ወቅታዊው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገራዊ ሚና

 • የማቀራረብ፣ የማስማማት እና የማስታረቅ አገራዊ ሚና ያላት፣ አገናኝ ተቋም ናት
 • ከመንፈሳዊ ተልእኮዋ እና ከታላቅ ማኅበራዊ ተቋምነቷ የመነጨ፣ ታሪካዊ ሚናዋ ነው
 • ተቃራኒዎችን ማቀራረብ፣ ታማኝነትንና የመንፈስ ልዕልናን የሚጠይቅ ሓላፊነት ነው
 • በመተማመን፣ የተጐዱ የሚካሱበትና ያጠፉ የሚታረሙበት ከበቀል የጸዳ ፍትሕ ይሰፍናል
 • ግጭቶች በውይይትና በዕርቅ እንዲፈቱ ያደረገችበትን ሚናዋን፣ ዛሬም ልትገፋበት ይገባል

*               *               *

Ukraine Orthodox priests between protesters and riot police in central Keiv

አገራችን ኢትዮጵያ ጽኑ ሕመም ይዟታል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች፣ ለዓመታት የታመቁ ቅሬታዎችና ምሬቶች ገንፍለው እየወጡ ለግጭቶች ምክንያት እየኾኑ ነው፡፡ በሕዝብ ሲቀርቡ የቆዩ ጥያቄዎች፣ ወቅታዊና ተገቢ ምላሽ ባለማግኘታቸው ያለማቋረጥ እየተከሠቱ ባሉ ግጭቶች፣ በርካታ ዜጎች እየተገደሉ፣ አካላቸው እየጎደለ፣ ለእስራትና እንግልት እየተዳረጉ ነው፤ የአገር ንብረትም እየወደመ ነው፡፡ በማኅበራዊ ግንኙነት፣ ላለፉት 25 ዓመታት፣ ከኢትዮጵያነት ይልቅ እንዲጎላና እንዲጠናከር ተደርጎ የተቀነቀነው ጎሳዊ ማንነትም፣ ግጭቶቹን እንዳያስፋፋና አጠቃላይ ህልውናችንን የሚያሳጣ አደጋ እንዳያመጣ ስጋቱ አይሏል፡፡

ገዥው ግንባር ኢሕአዴግ፣ ያለፉትን 15 ዓመታት ‹‹የሕዳሴ ጉዞ›› እና የወቅቱን ልዩ ልዩ የፖሊቲካ ዝንባሌዎች በጥልቀት ገምግሜበታለኹ ባለው፣ የነሐሴ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ድርጅታዊ መግለጫው፣ ‹‹በአኹኑ ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች ለዜጎችና የጸጥታ አስከባሪ ኃይሎች አሳዛኝ ኅልፈት ምክንያት የኾኑ ግጭቶች የተከሠቱ ቢኾንም፣ አገራችን ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ጥንካሬና ምቹ ኹኔታ ላይ ትገኛለች፤›› ብሏል፡፡

የሕዝብ ቅሬታዎች የተበራከቱትም፣ ‹‹በተዛባ የመንግሥታዊ ሥልጣን እይታ›› ሳቢያ ከአመራሩ ጀምሮ በሚፈጸም ድክመት መኾኑን ገልጧል፡፡ በመንግሥታዊ ሥልጣን የግል ጥቅምን ለማስከበርና ሀብት ለማከማቸት የሚፈጸመው ሙስናና ብልሹ አሠራር፣ ከአገራዊ ዕድገቱ ጋር የተፈጠሩ አዲስ የሕዝብ ፍላጎቶችን በዓይነትና በመጠን ለማርካት እንዳይቻልና የልማት ጥያቄዎችም በውጤታማነትና በወቅቱ እንዳይመለሱ ተጽዕኖ ማሳደሩን ጠቅሷል፤ በቀጣይም፣ የሕዝቡን ሰፊ ተሳትፎና ወሳኝ ሚና አጋር በማድረግ፣ ‹‹በመንግሥት ሥልጣን አጠቃቀም ዙሪያ የተከሠተውን ጉድለትና የዚኽ መገለጫ የኾኑ አስተሳሰቦችን›› ለማስተካከል ቁርጠኛ አቋም ይዞ እንደሚንቀሳቀስ አስታውቋል፡፡

በአንጻሩ የሚሰነዘሩ አስተያየቶች፣ የግንባሩ መግለጫ፣ ‹‹ሐቁን በማቃለልና በመናቅ በአደረጃጀት ላይ ብቻ የተንጠለጠለ ነው፤›› ሲሉ ይተቻሉ፡፡ ለኹሉም ችግር በልማትና በግምገማ መፍትሔ አመጣለኹ፤ የሚለው መግለጫው፣ ችግሩን በቁንጽል የሚያቀርብ በመኾኑ መሠረታዊና ዘላቂ መፍትሔ እንደማያመጣ ያመለክታሉ፡፡ የኅብረተሰቡ የልማት ፈላጊነት ባያጠያይቅም፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቹ በአግባቡ ካልተከበሩ፣ ልማቱም ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባና ግጭቶቹም አኹን በሚታዩበት አስፈሪ ገጽታ ከቀጠሉ ለአገር ደኅንነትም እንደሚያሰጉ ይጠቁማሉ፡፡ ‹‹የችግሩ መንሥኤ የኢሕአዴግ ፍርሃት ነው፤ መፍትሔው፣ የሕዝቡን ነጻነትና መብት ማክበርና ማስከበር ነው፤›› ይላሉ፣ ለሆርን አፌይርስ ድረ ገጽ የጻፉት ሥዩም ተሾመ፡፡

ሙስናና ብልሹ አሠራር ተወግዶ መልካም አስተዳደር ሊሰፍን የሚችለው፣ የዜጎች ነጻነትና የሕግ የበላይነት በተረጋገጠበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ በመኾኑ፣ የኅብረተሰቡ ጥያቄዎች፣ ከደም አፋሳሽ ርምጃዎች ተጠብቀውና በመሠረታዊ እውነታቸው ተመዝነው በሕጋዊ መንገድ እንዲስተናገዱ ይጠይቃሉ፤ ችግሮቹን በጸጥታ ኃይሎች ለማስታገሥ የተላለፈው ትእዛዝና የሚደረገው ከመጠን ያለፈ ሙከራም፣ ሰላማዊውን አማራጭ ከማመንመን በቀር ብዙ ርቀት እንደማያስኬድ ይናገራሉ፡፡

መንግሥት፣ በራሱ መዋቅራዊ አሠራርና በግምገማ የማያገኛቸው በርካታ ችግሮች መኖራቸውንም በመገንዘብ፣ ውስጡን ፈትሾ ራሱን በተጠያቂነትና በግልጽነት መርሖዎች ከማስተካከል ባሻገር፣ ከፖሊቲካ ፓርቲዎችና የተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር ለውይይት ቢቀመጥ፣ ለኹሉም የሚበጅ መፍትሔ ለማምጣት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል፡፡ ‹‹ከኃይለኛ ጋር ስትጋፈጥ መፍትሔው ኹሉ የሚኖረው በኃይለኛው እጅ ነው፤›› የሚሉት አንጋፋው ምሁርና የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም፣ ግንባሩም ሕዝቡን ማዳመጥ እንደሚገባው ያሳስባሉ፤ ማዳመጥም፣ ከሚፈልጉ ይልቅ የተጠየቁትን መመለስ ነው፡ተቀናቃኞችም፣ የአመራርና የድርጅት አቅማቸውን የሚያጠናክሩበት ምኅዳር ሊመቻችላቸው ይገባል፤ እንቅስቃሴአቸውም፣ ጥያቄውን የሚመጥንና ሓላፊነት የተሞላበት እንዲኾን ያስፈልጋል፡፡

በርግጥም፣ ሥልጣን በማጣትና በማግኘት ከሚቋጨው ጠባብ የፖለቲካ ፍላጎት በበለጠ፣ የአገራችን አንድነትዋና ህልውናዋ የሚያሳስባቸው ልጆችዋ፣ ከጠረፍ እስከ ጠረፍ የሚንጣትን ሕመምዋን ከመሠረቱ ተረድተው በጋራ የመፍትሔ ፍለጋ ውስጥ መግባት አለባቸው፡፡ በገዥው ግንባር – ‹‹ብሔራዊ መግባባት››፣ በተቀናቃኝ ኃይሎች ዘንድ ደግሞ – ‹‹ብሔራዊ ዕርቅ›› ቢባልም፤ ኹሉም ወገኖች፣ ለሰላማዊ ብሔራዊ ውይይት ራሳቸውን በማዘጋጀት ሐቀኛና መሠረታዊ መፍትሔ ሊያስገኙ ይገባል፡፡ ለዚኽም፣ ኹሉም ወገኖች የሚሳተፉበት መድረክ፣ በጥናትና በብዛት እንዲዘጋጁ የሚመክሩ ተማጥኖዎች እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡

ሕዝብን የሚያስማሙ ሰላማዊ አማራጮች ኹሉ፣ በልበ ሰፊነትና በጥሞና የሚፈተሹበትን መድረክ በማመቻቸት ረገድ፣ ተጠቃሽ ከኾኑት የአገር ልሂቃን(ምሁራንና ሽማግሌዎች)፣ የሲቪል እና የሞያ ማኅበራት ጋር፣ የእምነት ተቋማት የመሪነት ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡ ራሳቸውን ከፍርሃት ቆፈን አላቀውና ከአድርባይነት አባዜ አውጥተው፣ ያለማንም ጣልቃ ገብነትና ተጽዕኖ በነጻነት በመንቀሳቀስ፣ ብሔራዊ የዕርቅና የመግባባት መድረክ እንዲፈጠር አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ያለምንም አድልዎና ወገናዊነት አጥፊውን እየገሠጹና እያረሙ፣ ግድያና ውድመት እያስከተሉ ያሉ ግጭቶች በመቀራረብና በመነጋገር እንዲፈቱ ተነሣሽነቱን ሊወስዱ ይገባል፡፡ ለኢትዮጵያችን ዘላቂ ሰላምና ለሕዝቡ ህልውና ሲሉ፣ ‹‹የአገራችን ጉዳይ ያገባናል›› በሚል ቀናነት መሥዋዕት መኾን፣ መንፈሳዊ እና የዜግነት ግዴታቸው ነው፡፡

ነገር ግን፣ ይህንኑ ታሪካዊና ዜግነታዊ ድርሻቸውን ሲወጡ፣ በማንኛውም ፖለቲካዊ ኃይል ተጠልፈው የፕሮፓጋንዳ መሣርያ እንዳይኾኑ መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ቀደም ሲል ባሳዩአቸው አድሏዊ አቀራረቦች ሳቢያ እየተሰነዘሩባቸው ከሚገኙ የትችቶች ናዳ ሊማሩ ይገባል፡፡ በኹሉም ወገኖች ዘንድ ተኣማኒነትንና ቅቡልነትን የሚያተርፍላቸው፣ የመንፈስ ልዕልናቸውና ሞራላዊ ሥልጣናቸው በመኾኑ፣ ሕመሙን ከማባባስና በሕመሙ ለማትረፍ ከመሯሯጥ መከልከል አለባቸው፡፡

ግዛቸው አበበ የተባሉ ጸሐፊ፣ ‹‹ዐውቀው የተኙት የሕዝብ እረኞች›› በሚል ርእስ፣ በ‹‹ውይይት›› መጽሔት ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ የሃይማኖት ተቋማት በግጭቶች ዙሪያ ባወጧቸው መግለጫዎች፣ ‹‹የገዥውን ቡድን የልብ ትርታ ያዳመጠ፣ የሕዝብን ጥያቄ ብቻ ሳይኾን ደኅንነቱንና ሰላሙን፣ የአገሪቱንም መፃኢ ተስፋ ችላ ያለ አቋማቸውን አንጸባርቀዋል፤›› ሲሉ ነቅፈዋል፡፡ ሚዛናዊ መስለው በመታየት የአስመሳይነት ድራማ ለመሥራት የሞከሩ መኖራቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

‹‹የማናለብኝነትንና በጥላቻ የተሞሉ ዘለፋዎችን ጨምሮ ኢ-ፍትሐዊነትንና ኢ-ሰብአዊነትን ገና በእንጭጩ ለምን አልተቃወሙም? ለምን ምክራቸውንና አሳቢነታቸውን አላሳዩም?›› ሲሉ ይጠይቃሉ፣ ጸሐፊው፡፡ ዐመፅና ብጥብጥ የሚያቀጣጥሉ ዝምታዎችና ማድበስበሶች በዝተው ገንፍለው በወጡ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች፥ ሕይወት እየጠፋ፣ አካል እየጎደለና ንብረት እየወደመ ባለበት ኹኔታ፣ ‹‹የፈሪሃ አምላክ›› አብነት እንደ መኾናቸው፣ ለመምከር ብቻ ሳይኾን ለመገሠጽም ቀዳሚ መኾን ሲገባቸው፣ የአንድን ወገን አባባል ተከትለው ሌላውን ጥፋተኛ በማድረግ ያወጧቸውን መግለጫዎች፣ ‹‹የሚያስተዛዝብ›› ሲሉ ነው የገለጹት፡፡

‹‹ከያቅጣጫው የሚሰጡ መግለጫዎች ሆድ ለባሰው ማጭድ የሚያውሱ ናቸው፤ ራሳቸው ችግር ናቸው እንጂ ችግር የሚፈቱ አይደሉም፤›› የሚሉት የነገረ ቤተ ክርስቲያን ተመራማሪና ጸሐፊ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ‹ሌላው ቀርቶ የሃይማኖት አባቶች እንኳን የሚናገሩት ነገር ሃይማኖት፣ ሃይማኖት የሚል አይደለም፤›› ሲሉ ተችተዋል፡፡ የሚነሡ ጥያቄዎች፣ የሚሰጡ ምላሾችና የሚወጡ መግለጫዎች፥ ሕመም ላይ መኾናችንን እንደሚገልጡ ያስረዱት ዲያቆን ዳንኤል፣ የአገራችንን ሕመም ለማከም፣ ከጠላትነት ወደ ተነጋጋሪነት፣ ከአጥርነት ወደ ድልድይነት፣ ከተፃራሪነት ወደ ተደጋጋፊነት መምጣት እንደሚያስፈልግ ጽፈዋል፡፡*

አኹን ታመናል፡፡… ኹሉን አግባብቶ፣ ኹሉንም ሊያድን የሚችል መድኃኒት የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ኹነኛውን መድኃኒት ሊያመጣው የሚችለው የምር ውይይት ነው፡፡ ከአንድ አቅጣጫ የሚመጣ መድኃኒት የሚያድንበት ጊዜ አብቅቷል፡፡ በዚኽ ሒደት የሚፈራም የሚናቅም መኖር የለበትም፡፡ መድኃኒት፣ አንዳንድ ጊዜ የሚያስፈልግ እንጂ የሚፈለግ ላይኾን ይችላል፡፡ በዚኽ ሒደት ልናድናት ቆርጠን መነሣት ያለብን ኢትዮጵያን ነው፡፡ ሥርዓቶች፣ ፖሊሲዎች፣ አደረጃጀቶች፣ አወቃቀሮች ሊቀየሩ ይችላሉ፡፡ ከጠላትነት ወደ ተነጋጋሪነት፣ ከአጥር ወደ ድልድይ፣ ከተፃራሪነት ወደ ተደጋጋፊነት መምጣት ያስፈልግ ይኾናል፡፡

ቤተ ክርስቲያን፣ በባላንጣነት የሚተያዩ ወገኖችን በድልድይነት የማስታረቅ፣ የማቀራረብና የማስማማት ድርሻ ያላት፣ አገናኝ ተቋም(Cohesive Institution) ነች፡፡ ይህ፣ የላቀ ታማኝነትንና የመንፈስ ልዕልናን የሚጠይቅ ሓላፊነት፣ ከመንፈሳዊ ተልእኮዋ ብቻ ሳይኾን፣ ታላቅ ማኅበራዊ ተቋም ከመኾኗ የሚመነጭ አገራዊና ታሪካዊ ሚናዋ ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን በኹሉም የአገሪቱ ዜጐች ዘንድ ከፍተኛ የመንፈስ ልዕልናን የተቀዳጀችበት አንዱ ምክንያትም፤ ይኼው የማስማማት፣ የማስታረቅ፣ አንተም ተው፣ ኹላችኁም ተዉ የማለት ሚዛናዊ ድፍረትዋ፤ የተጐዳው እንዲካስ፣ ያጠፋው እንዲታረም፣ አልፎም ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ለማድረግ ያሳየችው ቁርጠኝነትዋ ነው፡፡

ጠበኞች የሚታረቁባት፣ የበደለ የሚካስባት፣ የሸሸ የሚማጠንባት፣ ምሕረትንና ፍትሕን የሚያገኝባት ታላቅ አገናኝ ተቋም የኾነችው ቤተ ክርስቲያናችን፤ በአኹኑ ወቅት፣ በአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች፣ እየተፈጸሙ ያሉ አሳዛኝ ግድያዎችና ደም አፋሳሽ ግጭቶች፥ በሰላም፣ በውይይት፣ በዕርቅና ኹሉም ወገን በሚያተርፍበት ኹኔታ የሚፈቱበትን መንገድ በማፈላለግ ታሪካዊ ድርሻዋ ልትገፋበት ይገባል፡፡

ከፖሊቲካ፣ ከኢኮኖሚና ከማኅበራዊ ጉዳዮች አንጻር፣ የቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ አገራዊ ሚና የተዳሠሠበት ተከታዩ የሐመር መጽሔት፣ ግንቦት/ሰኔ 1998 ዓ.ም. እትም፤ ግንባር ቀደም የይቅርታና ዕርቅ መልእክተኛነትዋ፣ ዋነኛ ማኅበራዊ ሚናዋ መኾኑን ያትታል፡፡ መላው ምእመናንዋና የአገራችን ዜጎች፣ ዛሬም ከቤተ ክርስቲያናችን አጥብቀው የሚፈልጉትና የሚጠብቁት ወቅታዊ ሚናዋ እንደኾነም ያሳስባል፡፡ ከ1997 ዓ.ም. ብሔራዊ ምርጫ ጋር ተያይዞ ተፈጥሮ የነበረውን ቀውስ መነሻ በማድረግ፣ ፍቅረ ሥላሴ ኣርኣያ የተባሉ ጸሐፊ ‹‹ወቅታዊው የቤተ ክርስቲያን አገራዊ ሚና›› በሚል ርእስ በመጽሔቱ አቅርበውት የነበረው ይኸው ጽሑፍ እንደሚከተለው ተስተናግዷል፡፡


የእምነት ተቋማት ባሉበት ማኅበረሰብ ውስጥ በርካታ ሚና ሊኖራቸው ይችላል፡፡ የተቋማቱን ሚና፣ ስፋት እና ጥልቅት በአመዛኙ የሚወስኑት፥ የየእምነቱ ተከታዮች ብዛት፣ የአመራር፣ ከመንግሥትና ከሌሎች የኅብረተሰቡ አካሎች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት እንዲኹም የተቋማቱ ዕድሜ እና ታሪክ ነው፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፥ ረጅም ታሪክ፣ በርካታ ምእመናን፣ ጉልሕ አገራዊ እና ማኅበራዊ ሚና ያላቸው የእምነት ተቋማት፣ የኅብረተሰባቸውን ችግሮች ለማቃለልና ሕዝብን ለማስተባበር፣ እንዲኹም የኅብረተሰቡን ልዩ ልዩ ክፍሎች ለማቀራረብ ከሌሎች የተሻለ ዕድልና ተቀባይነት የሚያገኙበት ዕድል ጥቂት አይደለም፡፡

የእምነት ተቋማት እና መሪዎቻቸው በኅብረተሰባቸው ውስጥ ሊኖሯቸው የሚችሉትን ዘርፈ ብዙ ሚናዎች፡- ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ብለን በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ልንከፍላቸው እንችላለን፡፡

ከመንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ተልእኮ የሚመነጭ ውሱን ፖለቲካዊ ተሳትፎ

ከአገራችን ፖለቲካዊ ሥርዓት እና ፖለቲካዊ ሒደት አንጻር የእምነት ተቋማት ታሪካዊ ሚና ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በአገሪቱ ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ ኹኔታዎች ውስጥ ለረጅም ዘመናት የነበራትን ሚና በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ የሮም ካቶሊክ በአውሮፓ እና በደቡብ አሜሪካ አገሮች፣ የፕሮቴስታንት እምነት ተቋማት በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ፣ የእስልምና እምነት ተቋማት መሪዎች በመካከለኛው ምሥራቅ እና በሰሜን አፍሪቃ አገሮች የነበራቸውንና ያላቸውን ፖለቲካዊ ሚናም ማስታወስ ይቻላል፡፡

በአጭሩ፣ ፖለቲካዊ ሚና የምንለው፥ የእምነት ተቋማቱ በመንግሥት ምሥረታ እና በመሪ አመራረጥ፣ እንዲኹም መንግሥት የሚከተላቸውን ፖሊሲዎች በመደገፍ ወይም በመቃወም ወዘተ… የሚኖራቸውን ተሳትፎ ነው፡፡ በዚኽ መሰሉ ፖለቲካዊ ተሳትፎ የእምነት ተቋማቱ እና መሪዎቻቸው ቀጥተኛ ተጠቃሚ ሊኾኑም ላይኾኑም ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም የተወሰኑ የእምነት መሪዎች የሚጠቀሙበት፣ ነገር ግን በአጠቃላይ እምነቱ/የእምነት ተቋሙ/ እና ተከታዮቻቸው የማይጠቀሙበት፣ አልፎም የሚጎዱበት የፖለቲካ ተሳትፎ ሊኖር ይችላል፡፡ በዚኽ መሰሉ አጋጣሚ በተቋሙ ተቀባይነት እና የመንፈስ ልዕልና ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከፍተኛ በመኾኑ ስብራቱን ለመጠገን ብዙ ጥረት ሊጠይቅና ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡

የእምነት ተቋማት የፖለቲካ ተሳትፎ ኹልጊዜም አንዱን ደግፎ ሌላውን ከመቃወም ጋር ብቻ የተያያዘ ነው ብሎ መነሣት ወደተሳሳተ ድምዳሜ ሊያደርስ ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡- የእምነት ተቋም(መሪ) የአማኞችን ሕይወት፣ አኗኗር ወይም በአጠቃላይ አገሪቱን ይጎዳል የሚለውን የመንግሥት ፖሊሲ ሊቃወምና ማሻሻያ እንዲደረግ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ፣ ፖሊሲው ለሕዘብ የሚጠቅም ኾኖ ሲያገኘው ሊደግፈው ይችላል፡፡ ይህም ማለት፣ ፖሊሲው ላይ ካለው አቅዋም ባለፈ ተቋሙ የአንዱ ፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊ፣ የሌላው ፖለቲካ ፓርቲ ተቃዋሚ ኾኗል ማለት አይደለም፡፡

በኅብረተሰባቸው ውስጥ ረጅም ታሪክ ያላቸው የእምነት ተቋማት፣ ከሚኖርባቸው ታሪካዊ እና ማኅበራዊ ሓላፊነት የተነሣ፣ አንዳንድ የመንግሥት ፖሊሲዎችን በቅርበት የመከታተልና አስተያየታቸውን የመስጠት መንፈሳዊ ግዴታ ሊኖርባቸው ይችላል፤ የሕዝበ ክርስቲያኑ እረኞች ማለትም ጠባቂና ተከባካቢዎች ኾነው ተሾመዋልና፡፡ ዮሐ.2115-17፤ የሐዋ.ሥራ 2028፡፡

የእምነት ተቋማት በኅብረተሰቡ ኹለንተናዊ ሕይወት ውስጥ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የመንፈስ ልዕልና እና ተቀባይነት የሚያገኙት በመንፈሳዊነታቸው ብቻ ሳይኾን ተቋማቱ፣ መሪዎቻቸውና ተከታዮቻቸው ከራሳቸው አልፈው ለሌላው ኅብረተሰብም የሚጠቅሙ ተግባራትን ሲፈጽሙም ጭምር ነው፡፡ እነዚኽ አካሎች ይህን ልዕልና ከሚቀዳጁባቸው ኹኔታዎች አንዱ ደግሞ በተገደበ (ውሱን በኾነ) ፖለቲካዊ ተሳትፎ (Limited political participation) መርሕ መጽናት ሲችሉና በዚኽ ተሳትፎአቸውም ተከታዮቻቸውንና መላውን ኅብረተሰብ በተጨባጭ ሊጠቅም የሚችል ሥራ ሲያከናውኑ ነው፡፡

church and state
ለዚኽም አንዱ ማሳያ፥ ተቋማቱ፣ መንግሥት እና ልዩ ልዩ ማኅበራዊ ተቋማት የሚያወጧቸው ፖሊሲዎችና የሚወስዷቸው ርምጃዎች፣ የኅብረተሰቡን ሰላማዊ እና ጤናማ አኗኗር የማያናጉ፣ ጠቃሚ ባህሉንና ልማዱን የማይጥሱ፣ ያለበትን ችግር የማያባብሱ… ወዘተ መኾናቸውን መከታተልና እንደ አስፈላጊነቱም ድምፃቸውን ማሰማታቸው ነው፡፡ ኹኔታው ጠቃሚ ሲኾን ደግሞ እገዛ ቢያደርጉና ቢያበረታቱ መልካም ነው፡፡ የእምነት ተቋማት ፖለቲካዊ ተሳትፎ በዋናነት ከመንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ተልእኮዋቸው እንደሚመነጭ ማረጋገጥ ግን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ አለበለዚያ ተቋማቱ የግለሰቦች የፖለቲካ አቋም ማስፈጸሚያ ከመኾን አያመልጡም፡፡ ከበጎ ጎኑ በመነሣት አንድ የቅርብ ምሳሌ ብንጠቅስ ነገሩን የበለጠ የሚያስረዳ ይመስለኛል፡፡

ታሪኩ በአጭሩ፡- ከጥቂት ዓመታት በፊት የግሪክ ፓርላማ አንድ ሕግ ለማጽደቅ ዕቅድ ይዞ ነበር፡፡ ዕቅዱ በአገሪቱ በተለይም በከተሞች ያጋጠመውን የመቃብር ቦታ ጥበት ለማቃለልና በዚኹ ምክንያት ለሦስት ዓመት የመቃብር ቦታ በሊዝ(በኪራይ) ለማግኘት የሚወጣውን ከፍተኛ ወጭ ለማስቀረት ይረዳል የተባለ የሕግ ረቂቅ ነው፡፡ የሕጉ ረቂቅ ማእከላዊ ጭብጥ፣ የሙታንን ዐፅም/አስከሬን/ ማቃጠል ሕጋዊ ማድረግ ነው፡፡ይህን ድርጊት በሕግ መልኩ ማውጣት ያስፈለገበት ምክንያት፣ ከግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና በእርሷ በኩል በአገሪቱ ተጠብቆ በቆየው ክርስቲያናዊ ባህል የተነሣ ነው፡፡

የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ ‹‹በትምህርታችንና በባህላችን አስከሬን ማቃጠል የተከለከለ ስለኾነ ይህን ሕጋዊ የሚያደርግ ሕግ ጸድቆ ሊወጣ አይገባም፤›› በማለቷ፣ በረቂቁ ላይ ለረጅም ጊዜ ውይይት ሲካሔድ ቆይቷል፡፡ ከ95 በመቶ የማያንሱት የግሪክ ዜጐች የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች በመኾናቸውና በታሪካዊ ምክንያቶች የተነሣ የአገሪቱ መንግሥት እና ፓርላማ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ይኹንታ ሳያገኝ ሕጉን ማውጣት የሚፈለገውን ውጤት እንደማያመጣ ያውቁ ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች ያልኾኑ ሰዎች እንኳ፣ ድርጊቱ ሕገ ወጥ በመኾኑ፣ በይፋ የሙታንን አስከሬን ማቃጠል ቢፈልጉ እንኳ አይችሉም ነበር፡፡ በመጨረሻም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር በተደረገ ሰፊ ውይይት፣ ‹‹ቢያንስ የግሪክ ኦርቶዶክስ ምእመናን ያልኾኑ ሰዎች እንዲጠቀሙበት እናድርግ›› ከሚል ስምምነት በመደረሱ ሊጸድቅ ችሏል፡፡

ይህም፣ የእምነት ተቋማት ከማኅበራዊ እና መንፈሳዊ ተልእኳቸው በመነሣት በተወሰነ መልኩ በፖለቲካዊ ሒደት የሚሳተፉበት ኹኔታ ሊኖር እንደሚገባ ለማሳየት ነው፡፡ ከዚኽ በተቃራኒው ግን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለየ ፖሊሲ በሚከተሉባቸው ጉዳዮች ላይ አስገዳጅ ኹኔታዎች ካላጋጠሙ በስተቀር የእምነት ተቋማት በምንም መልኩ አቋም ባይዙ ይመረጣል፤ ምክንያቱም ከተከታዮቻቸው መካከል ፖሊሲውን የሚደግፉም የሚቃወሙም ስለሚኖሩና ይህም የውስጥ መከፋፈልን ሊያስከትልባቸው ስለሚችል ነው፡፡

ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ የፋሽስት ኢጣልያን ወረራንና በንጹሐን ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋ በመቃወም የያዙት አቋም፣ በባሕርይው ፖለቲካዊ አቋም መኾኑ ባይካድም፣ መነሻው ግን፣ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ተልእኳቸው እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ እንዲያውም በወቅቱ ይህን አቋም ባያንጸባርቁ ኖሮ፣ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ልዕልናቸው ዛሬ የምንመሰክርላቸውን ያህል ባልኾነ ነበር፣ ብሎ መከራከር ይቻላል፡፡

ብፁዕነታቸው፣ በመንፈሳዊ ተልእኳቸው፣ በሮም ካቶሊክ ፖፕ ቡራኬ ኢትዮጵያን ወርሮ፡- መነኰሳትን፣ ሊቃውንትን፣ ካህናትንና ምእመናንን እያረደ፣ አብያተ ክርስቲያናትን እያቃጠለ፣ ቅርሶችንና ንዋያተ ቅድሳትን እየዘረፈ የነበረውን የፋሽስት ኢጣልያ ሠራዊት አውግዘዋል፡፡ በማኅበራዊ ተልእኳቸው ደግሞ፡- የግፍ አገዛዝን፣ ወረራን፣ ግድያን፣ ጭቆናንና ኢ-ሰብአዊነትን በመቃወም ለአገር ሉዓላዊነት፣ ለነጻነት፣ ለፍትሕና ለእኩልነት ቆመዋል፡፡

በፋሽስቶቹ ፊት መሥዋዕት ሊኾኑ ቀርበው የተናገሩት የሚከተለውን ነበር፤ ‹‹…ፋሽስቶች የአገራችንን ዐርበኞች ሽፍታ ቢሏቸው እውነት አይምሰላችኹ፡፡ ሽፍታስ ማለት ያለአገሩ መጥቶ የሰውን ርስትና ከብት የሚቀማ፣ አብያተ ክርስቲያናትን የሚያቃጥል፣ የክርስቲያንን ደም የሚያፈስ ይህ በመካከላችኹ የቆመው አረመኔው የኢጣልያ ፋሽስት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በርሱ እንዳይገዛ ውጉዝ ነው!! የኢትዮጵያ መሬትም እንዳትቀበለው የተገዘተች ትኹን!!››

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ በዚኽ ጽናታቸው፣ የኢጣልያን ‹‹ክርስቲያን ነኝ›› ባይነትና ሥልጡንነት ፈተና ውስጥ ከተቱት፡፡ ለሃይማኖታቸው ያላቸውን ቅንዐት፣ መሥዋዕት ለተፈጸመበትና ለጨበጡት መስቀል ያላቸውን ስሜት፣ ለሀገራቸውና ለወገናቸው ያላቸውን ታማኝነት አረጋገጡ፡፡ በፋሽስት መትረየስ ተደበደቡ፡፡ ዛሬ በዚያ ድርጊት ኢትዮጵያ ትኮራለች፣ ኢጣልያ ታፍራለች፡፡

ማርቲን ሉተር ኪንግ/ጁኒየር/፣ በአሜሪካ ጥቁሮች ላይ ይደርስ የበረውን የዘር መድልዎ በመቃወም እስከ መታሰር የደረሰበትን የታሪክ አጋጣሚም ማስታወስ ይቻላል፡፡ ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ በዚኽ ርምጃ፣ ከሌሎች የእምነት ተቋም አገልጋዮች ተቃውሞ ቢቀርብበትም፣ ‹‹ለሰው ልጆች እኩልነት መታገል መንፈሳዊና ማኅበራዊ ግዴታዬ ነው፤›› በማለት ባካሔደው ሰላማዊ ተጋድሎ ታሪክ የመንፈስ ልዕልናውን በክብር ያስታውሰዋል፡፡ /ማስታወሻ፡- ማርቲን ሉተር ኪንግ ለከሠሡት ካህናት ባልንጀሮቹ ከበርሚንግሐም እስር ቤት የጻፈላቸውን አስገራሚ ደብዳቤ ማንበብ የበለጠ ሐሳብ ይሰጣል/፡፡

የክርስትናን አስተምህሮ በማይቃረኑ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በመሳተፍና ልማታዊ አስተሳሰብን በመቅረፅ

የእምነት ተቋማት በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ የሚያደርጉትን ተሳትፎ በኹለት መልኩ ለያይቶ ማየት ይቻላል፡፡ በአንድ በኩል የእምነት ተቋማት፣ በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በቀጣይነት የሚያደርጉት ተሳትፎ አለ፤ ተቋማቱ ሕጋዊ ሰውነት እንዳለው አንድ አካል መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ይንቀሳቀሳሉና፡፡

ብዙውን ጊዜ የእምነት ተቋማት በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚሳተፉት፣ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎታቸውን ለማስፋፋት የሚያስችል ገቢ ለማግኘት ነው፡፡ በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች፣ መሬታቸውንና ጥሪታቸውን እየሸጡ ገቢውን ወደ ማኅበሩ አምጥተው በአንድነት አገልግሎታቸውን ያስፋፉ እንደ ነበር ይታወቃል፡፡ የሐዋ.ሥራ 2፥45፡፡ ይኹን እንጂ ተቋማቱ ኅብረተሰቡን ከድህነትና ኋላ ቀርነት አረንቋ ለማውጣትና የአገርን ልማታዊ እንቅስቃሴ ከመደገፍም አኳያ የማይናቅ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል፡፡ በዚኽ በኩል የካቶሊክ እምነት በቀዳሚነት ብትጠቀስም፣ ከክርስትና ትምህርት ጋር በሚቃረኑ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሳይቀር ትሳተፋለች እየተባለች ትወቀሳለች፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኩል፣ በተለይ ከቅርብ ዘመናት ወዲኽ ከቤተ ክርስቲያናችን ትምህርትና ትውፊት ጋር በማይቃረኑና እግረ መንገዳቸውንም ለኅብረተሰቡ ጠቃሚ አገልግሎት በሚሰጡ እንቅስቃሴዎች ጠንካራ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ ይህም ት/ቤቶችን፣ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማትን፣ የመኖሪያና የንግድ ሕንፃዎችን መገንባትና ማከራየትን፣… ወዘተ ያጠቃልላል፡፡

ኹለተኛው የእምነት ተቋማት ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ተደርጎ የሚታየው፣ ተቋማቱ፣ ከኢኮኖሚ ልማት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የሚሰጡትን ትምህርትና የሚፈጥሩትን አስተሳሰብ የተመለከተ ነው፡፡ ይኼ ርእሰ ጉዳይ በራሱ ሰፊ ማብራሪያ የሚጠይቅ በመኾኑ በዝርዝር የምገባበት አይኾንም፡፡ ዋናው ጥያቄ ግን፣ ሃይማኖቱ ሰዎች በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚኖራቸውን ተሳትፎ እንዴት ይመለከተዋል በሚለው ጥያቄ ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው፡፡

Orthodox priests pray as they stand between pro-European Union activists and police lines in central Kiev, Ukraine, early Friday, Jan. 24, 2014. A top Ukrainian opposition leader on Thursday urged protesters to maintain a shaky cease-fire with police after at least two demonstrators were killed in clashes this week, but some in the crowd appeared defiant, jeering and chanting "revolution" and "shame." (AP Photo/Sergei Grits)

Orthodox priests pray as they stand between pro-European Union activists and police lines in central Kiev, Ukraine, early Friday, Jan. 24, 2014.(AP Photo/Sergei Grits)

ግንባር ቀደም የይቅርታ እና ዕርቅ መልእክተኛ የመኾን ማኅበራዊ ሚና

ሦስተኛውና ከወቅቱ ኹኔታችን ጋር በጣም አስፈላጊው፣ የእምነት ተቋማት ማኅበራዊ ሚና ነው፡፡ በጥቅሉ ‹‹ማኅበራዊ›› የምንለው የእምነት ተቋማት ሚና፡- ከባህል፣ ከኅብረተሰብ ሰላምና የተሻለ አኗኗር፣ ችግረኞችን ከመርዳትና ከመሳሰሉት ጉዳዮች ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በዚኽ በኩል ቤተ ክርስቲያን እንደ አንድ ታሪካዊና ትልቅ ማኅበራዊ ተቋምነቷ የሚጠበቅባት መሠረታዊ ሚና፡- የማስታረቅ፣ የማቀራረብና የማስማማት ድርሻዋ ነው፡፡ በመሠረቱ ቤተ ክርስቲያናችን በምልጃዋ ዕርቅን፣ በዕርቁም ደግሞ ፍቅርንና ሰላምን ማስፈንዋ፣ በከበረ ደሙ በመሠረታት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጣት የባለሟልነት መብትዋ ነው፡፡ 2ቆሮ.5፥20፡፡

የኢትዮጵያን ታሪክ በሚገባ የተረዳና ዛሬ ያለንበትን ኹኔታ በቅርበት የሚከታተል ማንኛውም ሰው፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊኖራት የሚችለውን ቁልፍ የማረጋጋት፣ የማስታረቅ አገልግሎትዋን አስፈላጊነት በግልጽ ለማስተዋል ይችላል፡፡ ይህን እውነታም የቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን ያልኾኑ ዜጎች ሳይቀሩ የሚቀበሉት መኾኑ ደግሞ፣ ቤተ ክርስቲያናችን በዚኽ በኩል የምታደርገው ጥረት፣ ከመንፈሳዊ ተልእኮዋ ብቻ ሳይኾን ከማኅበራዊና አገራዊ ሓላፊነቷም የሚመነጭ መኾኑን ያለጥርጥር የሚያስረዳ ነው፡፡

በሥራ አጋጣሚ በልዩ ልዩ የአገራችን ክፍሎች በተዘዋወርኩባቸው ቅርብ ቀናት የተለያዩ እምነቶችን ከሚከተሉ በርካታ ሰዎች ጋር የመገናኘት ዕድል ነበረኝ፡፡ ከኹሉም ጋር በምናደርገው ውይይት በመጨረሻ የምንደርስበት አንድ መደምደሚያ ቢኖር፣ የአገራችን የእምነት ተቋማትና መሪዎች ያለንበትን ውጥረት ለማረጋጋትና ልዩነቱን ኹሉንም በሚጠቅም ሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁልፍ ሚና መጫወት የመቻላቸው እውነታ ነው፡፡ የእምነት ተቋማቱን በዚኽ መንገድ የመምራት ግንባር ቀደም ሓላፊነት ደግሞ፣ እንደ ብዙዎች ተስፋ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የወደቀ ነው፡፡

ይህ የብዙ ኢትዮጵያዊ ወገኔ አመለካከት ነው ብዬ አምናለኹ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ቀደም ሲል በታሪክ የነበራትን ቦታና አገልጋዮቿ አለመግባባቶችን በሰላምና በማስማማት ለመፍታት በኅብረተሰቡ ውስጥ ያደረጉትን ወሳኝ እንቅስቃሴ ያስተዋለ ተመልካች፣ ዛሬ ብዙ ቢጠብቅ የሚገርም አይኾንም፡፡

ከ1769 – 1855 /እ.ኤ.አ/ በአገራችን የቆየውና እርስ በርስ የተላለቅንበት ዘመነ መሣፍንት ሊከሠት ከቻለባቸው ምክንያቶች አንዱ፤ ጠበኞች የሚታረቁባት፣ የበደለ የሚካስባት፣ የሸሸ የሚማጠንባት፣ ምሕረትንና ፍትሕን የሚያገኝባት ታላቅ አገናኝ ተቋም(Cohesive Institution) የኾነችው ቤተ ክርስቲያን፣ በውስጥ መከፋፈልና በውጭ ተጽዕኖ በደረሰባት ጉዳት በመዳከሟ ነበር፡፡ በተለይም ደግሞ ለፖለቲካዊ ክፍፍሉ ርእዮተ ዓለማዊ መሠረት በመስጠት ይበልጥ ያከረረው በጸጋ እና ቅባት ተከታዮች የተፈጠረው ደም ያፋሰሰ ውዝግብ ነው፡፡ በዓለማችን ታሪክ በእምነት ተቋማት ልዩነት የተነሣ የተጫሩ ግጭቶች መኖራቸው ባይካድም፣ በተቃራኒው፣ በተቋማቱ ጥረት የረገቡ፣ በሰላም የተቋጩ ግጭቶች ብዛት ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡

churches' restorative role
አበው ካህናት፣ በቤተሰብ ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን፣ በተጎራባች የኅብረተሰብ አካላት እንዲኹም በተለያዩ ብሔረሶቦች መካከል የሚያጋጥሙ ግጭቶችን በማስማማት፣ በዕርቅና በይቅርታ እንዲፈታ በማድረግ የማይተካ ሚና እንደነበራቸው የታወቀ ነው
፡፡

ቤተ ክርስቲያን በኹሉም የአገሪቱ ዜጐች ዘንድ ከፍተኛ የመንፈስ ልዕልናን የተቀዳጀችበት አንዱ ምክንያትም፤ ይኼው የማስማማት፣ የማስታረቅ፣ አንተም ተው፣ ኹላችኁም ተዉ የማለት ሚዛናዊ ድፍረትዋ፤ የተጐዳው እንዲካስ፣ ያጠፋው እንዲታረም፣ አልፎም ዘላቂ መስማማት እንዲመጣ ለማድረግ ያሳየችው ቁርጠኝነትዋ ነው፡፡

ታሪኩ ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ባይኾንም፣ በደቡብ አፍሪቃ የተፈጸመውን የይቅርታ ታሪክ ማስታወሱ የእምነት ተቋማትንና መሪዎቻቸውን የማስታረቅ ኃይል የሚያሳይ ነው፡፡ የደቡብ አፍሪቃን የእውነትና የዕርቅ ኮሚሽን የመሩት ዴዝሞንድ ቱቱ፣ አፓርታይድን በመደገፍ እና በመቃወም የሚታወቁ የእምነት ተቋማትና መሪዎቻቸው፣ የአገሪቱ የሽግግር ወቅት እንደ ተጀመረ/እ.ኤ.አ በ1990/፣ ተሰባስበው በቅድሚያ እነርሱ ይቅር መባባላቸውን ያስታውሳሉ፡፡

‹‹አፓርታይድን ደግፈው ሲሰብኩ የኖሩት የእምነት መሪዎች ይቅርታ ለመጠየቅ ሲመጡ፣ ሌሎቻችን እንዴት ይቅርታን ልንነፍጋቸው እንችላለን፤›› በማለትም ይጠይቃሉ፡፡ ዴዝሞንድ ቱቱ እንደሚሉት፣ በዚያ ታሪካዊ ስብሰባ የእምነት መሪዎቹ ይቅር ተባብለው ታላቁን የይቅርታና የዕርቅ መልእክት በተግባር ማስተላለፍ ባይችሉ ኖሮ፣ የአገሪቱ የፖለቲካ መሪዎችም በተለያየ አቅጣጫ ለመጓዝ ሰበብ(ማመካኛ) ባገኙ ነበር፡፡

ቱቱ፣ የደቡብ አፍሪቃን የዕርቅ ጉዞ አስመልክተው በጻፉት መጽሐፋቸው፣ ‹‹ዕርቅን የማያውቅ ኅብረተሰብ ተስፋ የለውም›› ይላሉ፡፡ የይቅርታና የዕርቁ እርሾዎችም የእምነት መሪዎች መኾን እንዳለባቸው በስፋት ያብራራሉ፡፡ ዋናው መነሻችን፣ የራሳችን ታሪክና ያለንበት እውነታ ቢኾንም የእነዴዜሞንድ ቱቱ ተሞክሮ ራሳችንን እንድንመለከት የሚጋብዝ ነው፡፡

ዴዝሞንድ ቱቱ ስለ ሩዋንዳ ጉብኝታቸው ሲያስታውሱም፣ በአገሪቱ ብዙ ሰዎች ያለፈውን ስሕተት በሙሉ በፍርድ ቤት ፍትሕ ለማረም ይመኙ እንደ ነበር ይገልጻሉ፡፡ ባለጊዜ፣ ‹‹ቀን በጣለው ላይ›› የሚሰጠውንና ነገ ደግሞ ሌላው ባለተራ፣ በባላንጣው ላይ የሚደግመውን የበቀል ፍትሕ (Retributive Justice)በሐዳሲ/ጠጋኝ ፍትሕ (Restorative Justice) መተካት ካልተቻለ፣ አገሪቱ ከገባችበት የበቀል አዙሪት እንደማትወጣ ለሩዋንዳውያን መንገር ለቱቱ ግዴታቸው ነበር፡፡ አድርገውትማል፡፡ ከዚህ አዙሪት የመውጫው ብቸኛ መንገድም ዕርቅና ይቅርታ ብቻ መኾኑን ተናግረዋል፡፡ ለዚኽም ይመስላል፣ መጽሐፋቸውን፣ No Future Without Forgiveness የሚል ርእስ የሰጡት፡፡

በቤተ ክርስቲያናችን የቅርብ ጊዜ ታሪክ፣ ተመሳሳይ ኹኔታዎች ስለ መፈጠራቸው የማንበብ ዕድል ባይገጥመኝም፣ ቀደም ባሉት ዘመናት ግን ሊጠቀሱ የሚችሉ ታሪኮች መኖራቸው እሙን ነው፡፡ የአንዳንድ ነገሥታትን ዓምባገነንነትና የጭካኔ ተግባር የተቃወሙ፣ ለጦርነት የተሰለፉ የአካባቢ ገዢዎችን ማልደውና በፍቅር ተቆጥተው ያስታረቁ ወዘተ… የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች እንደ ነበሩ ማስታወሱ በራሱ በቂ ምሳሌ ነው፡፡

እኒኽን አብነቶች እየቀነጫጨብኩ ያቀረብኩት፣ የቤተ ክርስቲያን የማስማማት፣ የማስታረቅና የመገሠጽ ሓላፊነት አዲስ ነገር አለመኾኑን ለመጠቆም ያኽል ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ፣ ቤተ ክርስቲያን ለብቻዋም ኾነ ከሌሎች የእምነት ተቋማት ጋር በመኾን፣ በአገራችን ልዩ ልዩ ቦታዎችና ምክንያቶች የሚነሡ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች በሰላም፣ በውይይት፣ በዕርቅ፤ ኹሉም ወገን በሚጠቀምበት ኹኔታ የሚፈቱበትን መንገድ በማፈላለግ ታሪካዊ ድርሻዋ ልትገፋበት እንደሚገባ ለማስታወስ ነው፡፡ ይህም፣ መላው ምእመናንዋ እና የአገራችን ዜጎች፣ ከታላቋ ቤተ ክርስቲያን አጥብቀው የሚፈልጉትና የሚጠበቁት ወቅታዊ ሚናዋ ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያን፣ መሪ አስታራቂ መኾን አለባት ሲባል፣ አጥፊውንም ተጎጂውንም በደፈናው ታረቁ ትላለች ማለት አይደለም፡፡ ማስታረቅ፡- የተቃረኑት ወገኖች እርስ በርስ እንዲተማመኑ፤ ኹሉም ወገኖች ጥፋታቸውን በዝርዝርና በትክክል እንዲያምኑ ማድረግን፤ ለእነዚኽ ጥፋቶች የዳረጉትን ኹኔታዎች መመርመርን፤ ተጎጂውም በአግባቡ የሚካስበትን፣ ከጭፍን እልክ፣ ከቁርሾና ከቂም በቀል የሚጠበቅበትን መንገድ ማፈላለግን ወዘተ… የሚያጠቃልል፣ ታላቅ ታማኝነትንና የመንፈስ ልዕልናን የሚጠይቅ ሓላፊነት ነው፡፡

ይህን የመሰለ መስማማትና ዕርቅ በዴዝሞንድ ቱቱ አገላለጽ፣ ‹‹መታደስን የሚያመጣ ፍትሕን›› ያጎናጽፋል፡፡ አገራችን ከዚኽ መሰሉ ሰላም ተጠቃሚ እንድትኾን ቤተ ክርስቲያናችን ያላት ታላቅ ሚና፣ በማንምና በምንም የማይተካ ነው፡፡


* ሪፖርተር + አዲስ አድማስ + ሰንደቅ ጋዜጦች እና ‹‹ውይይት›› መጽሔት

Advertisements

9 thoughts on “ወቅታዊው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገራዊ ሚና

 1. Bere Berish September 1, 2016 at 1:55 am Reply

  The big point most of us missed is that Our church is also one of the main target destined to be destroyed or silenced. Why? there is one common perception among all Ethiopian foreign enemies ( European missionaries, Arab nations, and colonialists). They all believe that Ethiopian Orthodox church is the main source of strength for the country to remain independent (you can mention the role of our church in ADOWA VICTORY subsequent victories on Italians, Egypts, and Catholics). our foreign enemies also aware that during these periods, mostly the kings/leaders are from Amhara ethnic groups. SO, they all agree that hitting our church and Amhara hard is key to dismantle Ethiopia. To implement this, they brainwashed Woyane leaders from the jungle to palace with hatred and ethnic policies. As A result, current woyane learders, knowingly or unknowingly are implementing what they were trained to do.
  So, our church must actively participate in the fight against racist and divisive Woyane. we need to create awareness among the Christians about the historical reasons and sources of of our current situations. this is a big agenda we need to discuss in Sunday schools, but we all remained silence either we are afraid or we have wrong view of politics.

  this is not about AMHARA OR TIGRE OR OROMO. this is about the destiny of our country and Church.
  Creating awareness may force even the supporters of the regime to stand beside our Church and change their policy. We know there are millions of tigrians who have no clue about these historical reasons and their end goal of destruction. We can speak up from our church about the fact and create awareness. Either Woyane must change their hatred ethnic policies or they must be removed before the dismantle our countries. In this struggle, our church must actively participate and the Christians need to fight back with all necessary means. Then, we can be honored like our fathers, like Abune Petros and Abune Michael.

 2. Annonymus September 1, 2016 at 6:41 am Reply

  Yes! it is true! It is time for our Church(EOTC) to act accordingly”Haylin bemisetegn beKirstos hulun echilalehu…” must be the motto of our church leaders, Pops, Priests,…)

 3. Enoch September 2, 2016 at 12:27 am Reply

  አጻጻፉ ጥሩ ቢሆንም፡ “ዲሞክራሲ”፡”የእምነት ተቋማት”፡”ማርቲን ሉተር ኪንግ” እና “ዴስሞንድ ቱቱ” የሚሉት ቃላት በእኛ ቤተከርስቲያን አገልጋዮች ዘንድ መነሳታቸው አሳዛኝ ሆኖ ነው ያገኘሁት።

 4. Anonymous September 2, 2016 at 3:40 am Reply

  THE EPRDF IS NOT FOOLISH, IT UNDERSTOOD EARLY ON THAT THE PEOPLE OF ETHIOPIA WOULD SACRIFICE EVERYTHING FOR THE LOVE OF THE COUNTRY AND THE LOVE OF THEIR RELIGION. EPRDF DIVIDED THE COUNTRY AND DESTROYED THE UNITY OF THE PEOPLE AND APPOINTED TWO PATRIARCHS FROM THE SAME ETHNICITY BY REMOVING LEGALLY SELECTED PATRIARCH. THERE IS NO WAY THE PATRIARCH FROM TIGRE WILL CONDEMN THE KILLER TIGRE. IF HE WAS APPOINTED BY THE HOLY SPIRIT, WE KNOW FROM HISTORY, THAT HE WILL BE THE PEACE MAKER AND TAKES SIDE WITH THE POOR, THE HELPLESS AND THE DESPERATE. WHERE IS HE NOW? WHY IS HE HIDING? ISN’T HE DEAD ALREADY FOR THE TRUTH AND THE CHURCH., WHY DON’T HE SAY STOP, WHERE IS GOD’S AUTHORITY. HE IS JUST PROVING THAT HE IS A MEANS FOR OPPRESSION. A NON BELIEVER MARXIST JUNTA AND A SO CALLED PROTESTANT ARE DESTROYING THE COUNTRY AND THE CHURCH (UNITY). IF YOU DON’T HELP THE POOR WELL JESUS IS IN HIS THRONE YOU WILL BE CALLED SOON TO ANSWER.

 5. Anonymous September 2, 2016 at 5:02 pm Reply

  Why MK people are fooling themselves, when Ethiopia and the Eth. Orth Church was colonized for the last 25 years and on top of that a Genocide on Amhara people by Atheist Woyane is going on right at this time, still we are talking as if there is a responsible government and Holy Synod. Remember how the Debrelibanos Menekosat become a martyr during Italian invasion in defending this country and people.

 6. Anonymous September 6, 2016 at 10:25 am Reply

  የድሲና የአካባቢዉ ጳጳስ፣ ከሁለትቀን በፌት
  ህዝበ ክርስቲያኑን በድጋሜ አሣዘኑ የሀገራችን ህዝብ ደሙ እንደ ወንዝ ጂረት በወያኔ እየፈሰሰ
  እግዚዎ እንላለን ሰላማውይ ሰልፍ ግን አንወጣም በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል፡፡
  ለምንዉ ሰላማዊ ሰልፍ የማትወጣ? እግዚዎ ወያኔ ጳጳሳትም እየገደሉ እግዚዎ ይላሉ ይህነው መፍትየዉ
  ከግዚአብሔር ጋር አደባባይ ወጥቶ ላለምህዝ በደልን ማሰማት ነዉ ሰውም እግዚአብሔርም የዎገንን ጂግር ሊያዉቀዉ
  ይገባል

 7. Anonymous September 10, 2016 at 10:56 am Reply

  ለመለዉ የሀገራችን ህዝብ እንኳን ከዘመን ዘመን ሁላችንም አደረሰን በቅድሚያ
  ትንቢተ ኤሳ፵ ቁ፩ ህዝቤን አፅናኑ ይላል ምላካችን
  በተለይ በሀገራችን ኢትዮጵያ ያለፈዉ አመት የቤተክርስቲያንልጆች በገዡ ስራት ወንጌልእደ ይሰብኩ የተሳደድበት
  ሰለወገኖቻቸዉ እስራት መገደልና መሳደድ እደይናገሩ የተጨቆኑበት
  በፀራራፀሐይ በተወለዱበትሀገር እናት እያየች ልጆች የተገደሉበት
  ሽማግሌ አዛዉንንት እናት አባት የተደበደቡበት
  ምንም የማያዉቁ ህፃናትም የተገደሉበት ብሒርከብሔር ወያኔያሀደግ እየከፍፈለ ከተወለዱበት አካባቢ የተፈናቀሉበት
  የህግታራሚ ተብለዉ በስርቤት የሚገኙት የህግታራሚዎች በገዡወያኔ በሳት የተቃጠሉበት አስከሬናቸዉ ሣይቀር
  ወላጂእደያለቅሱበት ወላጂናት አባት የተከለከለበት በአማራ በወሮሞ የአሉእናቶች ሽማግሌዎች
  በአሰቃቂ ሁኔታ እናቶቻችን ያዘኑበት አመት ነበረ ሰለዚህ በዲሱ አመት ወያኔየሀደግ ከክፉሰራዉ ነስሐገብቶ ካልተመለሰ
  ጳጳስ መነኩሴ ቄስ ዲያቆን ወንጌልሰባኪ ቆራቢ አስቀዳሽ ወዘተ
  ሸህ ደረሣ ሙስሊም እምነት ያለዉ የለለዉ ሣአንል ሁሉምነገር በሐገርነዉና የሚፈፀመዉ
  ጩህታች አደባባይ በመዉጣት ለግዚአብሔር እናለአለም ህዝብ ማሰማት ይኖርብናል
  እነሱ እደሆን ስድሰት መቶ ስልሣ ስድስት ሰላረፈባቸዉ አግዚአብሔርን አይፈሩ ሰዉንም አያፍሩ
  ወገኖቸ አትፍሩ ከዚህ በለይ ምናለ ከዚህ በፌት ።ቦንሴን እምትባል የስድስት መቶ ስልሣ ስድስት
  ተከከታይ የሆነችዉን ጳዉሎስ ቅድስት ስላሤ ታቦት አዉጥቶ ክርስቲያኖችን አንገትያስደፍ
  በድሜ የገፋ አረጋዉያን ጳጳሳት መቆምተስኖአቸዉ ዘፍኟ በስሐቱ ባለመምጣቷ ምክንያት የወደቁምጳጳሣት ነበሩ
  ታዲያ በግፋለይግፍ እየጨመሩ እንዲትነዉ ዝም የምንለዉ
  በሀሀገራችን ኤትዮጵያ ወደ መሀላገር የወያኔ መነኮሣት ከመጡ ወዲህ ጵጵስና ምንኩስና ተዋርዶአል
  ይሄዉም ያለብቃታቸዉ እናያለችሎታቸዉ የስራቱ ተወላጂ በመሆናቸዉ
  ጵጵስና ተቩመዉ የኞን አባቶችሁሉ እያሰናከሉነዉ ያሉ መዳኔአለም እረ ባክህ ግፍችን ተመልከት ከናጥ ከድንግል ማርያም ጋር

 8. Grume T/Mariam September 17, 2016 at 2:03 pm Reply

  Patriarch Matiwos kadre or Weyane. He looks like Melee Zenawe in Ethiopian new year talked for supporting Weyane. He is not man of God. HE DOESN’T BELIEVE IN GOD INSTEAD HE BELIEVED IN MELEE ZENAWE AND WEYANE .

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: