ለኤጲስ ቆጶሳት ምርጫው: ከወሎና ከሰሜን ሸዋ አህጉረ ስብከት ለመጨረሻው ዙር ማጣርያ ያለፉ ዐሥር ተጠቋሚ ቆሞሳትና መነኰሳት

16patriarchabunetewophilos

 • በቀሪዎቹ 68 ተጠቋሚዎቹ ላይ፣ ማጣራቱ ይቀጥላል
 • እስከፊታችን ዓርብ 32ቱ ዕጩዎች ይታወቃሉ ተብሏል

በቅዱስ ሲኖዶስ የተሠየመው የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ፣ ከወሎ እና ከሰሜን ሸዋ አህጉረ ስብከት ለመጨረሻው ዙር ማጣራት የሚያካሒድባቸውን፥ ዐሥር ተጠቋሚ ቆሞሳትና መነኰሳት ለየ፡፡

በዚኽም መሠረት፣ እስካለፈው ሰኞ ድረስ፤ ከወሎ 15፣ ከሰሜን ሸዋ 13 የነበሩት ተጠቋሚዎች፣ ከእያንዳንዳቸው እንደ ቅደም ተከተላቸው፣ በዐሥር እና በስምንት ቀንሰው፣ ለመጨረሻ ዙር ማጣራት የሚካሔድባቸው አምስት፣ አምስት ተጠቋሚዎች መለየታቸው ታውቋል፡፡

ይህም ከ118 ጠቅላላ ተጠቋሚዎች ወደ 86 ቀንሶ የነበረውን ቆሞሳትና መነኰሳት ቁጥር፣ እስከ ዛሬ፣ ሐምሌ 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ባለው አኃዝ ወደ 68 እንዲወርድ አድርጎታል፡፡

ኮሚቴው፣ እስከ መጪው ሳምንት ዓርብ፣ ቀሪ ተጠቋሚዎችን የማጥናት፣ የመመርመርና የማጣራት ሥራውን በማጠናቀቅ፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምርጫ የሚቀርቡትን 32ቱን የኤጲስ ቆጶሳት ዕጩዎች እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል፡፡

ሹመቱ፣ ክፍት በኾኑና መንበረ ጵጵስና ላላቸው 16 አህጉረ ስብከት የሚደረግ ሲኾን፤ ለየመንበረ ጵጵስናው ኹለት፣ ኹለት ዕጩዎች በምርጫ ይወዳደራሉ፡፡

*                *                *

ከወሎ አህጉረ ስብከት ለመጨረሻው ዙር ማጣራት ያለፉ አምስቱ ተጠቋሚዎች፡-

 1. አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎርዮስ(የጎፋ ጥበብ እድ ማሠልጠኛ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ)
 2. አባ ሳሙኤል ገላነው(የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ መምህር)
 3. አባ ያሬድ ምስጋናው(የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገዳም መምህር)
 4. አባ ገብረ ሥላሴ በላይ(የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ)
 5. አባ ጽጌ ሥላሴ መዝገቡ(የደሴ ቅዱስ ገብርኤል አለቃ)

ከሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ለመጨረሻው ዙር ያለፉ አምስቱ ተጠቋሚዎች፡-

 1. አባ ፊልጶስ አሻግሬ(አሜሪካ – ሚችጋን ዴትሮይት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ደብር)
 2. አባ ለይኩን ግፋ ወሰን(መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት)
 3. አባ ኃይለ ማርያም አረጋ(የደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ አለቃ)
 4. አባ ማቴዎስ ከፍ ያለው(እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገዳም)
 5. አባ ተክለ ሃይማኖት ወልዱ(የናዝሬት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አለቃ)
Advertisements

5 thoughts on “ለኤጲስ ቆጶሳት ምርጫው: ከወሎና ከሰሜን ሸዋ አህጉረ ስብከት ለመጨረሻው ዙር ማጣርያ ያለፉ ዐሥር ተጠቋሚ ቆሞሳትና መነኰሳት

 1. Anonymous July 17, 2016 at 4:28 am Reply

  ሁሉም የተጠቆሙ አባቶች ችግር የለባቸውም? ስለእያንዳንዱ አጠር ያለ ገለፃ ቢደረግ።መልካም ነበር።

 2. ገላቲያ ገ/ፃዲቅ July 17, 2016 at 7:08 am Reply

  እግዚአብሔር ይመስገን ለመንጋው የሚራሩ አባቶችን ሹሙልን

  • Solomon July 17, 2016 at 8:32 pm Reply

   Egziabehare yemesgen betkrstiyanachen ahune gena teru sera eyteseranew abatochachen behasabe kenante gon nen ahunem bertulen kehezbe yemisetewone astyayet betsmona teketatelute kehezbe kmemenane yetdebek andem neger yeleme yememenane demtse nege tekawomo aysnesame selezi yeskawonu hidet dese yemil new bertulen

   • Anonymous July 18, 2016 at 4:59 am

    Bewnet yenet abba yared msganaw
    yegziabher new engi sew aydelem
    yemeretsachew lemn bitlugn bemnane
    hywetachew lehulum menekosat araya
    yemihon bemehonachew, bewkete derega yedgua,yebluy,yehadisu,yeakuakuamu ena yeknew profeser kemehonachew alfo bezemenawim keftetegna wtset
    bemamtsat yekeftegna tmihrt mruk
    bemehonachew yhe derega betkeke
    yemigebachew abat nachew lesachew
    yemiawkachw hulu ydelwo ydelwo endemil 100 persent ergtsegna negn
    enem ydelwo ydelwo ydelwo bialehu
    egziebher yagelglot zemenachewn yabzalachew amen.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: