አባ ሠረቀ ብርሃን የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊነት፤ ንቡረ እድ ኤልያስ የማሳተሚያ ድርጅት ሥራ አስኪያጅነት ተመደቡ፤ እነአባ ሠረቀ በልዩ ጽቤቱ ተገን ለጵጵስና እየቀሰቀሱ ነው

aba sereke birhan woldesamuel ed

 • ለ2ኛ ጊዜ በተመሳሳይ ወቅት ተዛውረዋል፤ከድጡ ወደ ማጡ ተብሏል
 • አባ ሠረቀ በሓላፊነታቸው ተገን ለጵጵስና እንዲታጩ እየተሯሯጡ ነው
 • በሹመኞች እና በአማሳኞች ድጋፍ አስመራጩን ለማስገደድ እየሠሩ ነው
 • የኮሚቴውን አባላት አማስነዋል ያሏቸውን ተጠቋሚዎች ሽፋን አድርገዋል
 • በራሴ ፍላጎት የሚሰጥ ጵጵስና ካለ ለሕይወቴ ካንሰር ነው፤” ብለው ነበር
 • የቤተ ክህነቱ ነገር ተቃራኒ ነው፤ ሹመት ለማይገባው ሹመት ይሰጣል፡፡”

/ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ሳሉ፣ የአባ ሠረቀ ብርሃንን የመምሪያ ሓላፊነት ምደባ በመቃወም ከተናገሩት/

*                *               *

 • በአዳማዊ የውርስ ኃጢአት በእመቤታችን ንጽሕና ላይ ከተሰነዘረው ኑፋቄ ጋር ተባብረዋል
 • በፓትርያርኩ አቅራቢነት ጉዳያቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ታይቶ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል
 • “አቋሜ ከኦርቶዶክሳዊው አስተምህሮ አይለይም” ቢሉም ቃላቸውን በጽሑፍ አላረጋገጡም
 • በቅዱስ ሲኖዶስ vs. በፓትርያርኩ፣ የበላይነትና ቅድምና(supremacy)መደናገር አለባቸው
 • በሎሳንጀለሱ የታቦትና የንዋየ ቅድሳት ስርቆታቸውም፣ ፓትርያርኩ በእማኝነት ተጠቅሰዋል
 • ሥልጣን፣ ገንዝብና ክብር በልጦባቸው የሰረቁ እና የዋሹ” በሚል ምንኵስናቸው ተነቅፏል!

*               *               *

እንደተገመተውና አስቀድሞ እንደተጠቆመው፥ አወዛጋቢው፣ ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ወደ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ተዛውረው የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጸሐፊ ኾነው እንዲሠሩ ተመድበዋል፤ ላለፉት ስድስት ዓመታት በቆዩበት የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያም፣ የትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ርእሰ ደብር መሐሪ ኃይሉ፣ በዋና ሓላፊነት ተተክተዋል፡፡ የቀድሞው የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ደግሞ፣ የማሳተሚያ ድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተመድበዋል፡፡

ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን፣ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ተፈርሞበት ከልዩ ጽ/ቤታቸው ወጪ የተደረገው ደብዳቤ ሐምሌ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. የደረሳቸው ሲኾን፤ ንቡረ እድ ኤልያስም ባለፈው ሳምንት ኃሙስ በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ በተጻፈ ደብዳቤ መመደባቸው ተገልጧል፡፡ ኹለቱም በተመሳሳይ ወቅት ከሓላፊነታቸው ሲዛወሩ የአኹኑ ለኹለተኛ ጊዜ ነው፡፡

አባ ሠረቀ ብርሃን፣ በ1998 ዓ.ም. ከአሜሪካ እንደተመለሱ በተመደቡበት የጠቅላይ ጽ/ቤቱ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሲሠሩ፣ ከእምነት አቋማቸውና ከአሠራር አለመግባባቶች ጋር በተያያዙ ተቃውሞዎችና ግፊቶች ወደ ትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ሓላፊነት እንዲዛወሩ የተደረገው ጥቅምት 29 ቀን 2004 ዓ.ም. ነበር፤ በወቅቱ የጠቅላይ ጽ/ቤቱ የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ኾነው እንዲሠሩ የተመደቡትም በዚያው ቀን ከፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ ነበር፡፡

ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ አኹን በሥራ አስኪያጅነት የተመደቡበትና ከአራት ዐሥርት ዓመታት ያላነሰ ዕድሜ ያስቆጠረው የትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት፣ በልዩ ልዩ ቋንቋዎችና በብዛት የሚያሳትማቸው የእምነትና የሥነ ምግባር፣ የሕግና የሥነ ሥርዓት፣ የታሪክና የትምህርት፣ የጸሎት፣ የዜማ፣ የነጠላና ትርጉምና የአንድምታ ትርጓሜ መጻሕፍት፤ ለአገልግሎት፣ ለትምህርትና ለምርምር ያላቸው ተፈላጊነት እያደገና እየጨመረ መምጣቱን በዓመታዊ ሪፖርቱ ገልጧል፡፡

የቤተ ክርስቲያናችንን ማዕከላዊነት በመጠበቅ ረገድም፡- የገንዘብና የንብረት ገቢና ወጪ ደረሰኞችን(ሞዴላሞዴሎችን)፤ የክርስትናና የጋብቻ ምስክር ወረቀቶችን፤ የካህናትና የምእመናን መታወቂያ ካርዶችን፤ የምእመናን መመዝገቢያ ቅጾችን፣ ማኅተሞችን፣ ቲተሮችንና የመሳሰሉትን ኹሉ በየጊዜው በማሳተምና በማሰራጨት የሚያበረክተው አገልግሎት በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ ድርጅቱ፥ በ2007 ዓ.ም. 38ሺሕ ቅዱሳት መጻሕፍትን፣ 614ሺሕ 330 ሞዴላሞዴሎችን፣ ማኅተሞችንና ቲተሮችን በማተም ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘቱን በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡ በወሳኝ አገልግሎቱና በትርፋማነቱ መጠን፣ የቤተ ክርስቲያንን መብትና ጥቅም የሚያስጠበቅ አስተማማኝ አመራር እንዲያገኝ ማድረግ ሲገባ፣ “የቦታ መጥፋት” በሚል ብቻ ንቡረ እዱ መመደባቸው እንዲታሰብበት ያስፈልጋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ባርከው፣ መርቀው፣ ቀድሰውና አስተምረው አባታዊ መመሪያ የሚሰጡባቸውን፣ የበጎ አድራጎት ልግስናዎችን የሚያደርጉባቸውንና እንግዶችን የሚያነጋግሩባቸውን መርሐ ግብሮች ማመቻቸትና ማስፈጸም የልዩ ጽ/ቤታቸው ተግባር ነው፡፡ ልዩ ጽ/ቤቱ፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ የተጣለባቸውን ሓላፊነት፥ ቤተ ክርስቲያንን ለመወከል፣ ክብሯንና ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን ለማስጠበቅ በሚያበቃ አኳኋን እንዲፈጽሙት ማስቻል ይኖርበታል፡፡ “ልዩ ጽ/ቤቱ ታላቅ ተቋምና በርካታ ሓላፊነቶች ያለበት ከመኾኑ አንፃር በሚገባና በትክክል ለማስኬድ ከፍተኛ ጥረት እንደሚጠይቀኝ ይረዳኛል፤” ያሉት ልዩ ጸሐፊው ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን፤ ከበላይ ሓላፊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ መመሪያ በመቀበልና የቀድሞው ልዩ ጸሐፊ ያመላከቷቸውን ዕቅዶች በማስፋትና በማጉላት ለመሥራት ማሰባቸውን፤ ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ኆኅተ ጥበብ መጽሔት ጋር ባካሔዱት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡

በመጪው የአገልግሎት ዓመት ፓትርያርኩ፣ ሀገራዊ ብቻ ሳይኾን ዓለም አቀፋዊ አጀንዳ እንዲኖራቸው በማድረግ ለሰላምና ለፍቅር ዓለም አቀፋዊ ጫና ፈጣሪ እንዲኾኑ መታሰቡን ልዩ ጸሐፊው ጠቁመዋል፡፡ “ታላላቅ ኮንፈረንሶችን በማዘጋጀት፣ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የመወያያ መድረኮችን በመክፈት፣ በኢኮኖሚያዊና በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሥራ እንደሚሠራ” ጠቅሰው በአፈጻጸሙም፣ “በርካታ ኤክስፐርቶች እንዲካተቱበት ይደረጋል፤” ብለዋል፡፡ “ቅዱስ አባታችን ከሙስና የጸዱ እጆች ይፈልጋሉ፡፡ ሙስናን የተጸየፈ አሠራርና አርኣያነት እንዲኖረን ያስፈልጋል፤” ያሉት ልዩ ጸሐፊው፣ “የቅዱስነታቸውን ራእይ ለማስፈጸም ከላይ እስከ ታች ወቅቱን በመዋጀት፣ ሕዝቡን በታማኝነትና በተጠያቂነት ማገልገል አለብን፤” በማለት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

አባ ሠረቀ ብርሃን ይህን ይበሉ እንጂ፣ የተመደቡበት ፊርማ ሳይደርቅ፣ ታማኝነታቸውንና ተጠያቂነታቸውን ክፉኛ ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ዝንባሌዎችንና ድርጊቶችን ከወዲኹ እያሳዩና እየፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ ከምደባቸው አስቀድሞ በንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ቦታ የመተካታቸው ዜና ከተጠቆመበት ጊዜ ጀምሮ፣ “ከድጡ ወደ ማጡ ነው” በሚል መዛወራቸውን የተቹት ጥቂቶች አይደሉም፡፡

ቅዳሴንና ቅኔን ከነአገባቡ ተምረው በመምህርነትም ማስተማራቸውንና በዘመናዊውም አንደኛ ደረጃን ማጠናቀቃቸውን የሚጠቅሱት አባ ሠረቀ ብርሃን፤ ቅዳሴ በተማሩበት የደብረ ኣባይ ገዳም መመንኰሳቸውን ይናገራሉ፡፡ አብረዋቸው የሠሩና በቅርበት የሚያውቋቸው ግን፣ እንደ መነኰስ መጠን ጠባያቸውን ገና ያላረሙ ችኩልና ቀዥቃዣ፤ እኔ ብቻ ዐዋቂና ትክክለኛ ነኝ የሚሉ ዓምባገነን መኾናቸውን ነው የሚገልጹት፡፡ ከምግባርም አኳያ፣ “ለእምነታቸው ሳይኾን ለሆዳቸውና ለገንዘብ የሚኖሩ፣ ያለፍርሃት የሚዋሹ፣ ያለኀፍረት የሚሰርቁ ከሰው ጋር ተባብረውና ተግባብተው መኖርን የማያውቁ፤ በሐሰት ማንኛውንም ኃጢአት ኹሉ ሊሠሩ የሚችሉ ሰው ናቸው፤” ይላሉ የሎስአንጀለስ ምእመናን ስለ እርሳቸው ሲመሰክሩ፡፡

“የተማረና ሰዎችን የሚያስተምር ጥሩ ካህን” በመፈለግ ነበር፣ ምእመናኑ፣ እ.አ.አ በመስከረም ወር 1993፣ አባ ሠረቀ ብርሃንን ከአዲስ አበባ ወደ ሎስአንጀለስ በመውሰድ በጻድቁ አቡነ አረጋዊ ስም ቤተ ክርስቲያን እንዲቋቋም ያደረጉት፡፡ ከጊዜ በኋላ ግን አባ ሠረቀ ብርሃን ከምእመናኑና ከሌሎች ካህናት ጋር ካለመስማማታቸውም በላይ፣ ‹‹ቤተ ክርስቲያን የለችም፤ አቡነ አረጋዊም የሚባል ቤተ ክርስቲያን የለም፤›› እያሉ በእምነታችን የሌለ ኑፋቄ መስበክ ጀምረው ነበር፤ ይላሉ ምእመናኑ።

አቤቱታቸውን በወቅቱ የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ለነበሩት ብፁዕ አቡነ ማትያስ አቅርበው፣ ብፁዕነታቸው ‹‹ተሳስባችሁ አብራችሁ ኑሩ›› ብለው አባ ሠረቀን ቢመክሯቸውም፣ “ከአኹን በኋላ እዚኽ አላገለግልም፤ ብርሌ ከነቃ…” የሚል መልስ እንደሰጧቸው ምእመናኑ ያስታውሳሉ፤ ሲሰናበቱም ታቦቱን እንዲያስረክቡ በሊቀ ጳጳሱ ቢታዘዙም፣ በብሪፍ ኬዝ የያዙትን መጽሐፍ ቅዱስ ታቦት ነው፤ በሚል እንዳታለሏቸውና ከሌሎች ንዋያተ ቅድሳት ጋር እንደወሰዱባቸው ምእመናኑ ገልጸዋል፡፡

ምእመናኑ፣ “ለጆሮ የሚከብድ ነው” ላሉት የአባ ሠረቀ ብርሃን ዝርፊያ፣ የወቅቱን ሊቀ ጳጳስ የዛሬውን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስንና ታቦቱን እንዲያረካክቡ ያዘዟቸውን የሳንዲያጎ ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ አባ ኢሳይያስን(በኋላ ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስን) በእማኝነት ይጠቅሳሉ፡፡ ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃንንም ዛሬ የሚያስታውሷቸውአባ ሰራቂ በሚል ስም ነው፡፡ የሥርዓተ ምንኵስናውን ድንግልናዊ ሕይወት በመጠበቅም በኩል፣ አባ ሠረቀ ብርሃን ለአርኣያነት የሚበቁ አይደሉም፡፡ በኪራይ በሚኖሩበት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕንፃ ላይ የሚጎራበቷቸውን ባልደረቦቻቸውን ጸጥታ፣ በሚዳሯቸው ሴቶች ካካቴ በማወካቸው ሳቢያ የቀረበባቸው ስሞታ በብዙዎች ዘንድ የሚታወቅ ነው፡፡ ከስም መነኰሳዪያትና ቆባቸውን ጥለው በትዳር የሚኖሩትን በማማገጥ ጭምር ከቀጠሉበት ሴሰኝነታቸው ጋር በተያያዘም የመድኃኒት ተጠቃሚ እንደኾኑ ነው በስፋት የሚነገረው፡፡

አባ ሠረቀ ብርሃን የሚቀርቡባቸውን ክሦች ኹሉ የሚከላከሉት፣ ”ጥርሱን ያገጠጠና ዓይኑን ያፈጠጠ ፈርጣማ ውሸትና የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው፤” በማለት ነው፡፡ “በማንነቴ፣ በንጹሕ ሃይማኖቴና በክብሬ ላይ ከባድ የግድያ ወንጀል ተፈጽሞብኛል፤” የሚሉበትን መንሥኤ ሲያስረዱም፣ “ከቤተ ክህነቱና ከቤተ መንግሥቱ እይታ ውጭ የኾኑ ስውራን ኃይሎች፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና ሥርዓት እንዲያከብሩና ሀብትዋና ንብረትዋ እንዲጠበቅ እጅግ መራራ ተጋድሎ በማድረጌና ባሳየኹት ውጤት ነው፤” ይላሉ፡፡

በሃይማኖታዊ አቋማቸውም፣ “አንድም ሕፀፅ ቀርቶ ዳኅፀ ልሳን እንደማይገኝብኝ የእውነት ባለቤት እውነተኛ አምላክ ምስክሬ ነው፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ባለኝ ጽኑ እምነት በአርኣያ ሥላሴ የተፈጠረ ሰው ይቅርና ጠላት ሰይጣንም አይመሰክርብኝም፤” የሚሉት አባ ሠረቀ ብርሃን፣ “ባይኾን ኦርቶዶክሳዊ አጥባቂና አክራሪ ነው ቢሉኝ የተሻለ ነበር፤” ሲሉ ይመልሳሉ፡፡ ዛሬም ድረስ ለፀራውያን አካላት የማይታይ እጅና መረጃ አቀባይ ኾነው ይሠራሉ መባላቸውንም፣ “መረጃ ቀርቦ እስካልተወገዙ ድረስ መገናኘቴ ሊያስጠረጥረኝ አይችልም፤” በማለት ነው ነገሩን የሚያቃልሉትና የሚያስተባብሉት፡፡

ይኹንና ከተግባር እንደታየው፣ አባ ሠረቀ ብርሃንን ስለቃላቸው ብቻ ለማመን ያስቸግራል፡፡ “በቅሎ እጸዳዳለኹ ስትል ንዋየ ውስጧን ታሳያለች” እንዲሉ፣ አባ ሠረቀ ብርሃንም፣ ንጹሕ ነኝ ለማለት ሲንፈራገጡ ከሚያነጥቧቸው ድብቅ አጀንዳዎቻቸው፣ በመንበረ ፓትርያርኩ ያሉ የተሐድሶ መናፍቃን ቁልፍ ሰው እንደኾኑ ለመረዳት አያዳግትም፤ ይላሉ፣ በቅርበት የሚያውቋቸው፡፡

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ ሳሉ፣ ሐምሌ 14 ቀን 2001 ዓ.ም. ከታተመው መሰናዘርያ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ “ፍጹም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጅ ነኝ” ቢሉም በክህነት አገልግሎታቸው ግን ልዩ ሃይማኖታዊ ማንነትን በሚያጠፋውና የተሐድሶ ኑፋቄ አንድ ገጽታ በኾነው የዩኒቨርሳሊዝም አስተሳሰብ(religious universalism) ውስጥ እንዳሉ ተጋልጧል፤ እምነት አልለይም፤ ፕሮቴስታንትም ከኾኑ ሙስሊሞችም ከኾኑ አገለግላለኹ፤” ብለው ነበር፤ በዚያ ቃለ ምልልሳቸው፡፡

“እምነት ሳይለዩ የሚያገለግሉት ካህን” አባ ሠረቀ ብርሃን፣ በቅዱስ ሲኖዶስ እና በፓትርያርኩ መካከል ስላለው የቅድምናና የሥልጣን የበላይነት(primacy) ጉዳይም ከፍተኛ ብዥታና መደናገር ውስጥ የሚገኙ ከመኾናቸው የተነሣ፣የቤተ ክርስቲያን ራስ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው የሚለውን ግልጽ ኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሕግ ሲጥሱና ሲዘነጉ ይታያሉ፡፡ ይህንንም በተለያዩ ጊዜያት ከጻፏቸው ደብዳቤዎችና ከሚጋጩ ንግግሮቻቸው መረዳት ይቻላል፡፡

“እውነትና ንጋት” በሚል ርእስ ባሳተሙትና ከቀድሞው የሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዛሬው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር፣ ከአዳማዊ የውርስ ኃጢአት አንፃር በነገረ ማርያም ተፈጥሮ ስለነበረው ውዝግብ ባስረዱበት የዶሴዎች ስብስብ መጽሐፋቸው ገጽ 78 እና 80 ላይ፣ “ከክርስቶስ በታች የቤተ ክርስቲያናችን ራስ” ቅዱስ ሲኖዶስ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ በተፃራሪው በዚኹ መጽሐፋቸው ገጽ 219 ላይ፣ “ልዩ ማስታወሻ ለቅዱስ ፓትርያርኩ” በሚል ርእስ ለቀድሞው ፓትርያርክ በጻፉት ደብዳቤ፣ ፓትርያርኩን፣ “ከክርስቶስ በታች የቤተ ክርስቲያናችን ራስ እንደመኾንዎ መጠን አመራር ቢሰጡበት” የሚል ሐረግ ተጠቅመዋል፡፡

ከኹለት ዓመት በፊት በተካሔደው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 33ኛ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ፣ አባ ሠረቀ ብርሃን፣ የፓትርያርኩን ሥልጣን ፍጹምነትና የበላይነት የሰበኩበት ንግግራቸው፣ በአዳራሹ በነበሩት ተሳታፊዎች ብቻ ሳይኾን በአጽናፈ ዓለም ባሉ ቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን በጽኑ ተወግዞ ነበር፡፡ የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያን በመወከል በጉባኤው የታደሙት አባ ሠረቀ ብርሃን፡- በምድር ላይ የአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፍጹም አባት፣ ክርስቶስን ወክሎ ድምፁን እንድንሰማ፣ እሺ በጄ ብለን እንድንታዘዘውና እንድናገለግለው የታዘዝነው አንድ አለ፤ እርሱም አንድ ቅዱስ ፓትርያርክ ነው፤” ነበር ያሉት፡፡

በወቅቱም በአንድ ቀናዒ ኦርቶዶክሳዊ ተሳታፊ የተሰጣቸውና በተሰብሳቢውም ከፍተኛ ተቃውሞ የተገለጸበት ምላሽ፡- “ፖፑ ኃጢአት አይሠራም፤ የማይሳሳት የክርስቶስ እንደራሴና ወኪል ነው ብላ የምታስተምረው ካቶሊክ ናት እንጂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አይደለችም፤ የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ በመመሪያ ማስተላለፍ የቅዱስ ፓትርያርኩ ተግባር ነው፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ይከበር!” የሚል ነበር፡፡

አባ ሠረቀ ብርሃን ግን ከስሕተታቸው የሚማሩ አይመስሉም፡፡ የቅዱስ ሲኖዶሱን ሥልጣንና የቅዱስ ፓትርያርኩን ተግባርና ሓላፊነት እያጋጩ ያስቸግራሉ፡፡ ባለፈው ሳምንት ለአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ኆኅተ ጥበብ መጽሔት በሰጡት ቃለ ምልልስ እንኳ፣ “ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ከክርስቶስ በታች የቤተ ክርስቲያን ርእሰ መንበር ናቸው፤ ርዕሰ አበውም ናቸው፤” የሚል ውጥንቅጥ አገላለጽ አንጸባርቀዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ርእሰ አበው ቢኾኑም ርእሰ መንበር መባላቸው ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር መዛመድ ሲገባው ቤተ ክርስቲያን ከሚለው ጋር መጫፈሩ አነጋጋራቸውን አሻሚ ያደርገዋል፡፡

ይህም በአንድ በኩል፣ በጉዳዩ ላይ ያላቸው ግንዛቤ ወይ ያልረጋ አልያም ከኦርቶዶክሳዊው ቀኖናና ሕግ ጋር ያልታረቀና ተፃባኢ መኾኑን ሲያመለክት፤ በሌላ በኩል ግን፣ የልዩ ጸሐፊነታቸውን ምደባ “የቤተ ክርስቲያኒቱ ራስ” ከሚሏቸው የፓትርያርኩ ሥልጣን ጋር በትይዩ በማስቀመጥ ፍቅረ ሢመታቸው የተጋለጠበትና ዓምባገነናዊ ሥነ አእምሯቸውን ያሳበቀባቸው ኾኖ ተወስዷል፡፡ ልዩ ጽ/ቤቱን ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ቀሲስ ከተረከቡበት ሐምሌ 13 ቀን ጀምሮ፣ ሓላፊነታቸው በሚሰጧቸው ዕድሎች ኹሉ በመጠቀም ለማዕርገ ጵጵስና ለመታጨት እየተሯሯጡ እንዳሉ ታውቋል፡፡

ለወጉ ሲናገሩማ፣ “ከመንፈስ ቅዱስ ምርጫ ውጭ በራሴ ፍላጎት የሚሰጥ የጵጵስና ማዕርግ ካለ ለሕይወቴ ካንሰር ነው፤” ነበር የሚሉት፤ ነገር ግን ቀድሞ እንደተጠቀሰው፣ አባ ሠረቀ ብርሃን ስለ ቃላቸው ብቻ ሊታመኑ እንደማይችሉ በውል የሚያውቋቸው የሎስአንጀለስ ምእመናን እንዳሉት፣ “ለሥልጣን፣ ለገንዘብና ለሆዳቸው ሲሉ በሐሰት ማንኛውንም ኃጢአት ኹሉ ሊሠሩ የሚችሉ” ናቸውና አይደንቅም፡፡ ‹‹የአቡነ ጳውሎስ እንደራሴ ነኝ፤ እኔ ማንንም መነኵሴ ጳጳስ እንዲኾን አስደርጋለኹ፤›› ከሚለውና እዚያው ሎስአንጀለስ ከኖረ ካህን ጋር ገጥመው እንደነበር ምእመናኑ ከኹለት ዓመት በፊት ያጋለጡት ጉዳይ ነበር፡፡ ዛሬ ግን፣ ከተቻላቸው፣ ለኤጲስ ቆጶስነት ከታጩት ቆሞሳትና መነኰሳት ዝርዝር ለመደመርና ለመሾም፤ ካልኾነም ሒደቱ ተሰናክሎ ሌላ አስመራጭ ኮሚቴ እንዲቋቋም፣ ከፓትርያርኩ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ጨምሮ ተጽዕኖ ሊፈጥሩ የሚችሉባቸውን መንገዶች ኹሉ ለመጠቀም እየተጉ ይገኛሉ፡፡

አባ ሠረቀ ብርሃን ቀድሞም ከተጠቋሚ ቆሞሳት ዝርዝር የገቡት፣ በዋናነት፣ በፓትርያርኩ አማካይነት ለኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ተጠቁመው ነው፡፡ የዛሬው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ሳሉ ለአባ ሠረቀ ብርሃን በነበራቸው ሚዛን፣ ስንኳን ኤጲስ ቆጶስነት የመምሪያ ሓላፊነት ሹመት እንኳ የሚገባቸው እንዳልነበሩ ራሳቸው በወቅቱ የተናገሩበት ጉዳይ ነበር፡፡ አባ ሠረቀ ብርሃን በ1998 ዓ.ም. ከአሜሪካ እንደተመለሱ፣ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ ኾነው መመደባቸውን የወቅቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማትያስ ተቃውመው ነበር፡፡ “ሀገረ ስብከቱ[የሰሜን አሜሪካ] ሊቀ ጳጳስ ሳይጠየቅ የመምሪያ ሓላፊ ኾነው መመደባቸው ትክክል አይደለም፤” በማለት ቅሬታቸውን ገልጸው የነበሩት ብፁዕነታቸው፣ “የቤተ ክህነቱ ነገር ተቃራኒ ነው፤ ሹመት ለማይገባው ሹመት ይሰጣል!” ሲሉ ነበር የአባ ሠረቀ ብርሃንን ምደባ ክፉኛ የተቹት፡፡

ብፁዕነታቸው በዚኽ መልኩ አባ ሠረቀ ብርሃንን፣ መተቸታቸውና መቃወማቸው፣ ካህኑ የሎስአንጀለስ ምእመናንን አደራ በልተው የፈጸሙባቸውን የጽላት ስርቆትና ከፍተኛ የእምነት ማጉደል ወንጀል በቅርበት ስለሚያውቁት ብቻ አልነበረም፡፡ ከዚያም በላይና ከዚያም በፊት፣ አባ ሠረቀ ብርሃን፣ ከአዳማዊ የውርስ ኃጢአት አንፃር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕናና ቅድስና ላይ በተሰነዘረው ኑፋቄ ተባባሪ የነበሩ መኾናቸውን በውል ስለሚረዱ ነው፡፡

በካንሣሥ ሲቲ ካንሣሥ ደብረ ገነት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ተከሥቶ በነበረው የነገረ ሃይማኖት ውዝግብ፣ መፍትሔ እናስገኛለን በሚል ከተሰበሰቡት ሰባት ካህናት መካከል አባ ሠረቀ ብርሃን አንዱ የነበሩ ሲኾን፣ ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ አልነበረባትም፤ የሚለው አባባል ከቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍትና ከቀድሞ አባቶቻችን ሊቃውንት የራቀ አድርጎ ማቅረቡን፤ ቅድስት ድንግል ማርያም ከአዳም የተላለፈ የውርስ ኃጢአት ነበረባት፤ የሚለው ኑፋቄ ከመጻሕፍት የወጣ ትምህርትና እምነት አይደለም ብሎ ማመኑን፤ ብፁዕነታቸው፣ ጥር 18 ቀን 1997 ዓ.ም. ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽፈውት በነበረው ደብዳቤ በስፋት አብራርተዋል፡፡

ብፁዕነታቸው በደብዳቤአቸው፣ የቤተ ክርስቲያናችንን እምነትና አስተምህሮ ለማስረዳት፣ ከብዙ የቅዱሳት መጻሕፍት አስረጅዎች ጋር ከጠቀሷቸው መካከልም፣ “አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኃጢአት(ጥንተ አብሶ) ያላገኛት፤ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት፤ ገና ከመወለዷ አስቀድሞ በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖር የነበረች ቅድስት ናት፤” የሚለውና “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና የውጭ ግንኙነት” (ምዕ. 7 ገጽ 49) በሚል ርእስ በቅ/ሲኖዶስ ፈቃድ በወጣው መጽሐፍ የሰፈረው ይገኝበታል፡፡


ዋናው ክርክራችን፡- እመቤታችን ከተወለደች በኋላ ስለተፈጸሙላት የቅድስና ጸጋዎች ሳይኾን፣ ስለ ጥንተ አብሶ(የውርስ ኃጢአት) ነው፤ ድንግል ማርያም ከውርስ ኃጢአት የነጻችው ከመወለዷ በፊት ነው ወይስ ከተወለደች በኋላ በሚለው ነጥብ ላይ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለተዋሕዶተ አካላዊ ቃሉ የመረጣት ስለኾነ ከእናቷ ማኅፀን ጀምሮ ንጽሐ ጠባይዕ ሳያድፍባት፣ ከአዳም በዘር ይተላለፍ የነበረው የውርስ ኃጢአት ሳያገኛት፣ በመንፈስ ቅዱስ ተጠብቃ ኑራለች፤ ሐቁ፣ ግልጹ፣ እውነቱ ይኼ ነው፡፡ እኔም የደገፍኹት ይኼንኑ ነው፡፡ መደገፍ ብቻ ሳይኾን እምነቴም ነው፡፡ ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት የለባትም፤ የሚለው እምነት የቤተ ክርስቲያኗ እምነትና ትምህርት ነው፤ የእኔም እምነት ነው፤ …ማኅበረ ካህናቱ የቀሲስ አስርተርአየ ጽጌን ትምህርት ደግፎ ውሳኔ አሳልፏል፡፡


አባ ሠረቀ ብርሃን በአንፃሩ እንደለመዱት፣ ብፁዕነታቸው ለቅዱስ ሲኖዶሱ ያቀረቡትን አቤቱታ፣ “የስም ማጥፋት ክሥ” በማለት ነበር ለማጣጣል የሞከሩት፡፡ ብፁዕነታቸው፣ በውል ሳይገነዘቡት የያዙት አቋም እንደኾነ አድርገውም ነበር፣ የተቹዋቸው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ግን፣ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ የኾኑ ሰባት ማኅበራትንና 16 ግለሰቦችን ጉዳይ፣ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጥምር ኮሚቴ በመመርመር ውግዘት ባስተላለለፈበት የግንቦት 15 ቀን 2004 ዓ.ም. ምልአተ ጉባኤው፣ በዚኹ የአባ ሠረቀ ብርሃን ጉዳይም ውሳኔ አሳልፎ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

አባ ሠረቀ ብርሃን በጉዳዩ ለላየይ የእምነት አቋማቸውን ለዐቢይ ጉባኤው እንዲያስረዱ ሲጠየቁ፡-

“የእኔ አቋም የቤተ ክርስቲያኔ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውና የሚሰጠው ውሳኔ ነው፡፡ ይኸውም፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና የውጭ ግንኙነት በሚል ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቅዶ በታተመው የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት፣ ስለ ነገረ ማርያም አስተምህሮ የተገለጸው ትምህርት፣ ቀድሞም የማምነው አኹንም የማረጋግጠው እርሱን ነው፤ ከዚኽ ውጭ ስለ ነገረ ማርያም አስተምህሮ የተናገርኹት፣ ያስተማርኹትና የጻፍኩት የለም፤ በነገረ ማርያም ያለኝ አቋምና ጽኑዕ እምነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነው ውሳኔ ብቻ ነው፤ አምላካችኹ ያየኛል፤ ከዚኽ የተለየ ዓላማና ተልእኮ የለኝም፤ ከዚኽም ሌላ የምሥራቸው ሥራዎች ኹሉ በሕግና በትክክለኛው መንገድ፣ ሕጋዊ በኾነ ግልጥ አሠራር ለቤተ ክርስቲያኔ ከምሠራ በቀር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መመሪያና ሥርዓት ውጭ የኾነ የእምነት ሕፀፅ የሚያስከትልና ኅብረተሰብን የሚጎዳ ሥራ አልሠራኹም፤ አልሠራምም፤”

በማለት የእምነት አቋማቸውን በቃል ገልጸው ነበር፡፡ ይኹንና ቀደም ሲል እንዳመለከትነው፣ አባ ሠረቀ ብርሃን፣ ስለቃላቸው ብቻ የሚታመኑ አይደለምና፣ ነገረ ማርያም አስተምህሮ ላይ ለአጥኚ/ጥምር ኮሚቴው በቃላቸው የገለጹትን እንደገና በጽሑፍ እንዲያረጋግጡ እንዲኹም፣ “እውነትና ንጋት” በሚል ባሳተሙት መጽሐፍ ገጽ 38 ላይ፣ የጥንተ አብሶ ትምህርትን አስመልክቶ ስለአሰፈሩት ጽሑፍ ለአጥኚ ኮሚቴው የጽሑፍ ማስተባበያ እንዲሰጡ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ወስኖባቸው ነበር፡፡

Holy Synod's decision on Aba Sereke Birhan Woldesamuel
እርሳቸው ግን፣ በቃል የተናገሩትን የእምነት አቋማቸውን በጽሑፍ በማረጋገጥ የታዘዙትን በውሳኔው መሠረት ከመፈጸም ይልቅ በአቋራጭ ንጽሕናቸውን ለማወጅ ነበር የተሽቀዳደሙት፡፡

ከምልአተ ጉባኤው ውሳኔ ቀደም ሲል ባሳተሙት “እውነትና ንጋት” መጽሐፋቸው፣ “በሃይማኖቴ ዙሪያ እንከን አለበት ብሎ የሚቃወም አንድም ሰው ከተገኘ ሙሉ በሙሉ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠኝን ፍርድ እቀበላለኹ፤” (ገጽ 90 እስከ 93) ቢሉም፣ የምልአተ ጉባኤውን ውሳኔ በሙሉ ቃሉና መንፈሱ ባልተገበሩበት ኹኔታ፣ ለምልአተ ጉባኤው የቀረበው የማጣሪያው ጽሑፍ ነፃ ስላደረገኝ የማስረጃ ወረቀት ይሰጠኝ ሲሉ ለቀድሞው ፓትርያርክ ባቀረቡት ማመልከቻ ብቻ “ለሚመለከተው ኹሉ” የሚል ደብዳቤ አጽፈዋል፡፡ ይህም ቢኾን ደብዳቤው፣ ከፓትርያርኩ በታዘዘው መሠረት የተሰጠ መኾኑን እንጂ አባ ሠረቀ ብርሃን የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ ስለመፈጸማቸው የሚያረጋግጥ ባለመኾኑ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

አባ ሠረቀ ብርሃን ግን፣ “ቅድስት ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት አለባት” የሚለውን አውግዘው የእምነት አቋማቸውን በግልጽና ቀጥተኛ ዐረፍተ ነገሮች ለማስረገጥ ለምን ከበዳቸው?! በመካከለኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ ግብፃዊው ጳጳስ አቡነ ክሪስቶዶሉ፣ “ሃይማኖትዎ ምንድን ነው?” ተብለው ሲጠየቁ፣ “ሃይማኖቴ ተዋሕዶ ነው” በማለት ፈንታ፣ “ሃይማኖቴ ከኔ በፊት እንደነበሩት እንደ አባ ማርቆስና እንደ አባ ሲኖዳ ነው፤” በሚል በሰጡት የአድርባይነት መልስ እርስ በርስ ያፋጁበት ዓይነት ተንኰል አኹን አይሠራም፡፡ ብፁዕ አቡነ ማትያስም፣ በዚያ ደብዳቤአቸው፣ በትክክልና በአግባቡ እንዳስቀመጡት፣ ይህ ተራ ነገር ሳይኾን የእምነት ጉዳይ ስለኾነ በሽምግልና የሚተው ነገር አይደለም! ያሉት መያዝ ይኖርበታል፡፡

ዛሬም ከአባ ሠረቀ ብርሃን ያለመታመን አኳያ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ የግንቦት 2004 ዓ.ም. ውሳኔ አፈጻጸም እንደዋዛ የሚታይበት ኹኔታ ሊኖር አይገባም፡፡ ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፣ ለኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ቢጠቆሙም፣ ከመጨረሻዎቹ 31 ዕጩዎች ያልተካተቱበት ምክንያት፣ ከእኒኽና መሰል እምነትና ምግባር ጠቀስ ጉድለቶቻቸው የራቀ መስሎ አይታይም፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው፣ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ በመጠበቅ ለተፈጻሚነቱ ታምኖ ሲገኝ፤ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ከነገረ ቀደም በባለቤትነት ላቀረቡትና፣ “በሽምግልና የሚተው አይደለም” ላሉት ሃይማኖታዊ ጉዳይ ጽኑ አቋም ይዘው ሊገኙ ያስፈልጋል፡፡

በኤጲስ ቆጶሳት ተጠቋሚ ቆሞሳትና መነኰሳት ማጥናት፣ መመርመርና ማጣራት ወቅት፣ አባ ሠረቀ ብርሃንን ወደ ዕጩነት ለማሳለፍ በተደጋጋሚ የተደረገው ጥረት አለመሳካቱን ተከትሎ፣ የተደረገላቸው የልዩ ጸሐፊነት ምደባቸው፣ እርሳቸውን “የማጽናናት” ፋይዳም እንዳለው እንደዋዛ ሲገለጽ ተሰምቷል፡፡ አባ ሠረቀ ብርሃን ግን፣ ሹመቱን ለመቀዳጀት ካልኾነም ሒደቱን አሰናክሎ የሚሾሙበትን ኹኔታ ለመፍጠር የልዩ ጽ/ቤቱን መዋቅራዊ አቅሞች ኹሉ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡

አንዱ መንገድ፡- በአስመራጭ ኮሚቴው እንቅስቃሴ ዙሪያ የባለሥልጣናትን ቀልብ የሚገዙ ውትወታዎችን በማናፈስና በደኅንነት ስም የሚነግዱ ግለሰቦችን በተለያዩ መንገዶች በማግባባት በአስመራጭ ኮሚቴው አባላት ላይ ጫና እንዲፈጥሩ ማድረግ ነው፡፡ በዚኽም ራሳቸውን ጨምሮ በስም የተጠቀሱ አራት ተጠቋሚዎች ወደ ዕጩነት እንዲያልፉና እንዲሾሙ፣ “የመንግሥት ፍላጎት ነው፤ እነርሱ ካልገቡ ሹመቱ አይካሔድም” በሚል የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት በቢሯቸው፣ በማረፊያቸውና በየመንገዱ ሳይቀር በስልክና በአካል እንዲዋከቡ አድርገዋል፡፡

አንዳንድ ተጠቋሚ መነኰሳት፣ በተወገዘው ሲሞናዊ መንገድ ጥረት ማድረጋቸውንና በዚኽም የተፈጠሩ ክፍተቶችን በመለጠጥ፣ የአስመራጭ ኮሚቴውን ጠቅላላ አሠራሮችና ውሳኔዎች ተቀባይነት እንዳይኖራቸው የማብከት ዘመቻም ይዘዋል፡፡ “እኔን ያስወጡኝ አምስት ሳንቲም ስላልሰጠኹ ነው፤ በእምነቴ ችግር የለብኝም” የሚሉት አባ ሠረቀ ብርሃን፣ “መነገጃ አድርገውታል፤ ራሳቸውን አብልጽገዋል” ያሏቸውን የኮሚቴውን አባላት በስም በመጥቀስ ለባለሥልጣናት ከሠዋቸዋል፡፡

ሌላው ተጽዕኖ የመፍጠርያ መንገዳቸው ደግሞበልዩ ጽ/ቤት ሓላፊነታቸው ተጠቅመው የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት በኾነው በአዲስ አበባ የአንዳንድ አድባራት ሓላፊዎችን ቀስቅሶ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር የሚገናኙበትን ኹኔታ ማመቻቸት ነው፡፡ ሕግንና መዋቅራዊ አሠራርን አስከብራለኹ በሚል ሌላውን ከመክሠሥ የማይቦዝኑት አባ ሠረቀ ብርሃን፣ ወደ ዓለምአቀፋዊ ሰውነት ተሸጋግሬበታለኹ በሚሉት ልዩ ጽ/ቤት፣ ደረጃውን የማይመጥን መርሐ ግብር ይዘው ተገኝተዋል፡፡ ቅስቀሳውን በማስተባበርም፣ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅና እንደ ምክትል ሥራ አስኪያጁ አፈ ወርቅ ዮሐንስ ያሉ ዋልጌዎች አግዘዋቸዋል፡፡

ይኹንና በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአድባራት አለቆችና የጽ/ቤት ሠራተኞች(ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎጎች ጋር ግንኙነት ያላቸው የላፍቶ ክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅ አባ አእምሮ ታከለ እና በአማሳኝነታቸው ሕዝብ ያባረራቸው የቀድሞው የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ አለቃ አባ ገብረ ሚካኤል ወልደ ሳሙኤልም አሉበት) ከኻያ የሚበልጡ አልነበሩም፡፡

ተቃውሞ የተባለው በቀረበበት ወቅትም፣ የአስመራጭ ኮሚቴው አባቶች ተዘልፈዋል፤ በአንፃሩ በማጣራቱ፣ በመመርመሩና በማጥናቱ ሒደት ከዝርዝሩ ከወጡት ተጠቋሚዎች መካከል በስም ተለይተው ባይጠቀሱም፣ “ለምን አልገቡም” በሚል ጠቁሞ የማሳየት ያኽል የተወደሱም መኖራቸው ከጀርባ የሚገፉትን ተጨማሪ ኃይሎች ለመለየት አስችሏል፡፡ ከእኒኽም አንዱ እንደ ‘አባ’ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ ያሉ አገር ያወቃቸው ምግባረ ብልሹዎች መኾናቸው ተደርሶበታል፤ በእነአባ ሠረቀ ብርሃንና በእነአፈ ወርቅ ዮሐንስ ምክር ከተደራጀ ተቃውሞ ጥንቱንስ ምን ይጠበቃል!?

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት ሳይወክሏቸው “ተወካዮች ነን” በሚል፣ በማጣራት ሒደት በወጡ ጥቂት ተጠቋሚዎች ግፊትበእነአባ ሠረቀ ብርሃንና አባ አፈ ወርቅ አስተባባሪነት፣ በዛሬው ዕለት ለፓትርያርኩ ጥያቄና ተቃውሞ ያቀረቡ የክ/ከተማ፣ የአድባራት አለቆችና የጽ/ቤት ሓላፊዎች፡-

 • አባ አፈ ወርቅ ዮሐንስ – (የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ምክትል ሥራ አስኪያጅ)፤
 • አባ አእምሮ ታከለ – (የላፍቶ ክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅ)
 • አባ ገብረ ሚካኤል ወልደ ሳሙኤል – (የቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ)
 • አባ ገብረ ሥላሴ አማረ – (የሰሚት መድኃኔዓለም አለቃ)
 • መልአከ ሣህል ዓለማየሁ – (የአውግስታ ማርያም አለቃ – የ‘አባ’ ቃለ ጽድቅ ቲፎዞ)
 • መ/ር ለይኩን – (የቀበና ኪዳነ ምሕረት አለቃ)
 • የቀበና ኪዳነ ምሕረት ጸሐፊ
 • የደብረ ዕንቍ ልደታ ለማርያም አለቃ
 • መስፍን ታከለ – (የፊልጶስ ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ)
 • ዲያቆን ደነቀ ተሾመ – (የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ)
 • ገብረ ሚካኤል (የደብረ አሚን አቡነተክለ ሃይማኖተት ቁጥጥር)
 • ቀሲስ ሠናይ ባያብል – (የግቢ ገብርኤል ቁጥጥር የነበረ)
 • መ/ር ቤዛ ፈንታ – (የዓለም ገና ስብከተ ወንጌል የነበረና አኹን በኑፋቄው የታገደ)
 • ግርማ ቀሬ – (የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ አገልጋይ) ይገኙበታል፡፡

በፓትርያርኩ ጥሪ በወቅቱ የተገኙት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ብፁዕ ዋና ጸሐፊውና ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ዘለፋውንም ውዳሴውንም በጥሞና አዳምጠዋል፡፡ የዘለፋውና የከንቱ ውዳሴው ዝናም ያዘነቡት፣ የአዲስ አበባ ተወካዮች ነን ባዮች ከተሰናበቱ በኋላም፣ ከፓትርያርኩ ጋር ኃይለ ቃል የተመላባቸው ምልልሶችን ማካሔዳቸው ተገልጧል፡፡ በአዲስ አበባ አድባራት ስም መርሐ ግብሩን ማን እንደሚያስተባብረው እንደሚያውቁና በስም ጭምር መጥቀስ እንደሚቻል ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ተናግረዋል፡፡ አቤቱታ አቅራቢዎቹ የሚታወቁና ማንንም ሊወክሉ እንደማይችሉ በግልጽ አስቀምጠዋል፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተመረጠና ክፍተቶች ካሉበትም መታየትና መታረም የሚገባው፣ በአማሳኞችና የመናፍቃን ወኪሎች ቲፎዞና ግርግር ሳይኾን፤ ቋሚ ሲኖዶሱ በወሰነበት አግባብ እንደኾነ ለፓትርያርኩ በአጽንዖት አስረድተዋቸዋል፡፡

በርግጥም፣ የታቀደው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫና ሢመት ሊካሔድ የሚችለው፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የቀረቡትን ዕጩዎች በምርጫ ሥርዓት ደንቡ ከተደነገጉት መስፈርቶች አኳያ መዝኖ ለዕጩነት የሚበቁ መኾናቸውን ሲያምንበትና ሲቀበል ብቻ ነው፡፡ ከመመርመሩ፣ ማጥናቱና ማጣራቱ ክንውን አኳያ፣ ተጠቋሚዎች በዋናነት በአካባቢያዊ ማንነት እንዲለዩ ከመደረጉ ጀምሮ ንጽሕናቸውና ብቃታቸው በሚገባ ሳይታይ ከደንቡ ውጭ በኾነ መንገድ በዕጩነት ያለፉ ካሉም ምልአተ ጉባኤው አይቶ የሚበጀውን እንደሚወስን ይጠበቃል፡፡ እስከዚያው ድረስ የካህናትንና የምእመናን ተሳትፎ በሚያረጋግጥ አኳኋን አስመራጭ ኮሚቴው በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በኩል አስተያየቶችንና መረጃዎችን እየተቀበለ እንደሚቆይ ተስፋ ይደረጋል፡፡

ከዚኽ በተፃራሪ ግን፣ ከሃይማኖቱም ከምግባሩም የሌሉበት የፀራውያን ወኪሎችና ጥቅመኞች፣ ከፍተኛውን የክህነት ማዕርግ በመቀራመት በቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አመራር ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠርና ለመቆጣጠር የሚያደርጉት መፍጨርጨር፣ በመላው ካህናትና ምእመናን በተለይም አደራው በተጣለበት አስመራጭ ኮሚቴና በኖላውያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከወገንተኝነት የጸዳና የነቃ ክትልል ሊደረግበት ያስፈልጋል፡፡ አንድ ብፁዕ አባት እንዳሉት፣ የእነአባ ሠረቀ ብርሃንንና ‘አባ’ ቃለ ጽድቅን ውጫዊ ገጽታ ብቻ በማየት፣ ከባዱን የኤጲስ ቆጶስነት ሓላፊነት መስጠት፣ በጅብ ትክሻ የአህያ ሥጋ መጫን ነውና፡፡


አባ ሠረቀ ብርሃን ለዚህ የተለየ ክብር ይቅርና በጥቆማው በራሱ መካተት የሌለባቸው ናቸው፡፡ በአንድ አባት ላይ እንደዚኽ ማለት ቢከብድም፣ ለዚኽ ግን የሚገባ ሥራና አገልግሎት የላቸውም፡፡ ማስታረቅ፣ መምከር፣ ማስተማር፣ ለሌሎች አርኣያ መኾንና ሰው የክብሩ ወራሽ እንዲኾን ጥረት ማድረግ… ወዘተ የአንድ መንፈሳዊ አባት አነስተኛው መገለጫዎች ናቸው፡፡ እርሳቸዉ ግን ለመክሠሥና ለጠብ የፈጠኑ አባት ናቸው፡፡ የሌሎቹን አምላክ ቢያውቅም የአባ ሠረቀ ብርሃንን መጠቆም ግን ከአኹኑ መቃወም አለብን፡፡ የቤተ ክርስቲያን ፈተና ነው የሚኾኑትና እንዳይመረጡ መጸለይ አለብን፡፡ ስለዚኽ ለእኔ በግሌ ሊመጥኑ አይችሉም፤ እንዲያዉም የሃይማኖት ሕፀፅና ፖሊቲካዊ ተልእኮ ሊኖራቸዉ ስለሚችል ነገሩ ቢጣራ ጥሩ ነው፡፡ (በፌስቡክ ገጽ ከተሰጡ አስተያየቶች የተወሰደ)


 

Advertisements

28 thoughts on “አባ ሠረቀ ብርሃን የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊነት፤ ንቡረ እድ ኤልያስ የማሳተሚያ ድርጅት ሥራ አስኪያጅነት ተመደቡ፤ እነአባ ሠረቀ በልዩ ጽቤቱ ተገን ለጵጵስና እየቀሰቀሱ ነው

 1. Anonymous August 1, 2016 at 8:32 pm Reply

  dedeb denkoro aba sereke kalteshome nan lishom new tadya poletika yalew mak bet new

  • Anonymous August 2, 2016 at 9:49 am Reply

   አባ ሰረቀ የማደራጃ መምሪያ እያሉ በቢሮአቸዉ ዉስጥ ከየ ሀገሩ ለመጡ የተሀድሶ ተወካዮች ስልጠና ሲሰጡ የዐይን ምስክር ነኝ። ከሰልጣኞች ከነበሩትም መጥቀስ ይቻላል። ብዙ ዝርዝር መረጃ አለን።

 2. Dawit Teklu August 2, 2016 at 7:09 am Reply

  እባካችሁ ለጵጵስና በታጩት በአባ ሄኖክ እና በአስተዳደራቸው ላይ ያሉንን መረጃዎች ልንሰጣችሁ እንፈልጋለን እና እንዴት
  ልናገኛችሁ እንደምንችል ንገሩን።

 3. Teddy August 2, 2016 at 7:38 am Reply

  አባ ሰራቂ በከንቱ ትደክማታለክ እንጂ ጳጳስ መሆን መቼም ላታገኘው ይናፍቅሀል!!!

 4. ገ/ሚካኤል August 2, 2016 at 10:47 am Reply

  የስድብ ምንጮች(ሐራ ማቅ) ሆይ እግዚአብሔር ይገሥጻችሁ። የቅዱስ ሚካኤል ለስድብ አባት ለዲያብሎስ ያለው ይህን ነውና። ማቅን እንደ ቡችላ ካላገለገለ የማትለጥፉበት ታርጋ የለም አይደል??? ምን እላለሁ እግዚአብሔር ይገሥጻችሁ። ሰዎች ሆይ ምንም ታርጋ ቢለጠፍባችሁና ሆናችሁ ካልተገኛችሁ ዋጋችሁ ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ። መስቀልን መሸከም እንዲህ ነውና። መስቀልን የምታሸክሙ ውሉደ ፈሪሳውያን ( አይሁድ ) ግን በመጨረሻው ቀን ምን ይሆን መልሳችሁ። እግዚአብሔር መመለሱን ይስጣችሁ።

 5. ገ/ሚካኤል August 2, 2016 at 10:49 am Reply

  የስድብ ምንጮች(ሐራ) ሆይ እግዚአብሔር ይገሥጻችሁ። ቅዱስ ሚካኤል ለስድብ አባት ለዲያብሎስ ያለው ይህን ነውና። እንደ ቡችላ ካላገለገለ የማትለጥፉበት ታርጋ የለም አይደል??? ምን እላለሁ እግዚአብሔር ይገሥጻችሁ። ሰዎች ሆይ ምንም ታርጋ ቢለጠፍባችሁና ሆናችሁ ካልተገኛችሁ ዋጋችሁ ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ። መስቀልን መሸከም እንዲህ ነውና። መስቀልን የምታሸክሙ ውሉደ ፈሪሳውያን ( አይሁድ ) ግን በመጨረሻው ቀን ምን ይሆን መልሳችሁ። እግዚአብሔር መመለሱን ይስጣችሁ።

 6. Anonymous August 2, 2016 at 11:18 am Reply

  አይ አንቺ ሀገር !!!
  አይ አንቺ ቤተ ክርስቲያን!!!
  የጥፋት አጆች መቸ ይሰበሰቡልሽ ይሆን ?
  መቸም ጠባቂሽ አያንቀላፋም እንጅ የጠላቶችሽ ነገር አይነሳ፡፡

 7. Buruk August 2, 2016 at 11:34 am Reply

  እድሜ ለ”አባ” ማትያስ። ገና ብዙ ዉርደት እንሰማለን!!!

  • Anonymous August 2, 2016 at 7:52 pm Reply

   ማሠሪያ ባታሳጥር መልካም ነው
   አታፍርም? ስለምናውቃቸው አባ ሠረቀ ብርሃን ነው የምታወራው? የዋሽንግተንና የበርጂንያ ሕዝብ ይታዘባቸዋል። አትሞኙ አባታችን ጠንቅቀን እናውቃቸዋለን። ይቅርና ገንዘብ ሊሰርቁ ቀርቶ የሚያገኙትን ገንዘብ ለራሳቸው የማይጠቀሙ ድሆችን ለመርዳት የማይታክቱ፡ ፍቅረ ሲመትና ፍቅረ ንዋይ የጠፋላቸው ናቸው። ንፅሐ ምነናቸው የተመሰረተላቸው ቅዱስ አባት ናቸው፡ እስኪ የጎንደር ሊቃውንትና ገዳማት ጠይቅ?
   ኣባ ሠረቀብርሃን ለሰው እንጂ ለራሳቸው የማይኖሩ ናቸው።ታሳዝናላችሁ? አሁንስ ምን ቀራችሁ?
   የአባ ችግር ነው ከተባለ ፡ በዘመናችን ቅዱስ ፡ፍቅረ ንዋይ የጠፋላቸው፡መናኝ ሊቅ እውነተኛ፡ ለቤተክርስቲያን የቆሙ፡
   እውነተኛ ሐዋርያ መሆናቸው ነው።አንድ ነገር ልጠይቅህ
   ለመሆኑ እውነተኛ ከሆንክ እስኪ የሎስ አንጀሎስ ቃለ አቀባይህ ስም ጥቀስ? ምእመኑ ስለ ታቦት ጉዳይ ይናገር
   ለመሆኑ አታስብ? ታቦቱ ለማን ሰጡት? ያልከው እውነትነት ቢኖረው ኑሮ እንዴት ቅዱስ አባታችን የጠቀስካቸው ጳጳሳት ዝም አሉ? ምእመኑስ ለምን አልከሰሱም? ማሠርያህን አታሳጥ።።we Love you So much our father and we so proud of you Keep going we very much know who your enemies are. But as you taught us. we believe that the Lord is with you.

   • axumita August 3, 2016 at 11:54 pm

    እኔ አባቶችን ደፍሬ መናገር ባልችልም ግን የቨርጂንያና የዲሲ ሰው ሚያቃቸው ግን አንተ ባልከው መንግ0ድ አይደለም ስለዚህ እኛን ሳይሆን እራስህን ወይም እራስሽን ወክለህ/ሽ ተናገሪ

   • axumita August 3, 2016 at 11:56 pm

    አንድ ሰው ስለ ቨርጂንያና ዲሲ ያውቃቸዋል ብሎ አስተያየት ለሰጠው ይሁንልኝ እኔ አባቶችን ደፍሬ መናገር ባልችልም ግን የቨርጂንያና የዲሲ ሰው ሚያቃቸው ግን አንተ ባልከው መንግ0ድ አይደለም ስለዚህ እኛን ሳይሆን እራስህን ወይም እራስሽን ወክለህ/ሽ ተናገሪ

  • Anonymous August 2, 2016 at 9:58 pm Reply

   አይ አንች ዓለም ዋ

 8. Anonymous August 2, 2016 at 7:06 pm Reply

  አንድ ነገር ግራ ያጋባኛል ሃይማኖት በቲፎዞ ሆነ እንዴ? እኒህ ሰው ያላቸውን የሥነ ምግባርም ሆነ የዘረኝነት በሽታ መናገር መልካም ሆኖ ሳለ የቤተክርስቲያናችንን አስተምህሮ ለመደባደቢያ መጠቀም ተገቢ አይመስለኝም።
  ቤተክርስቲያናችን ስለ ድንግል ማርያም ምን ትላለች ካቶሊኮች ምን ይላሉ ይህ መለየት ያለበት ጉዳይ ነው። ለመሆኑ እግዚአብሔር ሰው የማይችለውን ነው እንዴ እንዲያደርግ የሚያዘው? ድንግልንስ የተለየች አድርጎ ሠርቶ ነው እንዴ አመስግኑአት የሚለን?ለመሆኑ ቅዱስ ገብርኤል ሲያበስራት መንፈስ ቅዱስ ይጠብቅሻል አላላትም? ቅዱስ ያሬድስ ”አንጽሆ ስጋሃ አደረ ላእሌሃ“ አላለም እናንተ ከየት ያመጣችሁት ትምህርት ነው? ምናልባት ኢማኩሌት ኮንሴፕሽን የሚሉትን የካቶሊክ እምነት ይዛችሁ ይሆን? አንድ ጊዜ ፓትርያርኩ በእኛና በካቶሊክ ብዙ ልዩነት የለም ብለው እንደ ነበረ አንብበናል http://andadirgen.blogspot.com/2016/03/blog-post.html#more ይህ ከሆነ አስተሳሰባችን በግልጽ መውጣት አለበት ድሮም ቢሆን እምነት በምርጫ እንጅ በግድ አይሆንም።
  ከዚህ የተምታታ ትምርት የተነሳ እየተደረገ ያለውን ትንሽ ልግለጽ ቀሲስ አቡኑ ምንም አይነት የቤተ/ክን ትምህርት ሳይኖረው በጥራዝ ነጠቅ ሲያስተምር እግዚአብሔር ድንግልን ከንጹህ ሥጋ ለመፍጠር አስቦ ከአዳም ላይ ሥጋ ቀንሶ ማስቀመጡን ሲያስተምር፤ ዶ/ር ዘበነ ይህንሲ ገልጽ ሥጋ ሳይሆን ንጹህ ዘር ከአዳም እስከ ድንግል እንዴት እንዳለፈ ዳዊትን ጨምሮ እንዴት እንዳሳለፈላት እንዲህ ነው የገለጸው file:///C:/Users/User2/Desktop/New%20folder/Zebene%20on%20Q&A%20Immaculate%20Conception%20Radio%20Program%20on%20July%202,%202016%20-%20zenebecht@gmail.com%20-%20Gmail.html
  በጣም የገረመኝ ዳዊት ቤርሳቤህን እንዴት እንዳገባት ለማያውቅ ሰው ካልሆነ በስተቀር መጽሐፍ ቅዱስ ለሚያውቅ ዳዊት በንስሃው እንጅ በንጽህና ምሳሌ አለመሆኑን ምናልባት ዶ/ር ምን ማጣቀሻ እንዳላቸው አላውቅም የበለጠ የሚከፋው ከሰሎሞን እንዴት አይነት ንጹህ ዘር እንደተጠበቀ ነው! ብዙ ላለ መጻፍ ብየ ትቸው ነው። ዋናው ነገር እኛ የቱን እንደምንከተል ከአዋቂዎች ጠይቃችሁ ብትጽፉ መልካም ነበር በግል ከምታወናብዱን ማቴ 18፥6 ይህ እምነት በመጽሐፍት እንዲህ ተገልጿል http://eotcmk.org/site/-mainmenu-24/–mainmenu-26/2199-2016-07-14-13-34-25
  በካቶሊክ ደግሞ እንዲህ ነው https://en.wikipedia.org/wiki/Immaculate_Conception ለመሆኑ እግዚአብሔር የሚያዳላ አባት ነው እንዴ? ይህ አንድ መክሊት የተሰጠውን ሰው መልስ አይመስልምን? እግዚአብሔር ሰውን በነፃ ፈቃድ በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረ አምላክ፤ አንድያ ልጁን እንዲሁ እስኪሰጠን ድረስ የወደደን እንጅ ድራማ የሚሠራ ለይቶ አዳልቶ ፈጥሮ አመስግኑ የሚል ቧልተኛ አምላክ አይደለም። ለምን መለወጥ አስፈለገ አባቶቻችን መላእክት እንኳን ያልቻሉትን ሃጢአትን አለማሰብ አንቺ ሰው ሆነሽ እንዴት ተቻለሽ ሲሉ ምን ማለት ነበረ? የተፈጠረችው እንኳን በልዩ ነው ግን እርሷ እንደቻለችው አድርገን እናመስግናት ለማለት ነበር እንዴ? እግዚአብሔርማ በመፍጠሩ ምን ይደነቃል ብዙ ለአእምሮ የሚከብዱ ስራዎቹን እናውቅ የለም እንዴ!ሲያዳላ ካልደነገጥን በስተቀር፤ ቆይተን ሰው ሲፈጠር ለጽድቅና ለኩነኔ ተለይቶ ነው የሚሉትን ስንደግፍ እንዳንገኝ!አቡነ ሽኖዳ የጻፉትን መጽሐፍ ሲተረጉሙ ከመሐል ቆርጠው አውጥተው የተረጎሙ ወንድም እንዳሉ መጽሐፉን ያነበበ ይህንhttp://tasbeha.org/content/hh_books/the_holy_virgin_st_mary/index.html ሲያነብ ሊያረጋግጥ ይችላል በተለይም መካከል ላይ THE HOLY VIRGIN MARY IN THE CHURCH’S FAITH የሚለውን ልብ ብለው ያንብቡ በሌላ በኩል ምሥራቅ ኦርቶዶክሶች ምን ይላሉ ለሚለው ይህን ያንብቡ http://www.johnsanidopoulos.com/2010/06/patriarch-bartholomew-on-immaculate.html
  ድንግል እኮ የምትደነቀው ተደልቶላት አይደለም ሰው እንዲሆን ተፈጥሮ ያልቻለውን በመቻሏ እንጅ ለምሳሌ ሁለት ልጆች ያሉት ሰው አንደኛውን በግል ት/ቤት ሁለተኛውን በደከመ የመንግስ ት/ ቤት እያስተማረ በግል ት/ቤት የተማረው ጥሩ ውጤት አመጣ አመስግኑት ሸልሙት ማለት ሳያንሰው ሁለተኛውን ከአንደኛው ለምን አነስክ ብሎ ቢቀጣው ምን ይባላል? እንዲህ ነው ለእኔ የእናንተ ስብከት።

 9. Anonymous August 2, 2016 at 7:07 pm Reply

  አስተያየቴን አውጡና መልስ ስጡበት

 10. Anonymous August 2, 2016 at 9:56 pm Reply

  ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችው አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ አምኖ በመሰከረ አማኝ ንጹህ ልቡና ነው:: እንዲያው በእግዚአብሔር ስም የምጠይቃችሁ የትኛው የእምነት መጽሐፍ እና የቀኖና መጽሐፍ ሥልጣነ ክህነት ያለቸው አባቶችን አይደለም ሰው የሆነውን ሁሉ እኳን እንድትሳደቡ እንድታዋርዱ እንደፈቀደላችሁ እንድትመልሱልኝ ነው ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት ይውገራቸው ።
  እስኪ ትንሽ እንኳ ደረጃችሁን እወቁ የአማኝ የክርስቲያን ሽታ ይኑራችሁ : ለነገሩ አእምሮ የላችሁም እናነተም የአውሬው ናችሁ

  • Anonymous August 3, 2016 at 7:37 am Reply

   ይሕ እውነት እንኮን ቤሁን ምን ይደንቃል? አስመራጭ ኮሜቴው ስንት ንጹሐንን አሳልፎል? ምላተጉባኤውስ ማነው? ይህ አስመራጭ ኮሜቴየምላተጉባኤው አባል አይደለምን?ምን ትካሰሳላችሑ አባ ሠረቀን የግል ጸብ ከሆነ ደግማችሑ ጻፉ እንዳስነበባችሑን ከሁን ብዙ አባ ሠረቀዎች አሉ ሐራዎች አትድከሙ ብሎጋችሑ ለብዙ ዋልጌዎች በዝምታዋ ድጋፍን ሰታለች ሕዝብ ከኔ ጋር ነው በማለት በፈለገው የሹመት በፈለገው የውግዘት ድጋፉን ሰጥታ ውሳኔው እዚሕ ደርሶል ያለፍት እጩዎች ጅግና መሆናችውን ይናገራሉ በርግጥም ዘራፊ ናዘማዌ ድጋፍ አግኝቶ እዚህ መደርስ ጀግንነት ነው ክፍያው ስግደቱ ቃል መግባቱ ቃላል ውጌያ አልነበረም።እኔም እላለሑ አባ ሠረቀ ይገባችዋል የናንት እጩዎች ካደረጉት ውጭ የተለየ ምግባር የላችውም ምን አልባት እንደተባለው ማሕበረ ቅዱሳንን ይቃወሙ ይሑናል ልዩነቱ ይሔ ነው ማሕበረ ቅዱሳን ምንም እንኮን የቤተከርስቴያን የጀርባ አጥንት ነው ብለን አብረንው ብንጎዝም እውነታው ይሕ አይደለም መንፈሳዊ ስው ለሽፍታ ከለላ አይሰጥም ማሕበሩም ለዋልጊዎች አደላ አብረውት ያሉት አባቶች ማሕበሩን በመደግፍችው የቤተክርስቴያንን ክብር ማስቀደም አልቻለም ሲነገረን እንስማም ብለን ነበር አሑን ግን እውነትን አሳዳጅ ነው ከሚሉት እንዳንሖን ማሕበሩ አቆሙን ይፈትሽ ማንም ጳጳስ ሳይሑን ቤተ ክርስቴያን ነበረች ማንም ደጋፊ ሳይሆናችው ፣ቤትንብርትሳይኖራችው መኪና ሳይገዙ ጉቦ ሳይስጡ በመንፈሳዊ ማንነታቸው ለጵጵስና የተመረጡ አባቶች ያገለገሉበት ምላተ ጉባኤ መሑኑንአንዘንጋ ከምንስራው የአብነት ትምሕርት ቤት ይልቅ የምናፈርሰው የስላሴ ሕንጻ እንዳያመዝን እናስተውል ።

   • Anonymous August 3, 2016 at 6:59 pm

    shem on you.
    Seed of the evil one

 11. Anonymous August 3, 2016 at 11:11 am Reply

  አባ ሠረቀ ብርሃን አንዳንድ ደጋፊዎች ሊኖራቸው እንደሚችል አውቃለሁ፡፡ ደጋፊዎቻቸው ዘረኛ፣ ሙሰኛ እና ቤተ ክርስቲያናችን እንድትጠፋ ከሚፈልጉ እንዳንድ ባለስልጣናት (ለምሳሌ አባይ ጸሃዬ) እና የተሃድሶ ፕሮቴስታንት አቀንቃኞች (ደጋፊዎች) ውስጥ ናቸው፡፡
  አባ ሠረቀ ብርሃን የማይጨበጡ፤ ለተሃድሶ ፕሮቴስታንት አራማጆች ከፍተኛ ድጋፍ የሚሰጡ (እውነት እና ንጋት የሚለውን መጻሕፋቸውን መመልከት ይቻላል)፤ከተሃድሶ ድርጅቶች ጋር አብረው የሚሰሩ፣ ጊዜ ጠብቀው ቤተ ክርስቲያኗን አሁን ከሚጎዷት በላይ ለመጉዳት የተዘጋጁ አደገኛ ሰው ናቸው፡፡ የሚደግፏቸው አካለትም የአባ ሠረቀ ብርሃን ማንነትን ዘንግተውት ወይም ትክክለኛ ማንነታቸውን ሳያውቁት ቀርቶ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቶቹ በጥቅሉ አራት ናቸው፡፡ አንደኛው ቤተክርስቲያኗ እንድትከፋፈል እና ሰላም እንዳይኖራት ለማድረግ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አፈ ጮሌው አባ ሠረቀ ብርሃን ባይሾም እና በአስመራጭ ኮሚቴው የተጠቆሙት ቢገቡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የአካባቢው (ትግራይ) ተጽእኖ ፈጣሪነት ይቀንሳል ብሎ ከማስላት የመጣ ነው፡፡ ሦስተኛው ከባለስልጣናቱ ጋር ያለው ነባር የመላላክ ተልዕኮ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ስለሚፈልግ ጭምር ነው፡፡ ሌላው እና አራተኛው በእነሱ እሳቤ ከብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በኋላ ፓትርያርክ አድርጎ ለመሾም የማቀድ ውጤት ነው፡፡ አባ ሠረቀ የጥፋት ተልዕኮ መሣሪያ ናቸው፡፡

  • ገ/ሚካኤል August 4, 2016 at 3:55 pm Reply

   @Anonymous August 3, 2016 at 11:11 am የምታሳዝን ፍጥረት ነህ። በማሕበረ ቅዱሳን ዲስኩር ልብህ መታወሩን የተጋትከውን ካለምንም አመክንዮ በመትፋት አረጋገጥከው። አባ ሠረቀ ላይ ብቻ ሳይሆን በሚደግፉአቸው ሰዎች ማንነት ላይም እርግጠኛ ሆነህ ተናገርክ። በቃ የዘመኑ የማኅበረ ቅዱሳን ስሪቶችና አልቃይዳ በውሸት የጀነት ቆነጃጅት እያማለለ ቦምብ(ፈንጂ) የሚያሸክማቸው ምስኪን ህጻናት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ሆናችሁብኝ።ሌላው አሳዛኝ ጉዳይ አብዛኞቹ በነ ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ቅዱስ አግናጥዮስ እና ቅዱስ ቄርሎስ መንበር የተቀመጡ የዘመናችን ”ጳጳሳት” ከናንተ የባሱ እንደ የጋሪ ፈረስ ግራም ቀኝም ሳይመለከቱ ዝም ብለው የሚነዱ መሆናቸው ነው። አምላከ ቅዱሳን ሆይ መንጎችህን ከጨካኝ አውሬዎች ታደግ። አሜን።

 12. Anonymous August 4, 2016 at 9:31 am Reply

  “አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኀልቀ ኄር፣ አቤቱ አድነኝ ደግ ሰው አልቋልና” በሚል መሪ ጥቅስ የሚጀምረው ደብዳቤው “… ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የወደቀችበትን አዘቅት ስንመለከት ትንቢቱ ደርሶ ሊቃውንቱን፣ ካህናቱንና ምእመናኑን በብዙ መንገድ አንገት ያስደፋ ተግባር ተከስቷል፡፡ እየተከሰተም ይገኛል፡፡ በሁሉም ስፍራ በመንፈሳዊው አሰራርና አኗኗር ደግ ሰው አልቋልና አቤቱ አድነኝ የሚለው ዝማሬ የሁሉም እንጉርጉሮ ከሆነ ቆይቷል፡፡” ካለ በኋላ ቤተ ክርስቲያኗ “ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ያለው ጊዜ ቁልቁል የወረደችበት፣ የነበረው ክብርዋ ጥላሸት ተቀብቶ አኩሪ ታሪኳ ተቀብልሶ መብቷንና ኃላፊነቷን ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ አሳልፋ ለማይመለከታቸው አካላት ያስረከበችበት፣ ዶግማና ቀኖናዋ ፈተና ላይ የወደቀበት” ጊዜ መሆኑን ገልጿል፡፡ በማስከተልም አስመራጭ ኮሚቴው የፈጸማቸውን ስሕተቶችና ጥፋቶች በሚከተሉት ስድስት ነጥቦች ሥር በዝርዝር አቅርቧል፡፡
  ፩። ፍትሕ መንፈሳዊንና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን መጣሱ
  ፪። በምንኩስናና በመነኮሳት ህልውና ላይ የፈጠረው አደጋ
  ፫። የቤተ ክርስቲያንን ዓላማ በሚጻረር መልኩ ጵጵስናን በብሔርና በጎጥ እንዲሆን ማድረጉ
  ፬። ኮሚቴው የመንፈስ ቅዱስ ጥሪ የሆነውን ጵጵስናን ለገንዘብ ፍጆታ ማዋሉ
  ፭። ያለ ብሔራቸው የተቀመጡትና በአገልግሎት ላይ ያሉትን ሊቃነ ጳጳሳት የሚያፈናቅል ተግባር መሆኑ፣
  ፮። በሀገር ደኅንነትና ሰላም ላይ ሥጋትን የሚያመጣ መሆኑ በሚሉት ነጥቦች ስር በማስረጃ የተደገፈና ምክንያታዊ የሆነ አስተያየትና ሐተታ አቅርቧል፡፡
  በመጨረሻም በደብዳቤው ኮሚቴው ስለፈጸመው ስሕተት በሕገ ቤተክርሰቲያን እንዲጠየቅና የሄደበት የተሳሳተ መንገድ ያቀረበው የተጭበረበረ ጥቆማም እንደገና እንዲመረመር ተጠይቋል፡፡ ፓትርያርኩና ብፁዓን ጳጳሳት ጉዳዩን በቀላሉ እንደማያልፉት እምነት አለን ያሉት የተቃውሞ ድምጻቸውን ያሰሙት ሊቃውንቱ፣ የደብር አለቆቹ፣ ካህናቱና ሰባክያነ ወንጌሉ “በምንም ምክንያት እንዲሆን ከተደረገ ግን ከታሪክ ተወቃሽነት ለመዳንና ቤተ ክርሰቲያንን ለመታደግ ሲባል በአደባባይ ተቃውሞአችንን ለመግለጽ የምንገደድ መሆኑን ስናሳስብ በትሕትና ነው፡፡” ብለዋል፡፡
  ደብዳቤው ከተነበበ በኋላ ከተቃውሞ ድምጽ አሰሚዎቹ የተሰጡ አስተያየቶች የነበሩ ሲሆን ከአስተያየቶቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
  · ጵጵስናውን ላያገኙት ነገር ተደብቀው ያሉ ሁሉ ተሰድበዋል
  · አስመራጭ ኮሚቴው ሙያ ተኮር ምሁራንን አላካተተም ቢያንስ ላወጣው የቤተክርስቲያን መስፈርት ተጠያቂ መላሽ ጳጳሳትን አላካተተም፡፡
  · የቀረቡት ማስረጃዎች ፎርጅድ ለመሆናቸው ማረጋገጫ አለን፣ የሐዲሳት፣ የቅኔ፣ የመጻሕፍት መምህራን ነን ብለው ያቀረቡ ሰዎች በዚህ ሙያ እንዳላለፉ ማረጋገጫ አለን፡፡
  · ገንዘብ ተጠይቀን ሰጥተናል ያሉ ገጥመውናል እውነት ነው ማለት ነው፡፡
  · ጥሩ የዘሩ ተገልብጠው አሁን ኮሚቴው ጓያ ዘራበት
  · ሂደቱ አስከፊ ከመሆኑ የተነሣ የአብነት መምህራን፣ የቆሎ ተማሪዎች፣ ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን አላካተም
  ይባልንጂ ጉደዮ ሌላ ነው እሱም ከብሔር ብሔረሰቦች ጳጳስ መሾም ዛሬ አይደለም የተጀመረ ይህንን የከፈሉትና የቀደድቱ
  አባ ጳዉሎስ ናቸዉ የደብር እልቅና ያመክሮስራ ልምድየለላቸውን እየጠሩ የቮሟቸዉ
  አሁን ኮሚቴው በትክክል ነው የሰረው
  ነገሩ ግን የትግሬመነኮሣት በብዛት እኞስካልተቮምን ድረስ ሹመቱ እደይፈፀም አድማ እየቀሰቀሱ ነዉ
  ምክንያቱም በሁሉም ሀገሬቱ እነሱናቸዉ ቛንቛባይችሉም ልብሱን እያለበሱ የሚልዃቸዉ
  በትግረይ ግን ከትግሬዉጭ ወይፍንክች
  ለምሣሌ ምሥራቅ ሀረርጌ ትግሬ ምራብሀረርጌ ትግሬ አዳማትግሬ ጂማ ትግሬ ወላይታ ትግሬ ሙተዋልእንጂ ስለዚህ
  መተዳደሪያስላረጉት ለምንያመልጠናል በማለት ምግባረብልሹወች የትግሬ መኮሣት ናቸው ህዝቡ አልደገፈዉም
  ኮሚቴዉ በሙስና ወድቛል በለውየሀሰት ፓሮፓጋንደ ለፖትርያሬኩ እየነዙ ስራቸዉን እደያከናዉኑ እየረበሿቸዉ
  የሚገኙት ፀሎት ፀሎት ያስፈልጋል ይቆየን

 13. Anonymous August 4, 2016 at 10:58 am Reply

  ጉደዮ ሌላ ነው እሱም ከብሔር ብሔረሰቦች ጳጳስ መሾም ዛሬ አይደለም የተጀመረ ይህንን የከፈሉትና የቀደድቱ
  አባ ጳዉሎስ ናቸዉ የደብር እልቅና ያመክሮስራ ልምድየለላቸውን እየጠሩ የቮሟቸዉ
  አሁን ኮሚቴው በትክክል ነው የሰረው
  ነገሩ ግን የትግሬመነኮሣት በብዛት እኞስካልተቮምን ድረስ ሹመቱ እደይፈፀም አድማ እየቀሰቀሱ ነዉ
  ምክንያቱም በሁሉም ሀገሬቱ እነሱናቸዉ ቛንቛባይችሉም ልብሱን እያለበሱ የሚልዃቸዉ
  በትግረይ ግን ከትግሬዉጭ ወይፍንክች
  ለምሣሌ ምሥራቅ ሀረርጌ ትግሬ ምራብሀረርጌ ትግሬ አዳማትግሬ ጂማ ትግሬ ወላይታ ትግሬ ሙተዋልእንጂ ስለዚህ
  መተዳደሪያስላረጉት ለምንያመልጠናል በማለት ምግባረብልሹወች የትግሬ መኮሣት ናቸው ህዝቡ አልደገፈዉም
  ኮሚቴዉ በሙስና ወድቛል በለውየሀሰት ፓሮፓጋንደ ለፖትርያሬኩ እየነዙ ስራቸዉን እደያከናዉኑ እየረበሿቸዉ
  የሚገኙት ፀሎት ፀሎት ያስፈልጋል ይቆየን

 14. Anonymous August 4, 2016 at 2:29 pm Reply

  አንተ ፖለቲካህ የከሰረብህ ሰው ነህ፤ ፍጹም ዘረኛም ነህ፤ ለመሆኑ ስለ አባ ሠረቀብርሃን ምን ታውቃለህ
  አባ ሠረቀብርሃን ለእዉነት የቆሙ፤ ታላቅ ሐዋርያና መምህረ ትህትና አባት ናቸው፡፡ ችግራችሁ ለመቶ ዓመታት ትጫወቱበት ለነበረ ድብቅ ዓላማችሁ ስለማይመቹ ብቻ ነው፡፡ አባ ሠረቀብርሃን የማነኛውም የፖለቲካ መሪ ድካፍ አያስፈልጋቸውም፡፡ ሌለው አስብ ሃይማኖትህ ፊድልህ ሥርዓተ መንግሥትህ ዜማኅ ማንኛውም እመካበታለሁ የሚትለውን ሁሉ ያስረከበችህ ትግራይ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ለመሆኑ ከትግራይ ያልተረከብከው ምን አለህ;? ወርቅ ላበደረ ጠጠር እንደተባለው ካለሆነ በስተቀር፡፡ ታስገርማለህ 1 ወገኔ ለመሆኑ በእውነትና ንጋት መጽሐፋቸው የተሐድሶአውንያ ደጋፊ መሆናው የሚያረገግጠውን የመጽሐፉ ገጽ ለምን አልጠቀስከውም ፡፡
  ታሐድሶ መናፍቅማ አንተ ነህ፡፡ አማኝ ብትሆን ኑሮ የአባቶችን ስም በሐሰት ባልወነጀልክም ነበር፡

 15. axumita August 4, 2016 at 7:10 pm Reply

  እኔ ግን እፈራለው ድፍረታችን አባቶችን እስከመናቅ ማቃለል ነው ይሄ ደግሞ እኛን ወዴት እንደሚወስደን የታወቀ ነው።እስቲ ቆም ብለን እኛ የትኛው ደረጃ ላይ እንዳለን እናስብ እውነት አባቶቻችን ምንሰድብበት ላይ??
  አንድ ሰው ቤተክርስትያን ሲያቅ እና ፍቅሩ ሲገባው ትሁት እንደሚሆን እንጂ አወኩሽ ናኩሽ እንደሚጀምር አይመስለኝም
  የሁላችንም አስተያየት ምን ያህል መንፈሳዊ ህይወታችን እንድንመረምር ይረዳናል ከምንናገረው ነገር መቆጠብና እስቲ እንጸልይላቸው አለማለት መቻላችንም ቢሆን።
  አቤቱ ደግ ሰው አልቃልና ብለን በቸርነቱ አስበን ብለን ቆም ብለን እምናስብበት ጊዜ ያርግልን።

  ሌላ መናገር ምፈልገው የዚህ ብሎግ አላማው ምንድነው መንፈሳዊ ህይወት መገንባት ወይስ የአባቶችን ህጸጽ እያነበብን አባቶች ላይ መጦቃቀም ሀራዎች ብዙ መንፈሳዊ ነገር መማር እንፈልጋለን እየተከፋፈልን ነው በጎሳ በዘረኝነት መሀከላችን እንክርዳድ ባበቀሉ ሰዎች ብዙ አንባቢ አላችሁና ባካችሁን በክርስቶስ ክርስትያን አንድ መሆናችንን ንገሩን የድንግል ማርያም ፍቅር ልባችን ላይ እንዲቀረጽ ፍቅራን በረከታን ስበኩን እኛ ገና ወንጌልን አልጠገብንም ስበኩን ገድሉን ተአምራቱን ወንጌሉን አስተምሩን

 16. ማንአለብሽ ከጎንደር August 5, 2016 at 4:59 am Reply

  ሌባ ሁሉ አባ ሰረቀ ብርሀን የማይመቹት ለማህበረ አጋንንት ብቻ ነው እንጅ በጣም ብዙ ደጋፊ ያላቸው አባት ናቸው ። ግዴለም ለሁሉም ጊዜ አለው

 17. Anonymous August 5, 2016 at 10:25 am Reply

  Is what is written here is true?

 18. Anonymous August 5, 2016 at 10:29 am Reply

  A name of Debre enku astedadari is Aba Eperem Gedamu.

 19. Anonymous August 12, 2016 at 6:19 pm Reply

  Is Harra a christian web-page? Are you working from …. side Your writing is damaging our faith. Use your time to teach and bring the lost brothers and sisters to CHRIS LORD. Please stop planting the seed of evilness among brothers.
  May GOD bless us all.

  Thank you

  AYohannes

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: