኘት እንደሚገባው፤ ይህንን ተላልፎ በሚገኝም ላይ ስለሚወደው ርምጃ መወሰኑ ይታወቃል።

  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አክብራና ቦታ ሰጥታ የሊቃውንት ማፍሪያዋ ከሆኑት ከፍተኛ ተቋማቶቿ በአንዱ መምህር አድርጋ የሰየመቻቸው መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ በቅርቡ ወደ አሜሪካ አገር መጥተው «እዚህ ቦታ ለመምጣት ዋጋ ከፍየበታለሁ!» ብለው በገለጹትና በዳላስ በሚገኝው ከቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ውጭ በሆነ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስን ትዕዛዝ ተላልፈው ለመገኘታቸው መልስ እንዲሰጡ እየጠበቅን እያለ አሁንም በድጋሚ በእኛ ሀገረ ስብከት ውስጥ ወደሚገኝና በፍርድ ቤት ክስ መሥርቶ በገዛ ፈቃዱ ከቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደር ውጭ በሆነና የተወገዙ ካህናት እናገለግልበታለን በሚሉበት ቦታ ላይ ለማስተማር እንደሚመጡ ለማወቅ ችለናል።

  እምነት እና ሥርዓትን ለደቀ መዛሙርት ከማስተማር በፊት አንድ መምህር ራሱ ሥርዓቱን እና ሕጉን ሳይከፍልና ሳይቀንስ ሊያምን እና ሊፈጽም ሲገባው መጋቤ ሐዲስ ግን ቤተ ክርስቲያኗ እና ምእመናን የሰጠቻቸውን የክብር ቦታ ለራስ ሃሳብ ማስፈጸሚያ ማዋልን መርጠዋል። ስለሆነም ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በክብር ተስተናግደው በሄዱበት ሀገረ ስብከት ዛሬ ይህንን ለማድረግ የወሰኑበትን ምክንያት እንዲያስረዱ የተሰጣቸውን ዕድል ተጠቅመው እስኪያስረዱ ድረስና ይህንንም የሚገልጽ ደብዳቤ እስከሚደርሳችሁ ድረስ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ በሀገረ ስብከታችን ውስጥ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ማስተማር እንደማይችሉ ተገንዝባችሁ እርሳቸውን ከመጋበዝም ሆነ እንደዚያ ያለ ጉባኤ ከመሳተፍ እንድትቆጠቡ በአጽንዖት እናሳስባለን።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: