በቁልቢ ቅ/ገብርኤል በወር እስከ 250ሺሕ ብር ይመዘበራል፤ ምእመናን፣ አለቃውና አጋሮቻቸው በሕግ እንዲጠየቁ ለፓትርያርኩ አቤት ብለዋል

aba woldegiyorgis woldemariam kulubi

 • ከበዓላት ውጭ በወር ከ300ሺሕ ብር በላይ ቢገኝም፣ ለገዳሙ የሚገባው ከ100ሺሕ አይበልጥም
 • ለ24 ዓመት የቆዩት አለቃ፣ ከ20ሚ. ብር በላይ የባንክ ተቀማጭና የአክስዮኖች ባለድርሻ ናቸው፤
 • ከሒሳብ ሹሟ ጋር ምንኵስናቸውን እያዋረዱ፣ ለጵጵስና አለመጠቆማቸው በእጅጉ አሳዝኗቸዋል፤
 • ገቢውን በአራጣ ጭምር የሚያበድሩ የጽ/ቤቱ ሓላፊዎች፣ ከፍተኛ ሕገ ወጥ ሀብት አድልበዋል፤
 • እስከ25 ዓመት ያገለገሉ ካህናትና መዘምራን የማያገኙት፣ ከዕጥፍ በላይ ደመወዝ ይከፈላቸዋል፤
 • የካህናት ማሠልጠኛውና የተጀመሩ ቤተ ጉባኤያት፣ በትኩረትና በቁጥጥር ማነስ ተዘግተዋል፤
 • ስብከተ ወንጌልና ማኅበራዊ ልማት ባለመኖሩ፣ የምእመናን ቁጥር እያጠጠና እየተቀሠጡ ነው

*           *           *

kulubi faithfuls

 • የካህናትና ምእመናን ኮሚቴገቢውን በመቆጣጠርና ግልጽነትን በማስፈን ሚና ነበረው፤
 • የገዳሙ ሕግ ተሻሽሏል በሚል አባላቱ በመሰናበታቸው፣ ለምዝበራና ብክነት ተጋልጧል
 • መንበረ ፓትርያርኩ አቤቱታቸውን ችላ ብሎ ገቢ በመሰብሰብ ብቻ መወሰኑን ተችተዋል፤
 • ኮሚቴው እንዲመለስና ቆጠራውም የባንክ ሠራተኞች በተገኙበት እንዲካሔድ ጠይቀዋል
 • አሠራሩ ተስተካክሎ ምዝበራው ካልቆመ፣ ሓላፊዎቹን ለሕግ እንደሚያቀርቡ አሳስበዋል፤

*           *           *

 • ገዳሙን፣ የምሥራቅ ኢትዮጵያ የትምህርትና ሥልጠና ማእከል የማድረግ ጅምር ነበር፤
 • በታኅሣሥና በሐምሌ በዓላት፣ በስእለትና በምጽዋት ከ40 ሚ. ብር በላይ ገቢ ይቆጠራል
 • የሚሰበሰቡ ንዋያተ ቅድሳትም በቤተ ክህነቱ ገማች ኮሚቴ እየተሸጡ ትልቅ ገቢ ያስገኛሉ፤
 • ጠቅላይ ጽ/ቤቱ፣ ለኮሌጆችና ለገዳማት ድጎማ፤ ለፕሮጀክቶችም ማስፈጸሚያ እያዋለው ነው፤
 • ገቢውን የበለጠ ተቆጣጥሮ አገልግሎቱን የሚያጎለብት ቦርድና ኮሚቴም ተቋቁሞ ነበር፤

*           *           *

His Holiness with thier graces at kulubi st gabriel churchcomplaints of kulubi faithfuls00

 • ለበዓሉ የተገኙት ፓትርያርኩ፣ 205 የከተማዋ ምእመናን የፈረሙበትን አቤቱታ ተቀብለዋል፤
 • ገዳሙ በአግባቡ እየተመራ እንዳልኾነና ስለዕድገቱም የማሰብ ፍላጎት አለመኖሩን ተረድተዋል፤
 • አለቃው፣ ካለባቸው የጤና እክልና በዕድሜም ከመግፋታቸው የተነሣ መተካት ይኖርባቸዋል፤
 • ሸምግለዋል፤ ቦታውን እየመሩት አይደለም፤ ከዓመት ዓመት እየቀነሰ ነው፤ ደኅና ሰው ማሰብ ያስፈልጋል”/ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ/
Advertisements

6 thoughts on “በቁልቢ ቅ/ገብርኤል በወር እስከ 250ሺሕ ብር ይመዘበራል፤ ምእመናን፣ አለቃውና አጋሮቻቸው በሕግ እንዲጠየቁ ለፓትርያርኩ አቤት ብለዋል

 1. Sawul July 27, 2016 at 7:45 pm Reply

  wusha min agebash……. .MK Yemtzerfiw yebetekrstian habt aneshesh??

 2. Anonymous July 28, 2016 at 1:26 pm Reply

  hallo tikikli new gin min yderegal abatu dagna liju kemagns

 3. Anonymous July 28, 2016 at 1:29 pm Reply

  wye gud

 4. Belachew Aredo August 16, 2016 at 5:36 am Reply

  Hard to read about the the loss fund from the church revenue. weyane gov’t allow this to happen. whoever assigned cadres as church (Kes, Dikon etc.) to steal money & corrupt their
  leaders.

 5. Anonymous September 10, 2016 at 11:00 am Reply

  ለመለዉ የሀገራችን ህዝብ እንኳን ከዘመን ዘመን ሁላችንም አደረሰን በቅድሚያ
  ትንቢተ ኤሳ፵ ቁ፩ ህዝቤን አፅናኑ ይላል ምላካችን
  በተለይ በሀገራችን ኢትዮጵያ ያለፈዉ አመት የቤተክርስቲያንልጆች በገዡ ስራት ወንጌልእደ ይሰብኩ የተሳደድበት
  ሰለወገኖቻቸዉ እስራት መገደልና መሳደድ እደይናገሩ የተጨቆኑበት
  በፀራራፀሐይ በተወለዱበትሀገር እናት እያየች ልጆች የተገደሉበት
  ሽማግሌ አዛዉንንት እናት አባት የተደበደቡበት
  ምንም የማያዉቁ ህፃናትም የተገደሉበት ብሒርከብሔር ወያኔያሀደግ እየከፍፈለ ከተወለዱበት አካባቢ የተፈናቀሉበት
  የህግታራሚ ተብለዉ በስርቤት የሚገኙት የህግታራሚዎች በገዡወያኔ በሳት የተቃጠሉበት አስከሬናቸዉ ሣይቀር
  ወላጂእደያለቅሱበት ወላጂናት አባት የተከለከለበት በአማራ በወሮሞ የአሉእናቶች ሽማግሌዎች
  በአሰቃቂ ሁኔታ እናቶቻችን ያዘኑበት አመት ነበረ ሰለዚህ በዲሱ አመት ወያኔየሀደግ ከክፉሰራዉ ነስሐገብቶ ካልተመለሰ
  ጳጳስ መነኩሴ ቄስ ዲያቆን ወንጌልሰባኪ ቆራቢ አስቀዳሽ ወዘተ
  ሸህ ደረሣ ሙስሊም እምነት ያለዉ የለለዉ ሣአንል ሁሉምነገር በሐገርነዉና የሚፈፀመዉ
  ጩህታች አደባባይ በመዉጣት ለግዚአብሔር እናለአለም ህዝብ ማሰማት ይኖርብናል
  እነሱ እደሆን ስድሰት መቶ ስልሣ ስድስት ሰላረፈባቸዉ አግዚአብሔርን አይፈሩ ሰዉንም አያፍሩ
  ወገኖቸ አትፍሩ ከዚህ በለይ ምናለ ከዚህ በፌት ።ቦንሴን እምትባል የስድስት መቶ ስልሣ ስድስት
  ተከከታይ የሆነችዉን ጳዉሎስ ቅድስት ስላሤ ታቦት አዉጥቶ ክርስቲያኖችን አንገትያስደፍ
  በድሜ የገፋ አረጋዉያን ጳጳሳት መቆምተስኖአቸዉ ዘፍኟ በስሐቱ ባለመምጣቷ ምክንያት የወደቁምጳጳሣት ነበሩ
  ታዲያ በግፋለይግፍ እየጨመሩ እንዲትነዉ ዝም የምንለዉ
  በሀሀገራችን ኤትዮጵያ ወደመሀላገር የወያኔ መነኮሣት ከመጡ ወዲህ ጵጵስና ምንኩስና ተዋርዶአል
  ይሄዉም ያለብቃታቸዉ እናያለችሎታቸዉ የስራቱ ተወላጂ በመሆናቸዉ
  ጵጵስና ተቩመዉ የኞን አባቶችሁሉ እያሰናከሉነዉ ያሉ መዳኔአለም እረባክህ ግፍችን ተመልከት ከናጥ ከድንግልማርያምጋር

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: