የጋምቤላው አባ ተክለ ሃይማኖት ጵጵስና ከተሾሙ: “ምሥጢረ ክህነት ተራ ይኾናል፤ ቤተ መቅደስ ይረክሳል፤ የተሐድሶ መናፍቃን ይፈነጫሉ” ሲሉ አገልጋዮች አስጠነቀቁ

Aba Teklehaimanot Nigussieመጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ  ኤጲስ ቆጶስነት ቢሾሙ ምን ሊፈጠር ይችላል?

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡

ይድረስ፡- ለኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ

የጋምቤላ ክልል፣ ሊቀ ጳጳስ ሳይኖረው መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይኹን እንጂ፣ የጋምቤላና ደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የኾኑት፣ መጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት በኤጲስ ቆጶስነት ሊመረጡ መኾኑን ጭምጭምታ ስንሰማ፣ በጣም አዘንን፤ ምክንያቱ ምንድን ነው ከተባለ ከዚኽ በታች አቅርበነዋል፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያት በቀኖናቸው፡- ትምህርት ያለው ኤጲስ ቆጶስነት ይሾማል፤ ሥራውን ውሎ አድሮ ይማረዋል፤ በትምህርት መናፍቃንን ተከራክሮ ይረታልና ሥራ ያለው ይሾም፤ በትሩፋቱ በጸሎቱ ሰውን ያጸድቃልና፤ እንዳሉ እናውቃለን፡፡ በአንፃሩ፣ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት፣ ኹሉም የሌላቸው መኾኑን እናውቃለን፡፡

እኛ የጋምቤላ አገልጋዮች ይህን ጽሑፍ ስንጽፍ፣ ዓላማችን፣ ቤተ ክርስቲያንን በሥርዓት የሚያስተዳድር፤ ለቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ክብር የሚሰጥ አባት ቤተ ክርስቲያን እንድታገኝ ከመፈለግ አንፃር እንጂ፣ በእርሳቸው ቅናት፣ ምቀኝነት ወይ ጠብ ኖሮን አይደለም፡፡ የጻፍነው ኹሉ ትክክል መኾኑን በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መጥቻሁ ከምእመናንና ከቀሳውስት መረዳት ትችላላችሁ፡፡

ለደኅንነታችን ስንልም፣ የቀሳውስቱን ስም ዝርዝር በይፋ መጥቀስ አልፈለግንም፡፡ የማጣራት ሥራ ሲሠራም፣ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በተናጠል ካልኾነ ትክክለኛውን የሚሰጥ ሰው ላይኖር ይችላል፡፡
የራሳችንን ድርሻ ተወጥተን ቢሾሙም፣ ለእግዚአብሔር አሳልፈን ከኅሊና ወቀሳ ነፃ ነን፡፡

አባ ተክለ ሃይማኖት ቢሾሙ ምን ሊፈጠር ይችላል?፡-

 • ክህነት ያለመስፈርት በግፍ ይሰጣል፤ የክህነት ምስጢር ተራ ይኾናል፤
 • ቤተ መቅደስ ይረክሳል፤
 • የተሐድሶ መናፍቃን እንደ ልባቸው ይፈነጫሉ፤
 • የተማሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶች እንግልት ይደርስባቸዋል፤
 • ቤተ ክርስቲያን ከሥርዓት ውጭ ትኾናለች፤
 • ምእመናን እውነተኛውን ትምህርት ይዘነጋሉ፤

ይህ ኹሉ አኹን ከሚሠሩት ሥራ አንፃር የተረጋገጠ ነው፡፡

እግዚአብሔር መልካሙን አባት እንዲሰጠን እንመኛለን፡፡ አሜን፡፡


ምንኵስና፣ ከጣዕመ ዓለም የሞቱ መኾንና ዓለምም ከእርሱ ዘንድ የሞተች እንደኾነ ዐውቆ፤ በነፍስና በኅሊና ኹሉ እግዚአብሔርን ለማገልገል ወስኖ፤ ከንቱ ውዳሴን፣ ራስን ከፍ ከፍ ማድረግን ትቶ የክርስቶስን መስቀል መሸከም ነው፡፡ የምንኩስና ሕይወት፣ ከሥጋዊ ብዕልና ክብር ተለይቶ፣ እግዚአብሔርን በሥነ ፍጥረቱ እያሰቡ፣ ሥጋን ከርኵሰት በመጠበቅ በንጽሐ ነፍስ መኖር ነው፡፡

በሥርዓተ ምንኵስና የሚቀበሉት አስኬማ፤ ለዕረፍተ ነፍስ እንጂ ለዕረፍተ ሥጋ አይደለም፡፡ መነኰሴው፣ በታቦቱ ፊት እንደሞተ ሰው ተኝቶ ሲገነዝ፣ በጸሎተ ምንኵስና የሚፈጽመው ቃለ መሐላና የሚሰጠው መመሪያም፡-

“ዛሬ እግዚአብሔር አንተን መርጦሃል፤ ከዚኽ ዓለም ሕይወት ለይቶሃል፤ ሥርዓተ ምንኩስናን ከተቀበልክ ከማኅበረ መላእክት ጋር አንድነት አለኽ፤ ከዚህ ዓለም ሀብት፣ ንብረት፣ ሥጋዊ ምኞት ፈጽሞ ራቅ፤ ኅሊናህ ዘወትር በሰማያት ይኹን፤ እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ሐውልት እንዳትኾን ወደ ኋላ እንዳትመለከት፤ ከተስፋ መንግሥተ ሰማያት ነፍስኽን አትግታ፤ በሥራ ፈትነት ጊዜኽን አታባክን፤

ስንፍናን አስወግድ፤ ይህን ቃለ መሐላ ከተቀበልክ በኋላ የዓለማውያንን ሥራ ከምትሠራ ባትገባበት ይሻልኽ ነበር፤ የአንተ ታላላቅ መሣርያዎችህ፡- ሃይማኖት፣ ጾም፣ ስግደት፣ ጸሎት፣ ፍቅር፣ ደግነት፣ ቅንነት ናቸው፡፡ የአንተ ጠላቶችህ፡- ትዕቢት፣ ሐሜት፣ ቅንዓት፣ የተመረጡ ምግቦችን መመገብ፣ ሴሰኝነት፣ ጥርጥር፣ ሰውን መናቅ ናቸው፡፡

ያለስንፍና እግዚአብሔርን አገልግለው፤ ቀንና ሌሊት እግዚአብሔርን ከማገልገል አትቦዝን፤ መንፈሳውያን አባቶችህን፣ እናቶችህን፣ ወንድሞችህንና እኅቶችን በፍጹም ልብህ ውደድ፤ ደግነትን ተከተል፤ ይህ ከሰማያዊው ንጉሥ ፊት በደስታ እንድትቆም ያደርግሃል፤ ትሕትናን ገንዘብ አድርግ፤ እርሱ ከምድር ወደ ሰማይ ያወጣሃልና፤ ትእዛዘ እግዚአብሔርን እንድትጠብቅ የሚረዳህ ጾም ነው፤ አባትህ ይቅር ባይ እንደኾነ ይቅር ባይ ኹን፤” የሚል ነው፡፡

አንድ መነኰስ፥ ጸሎተ ወንጌል ደርሶ፤ ጸሎተ ሙሴ ተዚሞ፤ ጸሎተ ምንኵስናና የቅናቱ ጸሎት ከተፈጸመለት በኋላ ቅናት ይታጠቃል፡፡ ወደ ፍጹምነት ሲደርስ፣ የፍጻሜ ምንኩስና ምልክት ኾኖ በንጽሐ መላእክት የተሰየመውና 12 ትእምርተ መስቀል ያለበት አስኬማ ይሰጠዋል፡፡ ምንኵስና፣ ሕገ መላእክት ስለኾነ ልብሱም አስኬማውም የመላእክት ይባላል፡፡ “አልበስዎ አስኬማ ዘመላእክት” እንዲሉ፤ ገዳማውያን አባቶቻችን የመጡበት የተጋድሎ መንገድ ይህን ይመስላል፡፡


በዚህ ሕይወት፣ አባቶቻችን፥ ከፍትወታት እኵያት፣ ከኃጣውዕና ከአጋንንት ጋር የተጋደሉባቸው ገዳማት፤ አሠረ ፍኖታቸውን የተከተሉ፣ በርካታ ቅዱሳንና ተከታዮቻቸው አበምኔቶች፣ መምህራንና ባሕታውያን ፈልቀውባቸዋል፡፡ ከእነዚኽም አንዱ፣ የጋምቤላ ክልልና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ መጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ ናቸው፤” ይላል – “ስምዓ ጽድቅ ዘጋምቤላ” በሚል ርእስ፣ በሚያዝያ ወር 2008 ዓ.ም. በአህጉረ ስብከቱ ጽ/ቤት የተዘጋጀው ልዩ እትም መጽሔት፡፡

Aba Teklehaimanot Nigussie
መጽሔቱ፣ ሥራ አስኪያጁን አባ ተክለ ሃይማኖትን፣ ከገዳማውያኑ ተርታ ያሰለፋቸው፣በእውነተኛ የምንኵስና ሕይወት ኖረው፣ ልማት በማልማት፣ ወንጌል በመስበክ እና ከፍተኛ አገራዊ ተሳትፎ በማድረግ ስለሚታወቁ ነው፤” ብሏል፡፡

ሕይወታቸውን በዳሰስበት ክፍሉም፤ አባ ተክለ ሃይማኖት፡-

በቀን 150 ዳዊትን በመድገም፤ ውዳሴ ማርያም፣ ቅዳሴ ማርያም፣ አርጋኖን፣ ዕንዚራ ስብሐት፣ ኆኅተ ብርሃን፣ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ሳይደግሙ የማይውሉ መንፈሳዊና ጸሎተኛ የበረሓ መናኝ ናቸው፤ በዓመት ውስጥ በመንግሥትም ይኹን በቤተ ክህነት ስብሰባ ካልተጠሩ በስተቀር ወደ አዲስ አበባ በከንቱ መምጣትን የማይወዱ፤ ከገዳም ወደ ኪዳነ ምሕረት ቢሮአቸው፤ ከቢሮ ወደ ገዳማቸው እንጂ በሥራ ፈትነትና ለከንቱ ውዳሴ የማይዞሩ በዓታቸውን የማጽናት ጸጋ ያላቸው ባሕታዊ ናቸው፤ እንደ ሥራ አስኪያጅነታቸው የማይኮሩ፣ በሔዱባቸው አብያተ ክርስቲያናት ማዕጠንት ይዘው እንደ ሰሞንኛ በማገልገል፤ በሠርክ ጉባኤ ወንጌል በማስተማር፣ ከባዕለጸጎች ጋር ከመዋል ይልቅ ከድኃ ጋር መዋልን የመረጡ ትሑት አባት ናቸው፤ በየዕለቱ ማስተማርን ሥራቸው ያደረጉ ወንጌላዊ ናቸው፤ ወላጅ አልባ ሕፃናትን በመርዳት ለወግ ለማዕርግ ያደረሱ፤ ለ23 ለነዳያን በየሳምንቱ 50 ብር በመቁረጥ የሚረዱ፤ በየሔዱበት ለጥበቃ፣ ለሾፌሮችና ለሆቴል አስተናጋጆች የሚለግሱ ደግ አባት ናቸው፤ ዘመዶቻቸውና ወዳጆቻቸው ሁሉ በአሜሪካ እንደሚገኙና ዘመድ ቀርቶ የወንዝ ልጅ በሀገረ ስብከቱ የሌላቸው ዘረኝነትን የሚጸየፉ አባት ናቸው፤ በማለት አሞግሷቸዋል፡፡

ሐዋርያዊ ተልእኳቸውን ሲዘረዝርም፤

ከዐሥር ዓመት በፊት ወደ ሀገረ ስብከቱ ሲዘዋወሩ 17 ብቻ የነበረውን የአብያተ ክርስቲያናት ብዛት ወደ 53 ማድረሳቸውን፤ የመሠረት ድንጋይ ከመጣል ጀምሮ ፕላን ያወጡላቸውና የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴም በመኾን ማሠራታቸውን፤ የሽፍታ መሰማርያ በነበረው ቦታ ገዳም መሥርተው 17 መነኰሳትን በማምጣትና 12 የቃል ኪዳን ታቦት በማስገባት ከተማዋን እንደቀደሷት፤ የክልልና የወረዳ ባለሥልጣናትን ጨምሮ ኢአማንያንን አስተምረው ማጥመቃቸውን፤ ወደ ደቡብ ሱዳንም ተሻግረውና ከበርካታ የግድያ ሙከራዎች ተርፈው ስድስት አብያተ ክርስቲያናትን መመሥረታቸውንና ካህናትንና ዲያቆናትን መድበውላቸው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን፤ ከሞቃትነቱ የተነሣ በቀድሞው አስተዳደር ከመቱ በስልክ ይመራ ለነበረው ሀገረ ስብከት፣ መንበረ ጵጵስና በማሠራት ጽ/ቤቱን ማደራጀታቸውን፤ ትምህርት ቤቶችን፣ የገቢ ማስገኛ ሕንፃዎችን ከማስገንባታቸውም በላይ “ልማት ወደ ጋምቤላ፤ ጋምቤላ ወደ ልማት” በሚል መርሕ በየወረዳው የራስ አገዝ ልማትን ማስፋፋታቸውን፤ ከክልሉ መንግሥት ጋር ባላቸው ትብብርም፥ የሰላም እና የልማት አምባሳደር፤ የሃይማኖት ተቋማት ሰብሳቢ፤ የሰብአዊ መብት/የሕዝብ ክንፍ/ ሰብሳቢ ኾነው እየሠሩ እንዳለ አስፍሯል፡፡

“ለዛሬዋ ጋምቤላ ሰላም፣ የመጋቤ አእላፍ አባ ተክለ ሃይማኖት ሚና እጅግ የጎላ ነው፤” የሚሉት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ጋትሉዋክ ቱት ኮት፣ “ሰላሙ በዚኹ እንዲቀጥል፣ የክልሉ መንግሥትና የእምነቱ ተከታዮች ጳጳስ ኾነው ከእኛ ጋር እንዲኖሩ” በማለት ሥራ አስኪያጁ ኤጲስ ቆጶስነት እንዲሾሙላቸው፣ ለፓትርያርኩ ተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል፡፡

አባ ተክለ ሃይማኖትን ጵጵስና የማሾም ጥያቄ፣ በክልሉ መንግሥት ስም መቅረቡ፣ የሃይማኖትና መንግሥት ግንኙነት ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን የሚጥስ ብቻ ሳይኾን፤ ሰላምን በማስጠበቅ ስም በመንበረ ፓትርያርኩ ላይ አስገዳጅ ኹኔታ ፈጥሮ ፍላጎትን የማስፈጸም መነሻም እንዳለው የሀገረ ስብከቱ ካህናትና ምእመናን ይናገራሉ፤ “ሌላ ጳጳስ ከተመረጠ የማንቀበልና ከባሮ ቆላና ከኤርፖርት የማናሳልፍ መኾኑን እናሳስባለን” የሚለውን የርእሰ መስተዳድሩን ዛቻና ማስፈራሪያም በአስረጅነት ይጠቅሳሉ፡፡

የክልሉን ርእሰ መስተዳድር ያለአግባብ በማሳመንና በጥያቄው የካህናትና የምእመናን ድምፅ እንዳለበት አስመስሎ በፕሬዝዳንቱ ፊርማ ለቀረበበት፣ የቤተ ክርስቲያንን ሉዓላዊነት የሚጋፋ አካሔድ፤ ቀዳሚ ተጠያቂው፣ የአህጉረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ እንደኾኑ፤ የሀገረ ስብከቱ ካህናትና ምእመናን ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ባቀረቡት አቤቱታ ገልጸዋል፡፡ “የሕዝብ ጥያቄ ነው፤ መሾም አለብኝ፤” በማለት ርእሰ መስተዳድሩ በቀጥታ ለመንበረ ፓትርያርኩ እንዲጽፉት ያደረጉት ደብዳቤ፣ “በውሸት የተሞላ ብቻ ሳይኾን የሚያስጠይቃቸውም ነው፤” ብለዋል፡፡

አባ ተክለ ሃይማኖት፣ ጋምቤላ ከገቡ ጀምሮ ዋናው ፍላጎታቸው የጵጵስና ሥልጣን ማግኘት ነው፤” የሚሉት ምእመናኑ፤ በየዓመቱ፣ በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ ስለ ውጤታማነታቸው የሚያቀርቧቸውን ሪፖርቶች ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የሞከረ የለም እንጂ፣ “ከሰማንያ በመቶ በላይ ሐሰትና አባቶቻችንን ለመሸወድ የቀረበ ለመኾኑ” የ2007 ዓ.ም. ዘገባቸውን ማየት ብቻ በቂ እንደኾነ በማሳያነት ጠቅሰዋል፤ ቦታው ድረስ ሔዶ ማጣራትም እንደሚቻል አረጋግጠዋል፡፡

በወቅቱ ሪፖርታቸው፣ “12 የማጃንግ ብሔረሰብ ተወላጆችን በዲቁና አስተምረን በአኹን ሰዓት በዲቁና እያገለገሉ ነው፤ በቋንቋቸውም ወንጌልን እያስተማሩ ይገኛሉ፤” ማለታቸውን ያስታወሱት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፤ እንኳን ዲያቆን አንድም የተጠቀመ ማጃንግ የለም፤” ሲሉ አጋልጠዋል፡፡ በየዓመቱ፣ በአጠቃላይ ጉባኤው የሚያቀርቧቸው ባለሥልጣናት ኹሉም፣ ኦርቶዶክሳዊነትን ተረድተውና ተቀብለው ያመኑና የተጠመቁ ሳይኾኑ፤ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤያት በትእዛዝ ወጭ እያደረጉ የሚከፍሏቸው ውሎ አበል እንዳይቀርባቸው ሲሉ የሚያጅቧቸውም እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ራሳቸው ባለሥልጣናቱም፣ “እኛ ገንዘብ ስለሚሰጡን እንጂ ጥምቀቱን አልተጠመቅንም፤” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ የመታር፣ መኳይ እና የጋምቤላ ከተማ ኹለት ወረዳዎች አስተዳደርና የቀበሌ ሊቃነ መናብርት ለአብነት ተጠቅሰዋል፡፡

“የባለሥልጣናት መምጣት ለምን በየመድረኩ ይደጋገማል? የኅትመት ውጤቶችንስ [እንደ “ስምዓ ጽድቅ ዘጋምቤላ” ልዩ እትም መጽሔት ያሉትን] ለምን ያጣብባል?” ሲሉ የሚጠይቁት ካህናቱና ምእመናኑ፤ ሓላፊዎቹ፣ በእውነት የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ገብቷቸው ቢኾን በሥልጣናቸውና በስማቸው ሲነገድ ዝም አይሉም ነበር፤ በአጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ላይም፣ በማያውቁትና ለአባ ተክለ ሃይማኖት የሐሰት ሪፖርት ምስክርነት አይሰጡም ነበር፤” ሲሉ ይተቻሉ፡፡

በክርስትና ኹሉም እኩል ኾኖ ሳለ፣ ለጥቂት ባለሥልጣናት ትኩረት የተሰጠበት ኹኔታ፤ ቀደም ሲል፣ የክልሉ ተወላጆች የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርት ተምረውና ብሔረሰቦቻቸውን አስተምረው ወደ ክርስትና ሲመልሱበት በነበረው እንቅስቃሴ ላይ ፈተና ከመደቀኑም በላይ ለመጠመቅ መንገድ ላይ የነበሩትን ብዙዎች አስቀርቷል፡፡ የቅድመ ጥምቀት ትምህርታቸውን ጨርሰው፣ ለመጠመቅ ዝግጁ ቢኾኑ እንኳ፤ ባለሥልጣናቱ ከሌሉበትና ፓትርያርኩ ካልመጡ በሚል በቀነ ቀጠሮ እየተጉላሉ ተስፋ ቆርጠው እንዲበታተኑ የተደረገበት ኹኔታ፣ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጭና ሐዋርያዊ ነኝ ከሚል አንድ አባት የሚጠበቅ አይደለም፡፡

አባ ተክለ ሃይማኖት፣ በሥራ አስኪያጅነት ከመጡ በኋላ፣ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት በብዛት ታንፀዋል፤ መባሉ የተጋነነ ቢኾንም እንደሚያምኑበት የገለጹት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፤ በአሠራራቸውና በአገልግሎታቸው ግን፣ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ በትክክል እየተፈጸመባቸው ለማለት እንደሚቸገሩ አስረድተዋል፡፡

በአንድ ቤተ ክርስቲያን አንድ መቅደስ ውስጥ ማስቀመጫ እስከሚጠፋ ድረስ ከ3 እስከ 16 ጽላት እንዲቀመጡ ይደረጋሉ፤ ብዙዎቹም “ዘባረኮ …” የሌላቸውና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያልጠበቁ ናቸው፤ ለምሳሌ፡- የሪ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን መጎብኘት በቂ ነው፡፡ ዓመታዊ ክብረ በዓል እንኳ እንደማይደረግላቸው፣ በጀጀቤ ተራራ የጻድቁ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያንንና የጋምቤላ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወአቡነ ሐራ ድንግል ገዳምን መጥቀስ ይበቃል፤

tata monastery
የታታ ገዳምም፣ ቤተ ክርስቲያኑ ፈርሶ ጽላቱ የት እንዳለ አይታወቅም
፡ በቅርብ ርቀት አንድ ዓይነት ታቦት በማስገባት ምእመኑ ግራ እንዲጋባ ይደረጋል፤ ለምሳሌ፡- በጋምቤላ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል የቅዱስ ጊዮርጊስ ጽላት ባለበት፤ በቅርብ ርቀት በሚገኘው በጀጀቤ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጊዮርጊስ ጽላት ገብቷል፡፡ በአንድ ቤተ ክርስቲያን፣ አንዱን ጽሌ ካስገቡ በኋላ እየቀየሩ ሌላ ጽላትም ያስገባሉ፡፡ ለምሳሌ፡- በኢታንግ ወረዳ ተርፋም ቀበሌ ያስገቡት ጽላት የአባ ሊባኖስ ሲኾን፣ የጊዮርጊስ ጽላት ነው በማለት ምእመኑን አታለዋል፡፡

 • ይህ ኹሉ ለምን ይኾናል? በሚል የሚጠይቁና መፍትሔ ለመሻት የሚንቀሳቀሱ ካህናትን፥ “ክህነትኽን ቀምቼ አቶ አስብልሃለኹ፤ ለክልሉ ፕሬዝዳንት ነግሬ አሳስርሃለኹ” በማለት ችግር ይፈጥሩባቸዋል፤ ምእመናኑንም፣ ምን አገባችኹ? ይሏቸዋል፡፡ ብዙዎችም ይህን ዛቻና እስራት ፈርቶ፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲበላሽ ዝም ብሎ ለማየት ተገድዷል፡፡
 • ያለሕዝብ ፈቃድና ጥያቄ፣ ታቦታትን በተደራቢነት “በነጻ አመጣላችኋለኹ” ብለው ለሕዝቡ በዐውደ ምሕረት ቃል ከገቡ በኋላ፣ ዞር ብለው ደግሞ፣ ሰበካ ጉባኤው፣ በትንሹ ከ5ሺሕ እስከ 6ሺሕ ብር እንዲከፍል ያስገድዳሉ፤ አሳስራችኋለኹ እያሉ በክልሉ መንግሥት ስም ጭምር እያስፈራሩ ይቀበላሉ፡፡ ዐሥርና ዐሥራ አምስት ሰዎች፣ ያውም በጊዜአዊነት በመንግሥት ሥራ በሚኖሩበት አካባቢ፣ “ቤተ ክርስቲያን እተክላለኹ” በማለት አራት በአራት በኾነች ጎጆ ውስጥ ‘ታቦት’ በማስገባትና በኋላም ዞር ብሎ ባለማየት የሚታወቁ ናቸው – አባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ፡፡
 • በማጃንግ ዞን፣ የመንገሺ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያንና የዱባለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን፣ በአኹኑ ሰዓት ፈርሶ፣ ሰው ወዳለበት ወደ ከተማ ቀረብ ብሎ ተሠርቷል፤ ከመንግሥት ጋር ቅርበት አላቸው ተብሎ፣ ቦታ እንዲመራ ይረዱናል፤ ተብለው በተደጋጋሚ ቢለመኑም ፈቃደኛ አልነበሩም፤ ምክንያቱም፣ ዳጎስ ያለ ጥቅም አላገኝበትም ብለው ነው፡፡
 • “የቤተ ክርስቲያን መስፋፋት፣ የጽላት ቁጥር መጨመር ነው ወይስ የምእመናን ሕይወት ለውጥ?” ሲሉ የሚጠይቁት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፤ አባ ተክለ ሃይማኖት፣ እንደ “ትንሣኤ ዘጋምቤላ” እና “ስምዓ ጽድቅ ዘጋምቤላ” ባሉት መጽሔቶች፣ በሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ ለውጥ የታየው እርሳቸው ከመጡ በኋላ ቢናገሩም፤ በመሬት ላይ ያለው እውነታ ግን፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የተደፈረበት፤ ኢ-ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ የበዛበት መኾኑ ነው፤” ሲሉ ይቃወማሉ፡፡
 • ምእመናኑ፣ እንደትላንቱ ኹሉ ዛሬም የሚጾሙና የሚጸልዩ ቢኾንም፣ አባ ተክለ ሃይማኖት ከመምጣታቸው በፊት የሚቆርቡ፤ ዐሥራትና በኵራት የሚያወጡ ሰዎች ቁጥር ግን መቀነሱን የሚገልጸው አቤቱታው፤ የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መበላሸትን በምክንያትነት ያስቀምጣል፤ መንሥኤውም፣ በድብቅ እየተፈጸመ ያለው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ እንደኾነ ይጠቅሳል፤ አባ ተክለ ሃይማኖት፣ በቃል፣ “እኛ ተሐድሶ አንከተልም” ብለው ቢያስወሩም፣ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ችግር የኾነው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ፣ “በጋምቤላ ሀገረ ስብከት በእርሳቸው መሪነት የሚካሔድ ነው፤” ብሏል፡፡
 • በአስረጅነት የጠቀሱትም፡- በጋምቤላ፣ በዲማ እና በፑኝዶ፣ ሕዝቡ፥ በይፋዊ የሃይማኖት ሕፀፃቸው የያዛቸውን ሦስት መነኰሳት ወደ ሌላ ቦታ በመመደብ ከለላ መስጠታቸውን ነው፡፡ አባ ማቴዎስ፣ አባ ዕዝራ እና አባ መልከ ጼዴቅ የሚባሉት መነኰሳቱ፣ ቀድሞም ወደ ሀገረ ስብከቱ የመጡት በአባ ተክለ ሃይማኖት እንደነበረና ከተያዙም በኋላ፣ ሽፋን ሰጥተው እንዳስመለጧቸው፤ አንዱን ወደ አንድ የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲገባ ሲልኩት፤ የቀሩትም በላሬ፣ በዲማና በመታር እንዲኹም በአጎራባች ሀገረ ስብከት ወረዳና አጥቢያዎች በኅቡእ እንዲንቀሳቀሱ በመፍቀድ ምእመኑን አስቆጥተዋል፤ አንዳንድ የሰንበት ት/ቤት አባላትን፤ የተመረጡ ዲያቆናትንና ዘማርያም በመመልመል አህጉረ ስብከቱን የተሐድሶ ኑፋቄ መፈንጫ እንዲኾን አድርገውታል፡፡
 • ከሰንበት ት/ቤቶች አባላትን እየመለመሉ፣ አዲስ አበባ ወደሚገኙ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራት ይልካሉ፤ ሠልጥነው የተመለሱትም፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደማታማልድ፤ ቅዱሳት ሥዕላትን ማቃጠል ጽድቅ እንደኾነ፤ በቤተ ክርስቲያን ከነገረ ክርስቶስ ውጭ፣ ነገረ ማርያም እና ነገረ ቅዱሳን እንደማያስፈልጉ ይገልጻሉ፡፡

Aba TekleHN YeEwunet Kal Agelgilot

 • የእውነት ቃል አገልግሎት” ከተባለ ፕሮቴስታንታዊ ድርጅት፣ በ801 የፖ.ሣ.ቁ፣ “ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝህ ተቀበል” የሚል ጥቅስ ያለበት በራሪ ወረቀት እንዲኹም መጽሐፍ ቅዱስ ቲተራቸውን አትመው በጋምቤላ ከተማ አንቀጸ ብፁዓን ተክለ ሃይማኖት ገዳም ለሚኖሩት ያድላሉ፤ ራሳቸውም፣ “ተኣምረ ማርያም ማንበብ አያስፈልግም” እያሉ ለካህናቱ በግል ይነግሯቸዋል፤ የስም ሞክሼነቱን በመጠቀም፣ በራሳቸውና በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት መካከል ብዥታ የሚፈጥሩ መልእክቶችን ያስተላልፋሉ፡፡
 • ሰኔ 5 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ ከአዲስ አበባ መጥቶ በመንበረ ጵጵስናው በተሠራበት የሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት፣ በራሪ ወረቀት ሲያድል በምእመናን ተይዞ በጋምቤላ ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ሥር የነበረን መናፍቅ፣ በሀገረ ስብከቱ በኩል እንዲፈታ አድርገዋል፡፡
 • የስብከተ ወንጌል ጉባኤ፣ ‘ከዐቢይ ጾም ውጭ መደረግ የለበትም፤’ የተባለ ይመስል፣ አባ ተክለ ሃይማኖት፡- በየዓመቱ በዐቢይ ጾም ጉባኤ በማድረግና ከበሮ በማስመታት፤ ያለሰበካ ጉባኤው ዕውቅና፣ አጉራ ዘለል ሰባክያንንና ዘማርያንን በማስመጣት ገንዘብ እንዲከፈላቸው ያደርጋሉ፡፡ “ክርስቶስን እንሰብካለን” በሚል ሽፋን ለተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኝ መምህራንና ዘማርያን ሽፋን በመስጠት፤ ድብቅ ሤራቸውን እንዲያከናውኑ ሽፋን ይሰጣሉ፡፡
 • ሥልጣነ ክህነት የሌላቸውንና የተያዘባቸውን ክህነቱ ሳይመረመር በሀገረ ስብከት ደረጃ ቦታ ተሰጥቶአቸው እንዲሠሩ ይደረጋል፡፡ በቆሞስነት ክህነት ለመስጠት የማይችሉ ኾነው ሳለ፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ፣ ክህነት የሌላቸውን አመንኵሰው በራሳቸው ክህነት በመስጠት በቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪነት ሾመዋል፡፡ እኚኽ አባት በኢሉባቦር ሀገረ ስብከት ውስጥ እያገለገሉ እንደኾነ ሕዝበ ክርስቲያኑ ሲነቃባቸው፣ ወደ ጎደሬ ወረዳ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም አዛውረውታል፡፡ ያፈረሰ ቄስና ተራ ምእመን በቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪነት በመሾማቸው፣ በርካታ ምእመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ከመሔድ የማቋረጣቸው አዝማሚያ ወዴት ይመራናል፡፡ መንበረ ፓትርያርኩ ይህን ተግባር እያየና እየሰማ፣ አባ ተክለ ሃይማኖትን ጵጵስና ይሾማቸዋል ወይ?
 • ወደ ጋምቤላ ከተማ ተመድበው የመጡበትን ቀን፣ “በዓለ ሢመት” በሚል፣ በየዓመቱ በሆሳዕና ክብረ በዓል፣ በጋምቤላ ከተማ ያሉ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተው፣ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በገዳሙ እንዲከበር በማድረግ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንዲፋለስ አድርገዋል፡፡ በሌሎች አዘቦት ዕለታትም፤ ሰባኪው ወንጌሉን ማስተማርና መስበክ፣ ምእመኑም ቃለ እግዚአብሔርን መስማትና መማሩን ትቶ፣ የቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖትን ሥልጣን፤ ይህን ሠሩ፣ ያን አደረጉ ብሎ ካልሰበከ፤ ሙሉ ስማቸውን ካልጠራ በበነጋው ይባረራል፤ መጽሐፍ አልበው ኃይለ ቃል አውጥተው የሚያስተምሩ መምህራንን “አትችልም” በማለት የሥነ ልቡና ጫና ይፈጥራሉ፤ ያዋክባሉ፤ ያስፈራራሉ፡፡
 • በዚኽም ሳቢያ፣ የትምህርቱ ይዘት እየተዳከመ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣው የምእመን ቁጥር ከመቀነሱም በላይ፤ ንጹሕ ቃለ እግዚአብሔር ሲሰብኩ የነበሩ መምህራነ ወንጌልም፣ ተባረዋል፡፡ በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣ የመጽሐፍ መምህሩን ከልክለዋቸዋል፡፡ ያሬዳዊ ዜማ የኾነው ማሕሌት እንዳይቆም በመከልከል መሪጌቶች እንዳይኖሩ ተደርገዋል፡፡
 • የሚያስነቅፍ ምክንያት ባያገኙ እንኳ፣ በቅዳሴና በስብከት የሚያገለግሉ ካህናትንና መምህራንን፣ ከቅዳሴም ኾነ ከዐውደ ምሕረት አስወግዱልኝ፤ የሚሉትን ያኽል፣ ለጥፋት ሥራቸው ተባባሪ እንዲኾን የሚፈልጉትን ሰው ደግሞ፣ ከማረሚያ ቤት ካልወጣ በሚል ቤተ ክርስቲያንን ለትችት ዳርገዋታል፡፡ በሕገ ወጥ ደን መጨፍጨፍና ሕዝብን በማጋጨት ወንጀል ተከሦ በመጋቢት ወር፣ 2008 ዓ.ም. በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስድስት ዓመት ጽኑ እስራት የተፈረደበትን ሰው፤ “የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት በስልክ ፈቅደዋል” በሚል ውሸት፣ በራሳቸው ስምና ፊርማ በሚያዝያ ወር፣ 2008 ዓ.ም. በጻፉት የመፍቻ ደብዳቤ፣ “እስረኛውን ካልፈታችኹ” በማለት የማጃንግ ዞን ማረሚያ ቤትን ሲያስጨንቁ ቆይተዋል፡፡
 • ከማረሚያ ቤቱ ጋር ከፍተኛ ጭቅጭቅ በመፍጠር፣ ቤተ ክርስቲያን ከመንግሥት ጋር ሊኖራት የሚገባውን ሕጉን የጠበቀ ግንኙነት በማዛባት ክፉ ልምድ የተጠመዱት አባ ተክለ ሃይማኖት፣ የሕግ የበላይነትን የሚሸረሽር አደገኛ ጫና ማድረጋቸው ተገልጧል፤ በለመዱት ሕግ አፍራሽነት ጣልቃ በመግባት የተቋሙን ደንብ ለማፍረስና ሥርዓቱን ለመጣስ ያደረጉት እንቅስቃሴ፣ “ለወደፊቱ አሳሳቢ ነው፤ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር አንድ እልባት ሊገኝለት ይገባል፤” ሲል ነው፤ የማረሚያ ቤቱ አዛዥ፣ ለዞኑ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር ም/ቤት የጻፈው ደብዳቤ የሚጠይቀው፡፡
 • የሚገርመው ግን፣ በማረሚያ ቤቱ የእስር ቅጣቱን እየፈጸመ የሚገኘውና አባ ተክለ ሃይማኖት ይህን ያኽል ስሕተት የሠሩበት ካህን፣ ለቶሊ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ምክትል አስተዳዳሪ እንዲኾን ቢመድቡትም ሕዝቡ እንዳይመጣ ተከላክሎ ያባረረው መኾኑ ነው፡፡ በሌላ በኩል፣ በየአድባራቱ የጥፋት ሥራቸው ተባባሪ ለኾኑ ካህናት፣ የደብሩን አቅም ያላገናዘበ ደመወዝ እንዲከፈላቸው፣ ተዋረዱን ያልጠበቀ ደብዳቤ ይጽፋሉ፡፡ ታዲያ እኚኽ አባት፣ እንዴት ነው ዝም የተባሉት?

the showy aba tekle acting as a bishop

 • የዘፈቀደ ሥርዓት እንዲንሰራፋ፤ ምእመኑ ግዴለሽ እንዲኾን የማድረግ ዝንባሌ የሚታይባቸው አባ ተክለ ሃይማኖት፤ በቅዳሴ ጊዜ ሃይላንድ ውኃ ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ይዘው ገብተው ወንበር ላይ በማስቀመጥና በመጠጣት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ይዳፈራሉ፤ አርኣያ ክህነታቸውንም አይጠብቁም፤ ራሳቸውን “የጋምቤላ የተዋሕዶ አርበኛ” ብለው ባሳተሙት ቲሸርት፣ የራሳቸውን ፎቶ እንደ ሥዕለ አድኅኖ አድርገው በጨረታ መልክ በማቅረብ በባዛር ላይ ያጫርታሉ፡፡ ጳጰስ ሳይሆኑ በትረ ሙሴ በመያዝ በጋምቤላ ላይ በሚደረገው ዑደትና በጥምቀት በዓላት ጊዜ ያለሕገ ቤተ ክርስቲያን የማይገባቸውን በትረ ሙሴን በመያዝ ምእመናንን ግራ ያጋባሉ፡፡
 • ኧረ ለመኾኑ፣ አባ ተክለ ሃይማኖት መች ቅዳሴ ቀድሰው ያውቃሉ? አይደለም ለመቀደስ፣ በክብረ በዓላት ቀን በተገኙበት የቤተ ክርስቲያን ግጻዌ በሚያዘው መሠረት እንዳይቀደስ፣ “ወንጌል እንሰብካለን” በማለት ቅዳሴው እንዲያጥርና እንዳይቀደስ አድርገዋል፤ ምክንያት ካልከለከላቸው በቀር ዕለት ዕለት ሥጋውን ደሙን ለመቀበል መትጋት ሲገባቸው ሳይቆርቡ ሊኖሩ ነው? እንደ ጋምቤላ ባለ የጠረፍ ሀገረ ስብከት ሳይቀድሱና ሳያቆርቡ ሊኖሩ ነው? መቼም ዐሥር ዓመት ሙሉ ቀድሰው የማያውቁት በአጋጣሚ ሊኾን አይችልም፡፡
 • በ“ትንሣኤ ጋምቤላ” እና በ“ስምዓ ጽድቅ ዘጋምቤላ” መጽሔቶች ላይ፣ ከንባብ ጀምሮ ዳዊትና ቅዳሴ ተምሬአለኹ፤ ብለዋል፡፡ ቅዳሴ ይቅርና ውዳሴ ማርያም እንኳ መች ተምረው ያውቃሉ? መች በቃላቸው ይደግማሉ? መቼም ቅዳሴ ሲያልቅ ውዳሴ ማርያም፤ መልክአ ማርያምና መልክአ ኢየሱስ ደግመውና አስደግመው ያውቃሉ? ይህ ለምን ይኾናል የሚሉ ጠያቂዎች ቢመጡ፤ የዲማ፣ የጎደሬ፣ የፑኝዶው እና የላሬ አገልጋዮች ያዩትንና የሰሙትን ለመመስከር ዝግጁዎች ናቸው፡፡
 • የቤተ ክርስያናችን መተዳደርያ ደንብ በኾነው በቃለ ዐዋዲው አይመሩም፡፡ በኹሉም አድባራት የሰበካ ጉባኤያት በእርሳቸው መዳቢነት ነው እንዲሠሩ የተደረገው፡፡ እንደወደድሁት አደርገዋለኹ፤ ያሉትን ሰው፣ ከቤቱ ጠርተው በሰበካ ጉባኤው በማስገባት፤ ቃለ ዐዋዲውን ጠብቀን እንሠራለን፤ ያሉትን አባላት በማባረር፤ ያለደብሩ ጥያቄ አዲስ ሰበካ ጉባኤ በመምረጥ ሕዝቡን ያውካሉ፡፡ ምእመናን የራሳቸውን ተወካይ እንዳይመርጡ መብታቸውን ይገድባሉ፡፡ “ቃለ ዐዋዲው አይፈቅድም” ለሚላቸው ሰው፣ “እኛ በሥራ እንጂ በቃለ ዐዋዲ አናምንም” በማለት ጠያቂዎችን፣ መንግሥትን ከከላ በማድረግ ከማስፈራራት ጀምሮ እስከማሳሰር ይደርሳሉ፡፡
 • የልማት ኮሚቴ ሳይመረጥ፣ አብያተ ክርስቲያናት በዘፈቀደ የልማት ሥራ እንዲሠሩ ያደርጋሉ፡፡ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ኾነ የልማት ሥራ ከተሠራ በኋላ የገንዘቡ ገቢና ወጪ ሪፖርት እንዳይቀርብና እንዳይታወቅ ያከላክላሉ፤ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ያለምንም ደረሰኝ በ20 በመቶ ፈሰስ ስም ገንዘብ ይሰበስባሉ፤ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ በድብቅ በማቋቋም ከተሰበሰበ ገንዘብ ይወስዳሉ፡፡
 • የሰንበት ት/ቤት አባላት ባላመኑበትና የሰበካ ጉባኤ ባልተሳተፈበት፣ ራሳቸው አባ ተክለ ሃይማኖት፣ የሰንበት ት/ቤት ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ፣ ጸሐፊ፣ ገንዘብ ያዥ ይመርጣሉ፡፡ በጋምቤላ ከተማ የነበረውን የሦስቱ ሰንበት ት/ቤት አንድነት ጉባኤ በትነዋል፡፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተካሒዶ በነበረው አምስተኛው ሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ላይ ከሀገረ ስበከቱ የተላኩት የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች ሲኾኑ፣ ከሰንበት ት/ቤት የተሳተፈ አንድም ሰው አልነበረም፡፡
 • በሀገረ ስብከቱ የአብነት ት/ቤት አልነበረም፤ አኹን ይማራሉ የተባሉት እነማን ናቸው? ምንድን ነው የሚማሩት? ተማሪዎቹ እና መምህራኑ በሚላከው በጀት ምን ያኽል ይጠቀማሉ? መፈተሽ ይኖርበታል፤
 • ለጋምቤላ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ ደረጃ ኹለትና ሦስት ፎቅ ቤት እየተሠራ ነው፤ በማለት ከእያንዳንዱ ደብርና አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ለሕንፃው ማሠርያ፣ ከ3ሺሕ እስከ 6ሺሕ5 መቶ ብር በእስራት በማስፈራራት ሰብስበዋል፡፡ የሚገርመው ግን ብሩን በሞዴል ፴ መሰብሰብ ሲገባቸው፣ በሞዴል ፮(ስድስት) መሰብሰባቸው የአጥቢያውን ሰበካ ጉባኤም ኾነ ምስጢሩን የሠሙ ኹሉ አሳዝኗል፡፡
 • ካናቴራ “ቲሸርት” አሳትመውና “ስምዓ ጽድቅ ዘጋምቤላ – መጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት ከገቡ ጀምሮ” በሚል ባሳተሟቸው ፎቶግራፎች የሞሉበት መጽሔት፤ ቲሸርቱን በ150.00 ብር፤ መጽሔቱን በ100.00 ብር ለየደብሩ መቶ፣ መቶ ፍሬ በማከፋፈልና “ሸጣችኹ ተኩ፤ ብሩን ግን ከሰበካ ወጪ አድርጋችኹ አምጡ” ብለው በማስጨነቃቸው፣ የአድባራቱ የካዝና ብር ሲያልቅ ከግለሰብ ጭምር እየተበደሩ ከፍለዋል፡፡ እያንዳንዱ ካህን ለንስሐ ልጆቹ እንዲሸጥ፤ ካልኾነ ግን ከሥራ እንደሚባረርና እንደሚታሰር በመንግሥት በማስፈራራት ሲያስጨንቁ ቆይተዋል፡፡ ያም ኾኖ ሕዝቡ መጽሔቱን ባለመግዛቱ ሰበካ ጉባኤያቱ በዕዳ ተይዘዋ፤ ቀሳውስቱም በዚኹ ምክንያት ሥራቸውን እየለቀቁ ወደ ግብርና ሥራ እየገቡ ይገኛሉ፡፡
 • በመጽሔቱ፣ አባ ተክለ ሃይማኖት አጽንዖ በዓት ያላቸው፤ በቤተ ክርስቲያንና በመቃብር ቤት ውስጥ እንደሚያድሩ ይገልጻል፡፡ ነገር ግን የተሠራውን መንበረ ጵጰስና ትተው የሚያድሩት፤ ተፒ ሆቴል ቤት፤ ዐቢይ 03 በቡና ልማቱ ገስት ሐውስ(መዝናኛ ክበብ) ውስጥ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ሰበካ ጉባኤን እንኳ ስብሰባ የሚጠሩት ሆቴል ውስጥ ነው፡፡ በዐሥር ዓመታት መመሪያ ለማስተላለፍ እንጂ፣ ችግራችኹ ምንድን ነው ብለው ወረዳ ቤተ ክህነትንና አብያተ ክርስቲያናትን ጠይቀው አያውቁም፡፡

በአጠቃላይ፣ መጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ፣ ከዚኽም በላይ በርካታ አስከፊ ገጽታዎች ያሉ ሲኾን፣ ፈቃደ እግዚአብሔር ኾኖ ከተሾሙ ግን አንድም እግዚአብሔር ዓላማ ይኖረዋል፤ አልያም እኛ ተሳስተን ነበር ማለት ነው፡፡ ይኹንና አንድ ሐቅ አለ፤ አባ ተክለ ሃይማኖት፣ በገንዘብ ኃይል በምእመናንና በባለሥልጣናት ላይ ተጽዕኖ በመፍጠር፣ ሲሞናዊ ሥራ በመሥራት የቤተ ክርስቲያናችንን ሹመት ለግል ጥቅማቸው ለማዋል ሌት ተቀን እየደከሙ ይገኛሉ፡፡

ታዲያ ይህን እያየንና እየሰማን ጸጥ ማለት አባቶቻችን ያስተማሩን ባለመኾኑ ለሚመለከተው አካል አቤት ለማለት ተገደናል፡፡ ስለኾነም የሚመለከተው የቤተ ክርስቲያናችን አካል ይህን ጉዳይ መርምሮ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዲቻል፤ ከትውልድ ተወቃሽነትም ራሳችንን እንድናድን እኛ የጋምቤላ ምእመናን ፊርማችንን ከዚህ አባሪ ደብዳቤ ጋር ልከናል፡፡ እናንተም ለቤተ ክርስቲያን የሚበጀውን እንድትሠሩ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳችኹ ጸሎታችን ነው፡፡


ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር

Advertisements

16 thoughts on “የጋምቤላው አባ ተክለ ሃይማኖት ጵጵስና ከተሾሙ: “ምሥጢረ ክህነት ተራ ይኾናል፤ ቤተ መቅደስ ይረክሳል፤ የተሐድሶ መናፍቃን ይፈነጫሉ” ሲሉ አገልጋዮች አስጠነቀቁ

 1. Anonymous July 18, 2016 at 6:45 am Reply

  እግዚአብሔር ይስጥልን። ገና ለገና በማስፈራራት ጵጵስና። አይደረግም ተደርጎም አይታወቅ። ይገርማል እኮ። ለካ መናፍቅ ብዙ ተኩላ አፍርተዋ። የለኮሱት እሳት ቤተ ክርስቲያንን እያወደመ ነው። አረ ተው ግን እንዲህ ያለ ነገር እያለ እስከ ዛሬ ዝም ለምን ተባለ? የጋምቤላ መንግስት ቢሆን እምቢ ካለ ገደል ይግባ። በሃይማኖታችን ቀልድ የለም። እባካችሁ ማንኛውም አካል ሲያጠፋ ዝም አንበል። ለምን መልአክ አይሆንም። እናጋልጥ። አንሸፍን። ለሰጠኽን መረጃ በጣም ከልብ እናመሰግናለን። እኔማ ችግር ቢኖርባቸው ነው እንጂ እሱ ካልተሾመ ሌላ አናስገባም መባሉ። እንዲህ አይነት አጭበርባሪ ከሚመራችሁ እንዲሁ ዝም ብላችሁ እንደ ህገ-ልቦና ብትኖሩ ይሻላል። ቅዱስ ሲኖዶስ የመረጠው ወይስ በራሱ የመረጠ። ይህ ቅዥት ነው። ትልቁ ብልጥ ያለ አንድ ቀን አይበልጥ። ይህን ከነጓዙ አሸክሞ እንጦርጦስ ማውረድ ይገባል። በጣም ያበሳጫል። ይህን ሁሉ ጉድ ቤተ ክርስቲያን ተሸክማ እስከ መቼ? አይመረጡም በእርግጠኝነት። ስንት ደግ አባት ተቀምጠው ይህን ሌባ መሾም አይታሰብም።

  • የበገነዉ July 19, 2016 at 10:02 pm Reply

   ከስንት አመት ጀምረዉ ቤተ ክርስቲያን ሰራሁ እያሉ በስማችን አይነግዱ። ጁባ መጥታችሁ እዩን ዉሸትም ልክ አለዉ ምንም ባላደረጉበት ቦታ ዉሸትም ልክ አለዉ አረ ቤተ ክርስቲያንን ከመዉደድ ፍቅራችንን እንዲቀንስ አትድርጉን። በመጀመርያ ሰዉነታቸዉን በፆም ይቀንሱት አብዝተዉ በመብላት የተሸከሙትን ስጋ ይቀንሱት። እንደ ሴት ወይዘሮ እየተገላበጡ እንኯን ለአበዉ ስርዓት ቀርቶ ዘበኛ መሆን አይችሉም።

 2. Bete Zewudu July 18, 2016 at 10:05 am Reply

  bezuhezb krstyan adergewal ehamaniyanen melsewal yebalal 300,000sche belaye
  melsewal yegebahewal komos abba tekelehaemanot
  presdantu sayeker yasamenu yewengel gebee

 3. Bete Zewudu July 18, 2016 at 10:08 am Reply

  yedlo ygebahewal pepesena

 4. Anonymous July 18, 2016 at 10:45 am Reply

  የተሻለ ባለመኖሩ ተክሌ ቢሾም ይሻላል

  ይህን ፅሑፍ የፃፉትም ዕጭዎቹም የተግግማሙ በመሆናቸው የሚመጣውን ማየት ነው።
  አንድ እውነት ግን አውቃለሁ
  አባ ተክሌ በጣም ፀሎተኛ እንደሆነና በጭራሽ ሆቴል አድሮ እንደማያውቅ።

 5. Anonymous July 18, 2016 at 2:45 pm Reply

  ድሮም በመንግስት አካል መጠቆሙ አላማረኝም ነበር፡፡ አባቶቻችን የሚመረምሩት ይመስለኛል፡፡ የሚገርመው ሌላም ያለ ስልጣኑ በትረ-ሙሴ መቅደስ ውስጥ እየያዘ የሚያናድደኝ አለቃ ተጠቁሞ ነበር ግን 86ቱ ላይ ባለመካተቱ ደስ ብሎኛል፡፡ ይልቅ ትልቁ መማር አውቆ መገኘት ነበር፡፡ “… ረከብናሃ ለበትር ዘያደክማ ለሮሜ…” ብለው ሊቁ የተቀኙትን ቢያውቁ በትሩን ይረዱት ነበር፡፡

 6. Anonymous July 18, 2016 at 3:21 pm Reply

  እውነት ነው ይሄ ሁሉ?

 7. Anonymous July 18, 2016 at 9:46 pm Reply

  EGEZIHUBEHER TEWAGINEW SEMUM EGEZIHUBEHER NEW .YEASER AMETUN LEKESO ENEKASALEN SELEZIHIM ENEDE BERTOMIWOS ABEZETEN ENECHWE,

 8. Anonymous July 19, 2016 at 5:52 am Reply

  ene melew, hulu sew lenante tehadeso ena leba new?

  • Kibru July 19, 2016 at 10:05 pm Reply

   ከስንት አመት ጀምረዉ ቤተ ክርስቲያን ሰራሁ እያሉ በስማችን አይነግዱ። ጁባ መጥታችሁ እዩን ዉሸትም ልክ አለዉ ምንም ባላደረጉበት ቦታ ዉሸትም ልክ አለዉ አረ ቤተ ክርስቲያንን ከመዉደድ ፍቅራችንን እንዲቀንስ አትድርጉን። በመጀመርያ ሰዉነታቸዉን በፆም ይቀንሱት አብዝተዉ በመብላት የተሸከሙትን ስጋ ይቀንሱት። እንደ ሴት ወይዘሮ እየተገላበጡ እንኯን ለአበዉ ስርዓት ቀርቶ ዘበኛ መሆን አይችሉም።

 9. Anonymous July 19, 2016 at 7:26 am Reply

  Erte tew agelgayoch eneman nachew? MK mahbere kidusan nachew? hahahahaha

 10. Bete Zewudu July 19, 2016 at 11:13 am Reply

  ለአባ ተክለሀይማኖት ዘጋቤላ ጵጵስና ይገበዋል
  በረሐውን ተቋቁመው በስራ አስከሐጂነት ሰርተዋል ቁጥሩ በጣም ብዙ ህዝበ ክርስቲያን መልሰዋል
  የሚታይ የሚዳሰስ ስራሰርተዋል ሀገረስብከት ገብተዋል
  ብሬስዳንቱን ሳይቀር ወደአምልኮ ተእግዜብሔር መልሰዋል ስዚህ ይገበዋል
  ጵጵስና

 11. yesion July 19, 2016 at 1:02 pm Reply

  እንኳን ሃይማኖት ከፖለቲካ የሚለይ ህገመንግስት በተቀመጠበት በዚህ ጊዜ ቀርቶ ፣ ክርስቲያን መሆን በሚያሳርድበት ወቅት እንኳ፣ ክርስቲያን ነን እያሉ አንገታቸውን ለሰይፍ እየሰጡ እልፍ ሰማእታት ያለፉባት በእግዚአብሔር ጥበቃ እስካሁን ያለች የተዎህዶ ሃይማኖት ናት፡፡
  ዛሬ ታዲያ በዚች ቤተክርስቲያን ስር ተሸጉጠው የበቀሉ እንዲህ አይነት የአባት እርግማኖች፣ የትልቅ አንከርቶች፣ የወንጌሉ እንቅፋቶችን እንኳንስ ጵጵስና ቀርቶ በግብራቸው ክህነታቸውን እንኳን አሽቀንጥረው ጥለው ሲያበቁ፤ ማገልገያ እን ዲሆናቸው ሳይሆን መገልገያ ለማድረግ ፣ ለውዳሴከንቱ ጳጳስ እንዲሆኑ በእጂ፣ በእግር ሲያሻቸው የፕሬዘዳንት ድጋፍ አላቸው ተብሎ፣ ገና እንዲህ ባይሆን እንዲህ ይሆናል ተብሎ ተፈርቶ….. በቀኝም በግራም በውድም በግድም “ለመሾም” የሚደረግ ጥረት የሚያሳዝን ነው፡፡
  ሰውን ለማስደሰት ሰውን ላለማሳዘን ተብሎ ቤተክርስቲያንን የሚያፈርስ ስራ አባቶች እንደማይሰሩ ደግሞ እምነቴ ነው፡፡ እውነት ከስጋ ሞትም ቢሆን እንኳ የበለጠ ዋጋ የሚሰጥባት ቀጥተኛዋ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ለመሆኗ እንደጥንቱ ሁሉ የዛሬም አባቶች በማንኛውም መንገድ ከንደዚህ አይነት የቀን ጂቦች፣ የውስጥ ተኩላዎች ልትታደጓት እና ልትጠብቋት ተራው የናንተ ነው፡፡ እንደምታደርጉትም ተስፋየ ነው፡፡
  ይህ ባይሆን ግን በዚህ የሚጠይቃችሁ ባይኖር እንኳ በሰማይ ግን ጠያቂዎቻችሁ እልፍ ናቸው!
  ካህናት ሆይ፥ ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ አድምጡ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ፥ ልብ አድርጉ፤ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው። (ትንቢተ ሆሴዕ 5፥1 )

 12. petros July 20, 2016 at 12:09 am Reply

  Amliak kezy kezemene menafikan betihin ena hizbihin tebik….. enezy tehadiso menafikans lemin yerasachewun higawi minfikina ayzum zim bilewu kemiadenabiru……

 13. akbong July 20, 2016 at 10:15 am Reply

  ተክሌ ግብረ ሰዶማዊ ነው (እኔ ግብረ ሰዶማዊ ጳጳስ እግዜር ይፍታህ ሲለኝ ለማየት አልችልም ፼)
  ግብረ ሰዶማዊያን ሴት አይቀርቡም ተክሌ በዚህ ረገድ ሲወራ አንድ ጊዜም ቢሆን ደስተኛ አይደለም ይሄ የመጠቃቱ ምልክት ነው
  አብረውት የሚሰሩት በሴት ሲጠረጠሩ በጣም ይበሳጫል ልምን እንደሆነ ታወቃላችሁ እርሱ የሚሻው ተመሳሳይ ጾታን ነው፡፡
  በሴት አይጠረጠርም ሲባል እገረማለው ፡ በወንድስ፡
  በመንግስት ጫና ታላቁን የስልጣን ጥም ያለበት ሰው እንዴት ሹመት ይሰጠዋል ፡፡
  በየአመቱ ራሱን መላጨት፡ በትረ ሙሴ ፡አርዌ ብርት፡ ማሰራት ወዘተ ምን ያደርጋል እንደ ሎጥ ዘመን ሰወች ከወንድ ሁዋላ እየተርመጠመጡ፡፡
  ግብረ ሰዶማዊ መነኩሴ ጳጳስ መሆን ወይም ለጳጳስነት ማሰብ ይከብዳል ተክለሓይማኖት ጋር ተኝቶ ያልተበላሸ ሰው የለም አንዳንድ ጊዜ በሴት መጠርጠር እኮ ይሻላል ፡፡ ከዘማሪ እዝራ ጋር የነበረው ግንኙነት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ ዘርፌና እዝራ በተደጋጋሚ ጋምቤላ ይመጡ ነበር ፡፡ ዘርፌ አሁን ያለውን ባሉዋን (ልጅ እግሩ ቄስ) ከማግባቱዋ በፊት ከወንድ ጋር መተኛት አትችልም ነበር ይህም በልጅነትዋ በደረሰባት መደፈር ነበር ይሄ ዉሸት እንዳልሆነ ድፍን የጋምበቤላ ከተማ ነዋሪ ያውቃል ፡፡እርሱዋን ተመኝተው ወይን የጋበዙ ጀጀቤና ባሮ ማዶ በሚገኘው ሆቴል ያሳደሩዋት ሁሉ ምስክሮች ናቸው ፡፡ በዚህም ምክንያት ሴት ጋር የማይደርሰው እዝራ ከእርስዋ ጋር ይተኛ ነበር ፡፡ ተክሌ ደግሞ ከእዝራ ጋር …………………………..፡፡ይህን ሳወራ በማፈር ነው ፡፡ ጌታ ሆይ ይቅር በለኝ ፡፡ አሁን እኔ ግብረ ሰዶማዊ ጳጳስ እግዜር ይፍታህ ሲለኝ ለማየት አልችልም
  መሃይሙ ና መናፍቁ ከተሾመ ፡ ሆዳሙ ከተከበረ ምን እንላለን ቤተክርስቲያን ከመቸውም በላይ እየወደቀች ነው
  ደግሞም የተሃድሶ ቅጥረኛ ከሆኑቱ መካከል ግንባር ቀደሙ በግዋሻው ቤቱ ነበር እኔ ተክሌን አምሳሉ እያለ ገና በልጅነቱ መቱ ጎሬ ላይ አውቀዋለው እሱ ወደ ኮሌጅ ሲገባ እኔ ደግሞ ጋመቤላ ላይ ስራ ጀመርኩ ስለርሱ ብዙ ነገር አልሰማም ነበር ጋመቤላ ሲመጣ ደግሞ ደስ ካላቸው ሰዎች አንዱ እኔ ነበርኩ መጥቶ ደግሞ ሲያስተምር ደስ ይለኝ ነበር ነገር ግን አንድ ቀን እያስተማረ እያለ የሰውን ቀልብ የራሱ ለማድረግ መሬት ላይ ሲዘረር አይቼ ቲያትሩ ደበረኝ ከዚያም በውዳሴ ከንቱ ሲጠለፍ ማየጥ የዘወትር ልምዱ ሆነ እንደ አቡነ ጳውሎስና መንግሰቱ ሃይለማሪያም አቤት የስሙ መርዘም ውይ ስልችት ይለኛል አልነግረው ነገር አብሮ አደጌ ቀና ይለኛል ብዬ እፈራለው ፡፡
  እኔ ሳስበው የበርሃ ቀበሮ ከበርሃ ውጪ አይደላውም እርሱም መቼም ቢሆን አይተዋትም ከደቡብ ሱዳን ከሚመጡ ሰዎች የብር ዝውውር ይፈጽማል የዝሆን ጥርስ ከዲማ ደገሞ ወርቅ ይሸጣል ፡፡ በቤተክርስቲያን ስም ሲሚንቶ ዕያመጣ የት እንደሚያደርሰው እኔንጃ ይሄን ጉዱን ያወቁበት ሰዎች ባጃጅ ገዝቶ ዝም አስብሎዋቸዋል ፡፡ጋምቤላ ላይ ሰወች ተጠመቁ ይባላል ግን የት አሉ ፡ ከተማይቱ ላይ አንድም የተጠመቀ አሁን በመንፈሳዊ አቅዋም ላይ ያለ ሰው አታገኘኙም ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: