የአእላፍ ቅዱሳን ሀገር ኢትዮጵያ: የሀገር ሽማግሌ ዐጣችን?

kumneger-magazine-cover-pic

(ቁም ነገር መጽሔት፤ 15 ዓመት ቅጽ 15 ቄጥር 264፤ መስከረም 2008 ዓ.ም.)

/ተክለ ኪዳን አምባዬ/

መነሻ አንድ፤

በቅርቡ ለአራተኛ ጊዜ የበጎ ሰው ሽልማት መካሔዱ ይታወሳል፡፡ ከሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ቀደም ብሎ ስለ ዝግጅቱ በተጠራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ ለፕሮግራሙ አዘጋጆች ከጋዜጠኞች የቀረበ አንድ ጥያቄ ነበር፡፡ የበጎ ሰው ሽልማት ከሚሸልምባቸው ዘርፎች መካከል፣ ‹‹የዓመቱ የሰላም ሰው›› የሚል ነበር፤ ነገር ግን ዘንድሮ የለም፤ ለምንድን ነው? የሚል ነበር፡፡ ከፕሮግራሙ አዘጋጆች አንዱ፣ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ‹‹ለዘንድሮ ብቻ ሳይኾን ላለፉት ተከታታይ ዓመታት የዓመቱን የሰላም ሰው ለመሸለም ዝርዝራችን ውስጥ ነበር፤ ነገር ግን የሰላም ሰው ብለን የምንሸልመው መስፈርቱን የሚያሟላ ሰው ባለማግኘታችን ልንሸልም አልቻልንም፤›› የሚል ምላሽ ሰጥቶ ነበር፡፡ ይህም፣ ከአገራችን 90 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ውስጥ ለተከታታይ ዓመታት አንድም የሰላም ሰው መፍጠር አለመቻላችን፣ ማኅበረሰባችን ሕመም ላይ መኾኑን አመላካች ነው፡፡

መነሻ ኹለት፤

ባለፈው ሳምንት እሑድ በተከበረው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ማግሥት፣ አንጋፋው ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም፣ ከአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጣቢያ የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ‹‹የወቅቱን የሀገሪቱን ችግር በውል ተገንዝቦ ሀገር የሚያስማማ ሰው ጠፍቷል፤ የሀገር ሽማግሌ የሚባል የለም፤ የሃይማኖት መሪዎቹም ትኩረታቸው ሌላ ነገር ላይ ኾኗል፤ ሀገሪቱ የጎረምሳ ሀገር ኾናለች፤›› ብለው ነበር፡፡


ርግጥ ነው፤ አገራችን ታማለች፤ በሕዝቦች መካከል ከዚኽ በፊት ያልታየ ቅራኔ ተፈጥሯል፡፡ ዜጎች ከቀዬአቸው እየተፈናቀሉ ነው፡፡ ጉዳዩ በመንግሥት እና በሕዝብ በኩል በተለያየ መነጽር እየታየ ገመዱ እየተጎተተ ነው፡፡ በአንድ አገር የዚኽ ዓይነት ውጥረት ሲከሠትና የሰላም አየር ሲበከል፣ ‹አለን› ማለት ያለባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ዝምታ አነጋጋሪ ነው፡፡ የአገራችን መረበሽም ኾነ መፍረስ አንድን ወገን ብቻ በመጉዳት እንደማይቆም ግልጽ ነው፡፡ በእሳት ዳር ያሉ ማናቸውንም ግለሰቦች እና የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ እሳቱ መብላቱ አይቀርም፡፡ ባይበላ እንኳ፣ መጥፎ ጠባሳውን ትቶ እንደሚያልፍ በሌሎች አህጉር የታየው እውነታ ምስክር ነው፡፡

አገር በታመመችበት ወቅት፣ ‹‹አንተም ተው! አንተም ተው!›› ማለት ያለባቸው አካላት እና ዜጎች፣ ጉዳዩን በቸልታ መመልከታቸውና ግድ የለሽነታቸው ሊፈጥር የሚችለው አደጋ፣ እንደ ሩዋንዳ ያሉ አገሮች ያለፉበትን የእርስ በርስ እልቂት የልጆች ጫዋታ ሊያስመስለው ይችላል፡፡

አገር በፖሊቲካ ብቻ አትመራም፡፡ በሃይማኖት፣ በሞራል እና በዕውቀት ጭምር እንጂ፡፡ ይህን ማኅበረሰባዊ ሓላፊነት የተሸከሙ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ፖሊቲካውን ወደ ጎን ትተው ስለ አገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመምከር ሊሰበሰቡ ይገባል፤ ከውጥረቱም ኾነ ሊነድ ካለው እሳተ መዓት ለመዳን ሐሳብ ሊያዋጡ፣ ምክር ሊለግሡ በሚገባቸው ሰዓት ላይ ያለን ቢኾንም፤ ዳር ቆመው የመመልከታቸው አመክንዮ ግልጽ አይደለም፡፡

ጉዳዩ፣ የኹሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ጉዳይ ቢኾንም፣ ተደማጭ የሚባሉ አካላት፣ አጀንዳ አዘጋጅተው ኅብረተሰቡ ተቀራርቦ ሊነጋገር የሚችልበትን መድረክ ሲያፈላልጉ አይታይም፡፡ ከዚኽ ነፃ እና ገለልተኛ ውይይት የሚፈልቀው ሐሳብ፣ ኹሉንም ወገኖች የሚገሥጽና ተግባራዊ መረጋጋት እንዲመጣ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ይህ የውይይት መድረክ፣ የአገሪቱን ሕዝቦችም ኾነ የፖሊቲካ ኃይሎችን ወደ ብሔራዊ ዕርቅ እና ወደ ብሔራዊ መግባባት ጠረጴዛ ሊያመጣቸው ይችላል፡፡

የሃይማኖት አባቶች ሚና

ባለፉት ኃምሳ ዓመታት፣ በኢትዮጵያ ያሉ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፖሊቲካ ሥርዓቱ ተነጥለው ለመቆም ያደረጉት ጥረት አነስተኛ በመኾኑ ሳቢያ፣ የወቅቱ ዓይነት ችግር ሲከሠት ኅብረተሰቡ ከሃይማኖት አባቶች ተስፋ የሚያደርገው የአስታራቂነት ሚና ጠባብ እንደ ኾነ ይታወቃል፡፡ እንዲያውም ግልጽ በኾኑ መድረኮች ሳይቀር፣ ሕዝቡ ለሃይማኖት አባቶቹ ያለው ግምት እየተቀዛቀዘ በመምጣቱ፣ አገራችን የዚኽ ዓይነቱ ችግር ሲገጥማት ዓይኑን ወደ ሌሎች ማማተር ጀምሯል፡፡ የሃይማኖት አባቶች ሚና ላልቶ መታየቱም፣ ሊሰጣቸው ይገባ የነበረውን የአስታራቂነት ሚና አላሳጣቸውም ማለት አይቻልም፡፡

የሃይማኖት አባቶች ወደ አመራር የሚመጡበት መንገድ ፍጹም መንፈሳዊ መኾን ሲገባው፣ በአንድም ኾነ በሌላ መንገድ የመንግሥታት እጅ መኖሩ፣ ለተቀመጡበት ወንበርና ለተሠየሙበት መንፈሳዊ ሕይወት ታማኝ እንዳይኾኑ ጋሬጣ ኾኖባቸው ቆይቷል፡፡ አገራችን በሕገ መንግሥት ደረጃ፣ መንግሥት እና ሃይማኖት የተለያዩ መኾናቸውን፣ አንዱ በሌላው ጣልቃ እንደማይገባ በግልጽና በማያሻማ ኹኔታ የተደነገገ ቢኾንም፤ አብያተ ክርስቲያንና አብያተ መስጊዶች፣ የመንግሥት ካድሬዎች መፈንጫ መኾናቸው የዐደባባይ ምሥጢር ነው፡፡

በአገራችን፣ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ለታየው አለመረጋጋትና ረብሻ፣ የሃይማኖት አባቶች ሊጫወቱ ይገባ የነበረውን ሐቀኛ ሚና ሳይወጡ በመቅረታቸው ሳቢያ ውጥረቱ ከሯል፡፡ በሰባት የእምነት ተቋማት ከአምስት ዓመታት በፊት፣ ‹‹የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ›› የተሰኘ ማኅበር መመሥረቱ ይታወቃል፡፡ በአኹኑ ወቅት የሚመራው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ነው፡፡

‹‹በመከባበርና በሰላም አብሮ የመኖር ዕሴታችንን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ›› በሚል መርሕ በ2003 ዓ.ም. የተመሠረተው ይህ የእምነት ተቋማት ጉባኤ ዋና ዓላማው፣ በእምነቶች መካከል ስለሚኖረው ግንኙነት እንጂ በትውልዱ መካከል ስለሚነሡ ልዩ ልዩ ቅራኔዎች መፍትሔ ለማበጀት የሚችል አያስመስለውም፡፡ ጉባኤው የተመሠረተው በምእመናን ፍላጎትና ይኹንታ ሳይኾን በመሥራች የእምነት ተቋማቱ ዋና ዋና መሪዎች ፍላጎት መኾኑ ደግሞ፣ ወደ መንበሩ ከመጡበት መንገድ ፍትሐዊነት ጋር የተያያዘ ያደርገዋል፡፡ ችግር ሲደርስ ብቻ፣ ወደ ብዙኃን መገናኛ ብቅ እያሉ፣ መንግሥት ለወሰደው ርምጃ ቡራኬ የመስጠት አካሔድ፣ የጉባኤውንና የተቋማቱን ተኣማኒነትና መንፈሳዊነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ የከተተው ኾኖ ይገኛል፡፡

ባለፈው ዓመት፣ በአብዛኛው የኦሮሚያ ክፍሎች፣ ከአዲስ አበባ የማስተር ፕላን ማስፋፊያ ጋር በተያያዘ ውዝግብ በተቀሰቀሰበትና ብዙዎች ሕይወታቸውን ባጡበት ወቅት፣ በየካቲት ወር የተሰበሰበው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤው፣ ‹‹ለደረሰው የሰው ሞት አዝነናል›› ከማለት ውጭ፣ ግድያውንና ደም መፋሰሱን ሊያወግዝ አለመቻሉ የተጠበቀ ነገር ኾኗል፡፡

የሃይማኖት አባቶች፣ ኢ-ሰብአዊ እና ኢ-ፍትሐዊ ድርጊት ሲፈጸም፣ ለምን ብለው መጠየቅ ባይችሉ እንኳ፣ ለድርጊቱ ቡራኬ መስጠት በሚመስል አኳኋን መግለጫ ማውጣታቸው፣ በተኣማኒነታቸው ላይ ጥላ አላጠላም ማለት አይቻልም፡፡ ከዚኽ አለፍ ሲልም፣ የሰዎች ሕይወት አላግባብ ሲያልፍ እንደየእምነታቸው ጸሎት አለማወጃቸው፣ መንፈሳዊ ተልእኳቸውን መዘንጋታቸውን እንደሚያሳይ ነው ብዙዎች የሚያምኑት፡፡

የሃይማኖት መሪዎቹ በግለሰቦች የሚጠየቁበት አካሔድ ባይኖርም፣ በሚያምኑበት ፈጣሪ እንደሚጠየቁ መዘንጋታቸውን ማሳያዎች አሉ፡፡ በተለይም በየጊዜው በሚያወጧቸው መግለጫዎች፣ አማናዊ ፍርድና ፍትሕ የፈጣሪ ሥራ መኾኑን በመርሳት ወይም በመካድ፣ ‹‹አጥፊዎች ለፍርድ ይቅረቡልን›› ማለታቸው፣ ሃይማኖታዊ ትእዛዝን እንደ መጣስ ይቆጠርባቸዋል፡፡ አስቀድመው ያጠፉ ወገኖችን ገሥጸው ወደ ቀናውና ትክክለኛው መንገድ ከመመለስ ይልቅ፣ ለበለጠ ችግርና መከራ እንዲዳረጉ መማለድ፣ በአመራር ደረጃ ከተቀመጡ አባቶች የሚጠበቅ ነውን? ፈሪሃ እግዚአብሔር በምእመኑ ላይ እንዲያድር ከመሥራት ይልቅ፣ አምስት ዓመታትን እየጠበቀ የሚመጣውን ምርጫ ለመታዘብ በየምርጫ ጣቢያው መዞራቸውም አነጋጋሪ ነው፡፡

የምሁራን ሚና

አገራችን ደክማ ያስተማረቻቸው ምሁራን፣ የዚኽ ዓይነት ችግርና ውጥረት ሲከሠት ዳር ቆመው የመመልከታቸው ልምድ አዲስ አይደለም፡፡ በርግጥ በደርግ መንግሥት ውድቀት ዋዜማ ላይ እየመጣ ከነበረው አስፈሪ የእርስ በርስ እልቂት ለመዳን፣ ‹‹የራሳችንን አስተዋፅኦ ማድረግ አለብን›› ያሉ ምሁራን፣ የመፍትሔ ሐሳብ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡ ሐሳባቸው፣ በደርግም ይኹን በኢሕአዴግ ዘንድ ተቀባይነት ባያገኝም እኒኽን ምሁራን ታሪክ ያስታውሳቸዋል፡፡

በምሁራኑ የመፍትሔ ሐሳብ የቀረበለት የደርግ መንግሥት፣ በ11ኛው ሰዓት ላይ እንኳ ራሱን ለመመርመር ሳይችል የቀረ ቢኾንም፣ ምሁራኑ በጊዜው የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ ሓላፊነት ተወጥተዋል፡፡ አገራዊ ውጥረት በሰፈነበት ጊዜ ኹሉ፣ የምሁራን አስተዋፅኦ አስፈላጊ መኾኑን ብዙዎች ያምናሉ፡፡ ከጥቂት ዓመታት ወዲኽ ግን ምሁራን ራሳቸውን በልዩ ልዩ ምክንያት እየጀቦኑ፣ ከፖሊቲካም ኾነ ከማኅበራዊ ተሳትፎ መራቃቸው እየታየ ነው፡፡ የውይይትና የንግግር መድረኩን የመክፈት፣ ችግሩን የመተንተንና የመፍትሔ አቅጣጫውን የማመላከት ሞራላዊና ሞያዊ ድርሻ የምሁራን ነው፡፡

ከዚኽ በአንፃሩ፣ አንዳንዶቹ የመንግሥት ካድሬ መኾናቸውን አፍ አውጥተው ሲናገሩ፣ ሌሎች ደግሞ ራሳቸውን በጽንፈኝነት መድበው ይታያሉ፡፡ ሕዝብ በተለያዩ ግፊቶች ወደ ፍጅት ሲያመራ፣ በጎራ እንዲፈራረጁም ኾነ በዝምታ እንዲሸበቡ የቀሰሙት ዕውቀትና ምሁራዊ ሚናቸው አይፈቅድላቸውም፡፡ አንዱን ደግፈው ሌላውን ማውገዝ አይኖርባቸውም፡፡ በርግጥ እየተስፋፋ ያለው ሁከት በጊዜ መፍትሔ ካልተበጀለት ለከፋ ችግር ሊዳርገን እንደሚችል የሚናገሩ ጥቂት ምሁራን አሉ፤ በድምፃቸው ማነስ፣ የተንሰራፋው ምሁራንን የማግለል ዘመቻ ሰለባ ኾኑ እንጂ፡፡ በየጊዜው ከሚፈጠሩ ውጥረቶች አንዱ መውጫ መንገድ፣ ከምሁራን ጋር ግልጽ ውይይት ማድረግ ነው፡፡

የብሔራዊ ዕርቅ እና መግባባት አስፈላጊነትና ጥቅም

ብሔራዊ መግባባት እና ዕርቅ፣ እጅግ ተፈላጊ ማኅበራዊ እሴቶች እንደኾኑ ግልጽ ነው፤ ሀገርን ከውድቀት ለማዳን ዓይነተኛ መፍትሔዎች ናቸውና፡፡ ሰላምን ለመመሥረትና ለማጽናት ወሳኙ መሣርያ በግልጽ መነጋገርና መወያየት እንደኾነ በጉዳዩ ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች ያስገነዝባሉ፡፡ ብሔራዊ ዕርቅና መግባባት፣ ከሌሎች የትግል ስልቶች አግባብነትና አተገባበር ጋር የሚወዳደር አለመኾኑ ቢታወቅም፣ በተለይም ሥልጣን ላይ ያሉ መንግሥታት በቀላሉ እጃቸውን የሚሰጡለት ስልት እንዳልኾነም የጥናቱ ተግዳሮቶች ያሳያሉ፡፡

ብሔራዊ ዕርቅ እና መግባባት፣ ከሌሎች ሰላምን የማስፈኛ መንገዶች ጋር/ለምሳሌ፡- በጦርነት ከማሸነፍ ጋር/ ፈጽሞ የሚወዳደርና የሚነፃፀር አይደለም፡፡ በተለይም አገራችን አኹን ካለችበት ወቅታዊ ኹኔታ አንፃር፣ ብሔራዊ ዕርቅና መግባባት የሚያስፈልገው፣ ኢትዮጵያችን ያለችበት ዘርፈ ብዙ ችግር ተባብሶ ወደ ከባድ ቀውስ እንዳትገባ ስለሚያደርግ እንደኾነ ግልጽ ሊኾን ይገባል፡፡ ችግሮችን፣ በሕዝባዊ ዓመፅም ኾነ በጦርነት ለመፍታት መሞከሩ የሚያስከትለው ቀውስ፣ በቶሎ ማቆሚያ እንደማይኖረው፣ የበርካታ አገሮችን ተሞክሮ በመጥቀስ የሚያስጠነቅቁ ብዙዎች ናቸው፡፡

ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ “Democracy and Its’ Trade-off: Ethiopia’s Path to National Reconciliation” በሚል ርእስ እ.አ.አ በ2014 ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ እንዳመለከቱት፣ ‹‹ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በምርጫ፤ ካልኾነ በጦርነት፤ ካልተቻለ በሕዝባዊ ዐመፅ ማምጣት አደጋ ካለው በብሔራዊ መግባባት የትብብር መንግሥት ከመመሥረት ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ የለም፤›› ሲሉ የሰላም ማስፈኛ መንገዶችን ያመላክታሉ፡፡

ብሔራዊ መግባባትን ለማስፈን የየአገሮቹ ነባራዊ ኹኔታም ሊተኮርባቸው ከሚገቡ ነገሮች መካከል ዋናው እንደኾነ ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ፡- ሙሉ በሙሉ ወደ ውድመት እያመሩ ባሉ እንደ እነሶሪያ እና ሊቢያ ዓይነት አገሮች ውስጥ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ጊዜው ረፍዷል ለማለት ይቻላል፤ ምክንያቱም ግጭቱ ከቃላት አልፎ ወደለየለት ደም መፋሰስና አውዳሚነት ስለገባ ብሔራዊ መግባባትን ለማስፈን ተጨማሪ ጊዜ ይጠይቃል፡፡

ብሔራዊ መግባባት በኹሉም ወገኖች እስከሚታመንበት ጊዜ ድረስ፣ ለማፈንገጥ የሚሞክሩ ወገኖች መኖራቸው ነባራዊ ሐቅ ነው፡፡ ያም ኾኖ ቅራኔና ቁርሾ ባለበት ሀገር፣ መንግሥት ባለጠመንጃ በመኾኑ፣ ብሔራዊ መግባባቱን በተፈለገው ፍጥነት ለማምጣት ሊያስቸግር ይችላል፡፡ ይህን በተመለከተ፣ ተክሉ አባተ የተባሉ ጸሐፊ፣ “Reconciliation: the way out” በተሰኘ ጽሑፋቸው፣ ‹‹የመንግሥት ባለሥልጣናት ሳይቀሩ ስለሚፈልጉት፣ ብሔራዊ መግባባትንና ዕርቅን ለመተግበር የማይቻል አይደለም፤›› ሲሉ በሰላም የመኖር ፍላጎት የኹሉም ግለሰቦች ፍላጎት መኾኑን በመጥቀስ ይሞግታሉ፡፡

ብሔራዊ ዕርቅ በሚገባ ከተያዘና ከተጠናቀቀ ዓምባገነኖችን ሳይቀር ነፃ የሚያወጣ ነው፡፡ ኹሉም ተሳታፊ ስለሚኾን ጦርና የጦር ወሬዎች ታሪክ እየኾኑ ይሔዳሉ፤ ይህ መንገድ የሰው ሕይወትም ኾነ ንብረትና ሀብት አያጠፋም፡፡ በመኾኑም፣ ይህ የፖሊቲካ መሥመር ጭስ አልባ ሊባል ይችላል፡፡ በሚያስፈራ ዝምታ ውስጥ ያለውን የሰፊውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀልብ ሊስብ ይችላል፡፡ ለመግባባትና ለዕርቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ፣ በዓለም ኅብረተሰብ ዘንድ ተቀባይነት ስላለው፣ አስፈላጊው ድጋፍና ማበረታቻ ለማግኘት አይከብድም፡፡ በመጨረሻም ይህ የትግል ስልት ቀጣይነት ያለው ሰላምና ዕድገት እንዲመጣ ፈር ይቀዳል፡፡/ተክሉ አባተ፤ 2013/2014/

ርግጥ ነው፣ ዘላቂ ሰላም ለማስፈንና ጤናማ ማኅበረሰብ ለመፍጠር፣ መግባባትና ዕርቅ ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡ ዳዊት ተሾመ“On the question of national reconciliation” በሚል ርእስ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ፣ ብሔራዊ ዕርቅና መግባባት፥ በቋንቋ፣ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በፖሊቲካ ምክንያት ጥላቻ ያደረባቸውን አካላት ለማገናኘት እንደሚረዳ ጠቁመዋል፡፡

ምን ማድረግ ይቻላል?

ቀዳሚው ነገር፣ የችግሩ አሳሳቢነት ላይ ግልጽ አቋም መያዝ ነው፡፡ በጉዳዩ ላይ በግልጽ መነጋገር የሚችሉ ዜጎች ኹሉ፣ ሐሳባቸው ተደራሽ ሊኾን በሚችልበት መንገድ ሐሳብ ማዋጣት ያስፈልጋቸዋል፡፡ በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ፣ በመምህርነት ያሳለፉ፣ ሀገራዊ አጀንዳዎችን በግልጽ አውጥተው በመናገር የሚታወቁ፤ በማንኛውም የፖሊቲካ ፓርቲ ውስጥ ተሳትፎ ያላደረጉና በድጋፍም ይኹን በተቃውሞ ሐሳብ ሰጪነታቸው የማይታወቁ ግለሰቦች፤ ኹሌም የትውልዱና የአገራችን ትኩሳት የሚያሳስባቸውና ባገኙት አጋጣሚ ኹሉ ተቆርቋሪነታቸውን የሚያሳዩ የብዙኃን መገናኛና የኪነ ጥበብ ሰዎች እንዲኹም ሀገር ወዳድ ዜጎች ኹሉ ሊሳተፉበት ይችላሉ፡፡

በሀገራችን የተፈጠረውንና እያቆጠቆጠ የመጣውን ጎሳ ተኮር መጤ ጠልነት፣ ከሥር መሠረቱ ችግሩን አጥንቶ ለመንቀል፣ የጠፉት የሀገር ሽማግሌዎች ከያሉበት ብቅ ብለው ትውልዱን ሊታደጉት ይገባል፡፡ ሽማግሌነት በዕድሜ ብቻ የሚመጣ የሓላፊነት መንበር ሳይኾን፣ በዕውቀትና በአስተሳሰብ መረጋጋት ጭምር ነውና፣ ኹሉ የሚሳተፍበት መድረክ መኾን ይገባዋል፡፡ ለዚኽም፣ ኹሉም ዜጎች ወደ ሰላሙ ሜዳ በመግባት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ ይገባል፡፡

አገሬው የሚያከብራቸውና የሚከተላቸው ‹‹ሽማግሌ›› ዜጎች፣ በአንድ ዓላማ ሥር ተሰባስበው ሕዝብን፣ መንግሥትንና የተለያዩ ኃይሎችን ለማግባባት በሚያደርጉት ጥረት፣ ሕዝብም እንደ ሕዝብ፣ ሀገርም እንደ ሀገር ከጥፋት የሚድኑበት ይኾናል፡፡

የማጠቃለያ ሐሳቦች

ለሀገር የጸና ሰላምና ጤናማ ዕድገት ወሳኝ የኾነው ብሔራዊ ዕርቅና መግባባት እንዲመጣ፣ በዋናነት ግንባር ቀደም ሚና ሊጫዎት የሚገባው፣ መንግሥት ስለመኾኑ አያከራክርም፡፡ ኾኖም፣ ይህንኑ የመግባባት አስፈላጊነት ተንትነው ሊያቀርቡ የሚገባቸው፣ በገለልተኝነት የተደራጁ የሀገር ሽማግሌዎች ያስፈልጋሉ፡፡

የሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት ተቋማት ይኹን ከምሁራን ሊውጣጡ ይችላሉ፡፡ ከኹሉም የኅብረተሰብ ክፍል መውጣጣታቸውና መደራጀታቸው እንደተጠበቀ ኾኖ፣ ከዚኽ በፊት በታየ ፖሊቲካዊ ሒደት ተሳትፈው በኅብረተሰቡ ጥቁር ነጥብ ያልተሰጣቸው መኾን ይገባቸዋል፡፡

በመኾኑም ገለልተኛና አንፃራዊ በኾነ የዘረኝነትና የጎሰኝነት በሽታ ያልተያዙ ወይም የአንደኛውን ወገን የመደገፍም ኾነ የመቃወም ዝንባሌ ያላሳዩ፣ ንጹሕ ኢትዮጵያውያን የተሰባሰቡበት ብሔራዊ ሸምጋይ አካል መመሥረት ተገቢ ነው፡፡ ይህን አካል የሚያቋቁመው ስብስብ፣ የሚቋቋምበት መስፈርት፤ የሚኖረው ዝርዝር የሥራ ድርሻ፣ የሚጠቀማቸው ዘዴዎች… ወዘተ ጥርት አድርገው በማዘጋጀት ለውይይት ቢያቀርቡ መልካም ይኾናል፡፡ ይህ ቀላል ሥራ ስላልኾነ፣ የስብስቡ አባላት፣ ስሜታቸውን የሚቆጣጠሩና ሞራላዊ ብስለት ያላቸው፤ ዐዋቂዎችና አስተዋዮች እንዲኹም የመግባባትና ጫናን የመቋቋም አቅም ያላቸው ሊኾኑ ይገባል፡፡

ከዚኽ አንፃር የሚከተሉት ኢትዮጵያውያን፣ ብሔራዊ የመግባባት ሥራውን ለመጀመር ይችላሉ ብዬ አምናለኹ፡፡ ምናልባት ፖሊቲካዊ ፍላጎት ወይም አንዳች የፖሊቲካ ፍላጎት ያላቸው ከኾኑ በቅንነት ራሳቸውን ከስብስቡ ሊያገሉ እንደሚችሉ ታሳቢ ሊደረግ ይገባል እላለኹ፡፡ በጥቆማው የቀሩ ወይም መካተት ያለባቸው ካሉ አንባብያን ሐሳብ ሊሰጡበት ይችላሉ፡፡

 • አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ
 • አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ
 • ወ/ሮ አበበች ጎበና
 • አቶ ይመስገን ሞላ
 • አቶ ብንያም በለጠ(መቄዶንያ)
 • ፕሮፌሰር ገቢሳ እጀታ
 • ተ/ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው
 • ዶ/ር ምሕረት ደበበ
 • ዶ/ር ብርሃኔ ረዳኤ
 • ደራሲና ሠዓሊ አሰፋ ጉያ
 • ማኅደር ገብረ መድኅን
 • ወ/ሮ ቤተ ልሔም ጥላሁን
 • ኢ/ር ሰውነት ቢሻው
 • አትሌት ቀነኒሳ በቀለ
 • ገነነ መኩሪያ
 • መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ
 • ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
 • ዑስታዝ ሐሰን ታጁ
 • ዶ/ር ወዳጄነህ መሐሪ
 • አዜብ ወርቁ
 • አርቲስት ፈቃዱ ተክለ ማርያም
 • አርቲስት ሰሎሞን ቦጋለ
 • ጋሽ አበራ ሞላ
 • አርቲስት ፀሐዬ ዮሐንስ
 • አርቲስት ቻቺ ታደሰ
 • አርቲስት ሚካኤል በላይነህ
 • ሠርጸ ፍሬ ስብሐት

 

Advertisements

19 thoughts on “የአእላፍ ቅዱሳን ሀገር ኢትዮጵያ: የሀገር ሽማግሌ ዐጣችን?

 1. Anonymous September 18, 2016 at 2:49 pm Reply

  Prof. Ephrem Yishaq should be added.

 2. Anonymous September 18, 2016 at 3:29 pm Reply

  Dn. Daniel should be out!

 3. Anonymous September 18, 2016 at 4:32 pm Reply

  ato wubshet werkalemahu should be out

 4. Anonymous September 18, 2016 at 9:59 pm Reply

  One of the problem is religious interference, as indicated by Muslim protesters for years. I only saw a single Muslim in the list, do you not think this rises a serious legitimacy issue by our Muslim friends? My second point is being a national hero doesn’t make you a skilled person to resolve politial differences. Politics is one of the most complicated stuff on earth. As such crying blood, good speach or writing may not bring the much needed solutions. So, you need to include some technocrats and charismatics individuals cable of navigating the rugged terrain and inspire millions along the way. Please include some from the diaspora…

 5. ayahilush September 19, 2016 at 9:33 am Reply

  You are dangerous pretender including many of the names listed at the end. Shimgliina is only between equivalent opponents. Not between brutal murderers and mass victims. You have no courage to speak the truth in black and white manner because you have businesses to lose. People like you don’t stand with victims, but only calculate their business advantage with current or coming government. This article only exposes who you are. Nothing more.

 6. yinager adwa September 19, 2016 at 9:45 am Reply

  STOP!!! FEW INDIVIDUALS INTENTOINALLY AND MOST OF OTHERS INNOCENTLY ARE TRYING TO CREATE ESCAPE ROUTE FOR THE MURDERS. NEVER. NEVER. YOU ARE KILLING US AGAIN
  THE ONLY GODLY AND GENUINE SOLUTION IS PAY COMPENSATION FOR VICTIMS, STAND FOR TRIAL. AND CHANGE THE RACIST POLICIES. GOD KNOWS WHO YOU ARE. WE ALSO KNOW THAT YOU ARE PRETENDERS.

 7. Anonymous September 19, 2016 at 10:41 am Reply

  you are one of those people who crucified Jesus again and again!!!! What else the victims have to compromise apart from losing their loved ones from kids, BROTHERS, SISTERS, FATHERS, MOTHERS? what else???? Again, thousands are languishing in torture, arson. What else you want them to compromise for mediation??? you are snake, bearing just the name of Christians. you have no regard for life, pains , and deaths of innocents. we will fight back and destroy not only them and their supporters, but also wolfs like you….until justice is perfectly served.

 8. Anonymous September 19, 2016 at 10:56 am Reply

  This is a good idea. I don’t complain about the selected members, since I don’t have any one to add or since there is no one saying I can do it. The point is there has to be someone to start the process. While doing that if there is a problem a solution will be formulated STEP BY STEP. Complaining being blind folded is what we have been doing for as long as I know . Let’s start crafting solutions. Always there are problems, but if we can’t start from one how can we continue let alone solving?

 9. Abel September 19, 2016 at 12:01 pm Reply

  In the wake of clear brutality, if you don’t have courage to stand up with the victim, all you are doing is craving for more recognition. your recognition comes from at the expense of kids murdered? you are snake.
  this is not ye balina ye mist guday. it is the killer vs the dead. nothing to mediate. everyone will get what he/she deserve.

 10. Anonymous September 19, 2016 at 12:57 pm Reply

  ይህ ነገር የተቀደሰ ሐሣብ ነበረ ግን ልእቡ በሰይጣን መንፈስ የታጠበ ቡእድን መቸ ጀሮ አለዉ
  ከሐይማኖት አባት እስከ አገር ሽማግሌ ሁሉን ያሣዘነ ሁኖአል ይባስ ብሎ በዉቨቱ ቀጥሎበታል
  ለሀገር ክብር ያለዉን እና በፈራሔእግዜብሔር የሚኖረውን ያሀገርተረካቢ ወጣቶችን አንድባንድ እየገደለነዉ ያለ
  ባሁኑምሰሐአት ያለዉ ገዡዉ ወያኔ ለማንም ነገር ልቦናይስጠዉ ህዝቡእንደሆነ ከጠረፍ እስከጠረፍ አዉቆታል

  • Anonymous September 20, 2016 at 2:33 am Reply

   እነዚህ ሰዎች ሽማግሌ ሊመርጡ ነው ወይስ ራሳቸውን ሽምግልና ሊልኩ ነው? ቢሆንስ የፈሰሰው ደም፤ የጠፋውን ነፍስ፤ የወደመውን ንብረት የመሳሰለውን ምን ሊያደርጉት ነው? ወያኔን በገዳይነቱ እንዲቀጥል ምስኪኑ ሕዝብ ደግሞ እየተገደለ እንዲኖር ለማረጋገጥ… ወይስ የወያኔ አሰራርና እድሜ ማስረዘሚያ ዘዴ… እባካችሁ ሰዎች ምከሩዋቸው እነዚህ ሰዎች አርፈው ይቀመጡ

 11. Anonymous September 19, 2016 at 10:12 pm Reply

  this is called beating around the bush or dark shooting or ignoring the Elephant in the room…

  speak the truth…from where you will have clear direction on how to solve it. If you ignore the truth from the beginning, you can never bring real solution.
  you have the right to be scared, we accept that. if you are afraid, just keep quiet, Better than misleading innocents.
  most of you have clear understanding of the right and wrong, but you don’t want stand for that for any reason. it’s ok. But, trying to be smart on innocents will back fire. keep in mid that there are millions who read and listen to what you say critically. you don’t know them until it is too late.

 12. Anonymous September 20, 2016 at 2:41 am Reply

  I don’t understand what these people are going to do? who ask them to be mediators… and what are they going to say to the people? … keep going be killed … lose your land, dignity, etc. …. and say to Woyanie …. long live woyanie! so they can get free land, praise from their woyanie lords…. please stay away and live your own lives.

 13. Anonymous September 20, 2016 at 9:41 am Reply

  DANIEL kIBRET , WIBISHET WERKALEMAHU….????????????? ዳንኤል ክብረትና ውብሸት ወርቃለማሁ……..ቂቂቂቂቂ አለ፡፡ ጋዜጠኛው…….በጥላቻ ጥግ የያዙ ፣ ቀድመው ከራሳቸው ጋር መታረቅ ያቃታቸው……. እንዴት ? አስታራቂ ይሆናሉ …….እባካችሁ ሁሉንም ወርቃማ እድሎች እና ሐሳቦች በግል አስተሳሰባችሁ አትቃኙት አታበላሹትም፡፡

 14. Anonymous September 20, 2016 at 9:45 am Reply

  ዳንኤል ክብረትና ውብሸት ወርቃለማሁ……..ቂቂቂቂቂ አለ፡፡ ጋዜጠኛው…….በጥላቻ ጥግ የያዙ ፣ ቀድመው ከራሳቸው ጋር መታረቅ ያቃታቸው……. እንዴት ? አስታራቂ ይሆናሉ …….እባካችሁ ሁሉንም ወርቃማ እድሎች እና ሐሳቦች በግል አስተሳሰባችሁ አትቃኙት አታበላሹት፡፡

 15. Anonymous September 22, 2016 at 7:15 pm Reply

  በፍራንክፈርት እና በመለዋ ጀርመን ለምትገኙ ሀአገርወዳድ ኤትዮጵያውያን በሙሉ ያገራችን ህዝቦች በወያኔካድሬዎች
  ተገለዉ ሀዘናችን ሣይጠፍ በፍራንክፈርት ከተማ የወያኔካድሬ አባ ሲራክ ወልደስላሴ ግብራበሮቹ
  ከወያኔጳጳስ አባ ሙሴጋር የመስቀልን ባአል የሰይጣን ምሥል ያአለበትን ባዴራ ይዘዉ ደስታቸዉን ሊገልጡስለሆነ
  ሀአገርወዳድ ኢትዯጵያውያን በሰህአቱበመገኝት አዘናችን በተቃዉሞ እድንገልጥና የወያኔካድሬ ሲራክ ወልደበድን
  የተባለዉ የወያኔ ሰላይ ስደት ሲጠይቅ ጎንደነኝ የዉም አማራ ብሎ ሰለጠየቀ ፖስፖርቱም ጎንደር ሰለሜል እስካሁን በዜዉም
  እጂተፍንጂ ለጀርመን መንግስት እምናጋልጥበት እንዲሆን እያልን ትክክለኝዉን ባንዴራይዘን አቤትዉታችን ለጀርመንመንግስት
  እድናሰማና የገዳይወያኔ ተባባሬቄሶችን ለይትዮጵያዉያን እድናጋልጥ የወያኔቆንስላም እደሚገኝ ለማወቅችለናል
  ቦኦታ የተለመደዉ ፍረዉን ፍሬደን ኪርሸ ነዉ

  ወያኔ ሰራኡ መከፋፈል ካንድ መንግስት ኣገርን አመራለሁ ከሚል አካል ቀርቶ ካንድ ግለሰብ
  እንኳ በመይጠበቅ አንተ ኦረሞ አማራ ትግሬ እብቫንጉል ጉራጊ ወዘተ እያለ የሚከፋፍል
  አሁን እሒ ነዉ መንግስት ለምን አንድ ትሆናላችሁ ብሎ እናትና ልጅ የሚለይ አረመኔሰወበላ የወያኔ ሰወበላ
  የሰይጣን ቡድን ህዝብ እቢብሎ በግድ እየገደልኩ እገዛህአለሁ እያለስለሆነ ወያኔ እየገደለ ሊገዛን አይችልም

  የኢትጵያ ህዝብ ሆይ እስከ መቸ ነው እያንቀላፋን ቀኝ እምንገዛ በወያኔ
  ስለዚህ ሁሉም ለነጻነቱ ሆብለን እንነሣ እች ሐገር የሁላችን ናት ተጠቃሜወች ጥቂቶች ተጨቋኔዎች ብዙወች ለምን ይሆናል
  እንዲህ ሁኖ ከመኖር ሞትይሻላል ወያኔ

  ወያኔ ኢትዮጵያን እስከመጨረሸው በቀኝ እገዛት አለሁ ብሎነዉ ሰዉእየገደለያለዉ
  መዳኔአለም ከናቱከድንግልማርያምጋር ወያኔን ከይትዮጵያ ምድርያጥፍልን
  ድል ለምየ ኢትዮጵያ ሀገራችን ይሁን ላአል ሰሙ አሰሙ

 16. Kasse September 24, 2016 at 9:22 pm Reply

  አሁንስ ኢትዮጵያ በትክክል ሰው እንደሌላት ታወቀ አሁን ዳንኤል ክብረት ሽማግሌ ይሆናል አባቶችን የሚዘልፍ ተሳድልቢና መሀል ሰፋሪ ትልልቅ ሰዎችን ሳይቀር የሚንቅ አለኝ በሚለው እውቀቱ የሚኮፈስ ተመጻዳቂ ጉረኛ እግዜር ልቡና ይስጣችሁ ለማንኛውም ወያኔ ሞራልም ሀገራዊ እሴትን የናደ ማፍያ ቡድን ስለሆነ ሽማግሌ እያላችሁ አትቀልዱብን

 17. Anonymous October 11, 2016 at 5:03 am Reply

  really ‘Kasse ‘ sorry your the one how supporter TPLF

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: